Telegram Web Link
ንብ አትማረክም በአበቦች ፍካት፣
መአዛው ካልሳባት ነፍሷን ካላረካት፤
ድምቀቱ ቢያማልል ውበቱ ቢገዛም፦
ጣፋጭ ልቅሰም ብላ አታርፍም ከመርዛም!

#የግጥም_ቃና_በመክሊት_የ16ቷ
👇👇👇
@ilovvll
@ilovvll 👈ቤተሰብ ይሁኑ


💚ሰናይ 💛እለት
Happiness is not absence of sufferings but acceptance of sufferings ,Stop worrying about things which are beyond your control.

💛አንዳንዶቻችን ያሰብነውን ስራ እስክንይዝ፤ የምንፈልገውን ገንዘብ እስክናገኝ፤ የምንወደውን
ሰው በእጃችን እስንካስገባ፤ የምንፈልግበት የህይወት ደረጃ ላይ እስክንደርስ፤ እያልን ደስታችን ቤታችን እንዳይገባ እንከለክለዋለን። ሞኝነታችን እንግዲህ እዚህ ላይ ነው፤ ምን አልባት ያሰብነውን ብናገኝ እንኳን ላንደሰት እንችላለን፤ ምክንያቱም ደስታ ከውጫዊ ነገሮች ጋር አብሮ የሚቋጠር ቁስ ባለመሆኑ። ደስታ ሁሌም ከበራችን ቆሟል በቀጠሮ አላስገባ ብለነው ነው እንጂ።

❤️ወደ ደስታ የሚውስድ ምንም አይነት መንገድ የለም፤ ይልቁንም ደስታ
ወደምንፈልገው ቦታ የሚያደርሰን ብቸኛው መንገድ ነው እንጂ። ባለህ ነገር ደስተኛ ለመሆን ሞክር፤ ያኔ ፈጣሪ ይጎደለውን በተዓምሩ ይሞላዋል።

ዛሬ በመኖርህ አመስግን ፣ አሁንህን አጣጥም።

ውብ አዳር❤️
@kidapoim
Forwarded from የ ዳግም ሔራን ግጥሞች (ሔራ…ቶ…ዳግ)
[ ሌት የቀን ግልባጭ! ]
:
ከዚያ ነህ የማይሉት
ወዲህም ያልሆነ…የመሀል ተዛማጅ
ከወዴት ተነስቶ
የት እንደደረሳ…… ያልገባው ተራማጅ
ከ‘ሚራመድበት
ረግጦ ከ‘ሚያልፍበት
አዙሪታም መንገድ…ጡዘታም ጉዳና
ይገኝ ይሆን እያልኩ
ቀን ሌቱን ስፈልግ… …የኑረትሽን ዳና
እዚያ ትሆን ብዬ
ከወዲያ ለመድረስ…ያን ለማግኘት ሽቼ
በሰማይ ነድ እሳት
በፀሓይ ቃጠሎ…ከጥቁረት ጠልሽቼ
በተስፋ አለ መንገድ
እንዲያው ስመላለስ…ስርክ ስንጠራወዝ
በጠይም መውደድሽ
የተቸርኩት ጸዳል…ቢጠፋኝ የኔው ወዝ
:
:
የሆነውን ኹነት
ነገር አድራጎቱን… ወልድ እግዜር ላይ ጥዬ
በትዝታሽ ፈዘው
በናፍቆት ቦዝዘው
ትንሽ የሆኑትን
ተቅበዝባዥ ዐይኖቼን…ጣሪያው ላይ ተክዬ
ጌታ ሆይ ስለምን
ይኼ ሁሉ ነገር……በእኔ ይደረጋል
በመሄዷ ማግስት
ጨልሞ የቀረው
ሳይነጋ የመሸው……ቀኔስ መች ይነጋል??

እያልኩኝ ስጠይቅ… እሪ ስል ሳነባ
ከየት እንደመጣ
ያላወኩት ፍጥረት
ብርሃን ተላብሶ……ወደ ዓለሜ ገባ
የሀዘን ክረምቴ አልፎ
የደስታዬ ጅምር……መስከረሜ ጠባ!
:
አጀብ ! አንች ሆዬ
ፅልመት ከወረሰው
ድቅድቅ እልፍኜ ላይ
በነገሰው ብርሃን…ጥቂት ደነገጥኩኝ
ከመደንገጥ ጥጋት
መለስ ስለ ደግሞ
የመጣውን ፍጥረት
ስሪት ማንነቱን……ለማወቅ ቋመጥኩኝ

መቋመጥ የጫረው
ልክ እንደመሽኮርመም…እንደ ማፈር ያለ
የሆነ ዐይነት ስሜት
ድንጉጧ ነፍሴ ላይ……ተከምሮ እንዳለ
ያን ፍጥረት አየሁት
የማን ተፈጣሪ
ማን ምን እንደሆነ…በወጉ ለየሁት
ልቤ ላያ የዋለው
የሀዘኔ ክምር……ተንዶ አገኘሁት!
አጀብ ነው ይህ ነገር
በማለት ተደነኩ…ተገረምኩ እንደጉድ
ሲደፈን ተሰማኝ
እንባ የታቀፈው…የዋይታዬ ስርጉድ!!
:
:
አጀብ!

ይህን ስልሽ ደግሞ
ማን ስለመጣ ነው
እንባህ የነጠፈው…ሳቅህ የተመለሰው
ማን ስለመጣ ነው
የህመምህ ቁልል……ድንገት የፈረሰው
ማን ስለመጣ ነው
ፀሊሙ እልፍኝህ…ብርሃን የለበሰው
ማን ስለመጣ ነው
የመሽኮርመም ስሜት…አንተን የወረሰው

ብለሽ ከጠየቅሽኝ
እንዲህ እነገርሻለሁ
እንዲህ አስረዳሻለሁ……
:
:
እይማ እናቴዋ…
ተመልከች ዓለሜ
ምንጨ መገረሜ…የአድናቆቴ ቀለም
ጭሮሹ ከአንቺ አንጂ
ከማላውቀው ፍጥረት…ከሌላስ አይደለም
:
ይህ ማለት ምንድነው
አንቺን ከናፈቀው
ከኦና በዓቴ …ድንገት የተገኘው
ጸዳላም ፀዲሉ
ግርጡ እኔነት ላይ…እንዳሻው የናኘው
ያ ፍጥረት አንቺ ነሽ… አንቺው የኔ ናፍቆት
ሰሪ አምላክ የሰራሽ…የስስ ነፍሴ ባርኮት!
:
:
ግና ፍቅር_ዓለሜ
የብርሃን ልብሱን
ፀዲል ተጎናፅፈሽ…ድምቀቱን ተላብሰሽ
አመድ የለበሰን
የተዳፈነን ሳቅ……ፈገግታ ቆስቁሰሽ
መንጠፍ የማያውቅን
ረቂቅ እርካታን……ሀሴትን የቸርሽኝ
ተነስ በል ሳቅ ያልሽኝ
ህልም ነው በሚሉት
በእንቅልፍ ዓለም ንውዘት…ሀሳብ ስለነበር
ሌት ነግቶ ስነቃ
ደስታዬን አየሁት……ቀኔ ላይ ሲቀበር!!
:
አየሽ አንች ሆዬ
ዛሬም እንዳለፈው…እንደ ትላንቱ ቀን
የእንቅልፌ ላይ ሀሴት
…ሆኖ እየተገኘ…የገሃድ ሰቀቀን
ሌት ሌቱን በህልሜ
የቅዠት መሰላል
እርካብ እየሆነኝ
…በመንፈስ ከፍታ… ከፍ ብዬ አነጋለሁ
ንጋት ሲነጋ ግን
…በናፍቆትሽ ጅራፍ…ዳግመኛ እቀጣለሁ
:
አየሽ ውብ ዓለሜ
እንዲህ ያለው ዓይነት
የህልም ዓለም ኹነት…በገሃድ ሲነገር
እንኳን እና ያየው
………የሚሰማው ሁሉ አንደሚደናገር
ትዝታም እንዲያ ነው… …የመናፈቅ ነገር
ሌቱን ሳቅ ታቀፈው……ቀን በእንባ መቸገር!!
:
እንዲያ ነው! !
:
[ ዳግም ሔራን #ቅዱሱ_እብድ]
Join and share……………………👇👇
@heranawi
@heranawi
@heranawi ይቀላቀሉን 🙏
(ውዷ እንጀራዬ)
መቼስ አይድለሁም እንከን አልባ
ከሕይወቴ ፍሬ ፣ አይጠፋም ገለባ

እስቲ ልፃፍልሽ ፣ ውዷ እንጀራዬ
አሻራዬን ላኑርሽ ፣ ከሕሊናዬ

ይኽውልሽ አንዴ አድምጪኝ
ለደቂቃም ቢሆን ፣ ጆሮሽን አውሺኝ

እባክሽ ነይልኝ ፣ የእኔ አማካሪ
ናፍቆቴ ጨምሮ ፣ ሆኛለሁ ፆም አዳሪ

ይገባኛል የመሄድሽ ሚስጥሩ
ዳገት ሆኖብሽ ነው ፣ ከእኔ ጋር መኖሩ

አዎ እርግጥ ነው ፣ አስቀይሜሻለው
ከምስጋና ይልቅ ፣ ስሞታ አቅርቤያለው

ብቻ አላውቅም ፣ ምንእንደነካኝ በሰአቱ
ባህሌን ዘንግቼ ፣ ሆኜልሽ ነበር ከንቱ

እንደው ድፍረት አይሁንብኝና ፣ ልምጣ ከቤትሽ
በሻከረው ድምፄ ፣ ይቅርታ ብዬ ልማፀንሽ

ብቻ አንቺ ከልብሽ ይቅር በይኝ
ስምሽን ስጠራው አለሁልሽ በይኝ

እኔም ብሆን ቃልእገባልሻለው
እስከ እለተ ሞቴ አወድስሻለው።
# ቤዚቾ
@kidapoim
Forwarded from የ ዳግም ሔራን ግጥሞች (ሔራ…ቶ…ዳግ)
የጎደለ ጉድለት
[ @dagiamen12]

Join and share……………………👇
@heranawi
@heranawi
@heranawi ይቀላቀሉን🙏
ሆዴን ጅብ በበላው፣
አንጀቴን ባራሰው፤
የማያገኘውን እንዴት ይመኛል ሰው?

#የግጥም_ቃና
👇👇👇
@ilovvll
@ilovvll 👈ቤተሰብ ይሁኑ

💚ሰናይ💛ግዜ
Forwarded from Арбитражница dooradas (🦋ሱራ ቢራቢሮ 🦋)
ግን ይሁዳዬ?

ወዬ.......

ሰላሳ ዲናሩን ምን አረክበት?

ጥቁር ፣ቀይ ፣ሳልል በዳሁበት

: : : :

ይሄኔ'ኮ ያቺን ብሽቅ ነው

ይች ከንቱ!!! ምናምኒት


እሷን ሳስብ በምናቤ እንዲህ ያደርገኛል!


👉
@sufafel 👈
👉
@sufafel 👈
👉
@sufafel 👈
Forwarded from የ ዳግም ሔራን ግጥሞች (ሔራ…ቶ…ዳግ)
#ዜማ_ለበስ_ቃሏ!
:
[ @dagiamen12]

Join and share……………………👇
@heranawi
@heranawi
@heranawi ይቀላቀሉን🙏
Forwarded from የ ዳግም ሔራን ግጥሞች (ሔራ…ቶ…ዳግ)
[ ከአንድ ቃል በላይ : አንድ ዝምታ]
:
ንጣት ለበስ
ውብ ጥርስሽን :
ለአፍታ ግዜ : ለቅፅበታት ቆሞ ያየ
ተንቀልቃይ ፍም እሳት :
በመሰለ መልክሽ : ተቀጣጥሎ የጋየ
:
ሀር መሰሉን:
ልስልስ ፀጉርሽን : በ‘ሳብ መዳፉ : ደርሶ የዳበሰ
ልኬት በራቀው :
በኃያል መውደድ :ግለታም ፍቅርሽ የተጠበሰ
:
ድንገት በሚታይ
በጉንጭሽ ስርጉድ: ብርቱ ብርታቱ : ጉልበቱ የራደ
በአንድ አፍታ ጥቅሻሽ :
ክብሩን ጣጥሎ : የተዋረደ
:
ነፍስ የሚሰልብ :
ቅኝት ባቀፈ : ዜማዊ ቃልሽ : የተመሰጠ
ግዙፍ ክበረቱን:
የ‘ርሱን እሱነት:ለፍቅርሽ ግብር ጥሎሽ የሰጠ

ገዝፎ በሚገኝ :
ሎጋ ቆመትሽ : አጀብ እያለ የተደመመ
አማትሮ ሊያይሽ :
መውጫ መግቢያሽ ላይ የተሰየመ
:
እንደ እኔ ያለ
አፍቃሪሽ ነኝ ባይ : ፍቅሩን ሊገልፀው
በቃል ሸራ ላይ :
እንዴት አርጎ ነው : አንቺን ሚቀርፀው!!
:
ስል እያሰብኩኝ

ከሀሳብ ባህር ውስጥ
ሀሳብ ላሰግር :
መረብ ምናቤን : አንድ‘ዜ ጣልኩኝ
እርሷን ዝም እንጂ
ቃል አይገልፃትም :
የሚል አንድ ሀሳብ : ድንገት ተቸርኩኝ
:
ከዛም አንችዬ
ያንቺ አንቺነት
እንዲህ ነው ብሎ :
አስውቦ መግለጥ… መንገር ቢያቅተኝ
ከአንድ ቃል በላይ
አንድ ዝምታ
ጭጭ ይገልፃታል የሚል ሀሳቤ ዝም አስመረጠኝ!
:
እናም ዝም አልኩኝ
በዝም ገፄ ላይ …ገፅሽን ሳልኩኝ!
:
መገን! … መገን አንቺነት
…………………………………**
[ ዳግም ሔራን #ቅዱሱ_እብድ]
(@dagiamen12)
Join and share………………👇👇
@heranawi
@heranawi
@heranawi ይቀላቀሉን🙏
💛"Holding a grudge Doesn't make you strong; It makes you bitter. Forgiveness doesn't make you weak it sets you free" #forgive

ሁሌም በደልን ሳስብ አንድ ነገር ይመጣብኛል ፤ በአንድ ክፉ ሰው ስራ ስንት መልካም ሰዎች እድል ይከለከላሉ? በአንድ ሌባ ሰው ምክንያት ስንት ታማኞች እንደሌባ ይቆጠራሉ? በአንድ ከዳተኛ ምክንያት ስንት እውነተኛ አፍቃሪዎች እድል ሳይሰጣቸው ይገፋሉ? ....ምክንያቱም ይቅር ማለት ስለሚከብደን።

ይቅር ስንል ከበደሉን ሰዎች ይልቅ ቅልል የሚለን እኛን ነው። የተበደልነውን እያሰብን አቀርቅረን የምንኖር ከሆነ፤ ቁስላችንን ሊጠግኑ የሚችሉ፤ እንባችንን ሊያብሱ የሚችሉ፤ ካጎነበስንበት ቀና ሊያደርጉን የሚችሉ ሰዎች በአጠገባችን ሲያልፉ አናያቸውም። ይቅር ስንል ግን በሰው ልጆች ተስፋ አንቆርጥም።

💜ይህች አለም ክፉዎችንም ደጎችንም አሰባጥራ ይዛለች። በመጥፎ ሰዎች ስራ ግን ደጎች እንደሌሉ ይቆጠራሉ፤ ምክንያቱም መልካም ሰዎች በቂመኛ ሰው አይን ውስጥ ስለማይገቡ ነው። የበደሉንን እያሰብንን የሚክሱንን ባናርቃቸው መልካም ነው!!!

ይቅር በማለት እራሳችንን ነጻ እናውጣ!!!🙏

ሚስጥረ አደራው

ውብ ምሽት❤️
@kidapoim
Audio
እኔ አንተን ሰወድህ
ልክ እንደ ገጣሚ
ጨረቃ ታደሚ
አንቺ ኮከብ ስሚ
ምድር ሆዬ አድምጪ
ፍቅሬን አረጋግጪ።
ቅጠሉ ሁሉ ብዕር
ብራናዬ ባህር
ቢሆኑም አይበቁኝ ፍቅሬን ለመመስከር
ብዬ አልልህም
ጨረቃ ታድማ በፍፁም አታቅም
ምድር ስታደምጥ ታይቶ አይታወቅም
ቅጠሉም ባህሩም ላንተ ፍቅር ብሎ በፍፁም አይፅፍም
ይህ ሁሉ ዉሸት ነዉ ተሠምቶ አያዉቅም
.......................
.......................
እኔ አንተን ስወድህ
........................
........................
ሠላም ለኪ ለጥርስከ
ሠላም ለኪ ለከናፍርከ
.............................
.............................

በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ

@kidapoim
🥣🥣🥣🥣🥣🥣🥣🥣🥣🥣🥣🥣🥣🥣
ሙያ አለኝ ብለሽ ባልሽን ሸውደሽ
እንጀራ ለመስራት አጥሚት ያቦካሽው
ደና ነሽ እንዴት ነሽ😂😂

ሴቶቻችን እስከመቼ? ገላግሌ የሆነ መፅሀፍ ከኔ ዘንድ ያገኛሉ
👉 የዶሮ ወጥ አሰራር
👉 የበርበሬ አዘገጃጀት
👉 የምስር ወጥ አሰራር
👉 የጠጅ አጣጣል
👉 የአረቄ አወጣጥ ፣ የጆርዳና ምግቦች ....ወዘተ
#ጆርዳና ኩሽናና #የምግብና መጠጦች አሰራር ዘዴ በሚል ርዕስ ሁለት ድንቅ መፅሀፍት ፓኬጅ በዝቅተኛ mb አዘጋጅቻለሁ @ft2194 ላይ ወይም በስልክ ቁጥር +2510963168909 ላይ አውሩኝ።
@poimfitsae @poimfitsa
🍽🍽🍽🍽🍽🍽🍽🍽🍽🍽🍽🍽🍽🍽
Forwarded from Арбитражница dooradas (🦋ሱራ ቢራቢሮ 🦋)
ድንቡሽ ፣ ድንቡሽቡሽ
እንትፍ ፣ ጣል የጠላን ጉሽ።

ሱራ ቢራቢሮ🦋
ድንግል ውበት

ጫማ ካልተጫማው ከባዶ እግሮቿ
ኩልን ካልቀመሰው ከነጩ አይኖቿ
ልብስን ካለመደው ከእርቃን ገላዋ
በኢቫንጋዲ ምሽት ያምራል ጭፈራዋ

ከቡስካው አለም ውስጥ ድብቅ ሚስጥር አለ
በተፈጥሮ ውብት እንደተከለለ
በህግና ባህል እራሱን ያኖረ
የሐመር ምድር ላይ ድንቅ ህዝብ ተፈጠረ
በአለም የሌለ ቀድሞም ያልተዳሰሰ
አለም ተበሰረ
ያልተበረዘ አለም ክፋት ያልጎበኘው
በግልጽ አስተሳሰብ ፍቅር የሚዳኘው
ህግ ስልጣን የለው ባህል ያቆራኘው
የእውነት ፍትህ ካለው
ግን ግን ከቆመው ምሶሶ ካንጋጠጡ ህንጻዎች
ጨለማን ወሽተውት ከቆሙት መብራቶች
ከአለሙ አለም ከከተማው ድምቀት
ይሻላል የቡስካው ያ የጨረቃ ውበት

ውበት ግን ምንድ ነው ?
ውበት ማንነት ነው ጣፋጭ ህልውና
ባጭበርባሪ አለም ድንቅ ስብእና
አስቀምጦ ማለፍ ነው
ለተራማጆች ግን ውበት ያልገባቸው
እርቃንን ሸፍኖ እርቃን ማሳየት ነው
ባዶ ማንነትን ገልጦ ከማሳየት
ይሻለን ነበረ እነደ ሐመሯ ወጣት
በአንገት ክታብ ድምቀት በእርቃን መታየት

የአባቡ ልጅ
መነሻ ሀሳብ፦ ከቡስካው በስተጀርባ

@kidapoim
High quality...low price fidel tutor / ፊደል ቲቶር በአነስተኛ ዋጋ በከፍተኛ ጥራት ልጆችዎን እናስጠናለን።
Kg to university

For additional information
@ft2194
+251963168909
Forwarded from የ ዳግም ሔራን ግጥሞች (ሔራ…ቶ…ዳግ)
ምን ይሉት ቅሌት ነው?
ገጣሚ: አንባቢ…
#ዳግም_ሔራን ( @dagiamen12)
Join and share………………👇👇
@heranawi
@heranawi
@heranawi
፨፨፨ሀሳብና ስሜት ፨፨፨
በማሰብ ሀሳብ ዉስጥ ላለማሰብ ማሰብ
ባለማሰብ ይዘት በሀሳብ መጋለብ
ነጻ ሀሳብ መፈለግ እሱም አልሆን ሲለኝ
ውዥንብር ሀሳቤ ከስሜት ሲያጋጨኝ
ጭፍኑ ስሜቴም ከሀሳቤ ሲያጣላኝ
ለጃን መቀመጫ ለስልጣን መውረሻ
በሀያልነት ስሜት ለውስጤ መንገሻ
መንገድ እያበጁ ሀሳብና ስሜት
አንዴ በሀሳብ መንገድ
ስኳትን ስራመድ
በሌላኛው ደግሞ ለውስጣዊ ስሜት
ራሴን ሳስገዛ ስመዝን ስለካ
ማንን እንዳነገስኩ እኔ አላውቅም ለካ
በሀሳብ መንገድ ስራመድ በስሜት አፋፍ ስዳክር
በሀሳብ ግጭት ስሜት ግሎ ሲከራከር
ደግሞ አንዳንዴ በሰከነ መንፈስ ሀሳቤ ሲሰምር
ስሜቴን አስክኜ ራሴን ሳስገዛ ስመዝን ስለካ
ማንን እንዳነገስኩ እኔ አላውቅም ለካ
@kidapoim
የአባቡ ልጅ
🕰ሰዎች ስለወቀሱን የማይርድ፤ ስለኮነኑን የማይወድቅ፤ ስለፈረዱብን የማይሞት፤ ስለጠሉን የማይፈራ፤ ስለተዉን የማይደክም መንፈስ በውስጣችን ሊኖር ግድ ይለናል። ከፈጣሪ የተሰጠን እውነተኛው ማንነታች ይህ ነው። ብዙዎቻችን ደካማ ስለተባልን ደክመናል፤ ሃጥያተኛ ስለተባልን ቆሽሸናል፤ ወንጀለኛ ስለተባልን ታስረናል።የሌሎች ሰዎች አስተያየትና መስፈርት ከእውነተኛው ማንነታችን አርቆናል፤ ሰላም ካለበት ስፍራ አውጥቶ የይሉኝታ ሰፈር ኗሪ አድርጎናል።

እውነት ነው ማናችንም ከተጽዕኖ ማምለጥ አንችልም። በመልካምም ሆነ በመጥፎ ሞርደ በየእለቱ መሞረዳችን አይቀርም። ማንነታችን የቤተሰባችን፤ የጓደኞቻችን፤ የአካባቢያችን የባህልና የእምነታችን ውጤት ነው። ሁሉም ነገራችን ላይ የአካባቢያችን ተጽዕኖ ያርፍበታል፤ ልክ ጣሪያ እንደሌለው ቤት በውጪ ያለው ሙቀትና ቅዝቃዜ፤ ዝናብና ንፋሱ፤ አቧራና ሽታው የራሳቸውን አሻራ ያኖሩበታል። በሌሎች ሰዎች ጉንፋን እኛ እናስነጥሳለን፤ በማህበረሰብ በሽታ እኛ የአልጋ ቁራኛ እንሆናለን፤ በሌሎች የእምነት ጥበት እኛ እንጨነቃለን፤። ለዚህ ነው ደስታችን በብዙ ነገሮች ተጽዕኖ ስር የሚወድቀው።

🕰ብዙ ውጫዊ ነገሮች አስደሳች ቢሆኑም ከጊዜ ጋር የተሳሰሩና ሃላፊ ናቸው። ዛሬ ያስደሰተን ጓደኛ ነገ ላይኖር ይችላል፤ ዛሬ ያጌጥንበት ውበት ነገ ይረግፋል፤ ዛሬ የተመካንበት አስተሳሰብ ነገ በቆመበት አይጸናም። ከውጪ የምናገኘው ማንኛውም አይነት ደስታ በመጣበት እግሩ ጥሎን መሄዱ አይቀርም። ከዛም አልፎ ዋጋ ያስከፍለናል። ከጊዜ ጋር የማይለዋወጥ ደስታን ለማግኘት ብቸኛ መፍትሄው ደስታና ሰላምን በውስጣችን መፈለግ ነው። እንደ ኩሬ ውሃ ያነሰች፤ እንደ ኩራዝ መብራት የቀጨጨች፤ እንደ ሰናፍጭ ቅንጣት የደቀቀችም ብትሆንም እንኳን ውስጣዊ ደስታን በልባችን መትከል ነው። ይህ ነው ማንም ሊነካውና ሊደፍረው የማይገባው ስፍራ።

❤️በዚህ ስፍራ ውስጥ ሙሉ ነን፤ እውነተኛ እኛነታችን የሚታየው በዚህ ስፍራ ነው። ወደ ውስጣችን ዘልቀን በዚህ ስፍራ ላይ ቆመን ህይወታችንን ብናየው፤ እንደምናስበው ደካማ አይደለንም፤ የሚጎድለን ብዙ አይደለም፤ ከምንም በላይ በፈጠረን አይን ውስጥ ውብና ንጹህ ነን። ታዲያ ከዚህ በላይ ምን አለ? ደስታና ሰላማችን በሰው እጅ ፤ ፍርድና ቅጣታችን በሰው ወንበር ፈጽሞ አይሁን!!!

ውብ አሁን❤️
@kidapoim
Forwarded from የ ዳግም ሔራን ግጥሞች (ሔራ…ቶ…ዳግ)
ባክህ…
#ገጣሚ: ባለ_ቅኔ…ሙሉጌታ ተስፋዬ
#አንባቢ : ዳግም ሔራን [ @dagiamen12]
join and share……………👇👇
@heranawi
@heranawi
@heranawi
2025/02/06 18:55:49
Back to Top
HTML Embed Code: