Telegram Web Link
በእኔ ቢጠቁር ሰማይ
@gubaekidusan
በእኔ ቢጠቁር ሰማይ

በእኔ ቢጠቁርም ሰማይ
በእኔ ቢጠልቅም ፀሐይ
በነፋሳት የማይጠፋ ፋኖሴ
ኢየሱስ ነው የመኖር እስትንፋሴ

እርሱን ታምኜ እወጣለሁ
እርሱን ታምኜ እገባለሁ
ድብቅ ሰራዊት አለው ለእኔ
የሚጠብቀኝ በዘመኔ
እግዚአብሔር ለእኔ ብርሃኔ ነው
የሚያስደነግጠኝ የሚያስፈራኝ ማነው

ሰው አልባ ሁኜ በስደት
ወዳጄ የሆነኝ የእኔ አባት
ክርስቶስ ለእኔ ሕይወቴ ነው
እርሱን ታምኜ እኖራለሁ
የለም የሚያስፈራኝ በዘመኔ
ብርሃን ነውና እግዚአብሔር ለእኔ

መች ይሰጠኛል ለጠላት
አይሰለጥንም በእኔ ሞት
የሚጠብቀኝ ጌታ ነው
የትኛው ጠላት ሊደፍረው
በቤቴ መቃን ላይ ደም ይታያል
እኔን ከእግዚአብሔር ከቶ ማን ይለያል

ይኸው አቆመኝ በመቅደሱ
እየጠበቀ በመንፈሱ
እኔን ሊያከብር ራሱን ሰጥቶ
ግዝቶኛል ጌታ ሞቴን ሙቶ
ይገዛ ለስሙ ስጋ መንፈሴ
በእርሱ ነውና ለዛሬ መድረሴ

በዓለም ሳለሁ የዓለም
ብርሃን ነኝ። ዮሐ 9፥5

   ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ

@ortodoxtewahedo
" ፀሎት የምግባራት ሁሉ እናት ናት ሰይጣን እንደፀሎት የሚጠላው ነገር የለም ፀሎት የህይወት አጥር ነው ሰይጣን እንደፈለገ ገብቶ ፀጋን እንዳወርስ የበረከት ማጣት የሀጥያት መጀመሪያ የፀብ ሁሉ መነሻ የትዳር መቀዝቀዝ ያገኘነወ የማይባረከው ፀሎት ስናቋርጥ ነው ።"

አባ ገብረ ኪዳን

"ትግሁ ወ ፀልዩ ከመ ኢትባሁ ውስተ መንሱት"
                  
         "ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ፀልዩ"
             
                       ማትዮስ  26:41

@ortodoxtewahedo
" ፀሎት የምግባራት ሁሉ እናት ናት ሰይጣን እንደፀሎት የሚጠላው ነገር የለም ፀሎት የህይወት አጥር ነው ሰይጣን እንደፈለገ ገብቶ ፀጋን እንዳወርስ የበረከት ማጣት የሀጥያት መጀመሪያ የፀብ ሁሉ መነሻ የትዳር መቀዝቀዝ ያገኘነወ የማይባረከው ፀሎት ስናቋርጥ ነው ።"

              አባ ገብረ ኪዳን

"ትግሁ ወ ፀልዩ ከመ ኢትባሁ ውስተ መንሱት"
                  
         "ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ፀልዩ"
             
                       ማትዮስ  26:41

@ortodoxtewahedo
Audio
በ3 ነገሮች ማደግ አለብን
        
Size:-7.1MB
Length:-20:25

ምክረ አበው በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

@ortodoxtewahedo
ብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ
እንኳ ለብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ በዓል (ሐምሌ ፭) አደረሰን፤ አደረሳችሁ!!!
በመ/ር ጌታቸው በቀለ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሐምሌ ፭ ቀን “ጴጥሮስ ወጳውሎስ” በማለት ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ እና ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ መልካሙን የክርስትና ገድል ተጋድለው ሰማዕትነት የተቀበሉበትን ቀን በታላቅና በተለየ ሁኔታ ታከብራለች። በዚሁ ዕለት የጾመ ሐዋርያት ፋሲካ የሚከበርበት ዕለትም ነው፡፡
የክርስትና ሃይማኖትን በማስፋፋት ከፍተኛውን ሚና የተጫወቱት እነዚህ ቅዱሳን ሐዋርያት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መልእክታትን ጽፈዋል። ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ሁለት መልእክታትን ሲጽፍ፤ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ ዐሥራ አራት መልእክታትን ጽፏል።
ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ዓሣ ከማጥመድ ሥራ ለዚህ ታላቅ አገልግሎት ሲጠራ (ማቴ ፬፦፲፰)፤ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ ቤተክርስቲያን እና የክርስቶስ ተከታዮችን ከማሳደድ ላይ ሳለ “ሳውል ሳውል፥ ስለ ምን ታሳድደኛለህ? አንተ የምታሳድደኝ እኔ ኢየሱስ ነኝ፤ የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል” (ሐዋ. ፱፡፬-፭) በሚል የተጠራ ነው። በዛሬው ዝግጅታችን የእነዚህን ቅዱሳን ታሪክ በአጭሩ እንደሚከተለው እንመለከታለን፡-
ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ቅዱስ ጴጥሮስ በአባቱ የሮቤል፣ በእናቱ የስምዖን ነገድ ሲኾን፣ የተወለደውም በገሊላ አውራጃ በቤተ ሳይዳ ነው፡፡ ወላጆቹ ያወጡለት ስም “ስምዖን” ነበር፡፡ በቂሳርያ ከተማ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ «ማን ትሉኛላችሁ?» ብሎ በጠየቀ ጊዜ “አንተ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ” ብሎ ለአይሁድ ሊቃውንት የተሰወረውን ምሥጢረ ተዋሕዶ ገልጦ በመመስከሩ ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ጴጥሮስ” ብሎ ጠርቶታል፤ ትርጕሙም በግሪክ ቋንቋ ዐለት(መሠረት) ማለት ሲኾን፤ በአራማይክ ደግሞ “ኬፋ” ይባላል። የቅዱስ ጴጥሮስ ጥሪ ቅዱስ ጴጥሮስ የሚተዳደረው በዓሣ አጥማጅነት የነበረ ሲኾን፣ ሰዎችን በወንጌል መረብ እያጠመደ ወደ ክርስትና ሕይወት ይመልስ ዘንድ ጌታችን ለሐዋርያነት ጠርቶታል (ሉቃ. ፭፥፲፤ ማር.፩፥፲፮)፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ በአራቱም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ላይ በተቀመጡት የሐዋርያት ዝርዝር ቀዳሚውን ሥፍራ ይዞ ይገኛል። በበዓለ ሃምሳም ለደቀመዛሙርቱ መንፈስ ቅዱስ በወረደላቸው ጊዜ ለተሰበሰቡት አይሁድ አፈ ጉባኤ ሆኖ ወንጌልን የሰበከ ሦስት ሺሕ ምእመናንን አሳምኖ የመጀመሪያዋን ቤተ ክርስቲያን በኢየሩሳሌም የመሠረተ ነው (የሐዋ. ፩፥፲፮-፳፫፣ ፪፥፲፬-፴)፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ከሐዋርያት ሁሉ ቀደም ቀደም የማለት ባሕርይ ነበረው። ጌታ በጥብርያዶስ ባሕር ላይ ሌሊት በእግሩ ሲመጣ ቢመለከት “ወደ አንተ እመጣ ዘንድ እዘዘኝ” በማለት ካስፈቀደ በኋላ ወደ ጌታ ለመምጣት መንገድ ጀምሮ በመሐል ጥርጣሬ ገባውና መስጠም ስለ ጀመረ ጌታችን “ያመንክ እንጂ ያላመንክ አትሁን” ብሎ ገስፆ ከመስጠም አድኖታል (ማቴ ፲፬፥፳፪-፴፫)፡፡
በቅፍርናሆም ጌታችን ምሥጢረ ቁርባንን ሲያስተምር፣ አይሁድ ስላልገባቸው ወደ ኋላ አፈገፈጉ። ከደቀ መዛሙርቱም “ብዙዎቹ ወደ ኋላ ተመለሱ” በዚህን ጊዜ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “እናንተ ደግሞ ልትሄዱ ትወዳላችሁ?” ብሎ ሐዋርያትን ጠየቃቸው። በዚህ ሰዓት “ጌታ ሆይ ወደ ማን እንሄዳለን? አንተ የዘላለም የሕይወት ቃል አለህ። እኛስ አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ እንደሆንክ እናምናለን” በማለት ሐዋርያትን ወክሎ የመለሰ እርሱ ነው (ዮሐ ፮፥፷፮-፷፰)፡፡
ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታን ይወድ ነበር። ጌታችን ለደቀ መዛሙርቱ የሞቱን ነገር ቀድሞ ሲነግራቸው አይሁንብህ በማለት ተከራክሯል (ማቴ ፲፮፥፳፫)፡፡ በኋላም “ሁሉም በአንተ ቢሰናከሉ እኔ ከቶ አልሰናከልም” ብሎ በራሱ ቅንዓት ተማምኖ ተናግሮ ነበር። ጌታችን “ዶሮ ሳይጮህ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ” እያለው እንኳን “ከአንተ ጋር መሞት እንኳን የሚያስፈልገኝ ቢሆን ከቶ አልክድህም” በማለት የተናገረ ሰው ነው (ማቴ ፳፮ ፥ ፴፬)፡፡ አሁን ቅዱስ ጴጥሮስ በራስ መተማመኑ እንዳላዋጣው ዐውቆአልና “ትወደኛለህን?” ተብሎ ሲጠየቅ “አንተ ታውቃለህ” ነበረ መልሱ። “ግልገሎቼን አሠማራ፣ ጠቦቶቼን ጠብቅ፣ በጐቼን አሠማራ» በማለት አደራ የተቀበለ ነው (ዮሐ ፳፩፥፲፭-፲፯)፡፡
ቅዱስ ጴጥሮስ የሐዋርያት አለቃ ኾኖ ተሹሟል፡፡ ለአገልግሎት ከተጠራበት ጊዜ ጀምሮም በእስያ፣ በሮም፣ በሰማርያ፣ በልዳ፣ በኢዮጴ፣ በአንጾኪያ፣ በገላትያና በሌሎችም አገሮች እየተዘዋወረ ወንጌልን ሰብኳል፡፡ በስብከቱ ምክንያትም ልዩ ልዩ መከራን ተቀብሏል፡፡ በክርስቶስ ኀይል አጋዥነት ብዙ ድንቆችንና ተአምራትን አድርጓል፡፡ ከተሰጠው ጸጋ ብዛት የተነሣ በጥላው ሕሙማን ይፈወሱ ነበር (ሐዋ. ፭፥፲፭)፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በሮሜ አንድ ዓመት ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር ካስተማረ በኋላ የሮሜ ክርስቲያኖች እየበዙ ከመምጣታቸውም በላይ የክርስትናው ጉዞ እስከ ሮማ ባለሥልጣናት ደረሰ። በዚህን ጊዜ ኔሮን በቅንዓት ተነሣባቸው።
የቅዱስ ጴጥሮስ ሰማዕትነት
የቅዱስ ጴጥሮስ ምድራዊ የአገልግሎት ዘመኑ ሊፈጸም ሲቃረብም ኔሮን በ፷፬ ዓ.ም. እርሱ ከከተማው ወጣ ብሎ በሚገኘው ቤተ መንግሥቱ ተቀምጦ የሮማን ከተማ እሳት ለቀቀባት። የሮም ሕዝብ በደረሰው አደጋ እጅጉን ተቆጣ። ኔሮንም በክርስቲያኖች አመካኘ። የከተማው መጋየት ያበሳጨው የሮማ ሕዝብ፣ ክርስቲያን የሆነውን ሁሉ እያወጣ መግደሉን ተያያዘው። በቅዱስ ጴጥሮስና በሌሎችም ክርስቲያኖች ላይ የሞት ፍርድ ዐወጀ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም በሮም ሲያስተምር ቆይቶ የሮም መኳንንት እንዳይገድሉት ከሮም ሲወጣ ጌታችን መስቀል ተሸክሞ ተገለጸለት፡፡ በዚህ ጊዜ “አቤቱ ጌታ ሆይ ወዴት ትሔዳለህ?” ሲል ቢጠይቀው ጌታችንም “ልሰቀል ወደሮም እሔዳለሁ” አለው፡፡ “ዳግመኛ ትሰቀላለህን?” ባለው ጊዜም “አንተ ስትፈራ ጊዜ ነው እንጂ” ሲል መለሰለት፡፡ ያንጊዜም “ጐልማሳ ሳለህ ወገብህን ታጥቀህ ወደ ወደድኸው ትሔድነበር፡፡ ስትሸመግል ግን እጅህን ታነሣና ሌላ ሰው ያስታጥቅሃል፤ ወደ ማትወደውም ይወስድሃል” (ዮሐ. ፳፩፥፲፰) በማለት ጌታችን የነገረው ቃል አሟሟቱን የሚያመለክት መኾኑን አስታውሶ ወደ ሮም ተመልሶ ስብከቱን ቀጠለ፡፡

በሮማውያን ሕግ ቅጣት የተፈረደበት ወንጀለኛ የሮም አገር ተወላጅ ከኾነ የወንጀሉ ክብደትና ቅለት እየታየ ግርፋት ወይም ሞት ይፈረድበታል እንጂ በአንድ ወንጀል ሁለት ቅጣት አይቀጣም ነበር፡፡ ወንጀለኛው የውጪ አገር ዜጋ (ከሮም ውጪ) ከኾነ ግን ለምሳሌ ቅጣቱ ግርፋት ከኾነ ከተገረፈ በኋላ እስራት ይጨመርበታል፤ ቅጣቱ ሞት ከኾነም ከገረፉት በኋላ በመስቀል ወይም በሌላ መሣርያ ይገድሉት ነበር፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ዜግነቱ ሮማዊ አልነበረምና በግርፋትም፣ በእስራትም በሞትም እንዲቀጣ ተፈረደበት፡፡ ያን ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስን ይዘው አሠሩት። ከጥቂት ቀናት በኋላም ሮማውያን የመስቀያውን እንጨት አቀረቡለት። እንደ ሥርዐታቸውም ቅዱስ ጴጥሮስን ከገረፉት በኋላ ሊሰቅሉት ሲሉ ወታደሮቹን “እንደ ክብር ንጉሥ እንደ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስአቁማችሁ ሳይኾን፣ ዘቅዝቃችሁ ስቀሉኝ” አላቸው፡፡ እነርሱም እንዳላቸው አድርገው ዘቅዝቀው ሰቅለውታል፡፡ ሐምሌ ፭ ቀን በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ከዕብራዊያን፣ ከብንያም ነገድ ሲሆን የተወለደውም በጠርሴስ ከተማ ነው። ጠርሴስ በንግድዋ የታወቀች የኪልቂያ ዋና ከተማ ናት። ሮማውያን በሥራቸው ለሚተዳደሩት ሕዝቦች ሮማዊ ዜግነትን ይሰጡ ስለነበር፥ የቅዱስ ጳውሎስ አባት በዜግነት ሮማዊ ነበር። ይህም ለቅዱስ ጳውሎስ ተላልፎለታል።
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለአገልግሎት ከመጠራቱ በፊት “ሳውል” ይባል ነበር፡፡ ከኦሪቱ ምሁር ከገማልያል ሕገ ኦሪትንና መጻሕፍተ ነቢያትን ተምሯል፡፡ ለሕገ ኦሪት ቀናኢ ከመኾኑ የተነሣም የክርስቶስ ተከታዮችን ዅሉ ያሳድድ ነበር፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በአይሁድ ሸንጎ አባልነት ለኹለት ዓመታት በሠራበት ወቅት ለኦሪታዊ እምነቱ ቀናተኛ ፈሪሳዊ በመሆኑ ክርስቲያኖችን በማናቸውም አጋጣሚ ይቃወም ነበር። እንዲያውም ሊቀ ዲያቆናት እስጢፋኖስን በማስተማሩ ምክንያት ተከሶ ለአይሁድ ሸንጎ ቀርቦ በድንጋይ ተወግሮ በሰማዕትነት ሲያርፍም ቅዱስ ጳውሎስ የገዳዮቹ ልብስ ጠባቂ ነበር (ሐዋ. ፯፥፶፰፤ ፳፪፥፳)፡፡ ክርስቲያኖችን ለማሳደድ ወደ ደማስቆ ሲሔድ ከመንገድ ላይ ለሐዋርያነት ተጠርቷል (ሐዋ. ፱፥፩-፴፩፤ ፳፪፥፩-፳፩)፡፡

ሐዋርያው ጳውሎስ ወደ ከተማዋ ለመድረስ ጥቂት ሲቀረው ነበር ከሰማይ የወረደው ብርሃን አካባቢውን ያለበሰውና “ውል ሳውል ለምን ታሳድደኛለህ?” የሚለውን ድምፅ የሰማው። ሐዋርያው ጳውሎስም “ጌታ ሆይ ማን ነህ?” ብሎ ጠየቀ። “አንተ የምታሳድደኝ እኔ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ። የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል” ሲል መድኃኒታችን ተናገረው። ያን ጊዜም በወደቀበት ሆኖ እየተንቀጠቀጠ “ጌታ ሆይ ምን አደርግ ዘንድ ትወዳለህ?” ሲል ጠየቀ። ከዚህ በኋላ ተነሥቶ ወደ ደማስቆ እንዲገባ ተነገረው (የሐዋ. ፱፥፩)።
የሐዋርያው ዐይኖች ለማየት ሽላልቻሉ እየተመራ ወደ ደማስቆ ገባ። ለሦስት ቀናት ያህልም እህል ሳይቀምስ ቆየ። በዚያች ዕለት እግዚአብሔር አምላክ በደማስቆ ለሚገኘው ሐናንያ ለተባለው አባት በራእይ ተገለጠለት። ቅዱስ ጳውሎስም ያለበትን አድራሻ ነገረውና ሄዶ እንዲያጠምቀው አዘዘው። ሐናንያ አስቀድሞ የቅዱስ ጳውሎስን ማንነት ያውቃል። አብዛኞቹ በደማስቆ የሚገኙት ክርስቲያኖች ከኢየሩሳሌም በስደት የመጡ ናቸው። ያን ስደት ያስነሣው ደግሞ በቅዱስ እስጢፋኖስ ላይ የደረሰው መከራ ነው። በዚህ የቅዱስ እስጢፋኖስ ሰማዕትነት ደግሞ ዋናው ተዋናይ ሐዋርያው ጳውሎስ ነበር። ይህን የሚያውቀው ሐናንያ በቅድሚያ ከእግዚአብሔር ጋር መከራከር ጀምሮ ነበር። በመጨረሻ ግን “ይህ በአሕዛብም በነገሥታትም በእሥራኤልም ልጆች ፊት ስሜን ይሸከም ዘንድ ለእኔ የተመረጠ ዕቃ ነውና ሂድ፤ ስለ ስሜ ስንት መከራ ሊቀበል እንዲያስፈልገው እኔ አመለክተዋለሁና” በማለት እግዚአብሔር ሐናንያን ላከው። ሐናንያ ቅዱስ ጳውሎስን ካጠመቀውና ካስተማረው በኋላ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ዐረብ ሀገር መሄዱን ራሱ ተናግሮአል(ገላ ፩፥፲፯)፡፡ ለሦስት ዓመታት በዐረብ በረሓ ከቆየ በኋላ ወደ ደማስቆ ከተማ ተመለሰ። በዚያም በነበሩ አይሁድ መካከል በፊት ያሳድደው የነበረውን ኢየሱስ ክርስቶስን መስበክ ጀመረ። ከዚያ በፊት በፈሪሳዊነቱና ለአይሁድ ሕግ በነበረው ቅንዓት የሚታወቀው ጳውሎስ ዛሬ ወንጌል ሲሰበክ በማየታቸው አይሁድ ተነሡበት።
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በጠርሴስ ከተማ ለዘጠኝ ዓመታት ቆይቷል። ከኢየሩሳሌም ውጭ የአሕዛብ ከተማ በነበረችው በአንጾኪያ የክርስትና ሃይማኖት ተስፋፋ። ከኢየሩሳሌም የተሰደዱት ክርስቲያኖች የአንጾኪያን ሕዝብ ተግተው በማስተማራቸው ዝናው እስከ ኢየሩሳሌም ደረሰ። በዚህም ምክንያት በኢየሩሳሌም የነበሩት አበው በርናባስን ወደ አንጾኪያ ላኩት። በርናባስ የግሪክ ቋንቋ ችሎታ ያለውን፣ ከማንኛውም ሰው ጋር መግባብ የሚችለውን፣ ደግሞም እግዚአብሔር ለአሕዛብ ሐዋርያ እንዲሆን የመረጠውን ቅዱስ ጳውሎስን ከጠርሴስ በማምጣት በአንጾኪያ ሥራቸውን ጀመሩ።
የቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያዊ ጉዞ
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ የመጀመሪያው ጉዞ ያደረገው ከኢየሩሳሌም ወደ አንጾኪያ ከተመለሰ በኋላ በልዑል እግዚአብሔር ጥሪ በአሕዛብ ሀገር ወንጌልን ለመስበክ ከበርናባስ ጋር ወጡ። ይህም ጉዞ የተከናወነው በ፵፮ ዓ.ም.አካባቢ ነው። የተሸፈኑትም ሀገሮች ሲሊንውቂያ፣ ቆጵሮስ፣ ስልማን፣ ጳፋ፣ ጰርጌን፣ ገላትያ፣ ጵስድያ፣ ኢቆንዮን፣ ሊቃኦንያ፣ ልስጥራ፣ ደርቤን፣ ጵንፍልያ፣ አታልያና አንጾኪያ ናቸው።
ሁለተኛው ጉዞ በ፶ ዓ.ም. ገደማ የተከናወነው ነው። በመጀመሪያው ጉዞ ማርቆስ አብሮ ተጉዞ ነበር። ነገር ግን ጵንፍልያ ከተማ ሲደርስ እናቱ ስለናፈቀችው መመለስ በመፈለጉ በርናባስ ወደ ኢየሩሳሌም ይዞት መጣ። ስለዚህም በሁለተኛው ጉዞ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ሲላስን ይዞ ወደ ኪልቂያ ሶርያ ሲጓዝ በርናባስ ደግሞ ማርቆስን አስከትሎ ወደ ቆጵሮስ ሄደ። በዚህ ጉዞው ቅዱስ ጳውሎስ እስከ ግሪክ ደርሶአል። የተጓዘባቸውና ያስተማረባቸው ከተሞችም፦ ደርብያ፣ ልስጥራ፣ፍርግያ፣ ገላትያ፣ ሚስያ፣ጢሮአዳ፣ ሳሞትራቄ፣ ናፑሊ፣ ፊልጵስዩስ፣ ተሰሎንቄ፣ በርያ፣አቴና፣ ቆሮንቶስ፣ አንክራኦስ፣ አፌሶን፣ ቂሳርያ፣ ኢየሩሳሌምና አንጾኪያ ናቸው። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ የመንፈስ ልጁ ጢሞቴዎስን ያገኘው በዚሁ ጉዞው በልስጥራ ከተማ ነው።

ሦስተኛው ጉዞ የተከናወነው በ፶፬ ዓ.ም. ሲሆን የተሸፈኑትም ሀገሮች ገላትያ፣ ፍርግያ፣ ኤፌሶን፣ መቄዶንያ፣ ፊልጵስዩስ፣ ቆሮንቶስ፣ ጢሮአዳ፣ አሶን፣ ሚልጢኒን፣ አንጠቀከስዩ፣ ትሮጊሊዩም፣ መስጡ፣ ቆስ፣ ሩድ፣ ጳጥራ፣ ጢሮስ፣ ጵቶልማይስ፣ ቂሳርያ፣ ኢየሩሳሌም ናቸው። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ከልዩ ልዩ ሀገሮች ክርስቲያኖች የሰበሰበውን ዕርዳታ ለኢየሩሳሌም ቤተ ክርስቲያን በመያዝ ሦስተኛውን ጉዞ አጠናቅቆ ኢየሩሳሌም ገባ። ነገር ግን ኢየሩሳሌም የገባበት ጊዜ የፋሲካ በዓል ስለነበር ከልዩ ልዩ ሀገሮች የተሰበሰቡ አይሁድ በከተማዋ ነበሩ። እነዚህ በዝርወት የሚኖሩ አይሁድ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስን በየሀገራቸው በትምህርቱ የተነሣ ሲቃወሙት የነበሩ ናቸው።
የቅዱስ ጳውሎስ ሰማዕትነት

ለሐዋርያነት ከተጠራበት ጊዜ ጀምሮም በመላው ዓለም እየተዘዋወረ ወንጌልን በመስበክ ብዙዎችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሳምኗል፡፡ ለእግዚአብሔር መንግሥት አዘጋጅቷል (፩ኛ ቆሮ. ፱፥፲፱-፳፫)፡፡ ወንጌልን በመስበኩ ምክንያትም ከአይሁድና ከአረማውያን ዘንድ ብዙ መከራና ስቃይ ደርሶበታል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ከእግዚአብሔር በተሰጠው ጸጋ ብዙ ድንቆችንና ተአምራትን አድርጓል፡፡ በልብሱ ቅዳጅም ሕሙማን ይፈወሱ ነበር (ሐዋ. ፲፱፥፲፩)፡፡

አገልግሎቱን ሊፈጽም ሲልም የሮም ንጉሥ ኔሮን ቄሣር የክርስቲያኖች ቍጥር እየጨመረ የመጣው በቅዱስ ጳውሎስ ትምህርት በመማረካቸው ምክንያት መኾኑን ተረድቶ፤ ይልቁንም የቤተ መንግሥቱ ሰዎች ሳይቀር በቅዱስ ጳውሎስ በመማረካቸው ተቈጥቶ ቅዱስ ጳውሎስን ወደ ፍርድ ሸንጎው አስቀረበው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም ንጉሡንና ወታደሮችን ሳይፈራ የኢየሱስ ክርስቶስን የእግዚአብሔር ልጅነትና አምላካዊ ሥልጣን ይመሰክር ነበር፡፡
ንጉሡም በቍጣ ይሙት በቃ ፈረደበት፡፡ ወደሚገደልበት ስፍራ ሲወስዱትም በንግግሩና በአስተያየቱ ዅሉ ምንም ፍርኀት አይታይበትም ነበር፡፡ እንዳውም በጦርነት ድል አድርጎና ማርኮ እንደ ተመለሰ ወታደር ይደሰት ነበር እንጂ፡፡ ለሚገድሉትም ይቅርታን ይለምን ነበር፡፡

በመጨረሻ በ፷፬ ዓ.ም. ኔሮን በጥጋቡ የሮማ ከተማ ስትቃጠል ምን እንደምትመስል ማየት እፈልጋለሁ ብሎ አቃጠላት። የሮም ሕዝብ በከተማው መቃጠል በማዘኑና በማመፁ ነገሩን ሁሉ በክርስቲያኖች ላይ አሳበበ። በዚህም የተነሣ ክርስቲያን የተባለ ሁሉ መሰደድ፣ መሠየፍ፣ መታረድ እጣ ፈንታው ሆነ። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም በኒቆጵልዮን ከተማ ሲያስተምር በ፷፭ ዓ.ም. ተይዞ ወደ ወኅኒ ገባ። ለሁለት ዓመት ከስድስት ወር በጨለማ ቤት ታሥሮ ከቆየ በኋላ በ፸፬ ዓመት ዕድሜው በሮም ከተማ አንገቱን ተሰይፎ በ፷፯ ዓ.ም. ሐምሌ ፭ ቀን በሰማዕትነት ዐረፈ።

እንደ ማጠቃለያ
ቅዱሳን ጴጥሮስ እና ጳውሎስ ኹለቱ ሐዋርያት ከአጠራራቸው ጀምሮ የተለያየ ሁኔታ ቢታይባቸውም፤ ለእግዚአብሔር አገልግሎት ግን በተሰጣቸው የሥራ ድርሻ በታማኝነት ያገለገሉ ናቸው፡፡ በስብከተ ወንጌል አገልግሎታቸው ጨለማውን ዓለም በማድመቃቸው ‹ብርሃናተ ዓለም› ተብለው ይጠራሉ፡፡ የቅዱሳኑ አገልግሎት፣ ገድላቸው እና ተአምራቸው በመጽሐፈ ስንክሳር፣ በዜና ሐዋርያት እና በገድለ ሐዋርያት በሰፊው ተጽፎ ይገኛል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ኹለት፤ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ ዐሥራ አራት መልእክታትን ጽፈዋል። ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በ፷፯ ዓ.ም በኔሮን ቄሣር እጅ ቁልቁል ተሰቅሎ ሰማዕትነትን ተቀብሏል። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በ፷፯ ዓ.ም. በኔሮን ቄሣር እጅ አንገቱን ተቆርጦ ሰማዕትነትን ተቀብሏል፡፡

የቅዱሳኑ ሐዋርያት ረድኤትና በረከታቸው ከሁላችን ጋር ይሁን፤ አሜን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡

ምንጭ፡-

✍️ መጽሐፍ ቅዱስ
✍️ ገድለ ሐዋርያት
✍️ መጽሐፈ ስንክሳር ዘወርኃ ሐምሌ ፭
✍️ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ (1995)፡፡ ዜና ሐዋርያት
✍️ ቤተ ክርስቲያንህን ዕወቅ
✍️ Pope Shenouda. Saint Peter and Paul

@ortodoxtewahedo
እንኳን ለቅዱሳን ሐዋርያት ጴጥሮስ ወጳውሎስ ዓመታዊ የሰማዕትነት በዓል እንዲሁም ለሌሎች ቅዱሳን መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችኁ፤ አደረሰን።

"ሰላም ለከ ጴጥሮስ ተልሚድ፤ ዘኢያቅበጽከ ተስፋ ነገረ ኑፋቄ ወካህድ፤ እንዘ ትረውጽ ጥቡዐ ለመልእክተ ክርስቶስ ወልድ፤ አመ ለሊከ ወሬዛ ቀነትከ በእድ፤ ወአመ ልህቀ አቅነተከ ባዕድ።"

"ሰላም ለጳውሎስ ሃይማኖተ ክርስቶስ ዘአግሀደ፤ እስከ አቊሰልዎ በሰይፍ ወመተርዎ ክሣደ፤ ከመ ያግብእ ሕዝበ ህየንተ ቀዳሚ ሰደደ፤ በላዕለ አብዳን ተመሰለ አብደ፤ ወለአይሁድኒ ኮኖሙ አይሁደ።"

❖ ሐምሌ ፭ ❖

✞ ቅዱሳን ሐዋርያት ጴጥሮስ ወጳውሎስ [የምስክርነታቸው መታሰቢያ]፤ ቅዱሳት አንስት:- ዴውርስ፣ ቃርያ፣ አቅባማ፣ አቅረባንያ፣ አክስትያና (የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታዮች) [መታሰቢያቸው]፤ ቅዱስ መርቄሎስ ሐዋርያ (የቅዱስ ጴጥሮስ ደቀ መዝሙር) [መታሰቢያው] የሚከብርባት ዕለት ናት✞

@ortodoxtewahedo
"ቋሚ ቅዱስ ሲኖዶስ ለሰባት ተከታታይ ቀናት ጾምና ምሕላ አወጀ።

ሐምሌ 5 ቀን 2016 ዓ.ም

ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ ለሰባት ተከታታይ ቀናት በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የምሕላ ጸሎት እንዲደርስ ታውጇል።

የቋሚ ቅዱስ ሲኖዶሱ ሙሉ መልእክት እንደሚከተለው ቀርቧል።

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ በሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ገዳማት የሚፈጸመውን የምሕላ ጸሎት አስመልክቶ ከቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

‹‹ተማሕለሉ ወሰአሉ ኃበ አቡክሙ ሰማያዊ እስመ አብ ይሁበክሙ ኵሎ ዘሰአልክሙ…አባታችሁ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋልና ወደ ሰማይ አባታችሁ ለምኑ፣ ምሕላንም አውጁ›› ኢዩኤል 1፤14 ቅዱስ ያሬድ
በሀገር አስተማማኝ ሰላም ሲጠፋ በጾም በጸሎት በመወሰን፣ምሕላን በማወጅ ልባዊ በሆነ ተማሕጽኖ ሁሉን ማድረግ ወደሚችለው አምላካችን አግዚአብሔር ምልጃን ማቅረብ የሚያስፈልግ መሆኑን ከሀገራችን ሊቃውንት መካከል የመጀመሪያ የሆነው ቅዱስ ያሬድ ከሰማያውያን ዐውደ ማህሌት ሰምቶ በቀሰመው ጣዕመ ዜማ አበክሮ ይነግረናል፡፡

በመሆኑም ውሎ ማደር፣ ወጥቶ መግባት በአንዳንድ የሀገራችን አካባቢዎች ስጋት ከሆነ ሰነባብቷልና በእውነት የሚለምኑትን ሁሉ የሚሰማ እግዚአብሔር መተላለፋችንን ይቅር እንዲለን፣ ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም፣ ለቤተ ክርስቲያናችን ፍቅር አንድነት፣ ለሕዝባችን ደኅንነት እንዲሰጥልን ከአንድነት ገዳማት ኅብረት በቀረበው ጥያቄ መነሻነት ምሕላ ማወጅ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ በሁሉም የሀገራችን ክፍልና በሌሎችም አህጉራተ ዓለም የምትገኙ መነኰሳትና መነኰሳይያት ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ ለሰባት ተከታታይ ቀናት በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሃይማኖታዊና ቀኖናዊ ትውፊት መሠረት የገዳማት ኅብረቱን ጥሪ ተቀብላችሁ የምሕላ ጸሎት እንድታደርሱ፣ በጤና ችግር ምክንያት ካልሆነ በስተቀር እስከ ዕርበተ ፀሐይ በመጾም ሱባኤ እንድትይዙ፣ ቋሚ ሲኖዶስ በኅብረተ መንፈስ ቅዱስ ከአደራ ጋር ያሳስባል፡፡

ሁሉም የቤተክርስቲያናችን አገልጋዮችና ምእመናን ሀገራዊ ሰላምን፣ መረጋጋትንና ፍቅር አንድነትን ለማስፈን ጾምና ጸሎት በታወጀበት የምሕላ ሳምንት ለገዳማውያኑ ፀጥታ ሲባል ወደ ገዳማት የምታደርጉትን ጉዞ ለጊዜው እንዲቆይ አድርጋችሁ መደበኛ ሥራችሁን በያላችሁበት ቦታ እየሠራችሁ እግዚአብሔር የገዳማውያኑን ጸሎት ሰምቶ ለሀገራችንና ለሕዝባችን ምሕረትን እንዲሰጥ በኅሊና ዝግጅት፣ በሐሳብ አንድነት ሆናችሁ በጾም በጸሎት እንድተጉ ቋሚ ሲኖዶስ መንፈሳዊ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
‹‹እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ››
ሐምሌ 5 ቀን 2016 ዓ.ም.
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

@ortodoxtewahedo
"መረጋጋትንና ፍቅር አንድነትን ለማስፈን ጾምና ጸሎት በታወጀበት የምሕላ ሳምንት ለገዳማውያኑ ፀጥታ ሲባል ወደ ገዳማት የምታደርጉትን ጉዞ ለጊዜው እንዲቆይ አድርጋችሁ መደበኛ ሥራችሁን በያላችሁበት ቦታ እየሠራችሁ እግዚአብሔር የገዳማውያኑን ጸሎት ሰምቶ ለሀገራችንና ለሕዝባችን ምሕረትን እንዲሰጥ በኅሊና ዝግጅት፣ በሐሳብ አንድነት ሆናችሁ በጾም በጸሎት እንድተጉ ቋሚ ሲኖዶስ መንፈሳዊ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡"
ቅዱስ ሲኖዶስ

@ortodoxtewahedo
✤✤✤ #ሐምሌ_ቅድስት_ሥላሴ
ቅድስት ቀደሰ ከሚለው የግእዝ ግሥ የወጣና ትርጕሙም ልዩ ማለት ሲኾን የሥላሴ አንድነትና ሦስትነት ልዩ (የሥላሴን አንድነትና ሦስትነትን የሚመስል ስለሌለ፤ ቢመስልም ምሳሌ ዘየኀጽጽ) ስለኾነ ሥላሴን ቅድስት በሚል ቅጽል እንጠራለን፡፡

#ሐምሌ_7_ቀን_ቅድስት_ሥላሴ_ለአብርሃም_የተገለጹበት_ነው፡፡ ይኸውም ስለ ፫ት ምክንያቶች ነው፤
#፩ኛ) ለመልካም ነገር /በአብርሃም አንግዳ መቀበል ፀር የኾነ ሰይጣንን ለማሳፈር/ (ሰይጣን በምቀኝነት አብርሃም እንግዳ እንዳይቀበል የውሸቱን ወደ አብርሃም ቤት በሚወስድ መንገድ ላይ ግንባሩን ገምሶ፥ ደሙን አፍስሶ ሰዎች አብርሃም እንዲህ መጥፎ ነውን እንዲሉና እንግዶች ወደ ቤቱ ሂደው እንዳይስተናገዱ አድርጓል፤ አብርሃምም ለ3 ቀናት እንግዳ እየጠበቀ ጾሙን ውሎ ነበር፡፡ ይህን የሰይጣን ክፋት የአብርሃምን እምነትና እንግዳ መቀበል የተመለከቱ ፥ ምግብን የማይመገቡ ሥላሴ በአብርሃም ቤት ገብተው እሳት ቅቤን እንደሚበላ ተስተናግደዋልና ነው፡፡ መስተናገዳቸውንም መምህረ ጋሥጫ የኾነው ሊቁ አባ ጊዮርጊስ በመልክአ ሕማማት ድርሰቱ እንዲህ በግጥም አስቀምጦታል፤
ለንግሥክሙ ሰገደ አብርሃም በርእሱ፡፡
ቤተ ገብርክሙ እንዘ ይብል ገሐሡ፤
አጋዕዝትየ ዘትሤለሱ ግናይ ለክሙ፡፡
እዚህ ላይ ልናስተውለው የሚገባው አምላካችንም ኾነ ቅዱሳን መላእክት ለአብርሃምና ለሌሎችም ቅዱሳን በተለያየ አምሳል መገለጻቸውን ልብ ይሏል፡፡ ለአብነትም፤
፠ ለአብርሃም በአምሳለ አረጋዊ፤
፠ ለሕዝቅኤል በዘባነ ኪሩብ፤
፠ ለዳንኤል በአረጋዊ፣
፠ ለዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ በተለያየ አምሳል፤
፠ ለደብረ መጕናው (ሞጊና) ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን አቡነ አብሳዲ ደግሞ ራሱ መድኀኔዓለም ተገልጾላቸውና ተቀብለውት እንደ አብርሃም እግሩን ያጠቡት መኾኑን ልብ ይሏል፡፡

#፪ኛ) ዘርህን እንደ ምድር አሸዋ፥ እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛልሃለሁ ያሉት ሥላሴ ቃሉ የማይታበይ መኾኑን ለማሳየት (ሰማይና ምድር ያልፋል ፥ ቃሌ ግን አያልፍም ብሎ በኋለኛው ዘመን ጌታችንም እንዳረጋገጠው)፤ ለአብርሃምና ለሣራ ልጅ ሊሰጧቸው፡፡ አባታችን አብርሃም 99 ዓመት ፥ እናታችን ሣራ 89 ዓመት መልቷቸውና የመውለጃ ጊዜያቸው ባለፈበት ሰዐት እንደሚወልዱ ለማብሰር፡፡

#፫ኛ) ምግብ ተመግበን ካበቃን በኋላ አምላካችንን ማመሰገን እንደሚገባን ለማስተማር፡፡ (የታረደው ወይፈንም በተዓምራት ተነሥቶ ስብሐት ብሎ አመሰግኗል፤ ይህንንም መምህረ ጋሥጫ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ በመልክአ ሕማማት ድርሰቱ በግጥም እንዲህ አስቀምጦታል፤
ድኅረ በላዕክሙ ላሕመ እንበይነ ፍቅረ ሰብእ ፍጹም ፤
ዘበኀይልሙ ሐይወ ላሕም፤
ሥላሴ ክቡራነ ስም፡፡ ግናይ ለክሙ፡፡

@ortodoxtewahedo
2024/11/18 17:32:52
Back to Top
HTML Embed Code: