Telegram Web Link
#የአርባምንጭ ዝጊቲ አቦ ግዙፍ ፕሮጀት
~~~
ህንፃ መቅደስ ብቻ ሳይሆን የደቡብ ኦርቶዶክሳውያን ላይ ለውጥ የሚያመጣው የ1 ቢሊዬን ብር የአርባምንጭ ዝጊቲ አቦ ፕሮጀክት!

ይህ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በአንድ ውዷ እንስት በኩል የፈጸመችው የእዚህ ዘመን ግዙፉ መንፈሣዊ ፕሮጀክት ነው።

የአርባምንጭ ዝጊቲ አቦ ግዙፍ ፕሮጀት ከ1 ቢሊዬን ብር በላይ እየወጣበት ይገኛል ሲባል አንዳንዶች ግነት የተጨመረበት መሬት ላይ የሌለ ይመስላቸዋል።

በእዚህ ስፍራ የተደረገው ታምር የሚመስል ሥራ ልግለጽልህ

ዝጊቲ አቡዬ አሁን ያለው ይዞታ ይህ ፕሮጀክት ከመጀመሩ በፊት ካለው 1/20 ገደማ የሚሆን ጥበት ውስጥ የነበረ ነው። ከ20 እጥፍ በላይ የይዞታ ማስፋፍያ በግዢ ተከናውኗል።

ስፍራው ረግራጋማ ከመሆኑ የተነሳ ጥልቅ የመሰረት ቁፋሮ ተደርጎበታል። በ30 ሜትር ቁመት እና ከ500 በላይ ሜትር ርዝመት ያለው ሼሮል(የፌሮ እና ኮንክሪት ሙሌት) የህንፃ መቅደሱን መሰረት ብቻ ከናዳ ለመጠበቅ ተገንብቶበታል።

ህንፃ መቅደሱ በልዩ የምህድስና ጥበብ ይህን ግዙፍ ህንፃ መሸከም ይኖርባቸው ዘንድ ሊቆሙ የሚገባቸው ክብደት ተሸካሚ ምሶሶዎች(ኮለን) ከመሃል እንዲወጡ ተደርገዋል።

የህንፃ መቅደሱ የጉልላቱን መስቀል ጨምሮ ልዩ ልዩ የማስጨረሻ ቁሳቁሶች ከሀገር ውጪ የተገዙ ናቸው።

ይህ ፕሮጀክት ህንፃ መቅደስ ብቻ ሳይሆን 250 ደቀመዘምራንን የሚቀብል አብነት ትምህርት ቤት፣ባለ 2 ወለል መንበረ ጽጽስና ህንፃ፣የሊቃነጳጰሳት እና የቄሳውስት መካነ መቃብር ይሆን ዘንድ የታነጸ የቤዝመንት ህንፃ፣የዘይት መጭመቂያ ፋብሪካ አዳራሽ፣

የጸበልተኛ ማረፊያ የሚሆኑ በቁጥር ከ10 በላይ ሰፋፊ አዳራሾች፣ህንፃ መቅደሱን እና ቤቴሌሔሙን የሚያገናኝ ድልዲህ ፣ወደ ህንፃ መቅደሱ ሰውን የሚወስድ የእግረኛ መንገድ እና ዲልዲህ፣የግቢ ማስዋብ ግሪነሪ ሥራዎች ዋነኞቹ ናቸው።

ይህ ሁሉ ያካተተው  የዝጊቲ አቦ ልዩ መንፈሣዊ ፕሮጀክት ሲገነባ አንድም ቀን ስለአቦ ተብሎ ተለምኖ አያውቅም። እርሷ እና ጻድቁ ልብ ለልብ በሚግባቡት እህታችን እና ቤተሰቧ በኩል እየተፈጸመ ተገኘ እንጅ።

ለእህታችን እና ለቤተሰቧ ጻድቁ ረድኤት በረከት ይላክላቸው።

እግዚአብሔር ይመስገን !!!

@ortodxtewahedo
https://vm.tiktok.com/ZMrhmEgX4/

የኦርቶዶክስ ተዋሕዶን እንወቅ በቲክትክ መተናል ፎሎ በማድረግ አበረታቱን ።
በ ቀጥታ ስርጭት ተከታታይ ትምህርቶችን ለማስተማር አስበናል ቲክ ቶክ ምቹ ሆኖ አግኝተነዋል እሱን ለመጀመር 1000 ፎሎሎወር ያስፈልገናል ፎሎ በማድረግ ተባበሩን ።
Audio
አንቺ ከእኔ ጋር ከሄድሽ እሄዳለሁ
        
Size:-19.7MB
Length:-56:32

በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

@ortodxtewahedo
ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፤ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፤ ምስለ ኖኅ
ኪዳነ ዘአቀምከ፤ ለደቂቀ እስራኤል መና ዘአውረድከ፤
ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፤ ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ፤ ወሥነ
ገዳምኒ ምስለ ቅዱሳኒከ፤ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፤ ወከመ
ወሬዛ ኃየል መላትሒሁ ጉርዔሁ መዓርዒር አምሳሉ
ዘወይጠል፤ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፤ ሰማየ ወምድረ ዘአንተ
ፈጠርከ፤ ፀሐየ ወወርኀ ዘአስተዋደድከ፤ ወመኑ መሐሪ
ዘከማከ፤ በከዋክብት ሰማየ ዘከለልከ፤ ወመኑ መሐሪ
ዘከማከ፤ ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ፤ ወመኑ መሐሪ
ዘከማከ፤ ቀደሳ ወአክበራ አዕበያ ለሰንበት፤ ወአልዓላ
እምኵሉ ዕለት፤ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፤ ወኵሉ ይሴፎ ኪያከ፤
#ትርጉም
ከኖኅ ጋር ቃል ኪዳን የገባህ እንዳንተ ይቅር ባይ ማነው
ለእስራኤል ልጆች መናን ያወረድክ፤ ምድርን በአበቦች
ያስጌጥክ፤ እንዳንተ ይቅር ባይ ማነው ? የምድረ በዳውን
አራዊት ከወዳጆችህ ጋር ያስማማህ እንዳንተ ያለ ይቅር ባይ
ማነው፤ ጉንጮቹ እንደ ዋልያ እንቦሳ ፈጣኖች ናቸው፤
አንደበቱ ጣፋጭ ነው፤ ተወዳጅነቱ እንደ ፌቆ ግልገል ነው፤
ሰማይና ምድርን የፈጠርክ፤ ፀሐይና ጨረቃን ያስማማህ፤
ሰማይን በከዋክብት የሸፈንክ፤ ምድርን በአበቦች ያሸበረቅህ፤
ሰንበትን ያከበርካት ከዕለታትም ለይተህ ከፍከፍያደረግኻት፤
አቤት!! እንዳንተ ይቅር ባይ ማንም የለምና ኹሉም አንተን
ተስፋ ያደርጋሉ።
#እንኳን_ለዓለም_ጌታ_ለፍጥረታት_አምላክ_ለነገስታት_ንጉስ_ልዑለ_ባህሪ_ለሆነው_ለአምላካችን_ለመድሐኒታችን_መድኃኒዓለም_ወርሀዊ_በዓል_አደረሰን !

@ortodoxtewahedo
Audio
"" #የጥያቄዎች_መልስ_ ስለ_ሱባኤና ተያያዥ_ጉዳዮች ""

(ግንቦት 24 - 2012)

የጥያቄዎች መልስ

#1 ሱባኤ ምን ማለት ነው

#2 ሱባኤ ለምን እንገባለን

#3 ሱባኤ ሲገባ ምን ምን መደረግ አለበት

ዝርዝር መልስ የተሰጠበት ነው:: በተጨማሪ ለዚህ ዘመን ትውልድ ሁሉ ጠቃሚ ምክር አለው::በተለይ #ፍልስፍናው ለሚያሸፍታቸው !!

<<ይደመጥ::>>

በመምህር ዲ/ዮርዳኖስ አበበ

ዝክረ ቅዱሳን ጉባኤ ዘጎንደር
'
" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
https://www.tg-me.com/zikirekdusn

@ortodoxtewahedo
በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ የሚገኝ በፈዋሽነቱ የሚታወቀዉ የታላቁ መጥምቀ መለኮት ሸንኮራ ቅዱስ ዮሐንስ ዓመታዊ ክብረ በዓል እንኳን አደረሳችሁ።

- ከአዲስ አበባ 141 ኪ.ሜ
- ከባህርዳር 701 ኪሜ
- ከደብረ ብርሃን 274 ኪ.ሜ
- ከአረርቲ 11 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን ታሪካዊና ቅዱስ ቦታ ነው🙏🤲

@ortodoxtewahedo
ሰኔ30_መጥምቀ_መለኮት_ቅዱስ_ዮሀንስ_ነው እንኳን አደረስን አደረሳችሁ

#መጥምቀ_መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ማለት በጌታ የተከበረ ነቢይ እና
ጻድቅ ነው። “እውነት እላችኋለሁ፥ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል
ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም፤ ” በማለት
የተናገረለት ቅዱስ ኣባት ነው።
መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮውሃንስ የተሰጡት
ሃብተ ጸጋዎች
1፦ ነብይ-
2 ካህን
3 መምህር
4 ሃዋርያ
5 ፃድቅ
6 መጥምቅ
7 ሰማእት ነው።

ቅዱስ ዮሓንስ ከነቢያት ሁሉ የሚበልጥ መሆኑን
ጌታችን ሰናገር እንዲህ ብሎ ከሎ “ኣዎ ከነቢይ እንኳ የሚበልጥ
ነብይ ነው እላችሃለሁ” በማልት መስክሮለታል።
ዮሐንስ ሃቀኛ መምህር፤ ነቢይ፤ ካህን፤ ሰማዕት፤
ሐዋርያ በመሆኑ ከኣምላኩ ክብርን የተቀበለ ቅዱስ ኣባት ነው።
ስለዚህ ነው ደግሞ ጌታችን ኢየስሱ ክርስቶስ እራሱ ግልጽ
ኣድርጎ ስለ ዮሐንስ ክብር የተናገረው ። ትንቢት የተነገረለት
ዮሓንስ ክብሩ በመልኣኩ እንዲህ በማለት ነው በእግዚአብሔር
ፊት ታላቅ ነቢይ እንደሆነ፡ በመንፈስ ቅዱስ የተመረጠ
በንጽሕናው በኣገልግሎቱ በመላእክት ደረጃ የሚታሰብ ነው
ብሎታል።

መጥንቀ መለኮት ቅዱስ ዩሀንስ
እኛንም ካለብን ችግርአውጣን

የመጥመቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ረድኤት በረከት ይደርብን ኢትዮጵያን ይባርካት ይቀድሳት ይጎብኛት ፀሎት ምልጃው ይብዛልን ።አሜን ✝️ አሜን ✝️ አሜን ✝️

@ortodoxtewahedo
#ብዙሀነ ይትፌስሁ በልደቱ።

† ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ †

¤የቅዱሳኑ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ልጅ
¤በማኅጸን ሳለ መንፈስ ቅዱስ የሞላበት
¤በበርኀ ያደገና በገዳማዊ ቅድስና ያጌጠ
¤እሥራኤልን ለንስሐ ያጠመቀ
¤የጌታችንን መንገድ የጠረገ
¤ጌታውን ያጠመቀና
¤ስለ እውነት አንገቱን የተቆረጠ ታላቅ ሰው ነው::

††† ስለዚህም ቤተ ክርስቲያን:-
ነቢይ:
ሐዋርያ:
ሰማዕት:
ጻድቅ:
ገዳማዊ:
መጥምቀ መለኮት:
ጸያሔ ፍኖት:
ቃለ ዐዋዲ ብላ ታከብረዋለች::

††† ቅዱሱ በዚህች ዕለት ወደ እሥር ቤት ገብቷል::
ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
ንጉሡ ሔሮድስ የወንድሙን የፊልጶስን ሚስት ሔሮድያዳን በማግባቱና በመሰል ክፋቶቹ ቅዱስ ዮሐንስ ይገስጸው ነበር:: ቅዱስ ዮሐንስ "መምሕር ወመገስጽ: ዘኢያደሉ ለገጽ - ፊት አይቶ የማያዳላ" ነውና ገሰጸው::

ሔሮድስ ቅዱሱን ይፈራው: ያከብረውም ነበር:: በኋላ ግን ፈቃደ ሥጋው ስላየለበት: በተለይ ደግሞ ከሰባት ቀናት በኋላ ልደቱን ሲያከብር እንዳይረብሸው በመስጋት በዚህች ቀን በወታደሮቹ አስይዞ እሥር ቤት ውስጥ
ጥሎታል:: ለሰባት ቀናት በጨለማ ውስጥ አሥሮ መስከረም 2 ቀን አንገቱን እንዴት እንዳስቆረጠው ዕለቱን ጠብቀን እንመለከታለንና የዚያ ሰው ይበለን::

††† "ጌታ ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ ዮሐንስ ሊናገር ጀመረ . . . ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይን? አዎን እላችኋለሁ ከነቢይም የሚበልጠውን . . . እውነት እላችኋለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሳም . . . ነቢያት ሁሉና ሕጉ እስከ ዮሐንስ ድረስ ትንቢት ተናገሩ:: ልትቀበሉትስ ብትወዱ ይመጣ ዘንድ ያለው ኤልያስ ይሕ ነው:: የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ::"

†(ማቴ. ፲፩፥፯-፲፭)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †ኀ

@ortodoxtewahedo
2024/09/29 15:33:34
Back to Top
HTML Embed Code: