Telegram Web Link
መድኃኔዓለም....የዓለምን ኃጥያት ያስወገደ የእግዚአብሔር በግ
***

በጌቶች ላይ ጌትነቱን የሚዘረጋ፣በፍጹም አምላክነት የተመሰከረለት፣ለንግስናው መጨረሻ እና መጀመሪያ የሌለው ዘለዓለማዊ ዘውድን የጫነ፣ ክብር እራሱ ዝቅ ብላ የምታከብረው አንድ ሰም አለ......መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ

ነብያት በትንቢት ገልጸው ሊመለከቱት የናፈቁት፣ ሐዋርያት ስሙን ተሸክመው ዞረው የከበሩበት፣ ህይወትን ከአማናዊ መንገድ ጋር ፣እውነትን ከጥልቅ ፍቅር ጋር የያዘ አንድ ገዢ ስም አለ ....መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ

ከድንግል ተገኝቶ በሰው ልምድ ያደገ፣ በቅድስና ዙፋን ላይ ከብሮ ኃጢያትን የገደለ፣ ሞትን ወግቶ ሲዖልን የበረበረ የአንድ ልዑል የከበረ ስም አለ.....መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ

ልዑልና ከቅዱስና፣ንጽህና ከፍጹምነት ጋር ፣አዳኝነትን ከባህሪ አምላክነት፣ጌታነትነትን ከመድኃኒትነት ፣ፍጹም ዕረፍትን ከማያልቅ ሠላም ጋር ፣ገዢነትን ከዘለዓለማዊነት ጋር የያዘ የሚናፈቅ ስም አለ.....መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ

የእግዚአብሔር በግ፣የቀራንዮ ሙሽራ፣የድንግሊቷ ልጅ፣የሠላሙ አለቃ፣በብረት ብትር አሕዛብን ይገዛ ዘንድ የተወለደ የአንድ አዳኝ ስም አለ......መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ

ልዑል ሆይ....ስምህ ይቀድሰን። ቸርነትን ይከልለን፣አባትነት ይጠብቀን፣ቸርነትህ ጥላ ይሁነንን። ምህረትህ አይሰልቸን።

ቅዱስ የሆነ የአባትህነት መዳፍ ያሳርፈን

እንኳን አደረሰን

@ortodoxtewahedo
#አማኑኤል 28

#እግዚአብሔር ከኛ ጋር ሆነ

እኛ ከእርሱ ጋር መሆን ቢያቅተን እርሱ ከእኛ ጋር ሊሆን ልዑል ባህርዪን ዝቅ አድርጎ ከእኛ ጋር ሆነ። በባህርያችን ጎስቁለን የተፈጠርንለትን አምላካዊ መልክ ብናጎድፈው የሰውን አእምሮ በሚፈታተን የተዋህዶ ምስጢር እርሱ ሰው ሆነ።

እኛ አምላክን ወደ መምሰል ከፍ ማለት ቢያቅተን ይህን ክፍተት ያደላድል ዘንድ አምላክ ሰው ሆነ። ሰማያትን እንደ መጋረጃ የሚጠቀልላቸው እርሱን በጨርቅ ጠቀለሉት። ከአለት ውሀን ያፈለቀው አምላክ ከእናቱ ጡትን ለምኖ አለቀሰ።

በላይ ያሉ መላእክትን የሚልካቸውን ንጉስ ማርያምና ዮሴፍ ውሀ ለመቅዳት፣እንጨት ለማምጣት ላኩት።እርሱም በፍቅር ተላካቸው። ከመቅደሱ አገልጋዮች ይልቅ የተናቁትን ሰዎች ሐዋርያት አድርጎ መረጣቸው።

ከቀራጮችና ከሐጢአተኞች ጋር ተቀመጠ።ከእነርሱም ጋር በላ ጠጣ። ሰዎች የተፀየፋቸውን በመቃብር ስፍራ የተጣሉት በምህረቱ ጎበኘ። ከሰርገኞች ጋር ተደሰተ።

ከኀዘንተኞችም ጋር አለቀሰ። እስከመጨረሻም ከእኛ ጋር እንደሆነ እንረዳ ዘንድ የእኛን የሞት ፅዋ ተጎነጫት። መስቀል ላይም ከወንበዴዎች ጋር ተቆጠረ።

በሲኦልም አልተወንም።ከእኛው ጋር ነበር።በገነት መቆየት ያልቻለውን አዳም እስከ ሲኦል ተከተለው። ከዚያም አውጥቶ ወደ ቀደመ ክብሩ መለሰው።

"ከፍ ባልሁ ጊዜ ሁሉን ወደ እኔ እስባለሁ" ያለ አምላክ እኛነታችንን ከእርሱ ጋር ከፍ አድርጎ በዘለዓለማዊ ክብር በአብ ቀኝ አስቀመጠው። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ የተባለውም ተፈጸመ።

እኛም ከእርሱ ጋር ለመሆን ያብቃን!!

#መልካም ቀን

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo

📖📖📖📖📖📖📖📖📖
💚💛❤️ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ💚💛❤️

🏹ከየአቅጣጫው የምትገፋ
🏹ከየአቅጣጫው የሚሴርባት
🏹ከየአቅጣጫው የምትሰደብ
🏹ከየአቅጣጫው የምትንገላታ

👉ነገር ግን

👉ከየአቅጣጫው ትክክል የሆነች
👉ከየአቅጣጫው እንከን የማይወጣላት
👉ከየአቅጣጫው ውበቷ የበዛ
👉ቅድስት ርትዕት ንፅህት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ !!!

ኦርቶዶክስ ያደረከኝ አምላክ ክብርና ምስጋና፥ አምልኮትና ውዳሴ ላንተ ይሁን
አሜን

"ቤተ ክርስትያንን ከማጥፋት ፀሀይን ማጨለም ይቀላል ::"

ቅዱስ ዩሀንስ አፈወርቅ

@ortodoxtewahedo
እንኳን ለመጥምቀ መለኮት ለቅዱስ ዩሀንስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳቹ አደረሰን
በእዚህ እለት መጥመቀ መለኮት ቅዱስ ዩሀንስ አንገቱ በሰይፍ ተቆርጦ ሰማዕት የሆነበት ዕለት ነው። በረከቱ ይደርብን አሜን

#መልካም_በዓል

@ortodoxtewahedo
ዩሀንስ ማርያም🥰

@ortodoxtewahedo
"ጾማችን በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት የሚኖረው የተፈናቀሉት ወገኖቻችን ወደ ቀያቸው ተመልሰው ሰላማዊ ኑሮ መኖር ሲችሉ፣ የተራቡት ሲደገፉ፣ ፍትሕ ያጡት ፍትሕ ሲያገኙ ነው፡፡"
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ

#Ethiopia | ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የ 2016 ዓ.ም ዐቢይ ጾምን አስመልክተው መልእክት አስተላልፈዋል።

ቅዱስነታቸው ያስተላለፉት ሙሉ መልእክት እንደሚከተለው ቀርቧል።

መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

በሀገር ውስጥና በዓለም ዙሪያ ሁሉ የምትገኙ ምእመናንና ምእመናት ልጆቻችን በሙሉ!

እንኳን ለሁለት ሺሕ ዐሥራ ስድስት ዓመተ ምሕረት የጾመ ኢየሱስ ሱባኤ በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!

“ወእምዝ ኃደጎ ዲያብሎስ ወናሁ መጽኡ መላእክት ይትለአክዎ፡- ከዚህ በኋላ ዲያብሎስ ትቶት ሄደ፤ እነሆም ያገለግሉት ዘንድ መላእክት መጡ›› (ማቴ ፬፲፩)፡፡

በቀጣዮቹ ሁለት ወራት በከፍተኛ ሃይማኖታዊ ተመሥጦ የምንጾመው ጾም፣ ጾመ ኢየሱስ ተብሎ የሚታወቀው ነው፡፡ ይህ ጾም በጥንት ጊዜ ሰው በኃጢአት የወደቀበትን ምክንያት፣ እንደዚሁም ሰው ኃጢአትንና ዲያብሎስን እንዴት እንደሚያሸንፍ ጌታችን እኛን ያስተማረበት ጾም ነው፡፡

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በቅዱስ መጽሐፏ እንደምታስተምረን፣ ኃጢአትና ዲያብሎስ የአንድ ሳንቲም _ ሁለት ገጽታዎች ናቸው፤ ይህም ማለት ዲያብሎስ ባለበት ኃጢአት አለ ፤ ኃጢአት ባለበትም ዲያብሎስ አለ ማለት ነው፤ እነዚህ ሁለቱ የሚለያዩ አይደሉም፤ የመጨረሻ ግባቸው ደግሞ ሰውን መጣል ነው፡፡ዲያብሎስ የሰውን ደካማ ዝንባሌ ወይም በሆነ ነገር መጐምጀትን በሰው ሲመለከት ያንኑ የጐመጀበትን ክፉ ምኞት እንዲፈጽም፣ በረቂቅ የሰው ኅሊና ውስጥ ገብቶ በከፍተኛ ደረጃ ይገፋፋል፤ ሰውም በራሱ የመጐምጀት ዝንባሌና በዲያብሎስ ግፊት ለመንፈሳዊ ሕይወቱ ጐጂ የሆነውን ድርጊት ይፈጽማል ፤ ቀጥሎም ድርጊቱ በእግዚአብሔር ፊት በደል ይሆንና ከእግዚአብሔር ይለየዋል፡፡ ሰው ከእግዚአብሔር ከተለየ ደግሞ ዘለዓለማዊ ሕይወትንና ክብርን ጨምሮ ብዙ መልካም ነገርን ያጣል፤ ኃጢአት የሚባለውም ይህ ነው፤ በቀደሙት አባትና እናት ማለትም በአዳምና ሔዋን የተከሠተው ነገርም ይኸው ነው፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት

ኃጢአትን በጽድቅ፣ ዲያብሎስን በጾም በማሸነፍ የአሸናፊነትን መንገድ ሊያሳየን የመጣው አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአዳምና በሔዋን የተፈጸመው ውድቀት እንዴት እንደሚቀለበስ በዚህ ጾም አስተምሮናል፡፡ ጌታችን ዐርባ ቀንና ዐርባ ሌሊት ከጾመ በኋላ ተራበ፤ ዲያብሎስም መራቡን አይቶ ይጐመጅልኛል ብሎ በምግብ ፈተነው፡፡ የጌታችን መልስ ግን ሰው በእንጀራ ብቻ አይኖርም ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ የሚል ነበረ፣ በተመሳሳይም በፍቅረ ንዋይና በአምልኮ ባዕድ ፈተነው የጌታ መልስ ግን በተቃራኒው ነበረ፡፡

ዲያብሎስ በሦስቱም የማስጐምጃ ፈተናዎች ጌታ ሊሸነፍለት ካለመቻሉም በላይ "አንተ ሰይጣን ከኋላዬ ሂድ" ብሎ ሲገሥጸው ተሸንፎ ትቶት ሂዶአል፡ በአሸናፊነቱ የተደሰቱ መላእክትም ወዲያውኑ መጥተው በክብረ አምልኮ አገለገሉት፤ በዚህ ድርጊት የምንመለከተው እውነታ ቀዳማይ አዳምን ባሸነፈበት ስልት ዳግማይ አዳም ክርስቶስን ለመጣል ዲያብሎስ የሄደበትን ርቀት በአንድ በኩል ስናይ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ዳግማይ አዳም ክርስቶስ የቀዳማይ አዳም ተሸናፊነትና ውድቀት ለመቀልበስ ያሳየውን ጥብዓት እናያለን፡፡

በዚህም የቀደመው ውድቀት በኋለኛው አሸናፊነት ሙሉ በሙሉ ተቀልብሶ፣ ዲያብሎስ ጓዙን ጠቅልሎና ተስፋ ተስፋ ቆርጦ መሄዱን እናስተውላለን።

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!

ጌታችን የአሸናፊነትን መንገድ በቃልና በተግባር አስተምሮናል፤ አሳይቶናልም፤ ይህንም ያደረገው እሱ አሸንፎልናል እያልን ለመኵራራት ሳይሆን፣ በእሱ ኃይል እየታገዝንና እሱ ባሸነፈበት ስልት እየተጠቀምን እንድናሸንፈው ነው፡፡ ሰይጣን የሚሸነፍበት ስልት በሌላ ሳይሆን፤ ሥጋዊ መጐምጀትን ከአእምሮአችን አውጥተን በመወርወር ነው፡፡

ሥጋችን በፍቅረ ንዋይ፣ በሥልጣን፣ በዝሙት እንደዚሁም በተለያዩ ሥጋዊ ምኞቶች ሊጐመጅ ይችላል፤ ያን ጊዜ ሰይጣን እነሱን እንድንፈጽም ሊገፋፋን ከበኋላችን እንደቆመ እናስብና "አንተ ሰይጣን ከኋላዬ ሃድ” እንበለው፡፡ በቃል ብቻ ሳይሆን በተግባር ያስጐመጁን ነገሮችን ከኅሊናችን አውጥተን በመጣል እሱን ማሸነፍ አለብን፤ በዚህ ጊዜ ሰይጣን ይሸሻል፤ መላእክትም ወደኛ መጥተው ይረዱናል፣ ይጠብቁናል፤ ያግዙናል፣ ያድኑናል፡፡ ዲያብሎስ የሰዎችን የመጐምጀት ዝንባሌን ተከትሎ በመገፋፋት ዛሬም ዓለማችንን ለከፋ ውድቀት እየዳረጋት ነው፣ ሀገራችንን ጨምሮ በየአካባቢው የሚቀሰቀሱት አለመግባባቶችና ግጭቶች መንሥኤያቸው ከመጐምጀት ውጭ ሊሆን አይችልም፡፡ ግማሹ በሥልጣን፣ ግማሹ በሀብት፥ ግማሹ በራስ ወዳድነት፣ ግማሹ ደግሞ የበላይ ለመሆን በሚል እሳቤ የሰው ኅሊና በክፉ ምኞት ይጐመጅና በዲያብሎስ ገፋፊነት ወደ ተግባራዊ ጥፋት ይገባል፡ በውጤቱም ሰው ይጎዳል፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት

ጾም ማለት እህልንና የእንስሳት ውጤቶችን ከመመገብ መከልከል ብቻ አይደለም፣ የእንስሳት ውጤት የሆኑትን ላለመመገብ ከምንወስነው በላይ እኩያት ፍትወታትንና ኃጣውእን ላለማስተናገድ በቁርጥ መወሰን ይጠበቅብናል፡፡ ስንጾም መገዳደልን፤ መጣላትን መለያየትን፤ መገፋፋትን በሆነ ነገር መጐምጀትን እርም ብለን በመተው ዲያብሎስን የምናሸንፍበት የአሸናፊነት ኅሊና መላበስ አለብን፣ ከክፉ ኅሊና እና ተግባር የተለየን ያህል በአንጻሩ ደግሞ በጎ ነገርን ለመስራት በእጅጉ መበርታት ይጠበቅብናል፡፡

ዲያብሎስ ተስፋ ቆርጦ የሚሸሸው ይቅር ይቅር ስንባባል፤ ለሰላምና ለአንድነት፣ ለፍቅርና ለስምምነት ስንቆም ነው! ከዚህም ጋር በእግዚአብሔር ፊት እጅግ ጸያፍ የሆነው ግብረ ኃጢአት በዚህች ምድር እንዳይፈጸም ማኅበረ ሰባችን በተጠንቀቅ ሲቆም ነው፤ እንደዚሁም ደም መፋሰስ፣ አለመተማመንና በሴት ልጆቻችን የሚደርስው አካላዊ፣ መንፈሳዊና ሞራላዊ ጥቃት ሲቆም ነው፡፡ ጾማችን በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት የሚኖረው የተፈናቀሉት ወገኖቻችን ወደ ቀያቸው ተመልሰው ሰላማዊ ኑሮ መኖር ሲችሉ፣ የተራቡት ሲደገፉ፣ ፍትሕ ያጡት ፍትሕ ሲያገኙ ነው፡፡

ይህ ዓይነት መልካም ሥነ ምግባር በእያንዳንዱ የማኅበረሰብ አእምሮ ቦታ አግኝቶ ሲተገበር ትክክለኛውን ጾም ጾምን ማለት እንችላለን፣ ዲያብሎስም በእርግጠኝነት በዚህ ይሸነፋል፤ የሰው ጣዕመ ሕይወትም በዚህ ይለመልማል! ምድሪቱም በእግዚአብሔር በረከት ትሞላለች፡፡ ይህን ቅዱስ ተግባር በወርኃ ጾሙ በደንብ እንድንተገብረው ለመላው ኢትዮጵያውያን በተለይም ለኦርቶዶክሳዊው ማኅበረሰብ መንፈሳዊና አባታዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

በመጨረሻም

በሀገራችን ረሃብ የሚያጠቃቸው ወገኖች በበዙበት በአሁኑ ወቅት፤ ሳንመጸውት ጾምን ጾምን ማለት ማጣፈጫ ወጥ የሌለው ምግብ መመገብ ማለት ስለሆነ፣ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የቁርስ በጀቱን ለተራቡ ወገኖች በመለገስ ወገኖቹን በረሃብ ከመሞት እንዲታደግ ወቅታዊ ጥሪያችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፡፡
መልካም የጾም ወቅት ያድርግልን! እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ !! ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!! አሜን፡፡

አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት መጋቢት ፩ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም. አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ

@ortodoxtewahedo
."የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ።"

#ኤፌ 6፥11

"እርሱስ በአርምሞአችን ካልተጠቀመ በመናገራችን አይጠቀምም"

#አሞ 5፥13

"ስለዚህ ክፉ ዘመን ነውና በዚያ ዘመን አስተዋይ የሚሆን ዝም ይላል።"
#ያዕ.1፥19

"ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን"

#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው
ከፍ ከፍ አድርጋቸው/2/

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo
✞ እንኩዋን ለታላቁ "የጌታ ጾም (ጾመ እግዚእ)" በሰላም አደረሳችሁ ✞

+*" ጾመ እግዚእ "*+

=>ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በአዋጅ ምዕመናን
እንዲጾሟቸው የሠራቻቸው 7 አጽዋማት አሏት:: "ጾም" ማለት "መከልከል" ነው:: የምንከለከለው ደግሞ ከኃጢአትና ከክፋት ሲሆን አንድም ሰውነትን ወደዚያ ከሚወስዱ አዝማደ መባልዕት (የምግብና የመጠጥ ዓይነቶች) መከልከልን ይመለከታል::

+"7ቱ" አጽዋማት:-
1.ዓቢይ ጾም
2.ጾመ ፍልሠታ
3.ጾመ ሐዋርያት
4.ጾመ ነቢያት
5.ጾመ ድኅነት
6.ጾመ ነነዌ እና
7.ጾመ ገሃድ ይሰኛሉ::

+በእነዚህ አጽዋማት ከዓቢይ ጾም በቀር እስከ 9 ሰዓት
ድረስ መጾም ይገባል:: ዓቢይ ጾም ግን የተለየ ሥርዓት
አለው:: ስለ ጾም ሲነሳ አስቀድሞ የሚመጣው ጥያቄ
አስፈላጊነቱ ነው:: "ጾም ለምን ያስፈልጋል?" ብሎ
ከመጠየቅ "ሃይማኖት ለምን ያስፈልጋል?" ብሎ
መጠየቁ ይቀላል::

+ምክንያቱም ከሃይማኖታዊ ትዕዛዛት ትልቁ በመሆኑ
እርሱን መቃወም ሃይማኖትንና አዛዡን እግዚአብሔርን
መቃወም ነውና:: እኛ ሃገር ላይ የተለመደች ክፉ ልማድ
አለች:: የከበደችንን ነገር "አያስፈልግም" በሚል
እንከራከራለን::

+ደግሞ ጾምን ለመሻር ጥቅስ የሚጠቅሱ ወገኖች
በጣም ይገርሙኛል:: ኃጢአትን ለመሥራት : ጾምንም
ለመሻር ጥቅስን መጥቀስ አያስፈልግም:: እኛ ግን
¤ከፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጀምሮ (ማቴ. 4:2)

¤አበው ቅዱሳን ጾመው (ዘዳ. 9:19, ነገ. 19:8, ሐዋ.
13:3, ቆሮ. 4:11) አሳይተውናልና እንደ አቅማችን
እንጾማለን::

+የጾሙ የመጀመሪያው ሳምንት (ዘወረደ) የሚጾመው
እስከ 12 ሰዓት ሲሆን ከቅድስት (ከ2ኛው ሳምንት) እስከ
ተጽኢኖ (የኒቆዲሞስ ዓርብ) ድረስ ደግሞ እስከ 11
ሰዓት ይጾማል::
በሰሙነ ሕማማት ግን የምንጾመው "እስከ ይሠርቅ
ኮከብ" (እስከ ምሽት 1 ሰዓት) ድረስ ይሆናል::

+ነገር ግን ሁሉም እንደ መጠኑ ነውና ከመምሕረ ንስሃ
ጋር ሊጨዋወቱት ይገባል:: በዓቢይ ጾም ለቻለ ቂጣ
በጨው እየበላ: ውሃ እየተጐነጨ ሊጾም ይገባል::
በእነዚህ 55 ቀናትም ከዕለተ ሆሳዕና በቀር ከበሮ
አይጐሰምም:: ጸናጽል አይጸነጸልም:: ተድላ ደስታም
አይደረግም::

+አብዝቶ መብላት : ሳቅ ማብዛትና ጌጥን ማብዛትም
እንዲሁ አይገባም:: ለቻለ ደግሞ በሌሊት ሰዓታቱን፡
በግህ ኪዳንና ስብሐተ ነግሁን : በመዓልት ቅዳሴውን :
በሰርክ (ምሽት) ደግሞ ምሕላውን ሊሳተፍ ይገባል::

+በእነዚህ 55 ቀናት ፈቃደ ሥጋ ሊደክም : ፈቃደ ነፍስ
ልትሰለጥን ግድ ነውና:: ከሌላው ጊዜ በተሻለ ወቅቱ
ምጽዋትና ጸሎት የሚደረግበት ነው:: በዚያውም ላይ
ነገሮችን እያመቻቹ በእነዚህ ዕለታት ቅዱስ ቃሉን
መስማት (ማንበብ) ይገባል:: በትዳር ውስጥ ላሉም
መኝታን መለየት ግድ ነው::

=>ከ7ቱ አጽዋማት አንዱ የሆነው ይህ ጾም=
1.ዐቢይ (ታላቁ) ጾም
2.የጌታ ጾም
3.ጾመ ሑዳድ
4.የድል ጾም
5.የካሳ ጾም
6.አርባ ጾም
7.የፍቅር ጾም . . .
በሚሉ መጠሪያዎችም ይታወቃል::

=>የጾሙ መግቢያ የመጀመሪያ ሳምንት ደግሞ=
1.ጾመ ሕርቃል
2.ጾመ በረከት ዘሐዋርያት
3.ሰሙነ ዘወረደም ይባላል::

=>ጾሙን የሰላም : የፍቅር : የምሕረት : የፀጋ :
የበረከት ያድርግልን:: ጾሞ ለማበርከትም ያብቃን፡፡

=>+"+ አሁንስ ይላል እግዚአብሔር በፍጹም ልባችሁ
በጾምም በልቅሶና በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ:: ልባችሁን
እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ:: አምላካችሁም
እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ: ቁጣው የዘገየ: ምሕረቱም የበዛ: ለክፋትም የተጸጸተ ነውና ወደ እርሱ ተመለሱ:: +"+ (ትን. ኢዩኤል 2:12)

✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞

@ortodoxtewahedo
@ortodoxtewahedo
@ortodoxtewahedo
የዐቢይ ጾም ሳምንታት
(የመጀመሪያው ሳምንት)  

+++++++++++‹ዘወረደ›+++++++++++

ትርጕሙ ‹ከሰማየ ሰማያት የወረደ› ማለት ነው፡፡ ከሰማየ ሰማያት የወረደውን፣ ከድንግል ማርያም የተወለደውን በጥንት ስሙ ወልድ፣ ቃል በኋላ ስሙ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ አማኑኤል የተባለውን ሰው የኾነውን አምላክ ለማመስገን ርደቱን (ከሰማየ ሰማያት መውረዱን) ለመዘከር የሚጾም ጾም ነው፡፡

ጌታችን ጾመ ከማለት አስቀድሞ ከሰማየ ሰማያት መውረዱን ከድንግል ማርያም መወለዱን መናገር አስፈላጊ ነውና የመጀመሪያው ሳምንት ‹ዘወረደ› ተብሏል፡፡ ‹‹አንተ በሰማይ ወአንተ በምድር ወአንተ በባሕር ወአንተ በየብስ፤ አንተ በሰማይ አለህ፤ በምድር በባሕርም በየብስም አለህ፤›› የተባለውን በሰማይ በምድር ምሉዕ የኾነውን አምላክ ‹ወረደ፤ መጣ› ብሎ መናገር ‹ሰው ኾነ› ማለት ነው፡፡

ሰው ኾኖ መገለጡን ለማስረዳት ነው እንጂ መውረድ መውጣት የሚባሉ ቃላት በዅሉ ምሉዕ ለኾነው መለኮት አይስማሙትም፡፡ ቃላቱ ሰውኛ አነጋገርን የሚያመለክቱ ናቸውና፡፡ መተርጕማን አበው ‹‹‹ዘወረደ› ማለት ‹ሰው የኾነ› ማለት ነው›› ብለው ይተረጕማሉ፡፡ አምላካችን ሰው ከኾነ በኋላ ‹መጣ፤ ሔደ፤ ወረደ፤ ዐረገ› የሚሉ ቃላት ይስማሙታል፡፡

ምልዓቱን ሳይለቅ በሰው አካል ተወስኖ ታይቷልና፡፡ ስለዚህ ‹ወረደ› እግዚአብሔር ሰው ኾኖ መገለጡን፤ ‹ዐረገ› ደግሞ የሰውነቱን ሥራ መፈጸሙን ያሳያል፡፡ ዐረገ ስንልም ቀድሞ በሰማይ የለም ለማለት አይደለም፤ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመለኮቱ በዓለሙ ዅሉ ምሉዕ ነውና፡፡

ጾሙን ሐዋርያት፣ ስያሜውንና የምስጋናውን ሥርዓት ቅዱስ ያሬድ አዘጋጅተዋል፡፡ ቅዱስ ያሬድ ነቢያትን በንባብ፤ ሐዋርያትን በስብከት፤ ሊቃውንትን በትርጓሜ፤ መላእክትን በዜማ ይመስላቸዋል፡፡ ቅዱስ ያሬድ የመላእክትን የምስጋና ሥርዓት ወደ ምድር አምጥቷል፡፡

የነቢያትን ትንቢት፣ የሐዋርያትን ትምህርት በሚገባ ተርጒሞ፣ አብራርቶ፣ አመሥጥሮ አዘጋጅቶታል፡፡ ሐዋርያት ጾሙን ጾመው የጾም ሕግ ደንግገዋል፤ ቅዱስ ያሬድም ለጾሙ ስያሜ ሰጥቶ ምስጋና ከነሥርዓቱ አዘጋጅቶ አቅርቧል፡፡ቤተ ክርስቲያናችንም የመጀመሪያው የዐቢይ ጾም ሳምንትን (ዘወረደን) ስያሜ እንደ ቅዱስ ያሬድ ከሐዋርያት ተቀብላ ታስተምራለች፡፡

ይህ የመጀመሪያው ሳምንት ‹ጾመ ሕርቃል› እየተባለም ይጠራል፡፡ ሕርቃል (ኤራቅሊዮስ) በ፮፻፲፬ ዓ.ም የነበረ የቤዛንታይን ንጉሥ ነው፡፡ ለክርስቲያኖች ባደረገው ርዳታ ምክንያት አንድ ሳምንት ጾመውለት ነበር፡፡ ያላወቁ ‹ጾመ ሕርቃል› ብለው አንድ ጊዜ ጾመው ትተውታል፡፡ ጥንቱን የቅዱሳን ሐዋርያት መኾኑን ያወቁ ምእመናን ግን ዅልጊዜ በየዓመቱ ይጾሙት ነበር፡፡ ዛሬም ድረስ ጾመ ሕርቃል እየተባለ ይጠራል፡፡ ሙሉ ታሪኩ በፍትሐ ነገሥት ትርጓሜ አንቀጽ ፲፭ ላይ ይገኛል፡፡

አምላካችን እግዚያብሔር ሆይ ጾማችንን በሰላም እንድንጨርስ ቅዱስ ፈቃድህ ይሁንልን ። አሜን
        
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡

@ortodoxtewahedo
@ortodoxtewahedo
@ortodoxtewahedo
#ዘወረደ ብለን የጀመርንውን ፆም #ሆሳዕና ብለን እንድንጨርስ የእግዚአብሔር ቅዱስ ፍቃድ ይሁንልን አሜን!

ይህ ጾም ከእህል እና ውሃ የምንቆጠብበት ሳይሆን ለቤተክርስቲያናችን ለሃገራችን እና ለህዝቦቿ ምህረትን፣ ሰላምንና ፍቅርን የምናስገኝበት የቀድሞ አንድነቷ የሚመለስበት ከተፈራው ከሚወራው ሃገራችንና ህዝቦቿን የምንታደግበት ጾም ያድርግልን።

የታወረ አይነ ልቦናችን የሚገለፅበት፣ ሰላም የሚወርድበት፣ ሃጢአታችን የሚደመሰስበት፣የጠፋነው የምንገኝበት፣ እርስ በእርሰ ከመበላላት የምንፋቀርበት በዘር በሃይማኖት ተከፋፍለን በዲያብሎስ አይን ከመተያየት አንድ የምንሆንበት ጾም ያድርግልን አሜን ::

#አንድ_ሲኖዶስ
#አንድ_ፓትሪያሪክ
#አንዲት_ቤተክርስቲያን

@ortodoxtewahedo
@ortodoxtewahedo
@ortodoxtewahedo
2024/09/29 05:23:44
Back to Top
HTML Embed Code: