Forwarded from Арбитражница dooradas (የሆነ ቦታ የሚኖር ሰው)
ምን ሆንኩኝ
ምን አገኘሁ : ከምን ለመድኩ
በየቱ ንዳድ ስቃጠል ነው : እንዲህ ያመድኩ
ከየት ወጣሁ
የት ልገባ ወዴት ሄድኩኝ : ተራመድኩኝ
ምን ሳገኝ ነው : ምኔን ሁሉ : በገዛ እጄ የገደልኩኝ
በማን ታየሁ ማንን ዐየሁ
ምንን ለየሁ : በዝች እንጭጭ : ለጋ ዕድሜ
እንዴት ልኑር : ናፍቆት ሰራሽ : ብዙ ሀዘን ተሸልሜ !
:
እኮ ወዴት የት ፈልጌ : ስፍሬን ላግኝ : ልኬን ልወቅ
በምን ተስፋ :
እምነት ይሆን : የእንባ ሸማ : ከዐይኖቼ ላይ : ዛሬ ‘ሚወልቅ
:
:
የሚል ሀሳብ ተሸክሜ
ከፈጣሪ ከእግዜር ጋራ : ስነታረክ
እምነት እውነት ያሉት ሁሉ
መስሎ ታየቶኝ : የአጉል ተረክ !
ግራ ገቧ አንዲት ነፍሴ
ካ‘ምላክ እልፍኝ : ታዛ ራቀች
ለም ሐቋ ላይ :
ስንኮል እምነት : መጠርጠርን አፀደቀች
በፀደቀው ጥርጣሬ ተመርቼ
በእብሪት ሀሳብ : ንፁ ልቤ አጠልሽቼ
ሁሉን እውነት : ሀሰት ነው ስል
ሁሉን እምነት : ስህተት ነው ስል : ከኹሉ ጋር ተኳረፍኩኝ
ኩርፊያ ሰራሽ :ተናጥሎዬ በሰራልኝ :የእንባ ጅራፍ :ተገረፍኩኝ
:
:
አ
ዘ
ን
ኩ
ኝ …ተከፋሁ እኔው : በእኔው ከፋሁ
እኔው በእኔው ከፋሁ
ባዶነት ልለቅም : ሙሉነቴን ደፋሁ ! !
:
:
[ ወትሮስ እኔን መሰል ተፈጣሪ
ሸሽቶ ሲርቅ : ከወልድ እግዜር : ከፈጣሪ ]
እምነት ጥሎ
እኩይ ሀሳብ አንጠልጥሎ
ከገባበት የመጠርጠር : ጥልቅ ገደል
መውጫ ‘ሚሆን : የአምነት እርካብ ሳይታደል
ከሰሪ አምላክ
ከእግዜሩ ጋር ሊፎካከር
የሸቅቦሽ ወደ ሰማይ ሊወረወር : ሲነሳ አይደል
ንጥፈት የለሽ : ወዛም ፌሽታው : ደስታ ሳቁ የሚገደል !
:
ነፍስ ይማር ለሳቄ!
**
[ ዳግም ሔራን ]
።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋

#አልዋሽም
ቅፅበት
ቅጥፈት
ሹመት
ተብረቅራቂዎቹን
አሻግሮ መመልከት
ጭፍን እውርነት
ቁልቁል--ቁልቁልነት
ጩልሌ--- ጮሌነት
የአልመቃምር ጉዞ
እውነታን እመሬት
ነስንሶ ጎዝጉዞ
ይረጋግጣታል
ይጨፈልቃታል
ይሸረድዳታል
አዬ,,,,,, መዛበቱ
ይሸርድዳባቱ
የሆነው ሆነና
በቅፅበት,,,,,,,,,,,,ድቁና
በቅጥፈት,,,,,,,,,,,,,,ቅስና
ሹመት,,,,,,,,,,,,ጵጵስና
አዬ,,,,,,,,,,,,,, ሽርድድና
አዬ,,,,,,,,,,,,,,ቅድስና
አወይ,,,,,,,,,ሽርሙጥና፦
በትሩን ጨብጦ
ከላይ መፈናጠጠጥ
ተልባን ከልቃሚው
አደባልቆ መውቀጥ
ይመጣ ይሆናል
ወተቱን የሚንጥ፡፡
እኔ እናገራለሁ
እውነታን አልሸሽም
ቃሌን አልገሽሽም!!!
✍ቅዱስ አርዮስ✍️
🌗የግማሽ ዓለም ጣኦት🌗
።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
ቅፅበት
ቅጥፈት
ሹመት
ተብረቅራቂዎቹን
አሻግሮ መመልከት
ጭፍን እውርነት
ቁልቁል--ቁልቁልነት
ጩልሌ--- ጮሌነት
የአልመቃምር ጉዞ
እውነታን እመሬት
ነስንሶ ጎዝጉዞ
ይረጋግጣታል
ይጨፈልቃታል
ይሸረድዳታል
አዬ,,,,,, መዛበቱ
ይሸርድዳባቱ
የሆነው ሆነና
በቅፅበት,,,,,,,,,,,,ድቁና
በቅጥፈት,,,,,,,,,,,,,,ቅስና
ሹመት,,,,,,,,,,,,ጵጵስና
አዬ,,,,,,,,,,,,,, ሽርድድና
አዬ,,,,,,,,,,,,,,ቅድስና
አወይ,,,,,,,,,ሽርሙጥና፦
በትሩን ጨብጦ
ከላይ መፈናጠጠጥ
ተልባን ከልቃሚው
አደባልቆ መውቀጥ
ይመጣ ይሆናል
ወተቱን የሚንጥ፡፡
እኔ እናገራለሁ
እውነታን አልሸሽም
ቃሌን አልገሽሽም!!!
✍ቅዱስ አርዮስ✍️
🌗የግማሽ ዓለም ጣኦት🌗
።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
Forwarded from ግጥም 🇪🇹
🔥 ቀብርሽ ደማቅ ነበር 🔥
አንቺኮ ማለት
የሲኦል ደጃፍ
የሞት መላክ አክናፍ
ባለሁለት ጭንብል
እንደ ፍርደ ገምድል
መርህ አልባ ፍጥረት
ሲያፈቅሩሽ አቀበት
ሲገፉሽ ሰገነት
አንቺኮ ማለት
ልክ እንደ አርዮስ
ተፈጥሮ ምትሸሺ
ጠላት ምታነግሺ
ከሰማይ የተጣልሽ
ከምድር የተጣላሽ
የቃየል እናቱ
ደም ግባተ ከንቱ
አንቺኮ ማለት
ትህትና ማይገባሽ
ፍቅር የማይገዛሽ
ድቃቂ ነሀስ ቅቡ
ያኔማ ሳይገባኝ
ተሸከምኩሽ በእንቅብ
አይምሮሽ ደና ነው
ሀሳብሽ እንዴት ነው
ትኩረትሽስ ባክሽ
እዛጋ ሌላ ሰው እዚ ጋ ፍስሀ
ማንም ሚጎትትሽ
የመንገድ ዳር ውሀ
እጅግ አከብራለሁ
ለሴት ክብር አለኝ
ትህትና ጥሩ ነው
ከንቀት ምን ሊገኝ
ተፃፈ 🔥 በበረከት አሁን
@kidapoim
አንቺኮ ማለት
የሲኦል ደጃፍ
የሞት መላክ አክናፍ
ባለሁለት ጭንብል
እንደ ፍርደ ገምድል
መርህ አልባ ፍጥረት
ሲያፈቅሩሽ አቀበት
ሲገፉሽ ሰገነት
አንቺኮ ማለት
ልክ እንደ አርዮስ
ተፈጥሮ ምትሸሺ
ጠላት ምታነግሺ
ከሰማይ የተጣልሽ
ከምድር የተጣላሽ
የቃየል እናቱ
ደም ግባተ ከንቱ
አንቺኮ ማለት
ትህትና ማይገባሽ
ፍቅር የማይገዛሽ
ድቃቂ ነሀስ ቅቡ
ያኔማ ሳይገባኝ
ተሸከምኩሽ በእንቅብ
አይምሮሽ ደና ነው
ሀሳብሽ እንዴት ነው
ትኩረትሽስ ባክሽ
እዛጋ ሌላ ሰው እዚ ጋ ፍስሀ
ማንም ሚጎትትሽ
የመንገድ ዳር ውሀ
እጅግ አከብራለሁ
ለሴት ክብር አለኝ
ትህትና ጥሩ ነው
ከንቀት ምን ሊገኝ
ተፃፈ 🔥 በበረከት አሁን
@kidapoim
Forwarded from Арбитражница dooradas (የሆነ ቦታ የሚኖር ሰው)
💚💛❤️ችለነዋል 💚💛❤️
ጆጆ አሌክስ
።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
ጆጆ አሌክስ
።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
Forwarded from Арбитражница dooradas (ቅዱስ አርዮስ)
ጣዕም በምን ሊቀመስ?
?
በምራቅ ታጅቦ የሚደርስ
: : :
ጣዕም አልባ ማንነትስ.......
ምን?
ማለት ነው?
ሰውነትስ?
✍️ቅዱስ ዓርዮስ✍️
🌗የግማሽ አለም ጣኦት🌗
።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
?
በምራቅ ታጅቦ የሚደርስ
: : :
ጣዕም አልባ ማንነትስ.......
ምን?
ማለት ነው?
ሰውነትስ?
✍️ቅዱስ ዓርዮስ✍️
🌗
።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
✍️ቅዱስ ዓርዮስ✍️
🌗የግማሽ አለም ጣኦት🌗
።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🌗የግማሽ አለም ጣኦት🌗
።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
Audio
ከምኔው
✍️ዘምሽ የአልግዬ✍️
🖤የጠቆረ ልብ🖤
አንባቢ መሳይ
።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
✍️ዘምሽ የአልግዬ✍️
🖤የጠቆረ ልብ🖤
አንባቢ መሳይ
።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
Audio
ናፍቆት
ፀሀፊ ና አንባቢ
✍️ቅዱስ ዓርዮስ✍️
🌗የግማሽ አለም ጣኦት🌗
።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
ፀሀፊ ና አንባቢ
✍️ቅዱስ ዓርዮስ✍️
🌗የግማሽ አለም ጣኦት🌗
።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
https://vm.tiktok.com/ZM8gcBLeT/
ሰውዬ ጤና የለህም!!! 😂🤣😅አዝናኝ ቪዲዮ!
Subscribe for more funny amharic translated vedios.
ለሌሎች አዝናኝና በአማርኛ የተተረጎሙ አዝናኝ ቪዲዮዎች ለማግኘት ሊንኮቹን ይከተሉ!
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
*youtube
https://youtube.com/channel/UC6lhxeXubv3KTAqrOmI7rhQ
*tiktok
https://vm.tiktok.com/ZMRfTvYWA/
*Telegram
@poimfitsae

ከላይ ወደታች ያደገው ባል !!
(አሌክስ አብርሃም)
አንዷ ሜክሲኳይት ቆንጆ ከአንድ በእድሜ ሁለት አመት ከምትበልጠው ወጣት ጋር ፍቅር
ትጀምራለች ! 28 ዓመቱ ነው ፡፡ ብዙዎች ፍቅር አይደለም ሚስኪን ዶክተር እጮኛዋን
አፍንጫህን ላስ ብላ ይሄን ዘሎ ያልጠገበ ወጣት የተጣበቀችበት ሃብታም ስለሆነ ነው
ይላሉ ! በእርግጥ ልጁ የልጅ ሃብታም ነበር !ከውብ ቪላዎች እስከመዝናኛ ጀልባዎች ያለው
… የግል ጀት አውሮፕላን ሁሉ ባለቤት … የጥንት ታዋቂ ስዕሎችን ይሰበስባል ይሸጣል
ያሻሽጣል ! ስለስዕል ሲተነትን አፍ ያስከፍታል ! ይችንም ቆንጆ የተዋወቃት አንድ የስዕል
ጨረታ ላይ ነው … አንድ ነጥብ አምስት ሚሊየን ዶላር ሆጭ አድርጎ መክተፊያ የምታክል
ካንቫስ ላይ የተሳለች ሙጭርጭር ስዕል ሲገዛ !
የሆነ ሁኖ በሶስት ወር ውስጥ ድል ባለ ሰርግ ታገባዋለች ! ሰርጋቸው የሚያስቀና ነበር …
ልጅቱ የመጨረሻ ቆንጆ ስትሆን የባለሃብቱ ባሏ መልክ ደግሞ ወደመለዓክ የሚጠጋጋ
አይነት ነበር …እንደዛ አይነት ቆንጆ መልክ ታይቶ አይታወቅም ነው የሚሉት …..(ያው ሰው
ያጋንናል) ቀስ በቀስ ግን ትዳሩ ችግር ገጠመው … ለምሳሌ ልጅት ዳንስ ትወዳለች ማበድ
ትወዳለች ባል ደግሞ ሲበዛ የተረጋጋ ሲራመድም ሲናገርም ቀሰስ ያለ ሆነ !
ወደክለብ ይሄዱና አብራው ልትውረገረግ ስትሞክር ልጁ ልቡን ያፍነዋል …‹‹ሃኒ ይሄ ነገር
የልብ ህመም እንዳይሆን ታየው›› ስትለው አይስማማም …እሷም ብዙም አልገፋችውም
(ምናልባት ልቡ ቢቆምም ቢበዛ እንደአሸዋ የበዛ ሃብት ውርስ እንጅ ሌላ ምን ይመጣብኛል
ብላም ይሆናል) ችግሩ ግን በዚህ አልቆመም የዳንሱ ወለል ላይ የገጠመው ችግር
ወደምኝታ ቤታቸው ተከትሎ ገባ … ሳተናው ልፍስፍስ አለባት ! …ስንት የለመደች ልጅ …
ቢነቃቃ ብላ ምኝታ ቤቷ በዛ ውብ ሰውነቷ ራቁቷን ብትደንስ … ብትስለመለም ወፍ የለም !
እንደውም ዳንሷን ሳትጨርስ አጅሬው ማንኮራፋት ይጀምራል ! ‹‹ግዴለም ሰው በእንትን
ብቻ አይኖርም›› ብላ ዝም አለች …
ይባስ ብሎ ‹‹ሃኒ አይ ላቭ ዩ ›› ስትለው ‹‹እ ›› ማለት ጀመረ ጮክ ብላ ካልተናገረች
ጆሮውን ያዝ ያደርገዋል ለካ …. ግራ ግብት ብሏት ለማን አቤት ልበል እያለች በውስጧ
ስታምሰለስል ….አንድ ቀን ሌሊት …የምኝታ ቤታቸው በር ተገንጥሎ ካፍ እስከገደፋቸው
የታጠቁ የአገሪቱ ልዩ ሃይል ኮማንዶዎች ሁለቱም ግንባር ላይ መሳሪያቸውን አነጣጥረው
እጃቸውን እየቀፈደዱ ወሰዷቸው ….
በቀጣዩ ቀን ሚስት የፖሊስ ሪፖርት ተነበበላት!
‹‹ባልሽ ላለፉት አስራ አምስት ዓመታት በእግር በፈረስ ሲፈለግ የኖረ ታዋቂ የአደንዛዥ እፅ
አዘዋዋሪ ነው ›› አሏት ‹‹አብዳችኋል እሱ የታዋቂ ሰዓሊያንን ስእል የሚሰበስብ እና
የሚሸጥ ጥበብ የጠራቸው ሰው ነው አለች ›› ቀጥለው ‹‹ስሙ አሁን የምታዊቂው ሳይሆን
ሌላ ነው›› አሉና ሰምታው የማታውቀው ስም ነገሯት .... ግራ ገባት ሚስት ….‹‹መልኩም
ይሄ የምታይው ሳይሆን ይሄንኛው ነው ›› ብለው አንድ ጠባሳ የተጋደመበት ወመኔ ፎቶ ፊቷ
ላይ ጋረጡባት ለማየት እንኳን የሚቀፍ ፊት ! …
ልጅት ያንን ውብ ፈገግታዋን ፈገግ አለችና << እንዲህ ሰይጣን እንደያዘው ሰው
የሚቀባጥሩት አገሩ ሙስና ባህል የሆነበት ነው … ሳንቲም ፈልገው ነው>> ብላ
ወደመርማሪው ጠጋ አለች ‹‹ በቃ ገብቶኛል …ስንት ነው የምትፈልጉት ንገረኝ አሁኑ ቸክ
እፅፋለሁ ? ›› አለችው ! መርማሪው ከትከት ብሎ ከልቡ ስቆ ….
‹‹የኔ እህት የነገሩ ክብደት አልገባሽም .... ባልሽ የ57 ዓመት ሽማግሌ ነው ሪከርዳችን
እንደሚያሳየው ባለፉት አስራ አምስት ዓመታት ከ21 ግዜ በላይ የፕላስቲክ ሰርጀሪ አሰርቷል
… ወጣት ነው ብለሽ ያገባሽው ሽማግሌ ነው … ›› ብለው ከመጀመሪያ እስከመጨረሻ
በፎቶ የነበረውን ሂደት በፎቶ እያስደገፉ አሳዩዋት …›› ባሏ እንዴት ከላይ ወደታች እንዳደገ !
በመጨረሻም …ንብረቱ ቤሳቤስቲን ሳይቀር በአደንዛዥ እፅ የመጣ ነውና ከመኪኖችሽ
ጀምሮ እስከውድ ጌጣጌጦችሽ ለመንግስት ገቢ ተደርገዋል …. በርካታ እጀ ረጅም ጠላቶች
ያለው ሰው ስለሆነ የበቀል ጦሱ ለአንች እንዳይተርፍ በተቻለን ሁሉ ጥበቃ እናደርጋለን …
የተሻለው ግን ከቻልሽ ዞር ብትይ ነው ! ራቁቴን ወደዚህ ቪላ መጥቻለው ራቁቴንም
እሄዳለሁ እያልሽ አምልጭ !!
ወገኖቸ ፍቅረኞቻችሁ አንድ ሁለት አመት ቀሸቡ ብላችሁ አትነጫነጩ… ፍቅር እና ፕላስቲክ
ሰርጀሪ ካለ 57 አዲሱ 28 ነው !
@poimfitsae @poimfitsae

ፀሀፊና አንባቢ
ብሩክ
።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
ብሩክ
።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
#ህዳር ሲታጠን
አንድ ሰውዬ ነበር ።አይዘራም ፡ አያጭድም ፡ አይኮተኩትም፡ አይፈትልም ።አሊያም ነግዶ አያተርፉም። የቅዱስ ሚካኤል ወዳጅ ነው።
ወዳጅነት መገለጫው ምንድን ነው ? መባ፡ ስጦታ ፡ ምስጋና ወይስ ደጅ መጥናት ? ወይስ ውዳሴ ?
ሰውዬው ዕለት ዕለት ወደ ሀያሉ መላዐክ ደጅ እየቀረበ "አንተ የእስራኤል መጋቢ ጠባቂ ሆይ የዕለት ምግቤን ፡ የዓመት ጉርሴን ስለምን አትሰጠኝም ? በረሃብ ጅራፍ ስገረፍ ለምን ዝም ትለኛለህ ?………" እያለ ይወተውተዋል።
መቼም ፃድቃን ባይኖሩ ኖሮ ምድር በጭንቀት ቸነፈር ታልቅ ነበር ። ሐጢያተኛው የመዳን ጭላንጭል የት ያገኝ ነበር ? ሌላው ቀርቶ ብዙ የጭንቀት በሽተኞች እና ሐኪሞች ምድርን ይሞሉታል ። የምንዱባኑ የዕለት የዓመት ጉርስ እነዚሁ ፃድቃን ናቸው ።
ዓለም የራሷን በዓላት ታከብራለች ። ቲሸርት የመልበስ ቀን ፡ የፍቅረኞች ፡ የግራኞች፡ የአባቶች፡ የእናቶች ፡ የእንስሳት ወዘተርፈ እንደየ ዕውቀቷ አስባ ትውላለች ። ነገር ግን የትኛውም ምስኪን በዓለም በዓላት ቁራሽ አግኝቶ አያውቅም ። ይልቅ በተስፋ ልቡን እያሸፈተ በረሃብና በቸነፈር እሷኑ ይሰናበታታል። ከተሳካለት በውንብድና ያወዛግባታል።
ሰውዬው ዕለት ዕለት ደጅ መጥናቱን ቀጠለ ። እግዜር የደግነት ጥጉ ብዙ ነው ። በዝምታ ፡ በመናገር ፡ በገቢር ስራውን ይከውናል። ታዓምር ወዳጅ ፍጡር በዛ እንጂ …………
.ቀን ቀን ወልዶ ቅዱስ ሚካኤል ተገለፀለት። ለዛ ሰውዬ "አንተ ሰነፍ ! ስለ ምን በከንቱ ትወተውተኛለህ? እባርክልህ ዘንዳ አትሰራ! አታጭድ ! አሊያም ነግደህ አታተርፍ! "አለው። ሰውዬው ሌላ ሰበብ ከመደርደር አልተቆጠበም ።
"ተነስተህ ከቤተመቅደሱ ጠባቂ ገንዘብ ትበደር ዘንድ ልዋስህ ሰርተህም ነግደህም ትርፉን ወስደህ የተበደርከውን መልስ ፡ ይህንንም እንዳትረሳ !" ብሎት ሔደ
እንዲህ እንዲህ እያለ መንገድ የሳተውን ቀናውን መራው ።
ህዳር በሽታ የሚባል ተከስቶ ወሬ ነጋሪ እንዳይተርፍ አድርጎ ምድሪቱን አራቁታት ነበር ። ዛሬም የዛ ዝርያ ምድራችንን አያፈናት ነው።
እኛም በየመንደሩ እናጥናለን። ችግር ብሎ መከራው ይቆም ዘንድ ፈጣሪ ይርዳን ።
AMEN(፫)
…………………………
………………………………………………
………………………………………………………
Dt--✍✍✍ህዳር/፩፪/፼፩፬

አስራ ኹለት ግጥም
ፀሀፊ ✍️ሰለሞን ሽፈራው✍️
አንባቢ🌗የግማሽ ዓለም ጣኦት🌗
።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
ፀሀፊ ✍️ሰለሞን ሽፈራው✍️
አንባቢ🌗
።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
Forwarded from Арбитражница dooradas (የሆነ ቦታ የሚኖር ሰው)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ደሞ እንኩ ወኔ
።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
@kene_Alem_Wedenate
።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
@kene_Alem_Wedenate
ፀሎቴን ባሰማ ፥ እንደሰው ዝም አለኝ
እሱንም ዘመቻ ፥ ወሰዱት መሰለኝ
.......
የእቴሜቴ ጀምበር
©ሲራክ ወንድሙ
.
እረኛ አይዘምርም ፥ ዝም ነው አድባሩ
ፋኖስ ክሩን አጥቷል ፥ መሸ ደህና እደሩ
ቡሬ መንደር ራቃት ፥ የለችም ከቤቷ
በሌት አልዘመረች ፥ ከፍቷታል ወፊቷ
ማልዶ ሌት ሚያነቃኝ ፥ ዶሮ በጉድ ወጣ
የሌት ድምፁን ሸጦ ፥ መውዜር ይዞ መጣ
ወዲያም ወደ ሰማይ
ከጎጆዬ በላይ
ፀሎቴን ባሰማ እንደሰው ዝም አለኝ
እሱንም ዘመቻ ወሰዱት መሰለኝ
.
የዛች የእዝነት አርማ ፥ የህዋ ላይ ሰንደቅ
እንዴት ቀን ከፍቶባት ፥ ውብ ጀምበሯ ትጥለቅ
ከዛች ከገራገር ፥ ከደጊቱ ዳሴ
እንደምን ብርቅ ይሁን ፥ ሰላም ለእለት ጉርሴ
ኧረ እንደምን በምን
ኧረ እንደምን በምን
አምነን ያነገስነው ብራ ቀን ይዳምን
እኔን አፈር ይብላኝ ፥ ለእኔ ቀኑ ይክፋ
አንቺን ያሳጣችሽ ፥ ያች አለም ትደፋ
እስከ መች አስከ መች ፥ የአረር ሙዳይ ቋጥረን
እንደጃኖ ኩታ ፥ ዝናር ጥለት አርገን
ሀገር እያጠፋን ፥ ያልፋል እንላለን ?
እንዴት ነው መሰንበት ?
መውዜር እንደነዶ በሚመዘዝበት?
ኧረ እንደምን በምን
ኧረ እንደምን በምን
አምነን ያነገስነው ብራ ቀን ይዳምን?
.
ከጩኸትሽ ማዶ ፥ ካኮረፈው ሰማይ
ቄራ ከመሰለው ፥ ከአድማስሽ ሸራ ላይ
እብሪት ያጠላበት ፥ ምስል ድንገት ካየው
ለቸር አንመስለኝም ፥ ያን ጊዜ ፈራለሁ
አርብ አርቡን አመሻሽ
የሰማዩ ገላ ሲመስል የደም ሻሽ
ንትብ የለበሰ
ከወደ አንገቱ ዘሞ የተዘለሰ
ይሁዳሽን ባላይ ፥ ወድቆ ሲያንሰራራ
መስቀል ሆኗል ለሻጭ ፥ ገዢ ራሱን ያኩራ
ከክርስቶስ ይልቅ ፥ ይሁዳ ነውና ሚረከብ መከራ
ምክኒያቱም ......
ዘመን እያሰፉ
ትውልድ ለሚነቅፉ
ነገር ጠንቷል ዛሬ ፥ አውቀውት ይረፉ
ለሻጭ መስቀል ሊሆን ፥ ምሏልና ዛፉ
.
በኑረት ቀራንዮ ፥ በህይወት ጎለጎታ
ከገዳይሽ ቀዬ ፥ አንቺ ሆነሽ ጌታ
በሰማያ አኮርባጅ ፥ ወዲያ ስትላጊ
የመከራን መስቀል በሌት ተሸክመሽ ፥ መንገድ ስትፈልጊ
ጨረቃዋ ገባች ፥ ከደመና ጉያ
ከዋክቶች ሸሽተው ፥ እንደሰደድ ቋያ
ጠረንሽን ገፍተው ፥ ከገላሽ ሲርቁ
በንቄት ሸምቀው ፥ ሊጥሉሽ ዘለቁ
.
ዞር ብንል ወዲያ ፥ አራራይ መረዋ
ቀና ብንል ኦና ፥ የጠቆረ ህዋ
የፀሎትሽ ጩኸት ፥ ካልደረሰው ያ ' ቃል
እሱም እንደሰዉ ዘምቶልሽ ይሆናል።
..................... //// ..............
©ሲራክ ወንድሙ @siraaq
የእቴሜቴ ጀምበር
ህዳር ፳፻፲፬ ዓ.ም
https://www.tg-me.com/poimFitsae

Telegram
የፍፄ ግጥሞች
#አጫጭር ግጥሞች
#ወጎች
#መጣጥፍ እና ሌሎችም የጥበብ ስራዎች።
ለአስተያየት ፥ ጥያቄ ፥ እንዲሁም ፅሁፍ ለመላክ @ft2194
Follow