Telegram Web Link
Forwarded from HEY Online Market
•PlayStation 5
•Playstaion 5 Slim

•PlayStation 4 Slim
•PlayStation 4 Pro

•Playstaion portal
•PlayStation VR

Contact
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
ሮናልዶ የሳውዲ ሊግ ሪከርድ ሰብሯል !

ፖርቹጋላዊው የአል ናስር የፊት መስመር ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ የሳውዲ አረቢያ ሊግ በአንድ የውድድር አመት ብዙ ግብ የማስቆጠር ሪከርድ መስበር ችሏል።

ትላንት ምሽት አል ናስር አል ኢትሀድን 4ለ2 ባሸነፈበት ጨዋታ ሁለት ግቦች ያስቆጠረው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በውድድር አመቱ ያስቆጠራቸውን የሊግ ግቦች ሰላሳ አምስት አድርሷል።

የሳውዲ አረቢያ ሊግ በአንድ የውድድር አመት ብዙ ግብ የማስቆጠር ሪከርድ ከዚህ በፊት በሰላሳ አራት ግቦች በሀምዳላህ የተያዘ ነበር።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ በውድድር አመቱ ሰላሳ አምስት የሊግ ግቦች አስቆጥሮ አስራ አንድ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

የአምስት ጊዜ ባሎን ዶር አሸናፊው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በአራት የተለያዩ ሊጎች የሊጉ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ በመሆን ያጠናቀቀ የመጀመሪያው ተጨዋች መሆን ችሏል።

@tikvahethsport            @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ቼልሲ ማንን በሀላፊነት ይሾማል ? ከአሰልጣኝ ማውሪስዮ ፖቼቲኖ ጋር የተለያዩት ቼልሲዎች ስማቸው ከበርካታ አሰልጣኞች ጋር ሲያየዝ ቢቆይም የመጨረሻ እጩዎቹ ከታወቁ ሰንብቷል። አስቀድሞ እጩ የነበሩት የ 38ዓመቱ ኬረን ማኬና የመጨረሻ ዝርዝር ውስጥ #ሳይካተቱ መቅረታቸው ተዘግቧል። የቅጥር የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ እንደሚገኙ የተገለፀው ቼልሲዎች ኢንዞ ማርሴካ እና ቶማስ ፍራንክ ክለቡን ለመረከብ የቀረቡ…
ቼልሲ ኢንዞ ማሬስካን በሀላፊነት ሊሾሙ ነው !

ከአሰልጣኝ ማውሪስዮ ፖቼቲኖ ጋር የተለያዩት ቼልሲዎች የሌስተር ሲቲውን አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካን በሀላፊነት ለመሾም መቃረባቸው ተገልጿል።

አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ቼልሲን መቀላቀል እንደሚፈልጉ ለክለባቸው ማሳወቃቸው ሲገለፅ ሌስተር ሲቲ ከቼልሲ ጋር እንዲነጋገሩ ፍቃድ መስጠቱም ታውቋል።

ቼልሲዎች በቀጣይ ለአሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ የአምስት አመት ኮንትራት ለመስጠት ማሰባቸው ተገልጿል።

ሌስተር ሲቲዎች ከቼልሲ የካሳ ክፍያ እንደሚያገኙ ሲገለፅ የአሰልጣኙ ዝውውር በዚህ ሳምንት ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሰማያዊዎቹ በዝውውር መስኮቱ ይሳተፋሉ !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ በክረምቱ የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ትልልቅ ዝውውሮች ሊያደርጉ እንደሚችሉ ተገልጿል።

ሰማያዊዎቹ በዝውውር መስኮቱ ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ማሰባቸው ሲገለፅ አንድ ወይም ሁለት ጥሩ የመሐል ተከላካይ ለማስፈረም እንደሚንቀሳቀሱም ተዘግቧል።

በተጨማሪም ቼልሲዎች የፊት መስመራቸውን ለማጠናከር በትኩረት ለመስራት መዘጋጀታቸው ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኩርቱዋ ለብሔራዊ ቡድኑ ጥሪ አልቀረበለትም !

የሪያል ማድሪዱ ግብ ጠባቂ ቲቡዋ ኩርቱዋ በቤልጅየም ብሔራዊ ቡድን የ2024 አውሮፓ ዋንጫ ውድድር ስብስብ ውስጥ ሳይካተት ቀርቷል።

በአሰልጣኝ ዶሜኒኮ ቴዴስኮ የሚመራው የቤልጅየም ብሔራዊ ቡድን በቀጣዩ የጀርመን አውሮፓ ዋንጫ የሚጠቀመውን የቡድን ስብስብ አሳውቋል።

ሙሉ የቡድን ስብስቡ ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አዳም ላላና ወደ ሳውዝሀምፕተን ሊያመራ ነው !

እንግሊዛዊው የብራይተን የመሐል ሜዳ ተጨዋች አዳም ላላና በቀጣይ ወደ ቀድሞ ክለቡ ሳውዝሀምፕተን ሊያመራ መሆኑ ተገልጿል።

በብራይተን ቤት ስድስት አመታትን ያሳለፈው አዳም ላላና በዚህ ክረምት ውሉ ሲጠናቀቅ ክለቡን እንደሚለቅ ማሳወቁ ይታወቃል።

የቀድሞ የሊቨርፑል የመሐል ሜዳ ተጨዋች አዳም ላላና አሁን ላይ ዝውውሩ ባይጠናቀቅም የቀድሞ ክለቡን ሳውዝሀምፕተን ከአስር አመታት በኋላ ይቀላቀላል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ግሪንውድ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ተብሏል !

ሜሰን ግሪንውድ የላሊጋው ክለብ ሄታፌ የውድድር አመቱ ምርጥ ተጨዋች ተብሎ መመረጡ ይፋ ተደርጓል።

ሜሰን ግሪንውድ በውድድር አመቱ ለሄታፌ ባደረጋቸው ጨዋታዎች አስር ግቦች አስቆጥሮ ስድስት ለግብ የሆኑ ኳሶች አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

የውድድር አመቱን ከማንችስተር ዩናይትድ በውሰት ለሄታፌ በመጫወት ያሳለፈው ሜሰን ግሪንውድ በቀጣይ በሄታፌ እንደማይቀጥል ማሳወቁ አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አጓጊው ሪያል ማድሪድ ከ ዶርትሙንድ የሚያደርጉት የሻምፒየንስ ሊጉ ፍፃሜ ጨዋታ ተቃርቧል!
ይህንን አጓጊ ጨዋታ አሸንፎ ማን የዋንጫው ባለቤት የሚሆን ይመስላችኋል? ይገምቱ!

ከሄኒከን ጋር አብረን እንመልከት
Forwarded from WANAW SPORT
📢 የአጋርነት ጥሪ ለስፖርት ዝግጅቶችና ፌስቲቫል አዘጋጆች!

👉🏾 በሀገራችን ብሎም በተለያዩ የዓለማችን ክፍላት የተለያዩ የስፖርት አልባሳትን እያቀረበ የሚገኘው ዋናው ስፖርት ለስፖርት ዝግጅቶችና ፌስቲቫል አዘጋጆች ጋር ለተለያዩ የስፖርት ውድድሮች የሚሆኑ አልባሳትን በ5% ቅናሽ ከማቅረብ ጀምሮ በጋራ አብሮ ለመስራት ሙሉ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ሊያበስርዎ ይወዳል።

👉🏾 #ያናግሩን#ውድድርዎን ከእኛ ጋር ያከናውኑ!

🔥 #ውድድር ካለ #ዋናው አለ! 🔥

📍አድራሻችን:- ገርጂ መብራት ሃይል የካቲት ወረቀት ፊትለፊት፣ አለም ገብሬ ህንፃ፣ 2ተኛ ፎቅ።

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 0901138283፣ 0910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ወይም በቴሌግራም ቦት @WANAWSbot በኩል ይዘዙን።

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
አንቾሎቲ ስራቸውን በማድሪድ ማጠናቀቅ ይፈልጋሉ !

አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ የአሰልጣኝነት ስራቸውን በሪያል ማድሪድ ቤት የማጠናቀቅ እቅድ እንዳላቸው በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል።

ጣልያናዊው አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ በንግግራቸውም " አሰልጣኝነቴን በሪያል ማድሪድ ቤት አጠናቅቃለሁ ነገርግን መጀመሪያ ሌላ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ማሸነፍ እፈልጋለሁ።"ብለዋል።

በሪያል ማድሪድ እስካለሁ በአሰልጣኝነቴ እቀጥላለሁ ያሉት አሰልጣኙ የአሰልጣኝነት ህይወቴ የሚያበቃው ግን እዚሁ ሪያል ማድሪድ ነው በማለት ገልጸዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ቼልሲ ኢንዞ ማሬስካን በሀላፊነት ሊሾሙ ነው ! ከአሰልጣኝ ማውሪስዮ ፖቼቲኖ ጋር የተለያዩት ቼልሲዎች የሌስተር ሲቲውን አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካን በሀላፊነት ለመሾም መቃረባቸው ተገልጿል። አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ቼልሲን መቀላቀል እንደሚፈልጉ ለክለባቸው ማሳወቃቸው ሲገለፅ ሌስተር ሲቲ ከቼልሲ ጋር እንዲነጋገሩ ፍቃድ መስጠቱም ታውቋል። ቼልሲዎች በቀጣይ ለአሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ የአምስት አመት ኮንትራት…
ቼልሲ አሰልጣኝ ለመሾም ተስማማ !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ የሌስተር ሲቲውን አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካን በሀላፊነት ለመሾም ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ በሰማያዊዎቹ ቤት ለአንድ ተጨማሪ አመት የማራዘም አማራጭ ያካተተ የአምስት አመት ኮንትራት ይፈርማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በዚህ አመት ከአንድ አመት በኋላ ወደ ፕርሚየር ሊግ የተመለሱት ሌስተር ሲቲዎች ከቼልሲ የካሳ ክፍያ እንደሚያገኙ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ማስፈረም የምንፈልገው ታላላቅ ከዋክብቶችን ነው "

የሳውዲ አረቢያ ሊግ ስፖርት ዳይሬክተር ሜሼል ኤሜናሎ ሳውዲ አረቢያ በቀጣይ ለማስፈረም የምትጥረው በምርጥ አቋም ላይ የሚገኙ ከዋክብትን እንደሚሆን ገልጸዋል።

" ሳውዲ አረቢያ በቀጣይ በትልቅ ደረጃ ያሉ ከዋክብትን ለመሳብ ትጥራለች " ያሉት ሀላፊው የሳውዲ ሊግ ፍላጎት እንደ ኪሊያን ምባፔ እና ኤርሊንግ ሀላንድ አይነት ትልቅ ተጨዋቾችን መስፈረም ነው ብለዋል።

ሀላፊው አክለውም " ቀጣይ የምናስፈርመው እድሚያቸው የገፋ ተጨዋቾች ሳይሆን በምርጥ አቋም ላይ የሚገኙ ተጨዋቾችን ነው " ያሉ ሲሆን ዝውውሮችን በጥንቃቄ እንፈፅማለን ሲሉም ተደምጠዋል።

የሳውዲ አረቢያ ሊግ በቀጣይ የሚፈለገውን ነገር ያመጣል ብሎ ያመነበትን ተጨዋች የቱንም ያህል ገንዘብ የሚያሶጣ ቢሆን ለማስፈረም ጥረት እንደሚያደርግ ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
Malmo - Elfsborg
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
🏆 የአውሮፓ ኮንፈረንስ የዋንጫ ጨዋታ💥

⚽️ Olympiacos vs Fiorentina ረቡዕ ግንቦት 21 ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት በSSFootballFinal 222 ሜዳ ፓኬጅ ላይ

🔥 ዋንጫው የማን ነው? 

👉 ይህንን ደማቅ ፍልሚያ በSS Football 222 በሜዳ ለመከታተል ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ           

የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://mydstv.onelink.me/vGln/eth2

#EuropaConferenceLeagueAllonDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #GreatestFootballSeason
ክቫራትሼሊያ ወደ ፒኤስጂ ?

ጆርጂያዊው የናፖሊ የፊት መስመር ተጨዋች ክቫራትሼሊያ ከፈረንሳዩ ክለብ ፒኤስጂ የዝውውር ጥያቄ እንደቀረበለት ወኪሉ ገልጿል።

ፒኤስጂ ክቫራትሼሊያን ለማስፈረም እንደሚፈልግ እና ጥያቄም ማቅረቡን የገለፀው ወኪሉ አያይዞም ሁሉም ነገር የሚወሰነው በናፖሊው ፕሬዝዳንት ዲ ላውረቲስ መሆኑን ጠቁሟል።

ከፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ ጋር የተለያየው ፒኤስጂ በቀጣይ ትልልቅ ዝውውሮች ሊያደርግ እንደሚችል መዘገቡ አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቲሞ ቨርነር በቶተንሀም ሊቆይ ነው !

ጀርመናዊው የፊት መስመር ተጨዋች ቲሞ ቨርነር ለተጨማሪ አንድ የውድድር አመት በሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም ቤት ሊቆይ መሆኑ ተገልጿል።

ቶተንሀም ያለፉትን ወራት በውሰት በቡድናቸው ያሳለፈው ቲሞ ቨርነር ለተጨማሪ አመት ለማቆየት ከቡንደስሊጋው ክለብ ሌፕዚግ ጋር ንግግር ላይ መሆናቸው ተዘግቧል።

የ 27ዓመቱን የፊት መስመር ተጨዋች ቲሞ ቨርነር በቶተንሀም ቤት እስከ 2025 ክረምት ወር እንደሚቆይ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ማድሪድን የማስቆሚያ ጊዜው አሁን ነው " ቴርዚች

የቦርስያ ዶርትመንዱ ዋና አሰልጣኝ ኤዲን ቴርዚች የሪያል ማድሪድን የሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ተከታታይ ድል ግስጋሴ የማስቆሚያ ትክክለኛው ጊዜ አሁን መሆኑን ገልጿል።

" የሪያል ማድሪድ የስምንት ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ስምንት ድል ግስጋሴ ማብቂያ ጊዜው አሁን ነው " ያሉት አሰልጣኙ " ፍፃሜ መድረሳችን አላረካንም ዋንጫውን ወደ ዶርትመንድ መውሰድ እንፈልጋለን " ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ጋርዲዮላ በኮምፓኒ የሙኒክ ዜና መደሰታቸውን ገለፁ ! የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ እውነት ሆኖ የሚሳካ ከሆነ ቪንሴንት ኮምፓኒ ባየር ሙኒክን በሀላፊነት ለመረከብ መቃረቡ እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል። " እውነት ሆኖ ከተረከበ ዜናውን ስሰማ በጣም ተደስቻለሁ " ያሉት ፔፕ ጋርዲዮላ " ስለ ስራው ፣ ባህሪው እና የጨዋታ እውቀቱ ጥሩ አስተያየት አለኝ ትልቅ ነገር እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ…
ጋርዲዮላ ኮምፓኒን ለሙኒክ መምረጡ ተገለጸ !

የጀርመን ቡንደስሊጋው ክለብ ባየር ሙኒክ ቪንሴንት ኮምፓኒን በአሰልጣኝነት እንዲሾም የማንችስተር ሲቲው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ምክረ ሀሳብ መስጠታቸው ተገልጿል።

የባየር ሙኒክ ቦርድ ዳይሬክተር ሩሜንጌ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ቪንሴንት ኮምፓኒን እንዲመርጡ እንደረዷቸው የገለፁ ሲሆን ኮምፓኒ ትልቅ ተሰጥኦ እንዳለው ነግሮናል ብለዋል።

" አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ቪንሴንት ኮምፓኒን በደንብ ያውቀዋል ስለእሱ ለእኛ የነገረን አስተያየት ከከፍተኛ አድናቆት ጋር ነበር።"ሩሜንጌ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/09/28 05:20:50
Back to Top
HTML Embed Code: