Telegram Web Link
ኦሲሜን በጉዳት ከናይጄሪያ ስብስብ ውጪ ሆነ !

ናይጄሪያዊው የፊት መስመር ተጨዋች ቪክቶር ኦሲሜን ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት ከናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድን ስብስብ ውጪ መሆኑ ተገልጿል።

የናፖሊው የፊት መስመር አጥቂ ቪክቶር ኦሲሜን ያጋጠመው ጉዳት ቢያንስ ለአራት ሳምንታት ከሜዳ ሊያርቀው እንደሚችል ተነግሯል።

የናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድን በቀጣይ ከቤኒን እና ደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ ቡድኖች ጋር የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታውን ያደርጋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የላሊጋ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል ? በሪያል ማድሪድ አሸናፊነት የተጠናቀቀው የስፔን ላሊጋ የ2023/24 የውድድር አመት ምርጥ ተጨዋች አስር እጩዎች ይፋ ተደርገዋል። በዚህም መሰረት :- - ጁድ ቤሊንግሃም (ሪያል ማድሪድ) - ቪንሰስ ጁኒየር (ሪያል ማድሪድ) - ኩቦ ( ሪያል ሶሴዳድ ) - ግሪዝማን ( አትሌቲኮ ማድሪድ ) - ዶቭቢክ ( ጂሮና ) - ኪሪያን (ላስ ፓልማስ)…
ቤሊንግሀም የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ተብሏል !

በሪያል ማድሪድ አሸናፊነት የተጠናቀቀው የስፔን ላሊጋ የ2023/24 የውድድር ዘመን የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ይፋ ተደርጓል።

በዚህም መሰረት የሪያል ማድሪዱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ጁድ ቤሊንግሀም የላሊጋ የውድድር አመቱ ምርጥ ተጨዋች በመሆን መመረጥ ችሏል።

ጁድ ቤሊንግሀም በውድድር አመቱ አስራ ዘጠኝ ግቦች ማስቆጠር ሲችል ስድስት ለግብ የሆኑ ኳሶችም አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

ቤሊንግሀም ከሽልማቱ በኋላ " ለዚህ ሽልማት አመሰግናለሁ ለክለቤ ፣ ለቡድን አጋሮቼ እና ድምፅ ለሰጡኝ ሁሉ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።"ሲል ተናግሯል።

በተጨማሪም :-

- የጂሮናው ዋና አሰልጣኝ ሜቼል የላሊጋ የውድድር አመቱ ምርጥ አሰልጣኝ

- የባርሴሎናው የፊት መስመር ተጨዋች ላሚን ያማል የላሊጋው የውድድር አመቱ ምርጥ ወጣት ተጨዋች ሆነው ተመርጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ቲሞ ቨርነር በቶተንሀም ሊቆይ ነው ! ጀርመናዊው የፊት መስመር ተጨዋች ቲሞ ቨርነር ለተጨማሪ አንድ የውድድር አመት በሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም ቤት ሊቆይ መሆኑ ተገልጿል። ቶተንሀም ያለፉትን ወራት በውሰት በቡድናቸው ያሳለፈው ቲሞ ቨርነር ለተጨማሪ አመት ለማቆየት ከቡንደስሊጋው ክለብ ሌፕዚግ ጋር ንግግር ላይ መሆናቸው ተዘግቧል። የ 27ዓመቱን የፊት መስመር ተጨዋች ቲሞ ቨርነር በቶተንሀም ቤት…
ቲሞ ቨርነር በቶተንሀም እንደሚቆይ ይፋ ሆነ !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም ጀርመናዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ቲሞ ቨርነር ለተጨማሪ አንድ የውድድር አመት በውሰት ለማቆየት ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ቶተንሀም ተጫዋቹን በሚቀጥለው ክረምት የውሰት ውሉ ሲጠናቀቅ በአስራ ስድስት ሚልዮን ዩሮ የማስፈረም አማራጭ እንዳላቸው ተገልጿል።

የ 27ዓመቱን የፊት መስመር ተጨዋች ቲሞ ቨርነር ባለፈው ጥር ከጀርመኑ ክለብ ሌፕዚግ በውሰት ቶተንሀምን መቀላቀሉ ይታወሳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አቤል ያለው ቡድኑ እንዲያሸንፍ ረድቷል !

ለግብፁ " ZED " እግርኳስ ክለብ በመጫወት ላይ የሚገኘው ኢትዮጵያዊው የፊት መስመር አጥቂ አቤል ያለው ክለቡ ወደ ቀጣዩ ዙር ሲያልፍ ቁልፍ ሚናን መጫወት ችሏል።

በግብፅ ካፕ ጥሎ ማለፍ ጨዋታ " ZED " እግርኳስ ክለብ ኤል ዳክሌያን 2ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ አስራ ስድስቱን መቀላቀል ችለዋል።

በጨዋታው የ " ZED " እግርኳስ ክለብን የአቻነት ግብ ሙስጠፋ ዚኮ በመጨረሻ ደቂቃ ሲያስቆጥር ኢትዮጵያዊው የፊት መስመር ተጨዋች አቤል ያለው በጥሩ ሁኔታ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
•PlayStation 5
•Playstaion 5 Slim

•PlayStation 4 Slim
•PlayStation 4 Pro

•Playstaion portal
•PlayStation VR

Contact
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
በቤቲካ ፋስታ ወዲያው ያሸንፉ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
" ዋንጫ እንደምናሸንፍ እናምናለን " አርቴታ

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ትላንት ምሽት የግሎብ ሶከር የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የአመቱ ምርጥ አሰልጣኝ በመሆን ተመርጠዋል።

ከሽልማቱ በኋላ ስለ ቡድናቸው የወደፊት እቅድ አስተያየታቸውን የሰጡት አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ " የምንፈልገው ማሸነፍ እና ማሸነፍ ብቻ ነው " ሲሉ ተደምጠዋል።

አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ቀጥለውም " ቡድናችን ዋንጫዎችን ለማሸነፍ በመጓጓት ውስጥ ያለ እና ዋንጫ የራበው ነው በቀጣይ እንደምናሳካው እናምናለን " ሲሉ ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ባርሴሎና አዲስ አሰልጣኝ ሊሾም ነው ! ከአሰልጣኝ ዣቪ ሀርናንዴዝ ጋር እንደሚለያይ ያሳወቀው የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና በምትካቸውም አዲስ አሰልጣኝ ለመሾም ከስምምነት መድረሱ ተገልጿል። ባርሴሎና የቀድሞውን የጀርመን ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሀንሲ ፍሊክ በሀላፊነት ለመሾም መቃረባቸው ተገልጿል። አሰልጣኝ ሀንሲ ፍሊክ ባርሴሎናን ለሁለት የውድድር አመታት ለማሰልጠን ፊርማቸውን እንደሚያኖሩ ተዘግቧል።…
ሀንሲ ፍሊክ ወደ ባርሴሎና አምርተዋል !

ከስፔናዊው አሰልጣኝ ዣቪ ሀርናንዴዝ ጋር የተለያየው የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና አሰልጣኝ ሀንሲ ፍሊክን በሀላፊነት ለመሾም ተቃርበዋል።

የቀድሞ የጀርመን ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሀንሲ ፍሊክ ትላንት ምሽት ወደ ባርሴሎና ያመሩ ሲሆን ከባርሴሎና ሀላፊዎች ጋር የእራት ጊዜ እንደነበራቸው ተገልጿል።

አሰልጣኝ ሀንሲ ፍሊክ ባርሴሎናን ለሁለት የውድድር አመታት ለማሰልጠን በዛሬው ዕለት ፊርማቸውን እንደሚያኖሩ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ለቲያጎ ሲልቫ አቀባበል በርካታ ትኬቶች ተሸጡ !

ብራዚላዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ቲያጎ ሲልቫ ከቼልሲ ጋር በመለያየት ወደ ልጅነት ክለቡ ፍሉሚኔንሴ ለመመለስ ፊርማውን ማኖሩ ይታወሳል።

ከአስራ አራት አመታት በኋላ ወደ ልጅነት ክለቡ ፍሉሚኔንሴ የሚመለሰው ቲያጎ ሲልቫ በሚቀጥለው ሳምንት አርብ በክለቡ ደማቅ አቀባበል እንደሚደረግለት ተገልጿል።

በማራካኛ ስታዲየም ለቲያጎ ሲልቫ በሚደረገው አቀባባል ላይ ለመገኘት እስካሁን 40,000 ተመልካቾች ትኬቶችን መግዛታቸውን ክለቡ አስታውቋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሰር ጂም ራትክሊፍ ምን አይነት ህግ ሊያወጡ ነው ?

የማንችስተር ዩናይትድ አነስተኛ ድርሻ ባለቤት እንግሊዛዊው ቢሊየነር ሰር ጂም ራትክሊፍ በቀጣይ በክለቡ ውስጥ አዲስ ህገ ደንብ ሊያወጡ መሆኑ ተገልጿል።

ከዚህ በፊት በሰጡት አስተያየት ትልቅ ተጨዋች ከማስፈረም ይልቅ ተጨዋቾችን ታላቅ ማድረግ እንደሚመርጡ የተናገሩት ቢሊየነሩ ትልቅ ተጨዋች ላለማስፈረም በህጉ ውስጥ ማካተታቸው ተነግሯል።

ራትክሊፍ የሚያወጧቸው ህጎች ምን ይመስላሉ ?

- አዲስ ፈራሚዎች እድሜ ከሀያ አምስት አመት በታች የሆነ።

- አዲስ የሚፈርሙ ተጨዋቾች ስመጥር ተጨዋች ያልሆኑ።

- የቡድኑ የአጨዋወት ባህሪ በክለቡ ቴክኒካል ዳይሬክተር ጄሰን ዊሎክስ ይወሰናል።

- አሰልጣኙ እድሜአቸው ከ25 ዓመት በታች የሆኑ 5 ተጨዋቾችን ከአካዳሚ ወደ ዋናው ቡድን ማሳደግ ይኖርበታል።

- አሰልጣኙ አዲስ ተጨዋች የሚፈልጉበትን የሜዳ ክፍል እንጂ ተጨዋች መምረጥ አይችሉም።

- ባለቤቶቹ አሰልጣኙ እንዲመርጥ የሶስት ተጨዋች ስም ይልካሉ አሰልጣኙ ከተለኩ ስሞች የሚፈልጉትን ይመርጣል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ኤደርሰን ማንችስተር ሲቲን ሊለቅ ይችላል ! ብራዚላዊው የማንችስተር ሲቲ ግብ ጠባቂ ኤደርሰን በሚቀጥለው ክረምት የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ክለቡን ሊለቅ እንደሚችል ተገልጿል። የሳውዲ አረቢያ ክለቦች አሁን ላይ ብራዚላዊውን ግብ ጠባቂ ኤደርሰን ለማስፈረም ፍላጎት እንዳላቸው ተነግሯል። ተጨዋቹ ጥሩ የዝውውር ጥያቄዎች ከቀረቡለት በውድድር አመቱ መጨረሻ ለመመልከት ዝግጁ መሆኑ ተዘግቧል። @ti…
የኤደርሰን የማንችስተር ሲቲ ቆይታ ?

ብራዚላዊው የማንችስተር ሲቲ ግብ ጠባቂ ኤደርሰን ከሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ኢትሀድ የዝውውር ጥያቄ እንደቀረበለት እና እያሰበበት እንደሚገኝ ተገልጿል።

ኤደርሰን በክረምቱ የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ጥሩ የዝውውር ጥያቄዎች ከቀረቡለት ማንችስተር ሲቲን ለመልቀቅ ሊያስብ እንደሚችል መገለፁ ይታወቃል።

ማንችስተር ሲቲ በበኩሉ ተጫዋቹ በክለቡ እንዲቀጥል እንደሚፈልጉ የተገለፀ ሲሆን ከዚህ በፊት አቅርበውለት የነበረው አዲስ ውል እንዲፈርም ጥረት እንደሚያደርጉ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ግሪሊሽ ከፔፕ ጋርዲዮላ ጋር መነጋገሩ ተገለጸ !

በተጠናቀቀው የውድድር አመት ጥሩ የሚባል ጊዜን ማሳለፍ ያልቻለው እንግሊዛዊው የማንችስተር ሲቲ ተጨዋች ጃክ ግሪሊሽ ከአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ጋር ለንግግር ተቀምጦ እንደነበር ተገልጿል።

ተጨዋቹ በንግግሩ ወቅት የሚቀጥለው የውድድር አመት ከመጀመሩ በፊት ወደ ቀድሞ አቋሙ በፍጥነት እንዲመለስ እንደተነገረው ተዘግቧል።

ጃክ ግሪሊሽ በክረምቱ የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ማንችስተር ሲቲን የሚለቅበት እድል እንደሌለ ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
📢 ለእግር ኳስ እና ስፖርት አካዳሚዎችና አሰልጣኞች በሙሉ!

በኢትዮጵያ፣ በአፍሪካ ብሎም በተለያዩ የዓለማችን አህጉራት ዘርፈ-ብዙ የስፖርት አልባሳትን የሚያቀርበው ዋናው ስፖርት ከእግር ኳስና ከሌሎች ስፖርት አካዳሚዎች ብሎም አሰልጣኞች ጋር ለህፃን ሰልጣኞች ማልያዎችን በ600 ብር ከማቅረብ ጀምሮ በጋራ አብሮ ለመስራት ሙሉ ዝግጅቱን አጠናቋል።

በመሆኑም ከዋናው ጋር በአጋርነት መስራት የምትፈልጉ በሙሉ ከታች በተቀመጡት አድራሻዎች እንድታገኙን ስንል ጥሪ እናቀርባለን።

📍አድራሻችን:- ገርጂ መብራት ሃይል የካቲት ወረቀት ፊትለፊት፣ አለም ገብሬ ህንፃ፣ 2ተኛ ፎቅ።

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 09011382830910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
" የሲቲ ጋር በድጋሜ ተጫወቱ ብባል አልቀበልም " ቫልቬርዴ

የሪያል ማድሪዱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ፌዴሪኮ ቫልቬርዴ ቡድናቸው ከማንችስተር ሲቲ ጋር የነበረው የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ አስቸጋሪ እንደነበር ገልጿል።

ፌዴ ቫልቬርዴ በንግግሩም " ከማንችስተር ሲቲ ጋር የነበረን ጨዋታ በጣም ከባድ ነበር በጨዋታው ብዙ ተሰቃይቻለሁ ፣ ከሲቲ ጋር በድጋሜ እንድንጫወት ቢነገረኝ አይሆንም ነው የምለው።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሀንሲ ፍሊክ ወደ ባርሴሎና አምርተዋል ! ከስፔናዊው አሰልጣኝ ዣቪ ሀርናንዴዝ ጋር የተለያየው የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና አሰልጣኝ ሀንሲ ፍሊክን በሀላፊነት ለመሾም ተቃርበዋል። የቀድሞ የጀርመን ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሀንሲ ፍሊክ ትላንት ምሽት ወደ ባርሴሎና ያመሩ ሲሆን ከባርሴሎና ሀላፊዎች ጋር የእራት ጊዜ እንደነበራቸው ተገልጿል። አሰልጣኝ ሀንሲ ፍሊክ ባርሴሎናን ለሁለት የውድድር አመታት ለማሰልጠን…
ባርሴሎና በይፋ አሰልጣኝ ሾመ !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና በአሰልጣኝ ዣቪ ሀርናንዴዝ ምትክ ጀርመናዊውን አሰልጣኝ ሀንሲ ፍሊክ በሀላፊነት መሾማቸውን ይፋ አድርገዋል።

የቀድሞ የጀርመን ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሀንሲ ፍሊክ ባርሴሎናን እስከ 2026 የውድድር ዘመን ለማሰልጠን የሁለት አመት ኮንትራት መፈረማቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ታላቁ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ቅዳሜ በጊዮን ሆቴል በትልልቅ 360 ዲግሪ እስክሪኖች ጨዋታውን እንድትመለከቱ ዝግጅታችንን ጨርሰናል:: ይሄንን አጓጊ የፍፃሜ ጨዋታ ከሄኒከን ጋር በጊዮን ሆቴል አብረን እየተዝናናን እንመልከት!

#UCL #Heineken
የዩናይትድ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል

የእንግሊዝ ኤፌ ካፕ ዋንጫን ያሳኩት ማንችስተር ዩናይትዶች የወርሀ ግንቦት የወሩ ምርጥ ተጨዋች #ሶስት እጩዎችን ይፋ አድርገዋል።

በዚህም መሰረት ብሩኖ ፈርናንዴዝ ፣ ኮቢ ማይኖ እና ዲያጎ ዳሎት የአመቱ የመጨረሻ ወር የማንችስተር ዩናይትድ ምርጥ ተጨዋች እጩ ሆነው መቅረብ ችለዋል።

የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አንድሬ ሉኒን ወደ ለንደን ላያመራ ይችላል !

የሪያል ማድሪዱ ግብ ጠባቂ አንድሬ ሉኒን ባጋጠመው የጉንፋን ህመም ምክንያት ለሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ ከቡድኑ ጋር ወደ ለንደን ላያመራ እንደሚችል ተገልጿል።

ሎስ ብላንኮዎቹ የጉንፋን ህመሙ ወደ ሌሎች ተጨዋቾች እንዳይተላለፍ ለመከላከል አንድሬ ሉኒንን እስከ ቅዳሜ ስፔን ውስጥ እንዲቆይ ትተው ለመሄድ ማሰባቸው ተነግሯል።

አንድሬ ሉኒን የሪያል ማድሪድ ቁጥር አንድ ግብ ጠባቂ ቲቧ ኩርቱዋ ጉዳት ያጋጠመው መሆኑን ተከትሎ በውድድር አመቱ ለሪያል ማድሪድ ተሰልፎ ጥሩ የሚባል ጊዜን ማሳለፉ አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ባየር ሙኒክ አሰልጣኝ ለመሾም ተስማማ ! የጀርመኑ ክለብ ባየር ሙኒክ ቤልጂየማዊውን የበርንሌይ ዋና አሰልጣኝ ቪንሴንት ኮምፓኒ በአሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል ምትክ በሀላፊነት ለመሾም ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል። አሰልጣኝ ቪንሴንት ኮምፓኒ በባየር ሙኒክ ቤት እስከ 2027 የሚያቆየውን ውል ለመፈረም ከስምምነት መደረሱ ተዘግቧል። ባየር ሙኒክ ለበርንሌይ ለአሰልጣኙ የካሳ ክፍያ የሚሆን 12 ሚልዮን ዩሮ…
ባየር ሙኒክ በይፋ አሰልጣኝ ሾመ !

የጀርመኑ ክለብ ባየር ሙኒክ ቤልጂየማዊውን አሰልጣኝ ቪንሴንት ኮምፓኒ በአሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል ምትክ በሀላፊነት መሾማቸውን በይፋ አስታውቀዋል።

አሰልጣኝ ቪንሴንት ኮምፓኒ ባየር ሙኒክን ለሶስት የውድድር አመታት ለማሰልጠን እስከ 2027 የሚያቆያቸውን ውል በይፋ ፈርመዋል።

ባየር ሙኒክ ለበርንሌይ ለአሰልጣኙ የካሳ ክፍያ የሚሆን 12 ሚልዮን ዩሮ የሚጠጋ ገንዘብ መክፈላቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/09/28 07:19:32
Back to Top
HTML Embed Code: