Telegram Web Link
TIKVAH-SPORT
ባየር ሙኒክ በይፋ አሰልጣኝ ሾመ ! የጀርመኑ ክለብ ባየር ሙኒክ ቤልጂየማዊውን አሰልጣኝ ቪንሴንት ኮምፓኒ በአሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል ምትክ በሀላፊነት መሾማቸውን በይፋ አስታውቀዋል። አሰልጣኝ ቪንሴንት ኮምፓኒ ባየር ሙኒክን ለሶስት የውድድር አመታት ለማሰልጠን እስከ 2027 የሚያቆያቸውን ውል በይፋ ፈርመዋል። ባየር ሙኒክ ለበርንሌይ ለአሰልጣኙ የካሳ ክፍያ የሚሆን 12 ሚልዮን ዩሮ የሚጠጋ ገንዘብ…
" ባየር ሙኒክን ማሰልጠን ለእኔ ትልቅ ክብር ነው " ኮምፓኒ

የቡንደስሊጋውን ክለብ ባየር ሙኒክ በሀላፊነት የተረከቡት አሰልጣኝ ቪንሴንት ኮምፓኒ የተሰጣቸው ሀላፊነት ትልቅ ክብር መሆኑን ከፊርማው በኋላ ገልጸዋል።

" በባየር ሙኒክ አዲስ ፈተና ለመጋፈጥ ጓጉቻለሁ " ያሉት አሰልጣኝ ቪንሴንት ኮምፓኒ " በዚህ ክለብ ውስጥ መስራት ለእኔ ትልቅ ክብር ነው ሙኒክ በአለም እግርኳስ ትልቅ ቦታ አለው " ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማንችስተር ሲቲ ለተጫዋቹ ፍቃድ ሰጥቷል !

ማንችስተር ሲቲ አርጀንቲናዊው የፊት መስመር ተጨዋች ጁሊያን አልቫሬዝ በቀጣዩ የፈረንሳይ ፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር ሀገሩን እንዲወክል መፍቀዳቸው ተገልጿል።

የ 24ዓመቱ ተጨዋች ጁሊያን አልቫሬዝ ከአርጀንቲና የኦሎምፒክ ብሔራዊ ቡድን በቀጣይ ጥሪ ከደረሰው ወደ ፓሪስ የሚያመራ ይሆናል።

በኦሎምፒክ ውድድር ላይ ከ 23ዓመት በታች የሆኑ ተጨዋቾች የሚሳተፉ ሲሆን አንድ ብሔራዊ ቡድን ሶስት ከእድሜ ገደብ በላይ የሆኑ ተጫዋቾችን ማሳተፍ ይችላል።

ፊፋ ክለቦች ለኦሎምፒክ ውድድር ተጨዋቾቻቸውን ለብሔራዊ ቡድኖቻቸው እንዲለቁ የሚያስገድድ ህግ እንደሌለው ይታወቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
እረፍት | ኦሎምፒያኮስ 0 - 0 ፊዮረንቲና ( ኮንፈረንስ ሊግ ፍፃሜ )

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ተጠናቀቀ | ኦሎምፒያኮስ 0 - 0 ፊዮረንቲና ( ኮንፈረንስ ሊግ ፍፃሜ )

- ሁለቱ ክለቦች መደበኛውን የጨዋታ ክፍለጊዜ በአቻ ውጤት ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ ወደተጨማሪ ሰላሳ ደቂቃ አምርተዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
115 ' ኦሎምፒያኮስ 1 - 0 ፊዮረንቲና ( ኮንፈረንስ ሊግ ፍፃሜ )

ኤል ካቢ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኦሎምፒያኮስ የኮንፈረንስ ሊግ አሸናፊ ሆነ !

የግሪኩ ክለብ ኦሎምፒያኮስ ከጣልያኑ ክለብ ፊዮሬንቲና ጋር ያደረገውን የአውሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሻምፒዮን ሆነዋል።

የኦሎምፒያኮስን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ አዮብ ኤል ካቢ በተጨማሪ ደቂቃ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ኦሎምፒያኮስ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የአውሮፓ መድረክ ውድድር ሻምፒዮን መሆን ችለዋል።

በተጨማሪም ኦሎምፒያኮስ የአውሮፓ መድረክ ውድድር ዋንጫን ማሸነፍ የቻለ የመጀመሪያው የግሪክ ክለብ በመሆን አዲስ ታሪክ ፅፈዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
Cremonense - Venezia
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
Forwarded from HEY Online Market
iPhone 15 Promax
•256GB = 139,000 Birr
•512GB = 159,000 Birr

Samsung 24 Ultra
•256GB = 111,000 Birr
•512GB = 128,000 Birr

Contact us :
0953964175 @heymobile
0925927457

@Heyonlinemarket
አርቴታ ከፍተኛ ተከፋይ አሰልጣኝ ሊሆኑ ይችላሉ !

ስፔናዊው አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የሚቀጥለው የውድድር አመት ከመጀመሩ አስቀድሞ በአርሰናል ቤት ያላቸውን ውል ለተጨማሪ አመታት ሊያራዝሙ እንደሚችሉ ተገልጿል።

በክለቡ የአንድ አመት ውል ያላቸው አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በአዲሱ የኮንትራት የአርሰናል የምንግዜም ከፍተኛ ተከፋይ አሰልጣኝ ሊሆኑ እንደሚችሉ ተነግሯል።

አሰልጣኙ በአመት #አስር ሚልዮን ፓውንድ የሚደርስ የደሞዝ ክፍያ ሊቀርብላቸው ይችላል የተባለ ሲሆን ይህም ከፕርሚየር ሊጉ ከፍተኛ ተከፋይ አሰልጣኞች አንዱ ያደርጋቸዋል።

የማንችስተር ሲቲው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በአመት 20 ሚልዮን ፓውንድ በሆነ ክፍያ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ከፍተኛ ተከፋይ አሰልጣኝ ናቸው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማድሪድ የምባፔን ዝውውር መቼ ያሳውቃል ?

ሪያል ማድሪድ የፈረንሳዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ ዝውውር ከ2024 የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር መጀመር በፊት ይፋ ለማድረግ ማሰባቸው ተገልጿል።

የፈረንሳዩ ክለብ ፒኤስጂ ኪሊያን ምባፔ ከ2024 የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር በፊት ቀጣይ ክለቡን እንዲያሳውቅ ፍቃድ መስጠታቸው ተነግሯል።

ሎስ ብላንኮዎቹ አዲስ ፈራሚያቸው የሚሆነውን ኪሊያን ምባፔ የተለየ ይፋዊ አቀባበል ለማድረግ እያዘጋጁ እንደሚገኙ ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የሮድሪጎ የሪያል ማድሪድ ቆይታ ?

ብራዚላዊው የሪያል ማድሪድ የፊት መስመር ተጨዋች ሮድሪጎ በቀጣይ ሎስ ብላንኮዎቹን ስለመልቀቅ ሊያስብ የሚችልበት አጋጣሚ ሊፈጠር እንደሚችል ተገልጿል።

ተጨዋቹ አሁን ላይ በሪያል ማድሪድ ቤት ደስተኛ እንደሆነ እና ለመልቀቅ እያሰበ እንደማይገኝ ተነግሯል።

ይሁን እንጂ ሮድሪጎ በክለቡ ያለውን የመጫወቻ ጊዜ በሌላ ተጨዋች የሚቀማ ከሆነ ሌሎች ተጨዋቾች እንደሚያደርጉት ሁሉ በቀጣይ አዲስ አማራጭ ሊመለከት እንደሚችል ተገልጿል።

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ክለቦች በቀጣይ ሮድሪጎን ለማስፈረም ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሪያድ ማህሬዝ ጥሪ አልቀረበለትም !

የአልጄሪያ ብሔራዊ ቡድን በቀጣይ ላለበት የአለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ጨዋታዎች የሚጠቀመውን ስብስብ ይፋ አድርጓል።

በስብስቡ ውስጥ የአል አህሊው የፊት መስመር ተጨዋች ሪያድ ማህሬዝ ሳይካተት ቀርቷል።

ብሔራዊ ቡድኑ በቀጣይ ከጊኒ እና ዩጋንዳ ጋር የአለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ጨዋታዎችን የሚያደርግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ሻምፒየንስ ሊግ ከባሎን ዶር ይበልጣል " ሲልቫ

የማንችስተር ሲቲው ፖርቹጋላዊ የፊት መስመር ተጨዋች በርናርዶ ሲልቫ ለእሱ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ከባሎን ዶር ሽልማት የበለጠ ዋጋ እንዳለው ገልጿል።

" የቡድን አጋሮቼን ለማገዝ እና ለቡድናችን ጥሩ ነገር ለማድረግ ሁልጊዜም ያለኝን ሁሉ እሰጣለሁ " የሚለው በርናርዶ ሲልቫ " የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግን ማሸነፍ ባሎን ዶርን ከማሸነፍ ይበልጣል በፍጹም አልለውጥም።"ሲል ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አሌሀንድሮ ጋርናቾ በኦሎምፒክ ውድድር ይሳተፋል ?

የአርጀንቲና ኦሎምፒክ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ዣቪየር ማሼራኖ የማንችስተር ዩናይትዱን የፊት መስመር ተጨዋች አሌሀንድሮ ጋርናቾ በኦሎምፒክ ስብስቡ ውስጥ ማካተት እንደሚፈልግ ተገልጿል።

ማንችስተር ዩናይትዶች በበኩላቸው እስካሁን አሌሀንድሮ ጋርናቾ በኦሎምፒክ ውድድር እንዲሳተፍ መፍቀድ አለመፍቀዳቸውን አለማሳወቃቸው ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
📢 #ለቸኮሉ መፍትሔ ከ #ዋናው!

👉🏾 #ዋናው ስፖርት ጊዜዎን ቆጣቢ የሆነ ሁነኛ መፍትሔን ይዞሎት መጥቷል፣ አስቀድመው ተዘጋጅተው የሚወስዷቸው ማልያዎች!

🚀 #ይምጡ፣ ይህን ቀላል አማራጭ ይጠቀሙ!

📍አድራሻችን:- ገርጂ መብራት ሃይል የካቲት ወረቀት ፊትለፊት፣ አለም ገብሬ ህንፃ፣ 2ተኛ ፎቅ።

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 09011382830910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ወይም በቴሌግራም ቦት @WANAWSbot በኩል ይዘዙን።

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
የሳውዲ ክለቦች ቤከርን ማስፈረም ይፈልጋሉ !

የሳውዲ አረቢያ ክለቦች ብራዚላዊውን የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ቁጥር አንድ ግብ ጠባቂ አሊሰን ቤከር የማስፈረም ፍላጎት እንዳላቸው ተገልጿል።

ሳውዲ አረቢያዎች ባለፉት ወራት ሊቨርፑል አሊሰን ቤከርን ለሽያጭ ያቀርብ እንደሆነ ጥያቄ አቅርበው እንደነበር ተነግሯል።

ይሁን እንጂ ሊቨርፑልም ሆነ አሊሰን ቤከር የመለያየት ፍላጎት እንደሌላቸው ለክለቦቹ ማሳወቃቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኤቨርተን የተጫዋቹን ውል ሊያራዝም ነው !

የመርሲሳይዱ ክለብ ኤቨርተን የፊት መስመር ተጨዋቻቸው ዶምኒክ ካልቨርት ሌዊንን ኮንትራት ለማራዘም ንግግር መጀመራቸው ተገልጿል።

የ 27ዓመቱ የፊት መስመር ተጨዋች ዶምኒክ ካልቨርት ሌዊን በኤቨርተን ቤት ያለው ኮንትራት ሊጠናቀቅ አንድ አመት ይቀረዋል።

ተጨዋቹ በሌላኛው የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ክለብ ኒውካስል ዩናይትድ ለረጅም ጊዜ ሲፈለግ እንደነበር ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ስለ ማድሪድ ታሪኩ ይናገራል " ሳንቾ

የቦርስያ ዶርትመንድ የፊት መስመር ተጨዋች ጄደን ሳንቾ የቅዳሜው የሪያል ማድሪድ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ትልቅ ፍልሚያ እንደሚሆን ተናግሯል።

" የሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ በጣም የምወደው ጨዋታ ነው " ያለው ጄደን ሳንቾ " ትልቅ ጨዋታ ይሆናል የሪያል ማድሪድ ታሪክ በራሱ ይናገራል።"ሲል ተደምጧል።

" ሪያል ማድሪድ ውስጥ ቪንሰስ እና ቤሊንግሀምን የመሳሰሉ ጓደኞች አሉኝ ፣ ከሙኒክ ጨዋታ በኋላ አውርተናል በፍፃሜው እንገናኝ ብያቸዋለሁ ፣ ለጨዋታው ጓጉቻለሁ።" ሳንቾ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/09/28 13:20:31
Back to Top
HTML Embed Code: