Telegram Web Link
#ርዕሰ አድባራት ወገዳማት እንጦጦ ደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተክርስቲያን ::

@ortodoxtewahedo
❖ ሰኔ ፲፪ ❖

✞ ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት [በነገዱ ውስጥ፥ በመላእክት ሁሉ ላይ አለቃ ሆኖ የተሾመበት..፣ በእስክንድርያ ከተማ ቅዳሴ ቤቱ የከበረበት..፣ የሞት መልእክት የተጻፈባትን የቅዱስ ባሕራንን ደብዳቤ የለወጠበት..፣ ቅድስት አፎምያን ያዳነበት..፣ ለሰው ልጆች ሁሉ ምሕረትን የሚለምንበት..በእለኚህ ምክንያት ነው በዓሉን የምናከብረው] ✞

"ሰላም ለሚካኤል መሐሪ ውእቱ፤ ወተአዛዚ ለሰብእ በዲበ ሠናይቱ፤ ለቀርነ ዝንቱ መልአክ በድምፀ ንፍሐቱ፤ በከመ ኮነ ቀዳሚ ውስተ ሰማያት ዕርገቱ፤ ለእግዚአብሔር ይከውን ዳግመ ምጽአቱ።"

@ortodoxtewahedo
#ጾመ_ሐዋርያት

‹‹ይኽ ጾም በአላዋቂዎችን እና በቤተክርስቲያን ጠላቶች የሽማሌዎች ጾም እየተባለ ምዕመናን እንዳይጾሙት ብዙ ተለፍቷል..››

በየዓመቱ በዕለተ ሰኑይ የሚዠምሩ ሶስት አጽዋማት ብቻ አሉ ፡፡ ከእነርሱ መሀከል አንዱ ጾመ ሐዋርያት ነው ፡፡ ቅበላው በዕለተ እሑድ ይሆንና ጾሙ ሰኞ ይውላል ፡፡ የ2016 ዓ.ም ጾመ ሐዋርያት ሰኔ 17 ይገባል ፡፡

ይህ ጾም እራሱ ጌታቸን ኢየሱስ ክርቶስ ትንቢት የተናገረለት ጾም ነው፡፡
ይኽ ታላቅ ጾም የዛሬ 1902 ዓመት በፊት በራሳቸው በቅዱሳን ሐዋርያት የተጀመረ ጾም ነው ፡፡ ከሰባቱ አጽዋማት መሀከልም አንዱ ነው ፡፡
ፈሪሳውያ ጌታችንን ደቀ መዛሙርትህ አይጾሙም ብለው በጠየቁት ጊዜ እርሱም ‹‹ ሚዜዎች ሙሽራ ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉን ? ነገር ግን መሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል ፤ በዚያ ጊዜም ይጾማሉ ፡፡ በአረጀ ልብስ አዲስ እራፊ የሚያኖር የለም ፤ መጣፊያው ልብሱን ይቦጭቀዋልና ፤ መቀደዱም የባሰ ይሆናል ፡፡ በአረጀ አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም ፤ ቢደረግ ግን አቁማዳው ይፈነዳል የወይን ጠጁም ይፈሳል ፡፡አቁማዳው ይጠፋል ፡፡ ነገር ግን አዲሱን የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ያኖረዋል ሁለቱም ይጠባበቃሉ ፡፡›› ማቴ 9 ፥ 14-17 አላቸው ፡፡ይኽ ቃለ እራሱ ጌታችን መድኀኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ ስለ ጾመ ሐዋርያት የተናገረው ትንቢት ነው ፡፡

‹‹#መሽራው_ከተወሰደ በኃላ›› ማለት ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሰማይ ካረገ በኃላ ማለት ሲኾን ይኽን ጾም ከዕረገት በኋላ የምንዠምረው ፤ ይኽን ምሳሌ በማድረግ ነው ፡፡ ዐሥር ቀን ዘግይቶ መዠመሩም የሐዋርያት ሰውነት ለጾሙ መዘጋጀት ነበረበትና ነው ፡፡

የዚኽን ማብራርያ በቀጣይ ጽሑፋችን እንመለስበታልን፡፡
ይኽ ጾም በአላዋቂዎችን እና በቤተክርስቲያን ጠላቶች የሽማሌዎች ጾም እየተባለ ምዕመናን እንዳይጾሙት ብዙ ተለፍቷል ልናውቅ የሚገባው ነገር ግን ሐዋርያት ዓለምን ዞረው ከማስተማራቸው በፊት ይህን ጾም ጾመዋል ፡፡ በዚህም ጌታችን የተናረው ተንቢት ተፈጽሟል፡፡ ከሰባቱ አጽዋማትን አንዱ ነው ፡፡ በዚህ ምክንያት ይህን ጾም ታላቅ እና ልዩ ያስብለዋል ፡፡ ይኽንን አውቀን ሁላችንም በሕግ በሥርዓት ልንጾመው ይገባል ፡፡

@ortodoxtewahedo
Audio
የዕርገት መንገድ
        
Size:-54MB
Length:-2:34:56

በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

@ortodoxtewahedo
Audio
ራሳችሁን አታጥፉ ||የሚቃጠል መሥዋዕት
        
Size:-29.9MB
Length:-1:25:53

በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

@ortodoxtewahedo
Audio
ጰራቅሊጦስ ||እግዚአብሔርን መውደድ
        
Size:-28.7MB
Length:-1:22:33

በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

@ortodoxtewahedo
✥ቸርነትህ ነው ያደረሰኝ እስከ ዛሬ✥
✞ ጋሜል - ዘ ኦርቶዶክስ ✞
#ቸርነትህ_ነው

ቸርነትህ ነው ያደረሰኝ እስከ ዛሬ
ቸርነትህ ነው የጠበቀኝ እስከዛሬ
ላመስግንህ የኔ ጌታ በዝማሬ /2/

        #አዝ ………………
መክሊቴን ቀብሬ ባሳዝንህ
መብራቴንም ይዤ ባልጠብቅህ
በታላቅ ይቅርታ እዳትረሳኝ
በፍቅር ጎብኝተህ ከሞት አዉጣኝ
ከቤትህ እርቄ መች ጠገብኩኝ
በርሀብ በርዛት ተቸገርኩኝ
አምናለሁ ከምላኬ እድትምረኝ
በይቅርታ መጣሁ ተቀበለኝ

       #አዝ ………………
አንዳች እዴለለኝ አዉቀዋለሁ
ባንተ ቸርነት ግን እመካለሁ
የከበደው ሸክሜ ይቀለኛል
ይቅርታህ ለባሪያህ ይደርሰኛል
በመቅደስህ ቁሜ ለመዘመር
ስራህን ለትዉልድ ለመመስከር
እኔ ማነኝ ብየ አስባለሁ
አምላክ ቸርነትህን አደንቃለሁ
       
          #አዝ ………………
በሰዉ እጅ መመካት አቁሚያለሁ
እረዳቴ አንተ ነህ አዉቄያለሁ
አንተ ከጠበከኝ በህይወቴ
ቅጥሬ አይደፈርም መድኃኒቴ
የኔን ስራ ተወዉ ተግባሬንም
የመስቀሉንም ነገር መርሳቴንም
አዚሜን አንስተህ አንተን ልይህ
ኢየሱስ ክርስቶስ አምላኬ ነህ

@ortodoxtewahedo
የኤልያስ ሀብት ያደረበት ኤልሳዕም ነበረ በዘመኑም አለቆች አላስደነገጡትም ማንም ማን እሱን የተቋቋመው የለም።ከነገሩም ሁሉ የተሠወረው የለም ከሞተም በኋላ በድኑ ትንቢት ተናገረ።በሕይወቱም ሳለ ድንቅ ተአምራት አደረገ ከሞተም በኋላ ሥራው ድንቅ ነው።#ሲራክ_48÷12~14

የጸሎቱ ኀይል ከፍተኛ ለሆነ ኤልሳዕ ሰላምታ ይገባል፡ ነቢዩ ኤልሳዕ የዮርደኖስን ውኃ ከሁለት ከፍሎ ቆመ። መጥረቢያን በእንጨት ቅርፊት ከውኃው ውስጥ አወጣ። የምትመረውን ውኃ የምትጣፍጥ አደረጋት። ሞቶ ሳለ በድኑ የሞተውን ሰው አስነሣ። ስለዚህ ለርሱ ሰላምታ ይገባል።[አባ ጊወርጊስ ዘጋስጫ  ተአምኖ ቅዱሳን ]

ሰኔ 20 የእስራኤል ነብይ ቅዱስ ኤልሳዕ እረፍቱ ነው በረከቱ ይደርብን መልካም ቀን


@ortodoxtewahedo
#ሰኔ_21

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሰኔ ሃያ አንድ በዚች ዕለት የአዳምና የዘሩ ድኅነት የተደረገባት አምላክን የወለደች #የእመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም የታላቁ በዓል መታሰቢያና በዓለም ሁሉ የቤተ ክርስቲያን መታነፅ መታሰቢያ ነው፣ ከምስር አገር #ቅዱስ_ጢሞቴዎስ በሰማዕትነት ሞተ፣ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት #አባ_ከላድያኖስ አረፈ፣ #ሐዋርያው_ቶማስ በመሸታ ቤት ባረድዋት በአንዲት ሴት ላይ ላደረገው ተአምር መታሰቢያ ነው፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

🌹#እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም (ህንጸተ ቤተክርስቲያን)🌹

ሰኔ ሃያ አንድ በዚች ዕለት የአዳምና የዘሩ ድኅነት የተደረገባት አምላክን የወለደች የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የታላቁ በዓል መታሰቢያና በዓለም ሁሉ የቤተ ክርስቲያን መታነፅ መታሰቢያ ነው። ከሁሉ አስቀድሞ ያቺ ቤተ ክርስቲያን በሐዋርያት ዘመን ብቻዋን ታነፀች።

ይኸውም ጳውሎስና በርናባስ በአሕዛብ ውስጥ በሰበኩ ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ ከሰዎች ቤቶች በቀር ቅዱስ ቊርባንን የሚቀበሉበት ቤተ ክርስቲያንም አልነበራቸውም ነበር። ስለዚህም ወደ ጴጥሮስና ወደ ሐዋርያት ሁሉ ስለ ቤተ ክርስቲያን መታነፅ ጉዳይ እየለመኑ መልእክትን ላኩ።

ሐዋርያትም እንዲህ ብለው መለሱላቸው ክብር ይግባውና ያለ ጌታችን ፈቃድ እኛ ምንም ምን አንሠራም። ነገር ግን የምንሠራውን እስኪያስረዳን ድረስ ወደ እግዚአብሔር እየጸለዩና እየማለዱ አንድ ሱባኤ ይጾሙ ዘንድ ወደ ሃይማኖት የተመለሱ አሕዛብን እዘዙአቸው እንዲህም አዘዙአቸው።

በሱባዔውም ፍጻሜ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገለጸላቸው ሐዋርያትንም ሁሉ ከየአገሮች ሁሉ እስከ ፊልጵስዮስ በደመና ሰበሰባቸው ከእርሳቸውም ጋር ጳውሎስና በርናባስ ነበሩ ጌታችንም ባረካቸው እንዲህም ብሎ ነገራቸው "ይቺ ዕለት በእናቴ በማርያም ስም በአራቱ ማእዘነ ዓለም አብያተ ክርስቲያናት እንድታንፁ የፈቀድኩባት ናት።"

ይህንንም ብሎ ከከተማዋ በስተ ምሥራቅ በኲል አወጣቸው የቤተ ክርስቲያኒቱንም ቦታና መሠረቷን ወሰነላቸው ከእርሳቸውም ጋራ የእግዚአብሔር ኃይል ነበረ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሕንፃዋ እስከ ተፈፀመ ድረስ ደንጊያዎች በሐዋርያት እጆች ውስጥ ይለመልሙ ነበረ ጌታችንም ነዋየ ቅድሳቷን አልባሳትዋንና መሠዊያዋን አዘጋጀ።

ከዚህ በኋላ ጌታችን እጁን በጴጥሮስ ራስ ላይ ጭኖ በአራቱ ማእዘነ ዓለም ውስጥ "አርሳይሮስ" ብሎ ሾመው ይህም "ሊቀ ጳጳሳት" ማለት ነው። ለሐዋርያት አለቃ ጴጥሮስ ከጽንፍ እስከ ጽንፍ የጳጳሳት አለቃ ይሆን ዘንድ ይገባዋል ይገባዋል ይገባዋል እያሉ ሰማያውያን መላእክትና ምድራውያን ሰዎች ሦስት ጊዜ አሰምተው ተናገሩ።

ከዚህም በኋላ ጌታችን ሐዋርያትን የቊርባኑን ቅዳሴ ሥርዓት ያከናውኑ ዘንድ ለሕዝቡም ሥጋውን ደሙን ያቀብሏቸው ዘንድ አዘዛቸው እንዲህም የሚል አለ ራሱ መድኃኒታችን ቀድሶ ሥጋውንና ደሙን ለሐዋርያት አቀበላቸው። እንዲህም አላቸው በዚች ቀን የእጃቸውን ሥራ እንዳይሠሩ ሕዝቡን ሁሉ እዘዙአቸው ይኸውም በሰኔ ወር ሃያ አንድ ቀን ነው።

ከዚህም በኋላ መድኃኒታችን ከእርሳቸው ዘንድ በታላቅ ክብር ወደ ሰማያት ዐረገ። ከዚያችም ቀን ጀመሮ አባቶቻችን ሐዋርያት በዓለሙ ሁሉ ውስጥ አምላክን በወለደች በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም ቤተ ክርስቲያን የሚያሳንፁ ሆኑ።

በቂሣርያው ሊቀ ጳጳሳት በባስልዮስ ዘመን እንዲህ ሆነ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም ቤተ ክርስቲያን በሠራ ጊዜ በውስጡ የእመቤታችን የማርያምን ሥዕል ይሥልበት ዘንድ ሠሌዳ ፈለገ ሰዎችም በአንድ ባለጸጋ ዘንድ ስለ አለ አንድ መልካም ሠሌዳ ነገሩት።

ቅዱስ ባስልዮስም ሠሌዳውን እንዲሰጠው ወደ ባለጸጋው ላከ ባለጸጋውም ይህ ሠሌዳ ለልጆቼ ነው አለ እንጂ ፈቃደኛ አልሆነም። ከዚያም አልፎ በመድፈር በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ላይ የስድብ ቃል ተናገረ ወዲያውኑም በድንገት ወድቆ ሞተ ልጆቹም ፈሩ ያንንም ሠሌዳ ከብዙ ወርቅና እንቊ ጋራ ወደ ቅዱስ ባስልዮስ አምጥተው የአባታቸውን በደል ያቃልልለት ዘንድ ለመኑት።

ቅዱስ ባስልዮስም ያንን ሠሌዳ ወስዶ የእመቤታችንን ሥዕል ይሥልበት ዘንድ ለሠዓሊ ሰጠው። እመቤታችንም ቅድስት ድንግል ማርያም በሌሊት ራእይ ለቅዱስ ባስልዮስ ተገለጸችለት ሥዕሏንም በዚያ ሠሌዳ ላይ እንዳይሥል ከለከለችው። ከዐመፀኛ ሰው እጅ ወስዶታልና። እጅግም ያማረ የእመቤታችን ሥዕሏ የተሣለበት የሁለት ደናግልም ሥዕል ያንዲቱ በቀኝ ያንዲቱ በግራ ሆኖ የተሣለበት ቀይ ሠሌዳ ያለበትን ቦታ ነገረችው።

ቅዱስ ባስልዮስም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ አመለከተችው ወደዚያ ቦታ ሔደ ያንንም ሠሌዳ አገኘው ወደዚያች ቤተ ክርስቲያንም በታላቅ ደስታ አመጣው።

ከዚህም በኋላ ዳግመኛ በአንድ ጣዖት ቤት ሁለት ምሰሶዎች እንዳሉ አስረዳቸው እነርሱንም አምጥቶ በመቅደሱ ፊት ለፊት እንዲአቆማቸው በላያቸውም ሥዕሏን እንዲያኖር አዘዘችው።

ቅዱስ ባስልዮስም እነዚያን ምሰሶዎች ያመጣቸው ዘንድ ሔደ መሠርያኑም ሊከለክሉት ፈለጉ ጌታችንም ኃይላቸውን ደመሰሰ እነዚያንም ምሰሶዎች አምጥቶ በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት አቆማቸው በላያቸውም የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕሏን አስቀመጠ እግዚአብሔርም ከእነዚያ ምሰሶዎች በታች የውኃ ምንጭ አፈለቀ በውስጥዋም የሚታጠብ ሁሉ ከአለበት ደዌ ሁሉ የሚድን ሆነ።

እንዲሁም ከእመቤታችን ማርያም ሥዕል በሽተኞችን ሁሉ የሚፈውስ የዘይት ቅባት ፈሰሰ ይህ ሁሉ የሆነ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን በከበረችበት በሰኔ ወር በሃያ አንድ ቀን ነው።

በዚያችም ቀን እንዲህ ሆነ አንዲት ሴት መጥታ ታጠበች ወዲያውኑም ሁለመናዋ በለምጽ ተሸፈነ ቅዱስ ባስልዮስም ወደርሱ አስቀርቦ በእርሷ ላይ የሆነውን ጠየቃት እርሷም የእኅቷን ባል እንደወደደችና እኅቷን በመርዝ ገድላ እንዳገባችው ነገረችው። ቅዱስ ባስልዮስም ታላላቅ ሦስት ኃጢአቶችን ሠራሽ ግን ወደ እግዚአብሔር ንስሐ ግቢ ምንአልባት በደልሽን ይቅር ይልሽ እንደ ሆነ አላት በዚያን ጊዜም ምድር ተሠንጥቃ እንደ ዳታን ዋጠቻት እርሷ የረከሰች ስትሆን ወደ ቤተ ክርስቲያን መግባትን ደፍራለችና።

እኛ ሁላችን የክርስቲያን ወገኖች አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ለከበረች ድንግል ማርያም ለመታሰቢያዋ መንፈሳዊ በዓልን ልናደርግ ይገባናል ሰለ እርሷ ለአዳምና ለሁላችን ለልጆቹ ድኅነት ሆኖአልና ይህንንም በዓል ለማድረግ የሚተጋ የተመሰገነ ነው።

እርሷን ለመረጣትና ለወደዳት በሥጋም እንድትወልደው ላደረገ #ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በእርሷ በእመቤታችን #ድንግል_ማርያም አማላጅነት ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

@ortodoxtewahedo
💚💚💚💛💛💛❤️❤️❤️

እንካን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አምታዊ በ ዓል አደረሰን:: ስምሽ ጉልበት ሆኖኝ ወጣሁት ዳገቱን ድንግል ማርያም ባንቺ ምልጃ አለፍኩት ዳገቱን::

#መልካም እለተ

@ortodoxtewahedo

💚💚💚💛💛💛❤️❤️❤️..
Audio
ኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊነት
        
Size:-35.6MB
Length:-1:42:08

በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

@ortodoxtewahedo
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
“አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤”
— ኤፌሶን 4፥5

“ወዳጆች ሆይ፥ ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ፥ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ።”
— ይሁዳ 1፥3

@ortodoxtewahedo
💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️

"ወሀቢተ ፀጋ በከንቱ "
ስጦታን እንዲሁ
የምትሰጪ አንቺ ነሽ

ለመቀላቀል 👉 @ortodoxtewahedo

💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

ኦ ማርያም ናፈቅረኪ
ማርያም ሆይ እንወድሻለን

ለመቀላቀል 👉 @ortodoxtewahedo

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
.🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

"ወትቀውም ንግሥት በየማንከ
በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወሑብርት ስምዒ ወለትየ ወርእዪ ወአጽምዒ እዝነኪ" መዝ 44፥9

ለመቀላቀል👉

@ortodxtewahedo

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
2024/11/18 17:19:12
Back to Top
HTML Embed Code: