Telegram Web Link
ለአንድ ዘፋኝ፣ልድት፡
ይሄ ሁሉ፣ጩኸት፡
ምንድን ነው?፣ማካበድ፡
እንደዚህ ማሸርገድ፡፡

"ጎጃም ያረሰውን፣ለጎንደር ካልሸጠ፡
ጎንደር ያረሰውን፣ለጓጃም ካልሸጠ፡
የሸዋ አባት ልጁን፣ለትግሬ ካልሰጠ፡
የሀረር ነጋዴ፣ወለጋ ካልሸጠ፡፡"
እያለች በስንኝ፣ዜማ ም'ደረድር፡
እንዳሻን እንዳ'ኖር፣ተቧድነን በሰፈር፡
ዘፈኗ አልጣመንም፣ለኛ ለሆድ አደር፡፡

"የማያረጅ ውበት፣የማያልቅ ቁንጅና፡
የማይደረቅ የማይነጥፍ፣ለዘመን የፀና፡፡
ከጥንት ከፅንስ አዳም፣ገና ከፍጥረት፡
የፈሰሰ ውሀ፣ፈልቆ ከገነት፡
ግርማ ሞገስ፡
የሀገር ፀጋ፣የሀገር ልብስ፡፡"
ከኛ በላይ አባይን፣ልቃ በማሞገስ፡
የግሏ አ'ርጋዋለች፣በዚህም ትከሰስ፡፡

"አደዋ ዛሬ ናት፣አደዋ ትላንት፡
መቼ ተነሱና፣የወዳደቁት፡
ምስጋና ለነሱ፣ለአደዋ ጀግኖች፡
ለዛሬ ነፃነት፣ላበቁኝ ወገኖች፡፡"
ወራሪ ይርዳል፣በዚህ አስፈሪ ዜማ፡
አደዋ ዛሬ ናት፣ማለቷን ሲሰማ፡
ለባንዳ'ማ ጭራሽ፣ለጆሮው አይስማማ፡፡

"አንተ ልጅ አንተ ልጅ፣አንተ ልጅ ያሙሀል፡
ልብ ይበላል እንጂ፣አይሰጥም ይሉሀል፡፡
በዚ'ች በማተቤ፣እምልልሀለው፡
ፍቅርን ካልሰጠኸኝ፣እሞትብለሀለው፡፡"
በስርቅርቅ ድምፇ፣እንዲህ እያዜመች፡
ስንቱን ደንዳና ልብ፣በፍቅር አቀለጠች?።

ስለሀገር ስዘፍን፣በቅኔ አመሳጥራ፡
ፍቅርን ስታዜም፣ሒወትን ጨምራ፡፡
ለኛ አይመቸንም፣እንዲህ ያለ ነገር፡
ጥበብን ማበርከት፣ትውልድ የሚሻገር፡፡
ማታ የሚረሳ፣ጠዋት አስጨፍሮ፡
ይህን ነው የለመደው፣የኛ የአድማጭ ጆሮ፡፡

እና ለዚ'ች ዘፋኝ፣ማከበድ ምንድን ነው?:
ለንግስቷ ልደት፣ይህ ነው የሚገባው?:
እጅጉን እናካብድ፣ማካበድ ያንሳታል፡
ስሟም እጅግ አየው፣ብዙ ይገባታል፡፡

ሙዚቃ መልካም ልደት፡፡
(አድናቆት ክፍሌ የብርቱካን)

#የግጥም_ቃና
👇👇👇
@ilovvll
@ilovvll 👈ቤተሰብ ይሁኑ
Forwarded from Арбитражница dooradas (🌗የግማሽ አለም ጣኦት🌗)
መለዓከ ብርሀን


ብለፋ ብደክም፣ ባዶ ቢሆን እጄ
መሬቴን አረስኩት፣ መልዓክ ተጠምጄ፣

መቼም የኔ ነገር ፣ አልመጥንም ከሰው
ማልጄ ልነሳ ፣ መለዓኩን ልጥምደ፣

ቢቸግር ነው ፣ እንጂ አይጨከን ወዶ
ምን ይበቅል ይሆን? መልዓክ ተጠምዶ።


ገጣሚ መልዓከ ብርሀን
(ድብቅ አለም ቶ)

።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
ገላዬ....
ከመስኩ ላይ ቆሜ ፥ እምባን ባረገዘ
በናፍቆት ወይቦ ፥ በተድበዘበዘ
በዚያ መንታ አይኔ...
የመራቤን ጅራፍ ፥ የምኞቴን ጩኸት
ላንቀላፋው ጤዛ ፥ ለወፍ ጎጆው ምልዓት
ዘምሬ
ዘምሬ
ደስኩሬ
ደስኩሬ
ህቅ ባለው መንፈስ ፥ ምሬት ባየው ልሳን
ብናገር ለእነሱ ፥ የኔን እንዲህ መሆን
የአንቺ ወዲያ መቅረት ፥ የንጋት ሰቀቀን
በጉድ ወጣ እያሉ ፥ ለሰማይ ለምድሩ
ለሰው ላራዊቱ ፥ ለቀየው መንደሩ
መስቀሉ ናት ብለው ፥ ናፍቆት ወለፈንዴ
ተሸነፈ ብለው ፥ ያሙኝ ይሆን እንዴ?
.................. / / .....................
© ሲራክ ወንድሙ
@poimFitsae
@poimFitsae
Forwarded from Арбитражница dooradas (🌗የግማሽ አለም ጣኦት🌗)
#ወዲያ_ሽሽ_ይለኛል!

© ሲራክ ወንድሙ @siraaq
.
ኑረት ሲረክስብኝ ፥ ሲሆን እንደ እቃ 'ቃ ፣
አዎን ያስፈራኛል ፥ የዘመን አታሞ
.................... ፥ የዘመን ድለቃ ፤
የድግግሞሽ ሰልፍ ፥ የእሽ ፡ ክርክሪት ምልዓት ፣
ሰው ሆኖ ተኝቶ ፥ ትል ሆኖ እንደመንቃት ።

ንጋት አድባር ሆኖ ፥ የሀገር ጌጥ የሀገር ዳስ ፣
ጀምበር በሰረቀ በአመሻሹ ፈለግ ፥ እንደካህን መርከስ ፤
እንደምኩራብ ከብሮ ፥ እንደ እንትን መንኳሰስ ።

አዎን ያስፈራኛል...
ወዲያ ሽሽ ይለኛል...
ወዲህ ግድም እሩጥ ፣
ወዲህ ግድም አምልጥ ፤
ወዲያ ጥግህን ያዝ ፥ ይለኛል ይለኛል ፤
የዘመኑ ቅኔ የዘመኑ መንፈስ ፥ መንን ያሰኘኛል ፤
ወዲያ ሽሽ ይለኛል ።
.............. | ። | ...............
ነሐሴ ፳፻፲፫ ዓ.ም


ⓒሲራክ
።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
Forwarded from Арбитражница dooradas (🌗የግማሽ አለም ጣኦት🌗)
የሀገሯ ~ ገመገም
ከጥርሶቿ ~ ግርግም፣
ሳቋ ~ ሲያፍገመግም
ሳልፍና ~ ሳገድም።


አማትሬ ~ ባየው:
ተሰትረው ~ ኑረው
የቅርብ ሩቅ ~ ሆነው።


ኩንስንስ አመሏ
ጵስጡቂስ ጠረኗ
ኑረት አኳኃኗ፣

ዘንጠፍጠፍ እያለ
ቀልብ እያዋለለ፣


የገዛ ጥላዋ
ብርቅርቅ ገላዋ፣


ውልብ ይልብኛል.....
የድምጿ ሲርሲርታ
ያቃጭልብኛል።


እናማ......

ምናብ ሀሳብ ሲምስ
ሲያወጣ ሲመልስ፣


ጣዕሙን ሊያጣጥም
ምላስ ሲፈረጥም፣


እፀበሉ ግርጌ
ነጠላ አደግድጌ፣

ስለቴን ላስገባ
በእግዜሩ ሙሀባ፣

መጣሁ ከአድባርሽ
እቤተስኪያን ቅጥርሽ፣


የኔ እንዲያ መዋተት
ደርሶ መንከራተት፣

የኔ እንዲያ መውተረተር
ካንቺ ለመሰተር።


እነሆ አካሏን ጎብኝቶ ጠረኗን በምናቡ ምጎ ካጣጣመ በኃላ በዕውኑ አለም ፍለጋውን ማነፍነፉን ቀጠለ።


አንቺ ሆዬ ወዴት አለሽ?


ቅዱስ አርዮስ
🌗
የግማሽ ዓለም ጣኦት🌗

።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋
www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋
www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋
www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
#አንዳንድ ነገሮች ---------
__________________

በታሪኳዊታ ጎንደር ከማራኪ ወደ ፒያሳ ከዚያም ወደ አራዳ ለመሄድ ሶስት ሆነን በሚኒ ባስ ውስጥ ገባን ። ወራጅ አለ !! ሳንለው አስራ ስምንት ብር ከተፋን በኋላ አፄ ፋሲል ግንብ ፊት ለፊት ግምጃ ቤት ማርያም ጋር አራገፈን። ከሰማያዊቷ ታክሲ ከወረድን በኋላ በሶምሶማ እርምጃ በአደባባይ እየሱስ አድርገን በጃንተከል መዝናኛ በኩል የባቡር ሐዲድ በምትመስለው አስፓልት በቅዱስ ዮሃንስ ወልደነጎድጓድ ግርጌ አቀበቱን በወሬ ተያያዝነው ። ወዲያ ወዲህ በሚቅበዘበዙት ባጃጆች ዙሪያ ገባው ተጨናንቋል ። "እነዚህ ባጃጆች ይህቺን ጥንታዊ ከተማ አቆሸሿት!"
አቡሻ ነበር ። አቡሻ ያሻውን አውርቶ የወደደውን አድርጎ የሚኖር ነፃነት የሰፈነበት ጭንቅ የራቀለት ልጅ ነው ። አንድ ጊዜ
በቅድመ ምህንድስና (pre--Engineering)
እያለ የመካኒካል ድሮዊንግ(mechanical Drawing) ፈተና ሊፈተን የድሮዊንግ ማቴሪያሎች ይዞ ከፈተናው አዳራሽ ይሰየማል። ታዲያ የፈተና ወረቀቱ ይታደልና ሁሉም አስር ጊዜ ለክቶ አንድ ጊዜ ሊስል ይጣደፋል ። አቡሻ ትንሽ ከቆየ በኋላ ራመድ ራመድ አለና መምህሩን ከላይ ወደታች ካየው በኋላ
"ይህን አንተ እንዳወጣኸው አንተ ስራው ! "
ብሎ የጥያቄ ወረቀቱን አስረክቦ ይወጣል ።
አቡሻ እስከዚህ ድረስ ነው ። ጭንቅ ፡ድብርት በአጠገቡ አያልፉም ። የመሰለውን ከመናገር ከማድረግ አይቦዝንም።
በሞቀ ወሬያችን የፒያሳን ጎዳናዎች ሸኝተን አራዳ ገባን። ከፊት ለፊታችን የሚራመድ ፈርጠም ሰውነት የታደለው ወጣት በጎዳናው ላይ ቁጭ ብላ የዕለት ጉርሷን ለማግኘት የክብደት መለኪያ መሳሪያ አስቀምጣ ፍራንክ ለማግኘት ትዳክራለች።
ወጣቱም ተመዘነ። 74.5 ኪሎግራም ያነባል ሚዛኑ ። የሚዛኑን ተመን ሳይከፍል መንገዱን ቀጠለ ። ቀጭኗ ወይዘሪት እንዲህ አለችው።
"ማሰቢያህ ዝግ ነው አይደል !"
በዚህ ንግግር ከወጣቱ በላይ እኛ ነበር ያዘንነው ። ወጣቱ ዝም ብሎ ወደፊት እየተንጓተተ ሄደ።
በአንድ መፅሐፍ ላይ አንድ ወቅት
"አቅም የሌላቸው ሰነፎች ማጥቂያ መሳሪያ ናት! "ይላል ስድብ።
እዚህ አዱገነት ሸገር ላይ አንዲት ስጋዋ የከበዳት ዘርፋፋ ሴት
"ወንበሩ ለሶስት ትከፊያለሽ ይላታል !"
"ገንዘቤን ከፍዬ እኮ ነው። ስለ ውፍረቴ ምን ያገባችኋል ! ርካሾች ናችሁ ! " አለች በንዴት!!
እየተንተከተከች። ግንባሯ ላይ የተወጣጠሩ ጅማቶች ይታያሉ ። ሁሉንም በአንድ ካርቶን አሽጋ ርካሾች !!!YIKETLAL ………………………………
…………………………………………………………
Dt///፩፱/ ፪/፼፩፫//
@kidapoim
Forwarded from Арбитражница dooradas (🌗የግማሽ አለም ጣኦት🌗)
ከትቢያ ፥ ተጣብቆ ፥ እንዳል ፥ ነበር ክፉም : ደግም : ሀሳብ : በንፋስ : መልክ : ሽ'ው : ያለው። የቱማታው: ማርፊያውን : እንጃ እየተግተለተለ: ይላወሳል። መፃዕጉነቱ : ቢጠናበት ቀን ቆጥራ : ጅመረ። አዎ ቀኑ #19 ነው የአመቱ ገብርኤል ፥ የባለ : ቀኑን ስም ፍቺ መሰነጣጠቁን : ተያያዘው።

ገ ብ ር ኤ ል

አምላክ ሰው ሆነ
ሰው እምላክ ሆነ

በሚል ፥ ፍቺ ፥ ተዋህዶን ፥ እፀናት!

የዛር በቆሎ : እንደተጠናወተው : የግንባሩንም : ስጋ መሽሽግ አልፈለገም።የግማሽ ዓለም ጣኦትነቱን : አምኖ ከተቀበል : መክሩሙም አደል....

በገሚስ : ብርሀን :የሞላው : የእዕምሮው ክፍል : የባለ ቀኑን: ስም : ከነፍቺው መርምሮ : አወቀ : አውቆም ፣ ተደሰተ
ተደስቶም ፣ ከልቡ አመሰገነ።

የቀረው : ገሚሱ : ጨለምተኝነት ከእሱ ዘንድ : ተጣብቶት : ነበርና :ሀኔታው አልዋጥለት : ተብሎ : ነገር ይፈለፍል ፣ ይሰንጣጥቅ: ጀመር።

እንዴት ሰው አምላክ ሆን?

ጠየቀ......

ጥያቄውንም : በጥርጣሬ: አፀናው!!

በቀን : ከ 5 ግዜ በላይ :መርዛማ ፈሳሹን ልምትፋት እንደ ኮብራ : እባብ እንገት : የሚገትር: መቀንዘሪያው ልጓም : ሲበጥስ : ተመለከተው።

ጌታም : ሰው : በነበረበት : ግዜ ይህ ነገር : ገጥሞት : እንደነበር : አሰበ
:ባሰበበባት : ቅፅብትም : መብርቅ: ከምድረ: ገፅ መቶት አጠፋው።


ያኔም እግዜሩ ከላይ ሆኖ ከልቡ ሳቀ¡

የዛ መፃዕጉ ነፍስ የት ገብታ ይሆን?


🦋 ቅዱስ አርዮስ
🌗የግማሽ ዓለም ጣኦት🌗

።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋

#ጤዛው ይወጋኛል
ማለዳና እኔ ሁሌም ጠብ ነን። አንድ የሚያስማማን የጋራ ውል እንኳን ዬለም። በአጥቢያችን ባለው ድል አምባ አማኑኤል ቤተክርስቲያን ያሉት ኳህናት ለሊት ወደ ደብሩ ለአገልግሎት ሲፋጠኑ እያየሁ እቀናለሁ። በነገራችን ላይ እኔ የሌለኝን ነገር በሌሎች ሰዎች ላይ ሳይ አደንቃለሁ ። ታዲያ አንዳንድ ጊዜ ብዙዎቹ ለሰዎች ያልተፈቀደ ስራ ሲሰሩም ከመገረምም በላይ ከራሴ ጋር ሙግት እገጥማለሁ። ፈጣሪ በዓለም ሀያ ሁለት ፍጥረታትን ፈጥሯል ። ታዲያ ለሁሉም የሚኖሩበትን ባዕት ሰርቶላቸዋል ። ትንኝ በዝሆን ሰፈር ዝንብ በቆሻሻ መንደር ንብን በአበቦች ቀዬ ፣ የዱር እንስሳትን በዱር፤ እባብን በጎጥ ፡ ወፍን በጎጆ ፣ ዝንጀሮን በገደል ፡ ሰውን በየ ቤቱ አሊያም በዋሻ ብቻ! ማደሪያ አበጅቶላቸዋል። ታዲያ !የሚገርመው ትንኝ እንድትኖር በተፈቀደበት ዓለም ውስጥ ሰዎች እንዳይኖሩ ስለምን ይገደላሉ ???
ማለዳና ጤዛ ይፋቀራሉ ። ምናለበት! እኔም ከራሴ ሐሳብ ጋር ብፋቀር ! ማንስ ይሁን ከራሱ ሀሳብ ጋር በፍቅር የተጋመደው??
የማለዳ ሰዎች ስኬታማ ናቸው ። ይላሉ በምናቡ ዓለም ከብዕር ጋር የሚዳክሩ ብዕረኞች ና አጋፋሪዎች ! ወዲህ ያሉት ደግሞ ስኬት የተጀመረ የህይወት መንገድ ናት እንጂ መድረሻ ዬላትም ባይ ነኝ ! ሰዎች ስንባል አቅም የሚባል ደቃራ ባይበጅልን ኖሮ መንበረ ፀባኦትን ለመፈንቀል የምንታገል ፍጡራን ነን። እግዜርም ደግ ነው ። አቅም የምትባል የማትነቀል አረም በልባችን ላይ አትሟል ። ዳሩ ይህ ሆነና ምኞታችን ሁሉ ልኬቱ እስከ መመለክ ይደርሳል ።
ድሮ ነው አሉ ዲያብሎስ የሚባል ፍጡር ሁሉን ፈጠርኩ አለ ! የልቡን ያወቀው ፈጣሪ በፅልመት አዳራሽ አኖረው። የሰው ልጅ ጉብዝናው ልኩን አውቆ መኖር ነው ።
"ማለዳ የሚጠለየው ፀሎት ይሰምራል ይላሉ የሐይማኖት ጠበብቶች !" እኔም እላለሁ የሰመረው ፀሎት ፍሬው የታለ ምነው በለስ ሆኖ ቀረ? እርግጥ በየትኛውም ጊዜ ያደረስነው ምህላ የማናውቀን ቀዳዳ ደፍኖ ይሆናል ። ሰዎች እንደማለዳ ጤዛ አለት የሌለው ልመና እያደረስን የምንጠብቀው ምላሽ የውቅያኖስ ያህል ሆነና አራምባና ቆቦ ሆኖ ቀረ እንጂ ……………………………
.አምሳል ትባላለች ። ስምን መላዐክ ያወጠዋል እንዲሉ ስሟ ከግብሯ ግጥም ያለላት ያየችውን የምትሆን ዕስስት ነገር ናት።
ድስት ምኑን አያጣም ነበር የሚባለው?
"ግጣሙን ነው "
" ብዙ አታንብብ በነገራችን ላይ !" አምሳል ናት።
"ለምን ?" መለስኩላት
"YOU Know ብዙ ማንበብ ራስህን እንድታጣ ያደርግሃል…………ለማለት የፈለኩት ገብቶሃል አይደል " እጇን እያሞላቀቀች ምን ሳታስረዳኝ እንዲገባኝ ፈለገች ። አምሳል !!
"ማንበብ ትቺያለሽ ?" አልኳት ።
"ምን ማለትህ ነው እንዴዬ ……!" መለሰች በመገረም ንዴት…
"ትቺያለሽ?" ደገምኩት
"አዎ !" አለች።
"እንግዲያውስ ! ማንበብ እየቻለ የማያነብና መሐይም አንድ ናቸው ! ይላል አንድ ፈላስፋ"
አልኳት ። ወሬያችን በዚሁ ዙሪያ ቀጠለ ።
ብዙ ዘልማዳዊ ወጎቻችን እንደየመጡበት ዘመን በትውልድ መሃከል ተደላድለዋል። ለአብነትም ዘረኝነት !!
"አንድ ሞኝ የተከለውን ሺህ ሊቃውንት አይነቅሉትም !"
ከአፍላነት ዘመኔ ከሰማሁት ተረቶች አንዱ
"ለአህያ ማር አይጥማትም "! ይሰኛል።
እንደ ማለዳ ጤዛ ጥያቄና ምርምሩ የአደይ ጮራ እስኪፈነጥቅ ለጥቂት ደቂቃ በምናብ የሚመላለስ ተረት……… የጤዛውም ውጋት ቀጥሏል ። አህያ በዕውኑ ማር የት አግኝታ ቀምሳ ይሁን? እንኳንስ ለአህያ ለአዳሜና ሔዋኔ ይገኛል ?
………………ጤዛው ይወጋኛል……………YIKETLAL…………………
__________________________
#DT//////፴/፪/፼፩፫/////

@kidapoim
Forwarded from Арбитражница dooradas (🌗የግማሽ አለም ጣኦት🌗)


ከምንጭሽ ውሀ ስር
ለመቅዳት ስታትር፣

አንገቴ ሲል ዘንበል
በደጃፍሽ በኩል፣

ተጠምቼ ስግት
የተፈጥሮን ፍንክት፣


ሰው ሆኖ ሰው መስራት
ነፍሴን ከስጋዬ ነጥለሽ ሰወርሻት።


አወይ መታደልሽ!!

ቅዱስ አርዮስ
🌗የግማሽ ዓለም ጣኦት🌗

።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
Forwarded from ግጥም 🇪🇹
🌻 ስንቶች 🌻


ስንቶች ገዝፈው አነሱ
ስንቶች ካ'መድ ተነሱ
ስንቶች ሩቅ ፈለሱ
ስንቶች ተመላለሱ

ስንቶች በልተው ጠገቡ
ስንቶች ጥቂት ተራቡ
ስንቶች ገዝተው ዘነጡ
ስንት አጥንቶች ገጠጡ

ስንት አጥሮች ፈረሱ
ስንት ቤቶች ታመሱ
ስንቶች አግብተው ወለዱ
ስንቶች ከከፍታ ወረዱ

ስንት መፅሀፍት ታተሙ
ስንት ከተሞች ወደሙ
ስንት ሴራ ተቀመረ
ስንቱ ሀገር ተዋቀረ

ስንት ሲንግል ተለቀቀ
ስንቱ ሀገር ለቀቀ
ስንቱ አይምሮ ለቀቀ

ስንቶች በማታ ፈመሱ
ስንቶች በቀን ተረሱ
ስንቶች አፈር ቀመሱ
ህፃናት ጎጆ ቀለሱ

ስንት ክረምት አለፈ
ስንት ውሀ ጠፈፈ
ስንት በጋ ከነፈ
የፀሀይ መአት አለፈ

ስንት እንባዎች ረገፉ
ስንቶች ከላይ ተገፉ
ስንቶች ከሞት ተተፉ
ስንቶች በባህር አለፉ

ስንቶች ታጭተው ከሰሙ
ስንቶች አግብተው ሳሙ
ስንቶች ነግደው ከበሩ
ስንቶች ድንገት ከሰሩ

በዚህ ሁሉ ሁነት መሀል
ያንቺን መሄድ ስመዝነው
እጅግ በጣም ኢምንት ነው
ልረሳሽ እየጣርኩ ነው ....


የነበረከት

@kidapoim
Forwarded from Арбитражница dooradas (🌗የግማሽ አለም ጣኦት🌗)
🌗የግማሽ ዓለም ጣኦት🌗

።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
Forwarded from Арбитражница dooradas (🌗የግማሽ አለም ጣኦት🌗)
ቆይ ግን አንተ ማን ነህ?


የማንነት ጥያቄው እየተመላለሰ ሲያቃጭልበት ለፌ ወለፌ ወመሆኑን ለመንገር በግድ ጆሮው ላይ ተለጥፈው ሲያንሾካሹን ግንርታቸው እያስተጋባ ሲሰማው ያስጨንቀዋል።

ወደዚች በከቻ አለም ፈልጎ እንዳልመጣ ሁሉ ተፈልጎ እንደሚሄድ ለማሳበቅ አፋቸውን ያሾሉ እልፍ የኢብሊስ ወዳጆች አሉ የሁካታቸው ማፍገምገም
የሲቃቸው ሲርሲርታ ለሱ ጥዑም የነፍስ ምግብ ሆኖታል

ነፍሳት ሲቃጠሉና ግግር በረዶ ሰርተው በቁማቸው ጋንድያ ሲሆኑ የሚደሰተው
ሰይጣን ሁሉንም ነፍሳት ተራ በተራ መቅጣቱን ተያይዞታል

እሱም ተራው ደርሶት ግግር በረዶ ውስጥ ነፍሱን ተጣለች

የሲኦልን ሙቀትና ቅዝቃዜ ጠንቅቆ ያውቅ ነበርና ስቃዩ ሲበዛበት ከሲኦል ለማምለጥ መላ ይዘይድ ጀመር

ከብዙ ጥረትና ልፋት በኃላ ልጁ ከሲኦል ታወጣኛለች ያላትን ሻማ ሰራ
በድቅድቁ ጨለማ በሻማይቱ ብርሀንነት ሶስት እርምጃዎችን ወደፊት ተራመደ
ነገር ግን ጨለማውን ተገን አድርገው የከበቡት ብዙ ነፍሳቶች አሰፍስፈው ነበር ሻማይቷን ሊቀሙት

የተጨነቀች ነፍስ .....

ሻማይቱን ለቀቃት...

ሻማዋንም ለመያዝ እልፍ ነፍሶች ተራኮቱ
ተሻሙባት

እሱግን ሊሻማባት ሊሻቀጥባት አልፈቅድምና አፈገፈገ...
ወደ መጨረሻው ጨለማ ወደሚባለው የሲኦል ክፍል ራሱን አሽቀንጥሮ ጣለ



ከወደቀበት ሲነሳም ሰይጣኑ ለእግዜር ፀሎት የሚያደርስበት የገነት መስኮት ታየችው ወደ መስኮቷ ተጠጋ

"እግዚአብሄር እረኛዬ ነው
በለመለመች መስክ ያሳድረኛል"

የሚለው ፀሎት እውነት መሆኑን አመነ
ያመነውም ሲኦል ውስጥ ሆኖ ነው ያውም ሰይጣኑና እግዜሩ በሚገናኙበት በመስኮታቸው ቀዳዳ ተመልክቶ

ወቅቱ ፀደይ ነበርና የገነት ደጃፎች በአደይ አበባ ተንቆጥቁጠዋል

ወደ አበቦቹ አማተር
ከአበቦቹ መሀል ግን አይኑ ውስጥ የገቡት ስራቸው አንድ ቅርንጫፋቸው ለየቅል የሆኑትን ዕቡጦች ላይ አይኑ ተተክሎ ቀረ

ያለመታደል እጣ ፈንታዋ ሆነና አንድኛዋ መንታይቱ አበባ ከሰመች

በመክሰሟ ልጁ አዘነ

አንዷ አበባ አበበች
አንድኛዋ ከሰመች

እነሆ ርግብም በአክናፏ አየሩን ቀዝፋ መታ የቆረችጠውን አበባ በማንቁሯ ቀጠፈቻት ቀጥፋትም እሱ ሲኦል ውስጥ ሆኖ በሚያያት መስኮት በኩል በራ አረፈች። በማንቁሯ የያዘችውን አበባ እንዲቀበላት አንገቷን ወሱ ስክክ አድርጋ በተቀመለኝ አይነት ልምምጥ አይን አይኑን ታየዋለች

ይቀበላት ይሆን?

የኑሮን ውትፍትፍ ቀዳዳ መሙላት ባይችል እንኳን ሊሞላ የሚችል ደንዳና ጫንቃ እንዳለው ያወቀችው

ግን እሷ ማን ናት?

ሻማይቱ?
መንትያ አበቦቹ?
ወይስ ርግቢቱ?


✍️ቅዱስ አርዮስ✍️
🌗የግማሽ ዓለም ጣኦት🌗

🌗የግማሽ ዓለም ጣኦት🌗

።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
Forwarded from Арбитражница dooradas (🌗የግማሽ አለም ጣኦት🌗)
ደሞ እንኩ አጭሬ ግጥም!!!

ረድኤት

።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
Forwarded from Арбитражница dooradas (🌗የግማሽ አለም ጣኦት🌗)

እናት ስትረገም
በምጥ በሲቃ ደም፣


የርግማኗ ፍሬ
ከሷ ተፈጥሬ፣


ሌላ ዘር እሻለው...


ዘውትር መፀፀት
በዛች ባንዲቴ ቅፅበት
እናቴ የሳተች ለት።


ሳል'ፈለግ መጣሁ....


መንገድ ልያዝ ደሞ


ጉዞ በጨለማ
ከሱ እኔ ልስማማ።


እ ና ማ....







ሲጥ!!


✍️ ቅዱስ አርዮስ✍️
🌗የግማሽ ዓለም ጣኦት🌗

።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
Forwarded from Арбитражница dooradas (🌗የግማሽ አለም ጣኦት🌗)
ወፈፍታ


አንድም ወፍ አንድምታ
የአክናፍ ከፍታ፣
የቃል ሽሙንምታ
ሽልብ ሽልብታ፣
ቀልብን የሚሰውር
በጥበብ እርካታ፣

አካልን የሚሰልብ
ሰላቢ ወፈፍታ።

አንድም ወፍ
አንድምታ
እፍ'ታ ወፈፍታ።



✍️ቅዱስ አርዮስ✍️
🌗የግማሽ ዓለም ጣኦት🌗



👇👇👇👇
🦋🦋 @sufafel 🦋🦋
🦋🦋 @sufafel 🦋🦋
🦋🦋 @sufafel 🦋🦋
🌿❤️እንዴት አደርሽ🌿
Yohannes_Lawgaw ስለ እኔ @sleenee Yohannes Lawgaw sle enee
🌿ዛሬ ማለዳ በዛሬ ህይወት ሰላም በሆነች ንጋት.. እልፍ #ተስፋ ባለባት...🕊🌿ያንቺ እንደሆንኩ ነቅቻለሁ ♥️ እንዴት አደርሽ🌿
🌿#Morning_Queen #ጠዋት_ስትነቂ #ማለዳ #ፀሀይ
#ስጦታዬ #ፍቅር #ዕለተ_እሁድ

።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
ውድ ደንበኞቼ ምን ፕሮግራም አለባቹ
ምርቃት
ልደት
ቤቢሻወር
ኒካህ
ቀለበት
ወይስ ብራይዳል ለነዚህ ሁሉ ያማሩ ዲኮሮች እንሰራለን ይደውሉ ያሉበት መተን ፕሮግራሞን እናሳምራለን ቤቶን ብቻ ሳይሆን እርሶንም በሂና እሳስውቦታለን እጅና እግሮን በሚያማምሩ ዲዛይኖች እናስውቦታለን ቅንድብም በሂና(ሜሽ)በተመጣጣኝ ዋጋ እንሰራለን
ለበለጠ መረጃ ☎️ 0931043351
0922147573

@Ram21h
@Ram21h

@Ram21h
@Ram21h
@Mere611
@Mere611
@Mere611
Forwarded from Арбитражница dooradas (🌒የግማሽ አለም ጣኦት 🌗)
አንዲት ፥ ሻማ ፤
በጨለማ ፥ ልንሻማ
ምሉዕነት
ገሚስነት፣

እያሳየች
ትነጉዳለች
ትሰርጋለች።


አንዲት _ሻማ
እሷን ይዘን ልንሻማ።


ቅዱስ አርዮስ✍️
🌗የግማሽ ዓለም ጣኦት🌗

።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
Forwarded from Арбитражница dooradas (🌒የግማሽ አለም ጣኦት 🌗)
አንዲት ፥ ሻማ ፤
በጨለማ ፥ ልንሻማ
ምሉዕነት
ገሚስነት፣

እያሳየች
ትነጉዳለች
ትሰርጋለች።

አንዲት _ሻማ
እሷን ይዘን ልንሻማ።

ቅዱስ አርዮስ✍️
🌗የግማሽ ዓለም ጣኦት🌗

።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
✍🏾✍🏾✍🏾✍🏾
#ተስፋ
ተናግሬ ነበር ! ለምስጥሬ ፋና ፤
የጨለማ ድባብ ታልፎ ደመና ፤
የአርባ ዕለት መሃላ ፤
ጎደሎ ቀን ሲሞላ ፤
ሰው የሆነውን መሆን አይነሳም ፤
ማብቃቱ አይቀርም፤
ሲታደሉ ቀርቶ ሲታገሉ መኖር፤
ብርታት ቀናነቱ እስካልጠፋ በቀር።
_____________
Dt ፱፰/፫/፼፩፬
@kidapoim
2025/02/06 10:09:40
Back to Top
HTML Embed Code: