Telegram Web Link
ዋልያዎቹ ልምምዳቸውን ሰርተዋል !

በቀጣይ ላሉበት የአለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ጨዋታዎች በዝግጅት ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዛሬው ዕለት ልምምዱን በአዲስ አበባ ስታዲየም ሰርቷል።

በአሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ የሚመራው ብሔራዊ ቡድኑ በልምምድ ወቅት የእርስ በርስ ግጥሚያዎችን ማድረግ ችሏል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ግንቦት 29/2016 ዓ.ም ከጊኒ ቢሳው እንዲሁም ሰኔ 2/2016 ዓ.ም ከጅቡቲ ጋር ከሜዳው ውጪ የማጣሪያ ጨዋታውን ያደርጋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ማድሪድ በፍፃሜው በግብ ጠባቂነት ማንን ሊያሰልፍ ይችላል ? የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር ፍፃሜ ጨዋታቸውን ከዶርትመንድ ጋር የሚያደርጉት ሪያል ማድሪዶች በፍፃሜው ቲቧ ኩርቱዋን በቋሚ አሰላለፍ ለማስገባት በማሰብ ላይ መሆናቸው ተገልጿል። ሎስ ብላንኮዎቹ ከረጅም ጊዜ ጉዳት የተመለሰው ቲቧ ኩርቱዋ በቋሚነት መሰለፉ የቡድኑን በራስ መተማመን ለመጨመር ይረዳል የሚል እምነት እንዳላቸው ተነግሯል። …
ማድሪድ ቲቧ ኩርቱዋን በቋሚነት ያሰልፋል !

ሪያል ማድሪድ በነገው የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር ፍፃሜ ጨዋታ ቲቧ ኩርቱዋን በቋሚ አሰላለፍ እንደሚያስገባ አሰልጣኝ ካርሎ አንችሎቲ አረጋግጠዋል።

አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ በንግግራቸውም " አንድሬ ሉኒን የጉንፋን ህመም አጋጥሞት አሁን በጥሩ ሁኔታ ላይ ነው ነገ ቡድኑን ይቀላቀላል ነገርግን ነገ ኩርቱዋ ቋሚ ይሆናል እሱ ተጠባባቂ ይሆናል።"ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ ናፖሊን ሊረከቡ ነው !

የጣልያን ሴርያው ክለብ ናፖሊ ጣልያናዊውን አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴን በሀላፊነት ለመሾም ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ ናፖሊን እስከ 2027 ለሶስት የውድድር አመታት ለማሰልጠን ከስምምነት መድረሳቸው ይፋ ሆኗል።

አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ ከቶተንሀም ጋር ከተለያዩ በኋላ ለቤተሰባቸው ቅርብ ለመሆን የጣልያን ክለብ የማሰልጠን ፍላጎት እንደነበራቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አል ሂላል የሳውዲ ኪንግስ ካፕን አሸነፈ !

አል ሂላል ከአል ናስር ጋር ያደረገውን የሳውዲ አረቢያ ኪንግስ ካፕ ውድድር ፍፃሜ ጨዋታ በመለያ ምት 5ለ4 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሻምፒዮን መሆን ችለዋል።

ሁለቱ ክለቦች መደበኛውን የጨዋታ ክፍለጊዜ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

አል ሂላልን ግብ አሌክሳንደር ሚትሮቪች ከመረብ ሲያሳርፍ አይማን አህመድ አል ናስርን አቻ አድርጓል።

በፍፃሜ ጨዋታው ከአል ሂላል ሁለት እንዲሁም ከአል ናስር አንድ በድምሩ ሶስት የቀይ ካርዶች ተመዘዋል።

አል ሂላል በታሪኩ አስራ አንደኛ የሳውዲ አረቢያ ኪንግስ ካፕ ዋንጫን ማሳካት ችለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
Apple Vision Pro

🔹VisionPro provides a comprehensive set of vision tools for applications like inspection, gauging, and guidance.
🔸It's commonly used in industries such as automotive, electronics, pharmaceuticals, and more to improve manufacturing processes, ensure product quality, and increase productivity.

Contact Us
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
" ፍፃሜውን ለማሸነፍ ያለንን ሁሉ እንሰጣለን "

የሪያል ማድሪዱ ዋና አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ ከዛሬ ምሽቱ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ በፊት ከጋዜጠኞች ጋር ቆይታ አድርገዋል።

ካርሎ አንቾሎቲ ምን አሉ ?

- " በራሳችን እንተማመናለን ለዶርትመንድ ክብር አለን እዚህ መሆን ይገባቸዋል ነገርግን ጨዋታውን ለማሸነፍ ያለንን ሁሉ እንሰጣለን።

- እዚህ በመሆኔ ደስተኛ ነኝ የመጀመሪያ አይደለም የመጨረሻዬ እንደማይሆንም ተስፋ አደርጋለሁ ተጨዋቾቼን አምናቸዋለሁ ያላቸውን ሁሉ እንደሚሰጡ አውቃለሁ።

- ለጨዋታው ዝግጁ ነን በራሳችን እናምናለን የፍፃሜ ጨዋታው የውድድር አመቱ በጣም አስፈላጊው ጨዋታ ነው።

- በደንብ ጊዜ ወስደን ለጨዋታው ተዘጋጅተናል መልበሻ ቤት ዝግጁ መሆኑን ተመልክቻለሁ ጨዋታው በጥሩ መልኩ እንደሚሄድ ተስፋ አለኝ።"ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የክርስትያኖ ሮናልዶ የአል ናስር ቆይታ ?

ፖርቹጋላዊው የአምስት ጊዜ ባሎን ዶር አሸናፊ ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ በሚቀጥለው የውድድር ዘመን በአል ናስር ቤት እንደሚቆይ የክለቡ ሀላፊዎች አረጋግጠዋል።

የሳውዲ አረቢያ ሊግ የአንድ የውድድር አመት ብዙ ግብ የማስቆጠር ሪከርድን የሰበረው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በግሉ ስኬታማ የውድድር አመትን ማሳለፍ ችሏል።

ይሁን እንጂ ፖርቹጋላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከክለቡ ጋር ዋንጫ ማሳካት ሳይችል አመቱን ለማጠናቀቅ ተገዷል።

ሮናልዶ በውድድር ዘመኑ ለአል ናስር ባደረጋቸው ሀምሳ አንድ ጨዋታዎች ሀምሳ ግቦች አስቆጥሮ አስራ ሶስት አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ በቀጣይ ከሀገሩ ፖርቹጋል ጋር በ2024 ቱ የጀርመን አውሮፓ ዋንጫ ውድድር የሚሳተፍ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዩናይትድ በክረምቱ ምን ሊያስፈርም ይችላል ?

በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ የሚመራው ማንችስተር ዩናይትድ በሚቀጥለው ክረምት የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት የተከላካይ ክፍሉን ለማጠናከር ማሰባቸው ተገልጿል።

ቀያዮቹ ሴጣኖች በቀጣይ ክረምት የዝውውር መስኮት ሁለት የመሐል ተከላካዮች ለማስፈረም እንቅስቃሴ እንደሚያደርጉ ተነግሯል።

ክለቡ አንድ የግራ መስመር እና አንድ የቀኝ መስመር ተከላካይ ለማስፈረም እንደሚሰራ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-SPORT
ማድሪድ በሜዳው የፍፃሜ ጨዋታውን ያስመለክታል ! ሪያል ማድሪድ ከዶርትመንድ ጋር የሚያደርገውን የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ ወደ ለንደን ተጉዘው መመልከት ላልቻሉ ደጋፊዎች በሳንቲያጎ በርናቦ ስታዲየም እንዲመለከቱ ማዘጋጀቱ ተገልጿል። ክለቡ ሳንቲያጎ በርናቦ ስታዲየም ሜዳ ላይ ግዙፍ የጨዋታ መመልከቻ ስክሪኖችን በማዘጋጀት ለደጋፊዎቹ ክፍት እንደሚያደርግ አሳውቋል። ጨዋታውን በስታዲየሙ ተገኝቶ…
የበርናቦ ስታዲየም መግቢያ ትኬት ዋጋ ጨመረ !

ሪያል ማድሪድ ዛሬ ምሽት ከዶርትመንድ ጋር የሚያደርገውን የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ በሳንቲያጎ በርናቦ ስታዲየም በስክሪን ለመመልከት የትኬት ዋጋ መናሩ ተገልጿል።

የዛሬ ምሽቱን ጨዋታ በሳንቲያጎ በርናቦ ስታዲየም ለመታደም የመግቢያ ትኬቶች በከፍተኛ ደረጃ በመጨመር 275 ዩሮ በመሸጥ ላይ መሆናቸው ተነግሯል።

ጨዋታውን ለመመልከት እስከ 80,000 የሚደርሱ የሪያል ማድሪድ ደጋፊዎች በስታዲየሙ ሊገኙ እንደሚችሉ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" የእኛም ተጨዋቾች ፕሮፌሽናል ናቸው " - ገብረ መድህን ኃይሌ

👉🏻 “ አንድ ተጫዋች ቀንሰን ሰኞ እንጓዛለን “

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በቀጣይ ከሜዳው ውጪ በሚያደርጋቸው የአለም ዋንጫ ማጣርያ የምድብ ጨዋታዎች ዙሪያ የቡድኑ አሰልጣኝ ገብረ መድህን ኃይሌ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ለማጣሪያ ጨዋታዎቹ ጥሪ ቀርቦላቸው በዝግጅት ላይ ከሚገኙ ተጨዋቾች መካከል ብሔራዊ ቡድኑ #አንድ ተጨዋች በመቀነስ ወደ ስፍራው እንደሚያቀና አሰልጣኙ ገልጸዋል።

አሰልጣኝ ገብረ መድህን ኃይሌ በቆይታቸው ወቅት ከጋዜጠኞች የተለያዩ ጥያቄዎች ቀርበውላቸው ምላሽ የሰጡ ሲሆን ከእነዚህም መካከል :-

- " የተጋጣሚያችን ተጨዋቾች በታላላቅ ሊጎች መጫወታቸው ጫና አይፈጥርብንም ይህን መላመድ ይገባናል የእኛም ተጫዋቾች ፕሮፌሽናል ናቸው።

- በዝግጅታችን ወቅት የአሸናፊነት ስነልቦና እና የማዋሀድ ስራ ላይ ስንሰራ ቆይተናል።

- መድህን አሁን በጥሩ ሁኔታ ላይ ነው በተከታታይ እያሸነፈ ነው ለብሔራዊ ቡድኑ በራስ መተማመን ይጨምራል ፣ የአሸናፊነት መንፈስ ተፅዕኖ በተጨዋች ብቻ ሳይሆን በአሰልጣኝም ይኖራል።

- ኢትዮጵያ መድህን መሰረታዊ ለውጥ ነው ያመጣው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም በቀጣይ መሰረታዊ ለውጥ ያመጣል ብዬ አስባለሁ።

- ሱራፌል ዳኛቸው  ያለበትን ወቅታዊ አቋም ማወቅ ስላልቻለን በዚህ ጥሪ ልንዘለው ችለናል።

- አቤል ያለው ግብፅ ነው የሚጫወተው የተጫወተባቸው ጊዜያት ብዙ አልነበሩም የተጫወተው ጥቂት ደቂቃ ነው አለመጫወቱ ራሱ ተፅዕኖ አለው።"ብለዋል።

ብሔራዊ ቡድኑ ወደ ስፍራው መቼ ይጓዛል ?

ብሔራዊ ቡድኑ የፊታችን ሰኞ የማጣሪያ የምድብ ሶስተኛ ጨዋታውን ወደሚያደርግበት ጊኒ ቢሳው እንደሚያቀኑ አሰልጣኝ ገብረ መድህን ኃይሌ ገልጸዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቼልሲ ተጨዋች ለማስፈረም ተቃርበዋል !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ እንግሊዛዊውን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ቶሲን አዳራብዮ ከፉልሀም በነፃ ዝውውር ለማስፈረም መቃረባቸው ተገልጿል።

ኒውካስል ዩናይትድ ተጫዋቹን ለማስፈረም በመስራት ላይ የሚገኙ ቢሆንም ሰማያዊዎቹ ዝውውሩን ለማጠናቀቅ መቃረባቸው ተዘግቧል።

ቼልሲን በሀላፊነት ለመረከብ ከስምምነት የደረሱት አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ቶሲን አዳራብዮ የክለቡ የመጀመሪያ ፈራሚያቸው እንደሚሆን ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የማድሪድ ተጨዋቾች ስንት ትኬቶች ያገኛሉ ?

የሪያል ማድሪድ ተጨዋቾች ለምሽቱ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ ሁለት ነፃ የስታዲየም መግቢያ ትኬቶች እንደሚሰጣቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም #ሰላሳ በገንዘብ የሚቀርቡ የስታዲየም መግቢያ ትኬቶች አጠቃላይ ሰላሳ ሁለት ትኬቶች ለተጨዋቾቹ እንደሚቀርብላቸው ተነግሯል።

እያንዳንዱ የሪያል ማድሪድ ተጨዋች ለስታዲየም መግቢያ ትኬቶች 12,300 ዩሮ ወጪ ማድረጋቸው ሲገለፅ ሁሉንም ትኬቶች ለቤተሰባቸው እና ጓደኞቻቸው መስጠታቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዛሬ ምሽት የሚደረገውን የሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ ግዮን ሆቴል ከልዩ ምግብ እና መጦጦች እንዲሁም በዓለምአቀፍ ዲጄ ከታጀበ ሙዚቃ ጋር በ360 ዲግሪ ስክሪኖች ጨዋታውን ሊያስመለክታችሁ እናንተን  እየጠበቀ ይገኛል!።

ይህንን ድንቅ ጨዋታ ከሄኒከን ጋር እየተዝናን አብረን እንመልከት!
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
Dortmund - Real Madrid
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
2024/11/16 11:10:38
Back to Top
HTML Embed Code: