Telegram Web Link
የእግዜር ትዝብት
ልቤን እሱ ያቃል ይባላል በድፍን
ለአግዜር እይታ የማይቀርብ ልብ ይዘን
አዎ እሱማ አውቆ ልቋል
እንኳንስ የኛን ልብ አለምን ይገዛል
እኔ ማይገባኝ ግን
ልቤን እሱ ያቃል በምትል ሽንገላ
ከጻድቅ ተመስለን ስንታይ በሌላ
አዎ እሱማ ያቃል
በምላስ ሽንገላ የዕምነት ስንቅ አጊንቶ
ባመነው ልብ ላይ ታማኝነት አጥቶ
በፈገግታዬ ልክ ወዴጁ ጠላቱን
በዕኩል ጥርስ አኝኮ መዋጡን
አዎ እሱማ ያቃል
ልቤ አይሸፍትም ብሎ ተገዝቶ አይኔ ሲማትርም
በሁለቱ እግሮቼ ሁለቱ ዛፎች ላይ ለመውጣት ስመኝም
የቃሌ እምነት ዕዳ ቅንጣት ሳይሰማኝ
በምላስ ድለላ በውሸት ፈገግታ ወዳጄን ሳሞኝ
አዎ እሱ ያቃል
የጥፋት ዱካዬ የረገጠው ሜዳ
የቃላቴ ግለት ቢያመጣ የአምነት ዕዳ
ጥፋቴን ሳላምን ልቤ ቢደነድን ፍፁም ሳልፀፀት
ይቅርታን ብፈልግ ሰው ሞኝ ነውና በምላሴ ቅጥፈት
ይቅርታ ሳይገባኝ ይቅርታ አገኛለው
ልቤን እሱ ያቃል ብዬ ደልላለው

ግና ትዝ ሲለኝ እውነት ያቃል ልቤን
በግፉ ጎተራ የሞላው ሀጢያቴን
ልጓም ባጣ ፈረስ በሀሰት መጋለቤን
ፍቅርና እምነት ከልቤ አርቄ በአንደበት ማሰሬን
አዎ እሱ ያቃል
ይህ ልቤን ስላየው እግዜርም ምናልባት ታዝቦኝ ይሆናል
ልቤን እሱ እሱ ያውቃል ብዬ ስሸነግል
የማይታይ ልቤን እያየው ይሆናል

የአባቡ ልጅ
@kidapoim
Forwarded from Арбитражница dooradas (🌗የግማሽ አለም ጣኦት🌗)
እስስት : ስትጎተትና : ስትቀያየር እንደምትጠላ : አታውቅም : አካሄዷም : ቢሆን ፥ አይኗ : ልቧን : ይመራዋል : እንጅ ልቧ : አይኗን : እንደሚከተለው : አታውቅም.....
ግንኮ : አይን : ያየውን : ለልብ : ካልነገረው : ልብም : አድምጦ : ካላመነበት : አይንን : ይከተለዋልን?

መቼም አንዴ ለጉዞ ፈጥሮኛልና መንገድም : እወድ የለ .....
በጉም : ላይ : እየተረማመድኩ : ሳለ ብቻዬን : አግዜሩን : አግኝቸው : ነበር : በምናባዊ : ፀዳል እንደምናስበው : አደለም : ኮስማና ነው።

እናተ : ሰዎች: ለምን : ትጠሉኛላችሁ : ስለምንስ ከክብሬ : ቁልቁል : አፈረጣችሁኝ : ማቅለላችሁ : ሳይቀር : ለሌሎች : መሳለቂያ : አረጋችሁኝ ፥ ከዙፋኔ እያለሁ : እንደሌለሁ : አበሸቀጣችሁኝ ለምን? ስለምንስ? ተጠራጣሪ : ሆናችሁ : በኔ ለምን? እንባ እንቅ እንባ እንቅ ,,,,,
እያረገው : ሶስት : የእንባ : ዘለላ :ከገፁ ፥ ሲረግፍ እየሁ።

እንባው ፥ ወደስቅለቱ : ትዝታ : እያላጋ : ወሰደን በስቅለቴ : ግዜ አንድ : ደንባራ : ወታደር : በጦር ጎኔን ሲወጋኝ : ህመሙን : አታውቅም : ይሁዳ : በከንፈሮቹ ሀሞት : ተጎንጭቶ : ጉንጨ : ላይ : ሲተፋብኝ : የተሰማኝን : አታውቅም : ጴጥሮስ : ሶስት : ግዜ : አንድ ለአብ አንድ ለወልድ አንድ ለመንፈስቅዱስ ለያንዳንዳችን : በአንድነት : የክህደትን : ኮሶ : ሲያግተን : ምሬቱን : አታውቅም።

40 ቀን 40 ለሊት ስፆም ሰይጣን በእባብ ተመስሎ ሲፈትነኝ የፈጠርኩትን መልሶ የኔ ሊያረጋቸው ሲደራደረኝ ቤተ መቅደሴን ሲሻቀጡበት እናቴን ከቁሻሻ መሀል ትቢያ እንደተደፋ ልቅላቂ ሲጠየፏት አታውቅም።

አዎ አታውቅም ........ እናት ሰዎች ህመሙን አታውቁም .........

የእግዜር እንባ ግን ምን አይነት ነው?

እኔም: ሆድ : ብሶኝ : የልቤን : ዘረገፍኩለት :ጌትዬ : በሁለት : አለም : ሰካር : ውስጥ: አየዳገርኩ: ለምን ዝም አልከኝ? አንተኮ: ብትታመምም : አምላክ ነህ የአምላክነትህ : ባህርይ ረቂቅ : ነው ያስችልሀል::

ግን ለምን ፈጠርከኝ? ማጥ: ረመጥ : ውስጥ : ከተትከኝ? እውነት አውጣኝ : ብዬ : ስለምንህ: ሳትሰማኝ : ቀርተህ ነው?
የህይወትስ ጣዕሙ በምን ይለካል ? በድን : አካልን አሸክመኸኝ : ለአመመታት : መክረሜን ዘንግተኸው ነውን?

እኔ : የነካሁት : ሁሉ : ርኩሰትን : እንዲላበስ : ሁሌ እንድሸሸግ : የምታረገኝ : ራሴን : በራሴው እንደ እፉኝን : ስውጥ አላሳዝንህምን?

የእናትህስ : ህመም : አንተን : ብቻ : የሚቆረቁርህ ይመስልሀል?
እሷኮ : አምጣ : አልወለደችህም : ደም : አልፈሰሳትም
ምነው_ቸሩ _መድሀኔ_አለም : የኔዋ : እናት: ወዝ ወዘናዋን : አጠንፍፋ : ባማጠች : የህመሟን ሲቃ ባስረቀረቀች : አኔን : ወልዳ : እንኳ_ማርያም : ማረችሽ ቢሏት : አንተው : የማርካት መሰለህ? በድኩም : አካሏ : ተንፏቃ : አፈር : ልሳ : ብትለምንህ : መች ምሬሻለው : አልካትና? የማርያም ልጅ...!!

አንተ : ብትፆም :ባህሪህ : ቅዱስ : ነህና : ይፈቅድልሀል እኛስ :አንጀታችን :ሲታለብ :ቆርቆሮ :ቤታችን :ውስጥ : በችጋር : ስንለበለብ :ዞር ብለህ : አይተኸናል : እንዴ?
ቅፅበታዊ : ደስታን : አሳይተህ : ዛላቂያዊ : ህመምን ከልባችን : የቸነከርከው : እውነት : ከሳዶርና ፣ አላዶር የሚተናነሱ : ይመስልሃልን?

ተው : እንጅ : ቤዛ ከሉ መድሀኔ አለም..... ተው እንጅ የማርያም ልጅ!!

ተስፋዬን : በምኞት : ደግፌ : ብጓዝ :ባንተ : አይደል የጨነገፈው : ማያዬ :መመልከቻ : አድማሴን : ባገኛት
ባንተም : አይደል : ያጣኃት? እንደኩታ : አይሽሞንሙነህ : ያለበስከኝ : ይህን :ማንነት አንተም አደል : የፈጠርከው ? ይኸው : እሷም /ወደመሸሹ አጋደለች....
እስቲ : ልወቀው : ጥፋቴን :ለምን : ግራ አርገህ ፈጠርከኝ?
ምን ትለኝ ይሆን? ምንስ ምላሽ ይኖርህ?

ግን ለምን አትወስደኝም? ኖሬ : የህይወት : ጣዕሙንስ በምን :ምላሴ : ላጣጥመው? ምላሴን : ቆርጠህብኝ ......ሳላጣጥመው : ኮመጠጠኝ።

ተፈጥሮ : ፊቱን : አጨፍግጎብኝ : ሳለ : ከነፍሴ የተጣባች : እንስትን : ወዳንተ : ልካኝ : ነበር። አንተ የምድርና ፣ የሰማይ : ጌታ : ሆይ : ቸኮሌት : ላክልኝ ብልሀለች።

ከጥሪው : መዝብ : ሳሟ :ሳይሰፍር : ወደኔ መታ የነበረችው : ማያዬን አወካት?

ለነገሩ : አንተ : ብታቅም : አላቅም :ከማለት : ወደኃላ አትልም...... ብቻ እሷ ታቅሀለች።

በቃና : ዘገሊላ :ግዜ : ውሀውን : ወይን : ጠጅ : አድገህ : ነበር : በሰው : ሰርግ : እንደዚ : የሆክ : በራህ : ሰርግ : እንዴት: ትሆን?
በስቅለትህ : ወቅት : ጎንህን : ሲወጉህ : ውሀ፣ ደም፣ ወተት : ፈሶህ ነበር ።

በመጀመሪያ :ቀን : ማያዬን : ሳገኛት : ውሀ ጠጥታ ነበር ።
በሁለተኛው : ቀን : ስንገናኝ : በተፈጥሮ : ደም እየፈሰሳት :ነበረ ።
በሶስተኛ : ቀን : ፈጣሪ : ቸኮሌት : በኔ : በኩል እንዲልክላት : ጠይቃኝ ነበር።

በቸኮሌት: ውስጥ : ወተቱን : ለማግኘት :ፈልጋለው ይሆናላ....


ቸኮሌቷን : አንድቀን : ይዤላት: እንምመጣ :ታውቅ ይሆን?

አታውመቅም.........

የእግዚአብሄርን : ልጅ : ሰርግ : አይቼ : ከድግሱ : በልቼ ጠጥቼ : መሞቴን : እንኳን : አታውቅም..........


አዎ አታውቅመም.....

አደራ
******ንገሩልኝ******


ሱራፌል ጌትነት
🦋ሱራ ቢራቢሮ🦋
(የግማሽ አለም ጣኦት🌗)

።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
Forwarded from Арбитражница dooradas (🌗የግማሽ አለም ጣኦት🌗)
አታውቅም


።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
Forwarded from የ ዳግም ሔራን ግጥሞች (ሔራ…ቶ…ዳግ) via @like
" ነፍሴ ሆይ እንጃልሽ ! "
ገጣሚ : ዳግም ደጀኔ ( ሔራን)
@dagiamen12
Join and share………………👇👇
@heranawi
@heranawi
@heranawi ይቀላቀሉን 🙏
Forwarded from የ ዳግም ሔራን ግጥሞች (ሔራ…ቶ…ዳግ) via @like
[ ጥበብሽ ነኝ ]
:
ከሞት ከፍ አ‘ርጋ ካለ አሳንሳ፣
በክደት ፍመት መወደዴን ጠብሳ፣
የማጣት ሸማ ደርባ አልብሳ፣
:
ሳፈቅራት ጠልታኝ፣
ስቀርባት ገፍታኝ ርቃ ሄዳለች፤
ለአዲስ ኑረቷ
አዲስ አፍቃሪ ወዳጅ መርጣለች፤
ይሁነኝ ብላ ከመረጠችው
አዲስ ገላ ስር ተለጥፋለች፡፡
ብለህ ምታማኝ፣
አንተ ቆይ ማነህ አንዳፍታ አስረዳኝ!
(ብለሻል አሉ)
:
አቤት አንችዬ
እንደምን ጠፋሽ
እንዴት ተረሳሽ የኔ ማንነት፣
የድኩም ልቤ
ስትኖሪ የመቆም የመፅናት እውነት፣
:
ግና መውደዴ
ካለሽ ንገረኝ
:
እኔኮ ማለት…
ስትሄጅ የምፈርስ ስትመጭ ምሰራ፣
ያንቺው ጥበብ ነኝ፤
ሳጣሽ ደፍርሼ ኖረሽ ምጠራ፡፡
:
…………………………………………………**
[ ገጣሚ ዳግም ሔራን @dagiamen12 ]
Join.and share…………………👇👇
@heranawi
@heranawi
@heranawi ይቀላቀሉን🙏
Forwarded from Арбитражница dooradas (🌗የግማሽ አለም ጣኦት🌗)
ምሽቴን በ( Ali_faraka)

ዘፈን ነውዝ


🌗የግማሽ አለም ጣኦት🌙


።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋
www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋
www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋
www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
Forwarded from የ ዳግም ሔራን ግጥሞች (ሔራ…ቶ…ዳግ)
" ዕልፍ ትንሽ "
ገጣሚ: ዳግም ሔራን
( @dagiamen12)
:
Join and share……………👇👇
@heranawi
@heranawi
@heranawi
Forwarded from የ ዳግም ሔራን ግጥሞች (ሔራ…ቶ…ዳግ)
" ቅፅበትሽ ! "
ገጣሚ: _ ዳግም ሔራን
( @dagiamen12)
:
Join and share………👇👇
@heranawi
@heranawi
@heranawi
Forwarded from የ ዳግም ሔራን ግጥሞች (ሔራ…ቶ…ዳግ)
" የለምን ጥያቄ! "
ገጣሚ: ዳግም ሔራን
( @dagiamen12)
Join and share… ……👇👇
@heranawi
@heranawi
@heranawi
Forwarded from የ ዳግም ሔራን ግጥሞች (ሔራ…ቶ…ዳግ)
" የመለክያ ስህተት "
ገጣሚ: ዳግም ሔራን
( @dagiamen12)
Join and share……………👇👇
@heranawi
@heranawi
@heranawi
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አስናቀችን አማልላለሁ ብዬ!! አዝናኝ ቪዲዮ!

Subscribe for more funny amharic translated vedios.

ለሌሎች አዝናኝና በአማርኛ የተተረጎሙ አዝናኝ ቪዲዮዎች ለማግኘት ሊንኮቹን ይከተሉ!
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

*youtube
https://youtube.com/channel/UC6lhxeXubv3KTAqrOmI7rhQ

*tiktok
https://vm.tiktok.com/ZMRfTvYWA/

*Telegram
www.tg-me.com/poimfitsae
Forwarded from Арбитражница dooradas (🌗የግማሽ አለም ጣኦት🌗)
አልቦ : መጋት : ምን ይሉታል? ምንስ : ይሉት ፥ የአንጀት እከክ : ቢጣባው : ነው?
ደርሶ :ግንፍል ፣ ክብልል የሚያደርገው።

መቼም : ዲያቢሎስ : ሹክ : ብሎት ነው እንጂ.... እንዲህ : ልቡ : የደነደነው።
ልጓሙን : በጥሶ : ያጠጠው .እወነት : ለመገራት : ልቡ : ባይከጅል ነው እንጂ : እውነታው : ሳይገዝፍበት ቀርቶ አደለም።

ሲናውዝ : የዋለው : በከቻ : ስጋውን : ሊያሳርፍ : ከመደቡ : ላይ ዝለታም አካሉን : ጣለው።

ሁፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍ,,,, ተመስገን አለ።

ቤቱ : ግድግዳ : ላይ ኢየሱስ : በመስቀል የተቸነከረበትን : ምስል አንጋጦ : እያየ።

ልቡናው : የተሰለበው : ከእሷ ዘንድ ነበርና : የዛለውስ : ያመሰገነውስ : እሷን በማግኘቱም : አደል።

ጌታን : ያለ : መስቀል : እሷን : ያለ : ሀፍረቷ : ሊስላቸው : መቼ ፈቅዶ!!

ወትሮስ የባተሌ ነገር........

🦋ቅዱስ አርዮስ🦋
🌗የግማሽ አለም ጣኦት🌙

።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
መተሽብኝ ነበር :
ለሊት ላይ በህልሜ፣
አቤት ብዬም ነበር :
ስምሽ መስሎኝ ስሜ፣
ግና ሳልጨርሰው :
ፍቅርን አጣጥሜ፣
ፍጥን እንደ ንፋስ :
እጥር እንደ #ጳጉሜ
..............አልሽብኝ አለሜ ።

Yibest Belay
@kidapoim
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
https://youtu.be/6SSGZzUfm50

ደም ግፊት አለብኝ ፣ ስኳር...!! አዝናኝ ቪዲዮ!

Subscribe for more funny amharic translated vedios.

ለሌሎች አዝናኝና በአማርኛ የተተረጎሙ አዝናኝ ቪዲዮዎች ለማግኘት ሊንኮቹን ይከተሉ!
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

*youtube
https://youtube.com/channel/UC6lhxeXubv3KTAqrOmI7rhQ

*tiktok
https://vm.tiktok.com/ZMRfTvYWA/

*Telegram
www.tg-me.com/poimfitsae
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
እንኳን ለአዲሱ አመት መዳረሻ አደረሳችሁ ውድ የፍፄ ግጥሞች ቤተሰቦቼ!!

አዲስ አመት መቶ አበባው ሲፈካ
ምድር አምራ ደምቃ ፈንዲሻው ሲፈካ
እንኳን አደረሰህ
እንኳን አደረሰሽ ለማለት ወዳጅዎን
@ft2194
በዚህ ሹክ ይበሉኝ
አጠር ያለች ቅኔ
ፈጥኜ እልካለሁ የሚያርስ አንጀትዎን

በግጥም በቅኔ አዲስ አመትን እንኳን አደረሰህ እንኳን አደረሰሽ ለመባባል @ft2194 ን በመጫን አዋሩኝ።
@poimfitsae @poimfitsae
@poimfitsae @poimfitsae
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
ተው ማራት ሀገሬን......🇪🇹🇪🇹🇪🇹

ተው ማራት ሀገሬን
የኔ መጠሪያዬን💚💛❤️

ይችን የዋህ ሀገር
ይችን ሚስኪን ሀገር😥

ለዘንድሮ ተዋት
ለከርሞም ጠብቃት

ተው ማራት ሀገሬን......🇪🇹

አዲስ ቀን ይውጣላት
ሁሌ ስቃ ልያት 😥

✍️✍️✍️ሐና ይመር


@kidapoim
Forwarded from Арбитражница dooradas (🌗የግማሽ አለም ጣኦት🌗)

እንደ ይሁዳ ሳመችኝ.....

እንደ ጌታ ተሸጥኩላት !


🦋ቅዱስ አርዮስ🦋
🌗የግማሽ አለም ጣኦት🌙


።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
Forwarded from Арбитражница dooradas (🌗የግማሽ አለም ጣኦት🌗)
አምሳለ ሰው አምሳለ በግ

እምበበበበበበ.......
ለተራበ
ለሞላለት ፥ ለተካበ

እሰይ! ለተከፋ ፣ የተደፋ
መጥፎ ሽታ የከረፋ!

ምናምንቲያም ፥ ምናምኒት
የዶሮ ጦስ ሽክርክሪት፣

ሽክርክር.... ሽክርክር....
ደቂቃ ሰአታት
አብረን ስንቆጥር፣
አስትንፋስ በደም ውስጥ
ዘልቆ ሲዘዋወር፣
በአራራይ ዜማ ጮህ ብዬ ስናገር
ፋታም አላቆየኝ ከህመሜ እስክሽር።

ሽክርክር...... ሽክርክር.....
አስብቶ ሸክ አንገት ክርክር
ሽክርክር...... ሽክርክር.....

ከቀኝ ወደግራ ከግራ ወደቀኝ
እንዲያው ቢራራልኝ፣

ቃኘት አየት መለስ
ገረፍ ቀለስ መለስ፣

በአይነ ድምፅ በአራራይ
ላይሰማ በለሆሳስ የምሰቃይ፣

በአርምሞ
ካራ ከአንገት ተቀጣጥሞ፣

ሸክ!
ክርክር!
ብጥስ!
አንገት ቅንጥስ፣

ቀይ ደም ፍስስ
ከአፈር ልውስ፣

የገዳይ አንጀት ሲርስ
ሟች ቅልስልስ።

እምበበበበበበበበበ.....

እምበ ለተራበ


ጠኔ ሆዱን ገዝግዞት በሙክቱ ከጠረቃ በኃላ ማሰብ ጀመረ ሲያብሰለስል ከአስርቱ ትእዛዛት ውስጥ አትግደል የሚለው ትውስ አለው
አትግደል ብሎ መግደል ምን ይሉታል? አይ እግዜር ሞኝ ነህ ልበል....



እርሱም ሚስጥር መቋጠር አይችልም። ብናበላውና ብናጠጣው ካባቱ ዘንድ ያየውን ሁሉ ነገረን (የዘር ያዕቆብ ንግርት ትውስ አለው)

ከልቡ ፈገግ...... አለ

አዬ ...ሆድ አምላኩ¡


ቅዱስ አርዮስ
🌗የግማሽ አለም ጣኦት🌗


።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋
www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋
www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋
www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
2025/02/06 16:18:27
Back to Top
HTML Embed Code: