Telegram Web Link
goodness inclined him toward forgivness. In the
end Menelik took consel of ABUNE MATEWOS,
who sides with Taitu, Alula, Mengesha and the
others"
ጦርነቱ ላይ የተከናወኑ ሌሎችም በርካታ ውሳኔዎች ላይ አቡነ
ማቴዎስ ነበሩ::
እና ምን ለማለት ነው
*
አድዋ ጦርነት ዲሎማሲ ዘመቻ ላይ አንዷ ዲፕሎማት
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ነበረች( እነ ቄስ
ወልደሚካኤል)
ዲፕሎማሲው ፈርሶ ጦር ሲታወጅ አንዷ ዘማች የኢትዮጵያ ቤተ
ክርስትያን ነበረች:: የቀረ የለም:: ጽላቱ: ካህኑ: መነኩሴው :
ጳጳሱ ዘምቷል
ጦርነቱን በበላይ ሲመሩ ከነበሩ አካላት አንዷ የኦርቶዶክስ
ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ጳጳስ አቡነ ማቴዎስ ነበሩ
የጦሩ ጠቅላይ አዛዥ ለዋና ዋና ውሳኔ ዋና አማካሪያቸው ጳጳሱ
አቡነ ማቴዎስ ነበሩ
አቡነ ማቴዎስ የውጊያ ውሎን ይገመግሙ ነበር:: የተበላሸ
ሲመስላቸውም የጦር መሪዎችን ይገስጹ ነበር
አረ ሰራዊቱን በዙር ቦታ እያስያዙ የሚያሰፍሩት መነኮሳቱ ነበሩ
ወዘተ ወዘተ
እናጠቃለው
****
ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን የነጻነታችን
ባለውለታ ናት:: በባርነት ቀንበር ስር እንዳንማቅቅ ተጋድለውና
ተሰውተው ለሀገራችን ነጻነትን የሰጧት ቅዱሳን መንፈሳዊ
አባቶቻችንም
ጭምር ናቸው:: አድዋ ላይ ጣልያንን ድል ያደረግነው -በቅዱሳን
አባቶቻችን መንፈሳዊ ጸሎትና ስጋዊ ተጋድሎም ጭምር ነው::
አድዋ ሲነሳ ባለታሪኳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ
ክርስትያንም አትረሳ:: ስሟ ይነሳ:: ዋናዋ የድል መሀንዲስ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ናትና!

@ortodoxtewahedo
@ortodoxtewahedo
@ortodoxtewahedo
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አትሩጡ…!

እምነታችሁ ያድናችኋል፤
ቅዱስ ጊዮርጊስ ያድናችኋል፤
አትሩጡ ፈረሰኛው ይመጣል።
እንደዚህ እንዳስለቀሱን አይቀርም።

እምነት_ፅናት_ሀገር ወዳድት

@ortodoxtewahedo
@ortodoxtewahedo
@ortodoxtewahedo
"መዊቶ ጻድቅ ይኴንን ረሢኣነ"

ደግ ሰው ሞቶ ዝንጉዎችን ይገዛል።
(ጥበ ፬÷፲፮)
ንጉሡ!
ሺህ ዘመን ይንገሡ!!
ማለት ይህ ነው።

@ortodoxtewahedo
ፀረ ኦርቶዶክሱ ጥቃት። ታሪክ መዝግቦታል። እንኳን በሕይወት እያለን አፅማችን አይረሳውም።

@ortodoxtewahedo
@ortodoxtewahedo
@ortodoxtewahedo
#ዓድዋ

የካቲት 23-የልዳው ፀሐይ ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ በጦርነት ላይ ሳለ ሣህለ ማርያምን (ዐፄ ሚኒልክን) በመርዳት ጠላትን ድል እንዳደረገ የሚናገር ተአምር ይህ ነው፡- ‹‹ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ልደት 1854 ዓመት በኋላ የኢትዮጵያ ነጉሠ ነገሥት ዳግማዊ ምኒልክ በነገሠ በ26ኛ ዓመት የምኒልክ የጦር አለቃ ገበየሁ ድል ካደረጋቸው በኋላ እንደገና ምኒልክን ወግተው ኢትዮጵያን በቅኝ አገዛዝ ሊገዙ የሮም ሰዎች መጡ፡፡

ከዚህም በኋላ የኢትዮጵያው ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ ‹አገሬ ኢትዮጵያን እወዳለሁ የሚል ኢትዮጵያዊ ሁሉ በአስቸኳይ ይነሣ፣ መስቀለ ሞቱንም ተሸክሞ ይከተለኝ፡፡ እግዚአብሔር የወሰነልንን የባሕር ወሰን አልፎ አገር የሚያጠፋ፣ ሃይማኖት የሚለውጥ ጠላት መጥቷልና› ሲል አዋጅ አስነገረ፡፡ ዳግመኛም በፈረሶቻቸው መጣብር ላይ በጦራቸው ላይ በጋሻቸው ላይ የመስቀል ምልክት እንዲያደርጉ ወታደሮቹን አዘዛቸው፡፡ መስቀል ጠላትን ድል አድራጊ እንደሆነ አስቀድሞ ያውቅ ነበርና፡፡ ከዚያም ተነሥቶ ወደ ትግራይ ክፍለ ሀገር ዘመተና ከትግራይ አውራጃዎች አንዷ የምትሆን አድዋ ከምትባል አገር ደረሰ፡፡

የሣህለ ማርያም (ዐፄ ሚኒልክ) ሚስት ወለተ ሚካኤል (እቴጌ ጣይቱም) በንጉሡ ትእዛዝ ታቦተ ቅዱስ ጊዮርጊስን አሲዛ ከሊቀ ጳጳሱ ከአባ ማቴዎስ እንዲሁም ከቀሳውስቱና ከመነኮሳቱ ጭምር ከንጉሡ ጋር ወደ ጦርነቱ ተጓዘች፡፡ በዚያም ጊዜ የአክሱም ጽዮን መነኮሳትና ካህናት የእመቤታችንን ሥዕል ይዘው ወደ ንጉሡ ወደ ምኒልክ መጥተው ከሊቀ ጳጳሱ ከእነ አቡነ ማቴዎስ ጋር ተቀላቀሉ፡፡

ከዚያም ሌሊቱን ሙሉ ጸሎተ ምሕላ ሲያደርሱ አደሩ፡፡ ቅዳሜ ማታ ለእሑድ አጥቢያ ይኸውም የካቲት 22 ቀን ነው ንጉሡ ሣህለ ማርያም (ዐፄ ሚኒልክ) የጦር ልብሱን ለብሶ ከሠራዊቱ ጋር ወደ ጦር ግንባር ሄደ፡፡ ከዚያም ከሮማውያን የጠላት ጦር ጋራ ተገናኝቶ ከሌሊቱ በዓሥራ አንድ ሰዓት ጦርነቱን ጀመረ፡፡

የንጉሥ ሣህለ ማርያምን ሚስት ወለተ ሚካኤል (እቴጌ ጣይቱም) ሌሊት በታቦተ ቅዱስ ጊዮርጊስና በእመቤታችን ሥዕል ፊት በጸሎትና በስግደት እያደረች ሲነጋ ወደ ጦርነቱ ቦታ በመሄድ እጅግ በሚያስደንቅ የአነጋገሯ ኃይለ ቃል በጦርነቱ መካከል እየተገኘች ለንጉሡ ወታደሮች የሞራልና የብርታት ድጋፍ ትሰጣቸው ነበር፡፡ በዕውነትም ለተመለከታት ሁሉ እንደኃይለኛ ተጋዳይ አርበኛ ትመስል ነበረ እንጂ የሴቶች የተፈጥሮ ባሕርይ በእርሷ ላይ አይታይባትም ነበር፡፡ የንጉሡም ወታደሮች የንግሥቲቱን የጀግንነት አነጋገር በሰሙ ጊዜ በእሳት ላይ እንደተጣደ የብረት ምጣድ ልባቸው ጋለ፡፡ ይልቁንም ላም እንዳየ አንበሳና ፍየል እንዳየ ነብር እየተወረወሩ በጦርነቱ መካከል በመግባት የጠላትን ጦር በሰይፍ ይጨፈጭፉት ነበር፡፡ መጽሐፍ ‹ሹመቱን ሽልማቱን ያየ አርበኛ ከጦርነት ከሰልፍ ወደኋላ አያፈገፍግም› ብሎ ተናግሯልና፡፡

በዚያንም ጊዜ ንጉሡ ሣህለ ማርያም በጦርነቱ መካከል ሳለ ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ማቴዎስ እንዲሁም የአክሱም መነኮሳት ሌሎቹ ካህናት በሙሉ ታቦተ ቅዱስ ጊዮርጊስንና ሥዕለ ማርያምን ይዘው ከንጉሡ በስተኋላ በደጀንነት ቆመው ጸሎተ ምሕላ ያደርሱ ነበር፡፡ ንግሥቲቱ ወለተ ሚካኤል በጸሎት ጊዜ በመዓልትም በሌሊትም ከእነርሱ አትለይም ነበር፡፡ የጽዮን አገልጋዮችም በእግዚአብሔር በሕጉ ታቦት ፊት መለከት ይነፉ ነበር፡፡ በዚህም ዕለት ይኸውም የካቲት 23 ቀን በሮማውያንና በኢትዮጵያውያን መካከል ከፍተኛ ጦርነት ሆነ፡፡

@ortodoxtewahedo
ከመልአከ ምህረት ግሩም አለነ
በሀገረ ስብከታችን <<የቤተ ክርስቲያናችን ግንባር ቀደም መንፈሳውያን ሠራዊት ደቀ መዛሙርት>> ላይ ከተፈፀሙ ግፎች በከፊል

[በኃዘን ድንኳን ውስጥ የተጻፈ ትክክለኛ
ክታብ ነው!]

➛እነዚህ በዓይናችን እያየን የታረዱብን፣በእጆቻችን ገንዘን የቀበርናቸው እና መተኪያ የሌላቸው ድንቅ ወንድሞቻችን ናቸው።

➛፩ኛ፦
መስከረም 28 ለ29 ምሽት/2016 ዓ/ም በሰሜን ጎጃም ሀገረ ስብከት በአዴት ከተማ በጌቴ ሴማኒ ፍልሰታ ለማርያም ደብር በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በግፍ የተገደሉ የአቋቋም ደቀ መዛሙርት ስም ዝርዝር፦

1ኛ መምሕር ትኅትና የቅኔ መምሕር ደቡብ ጎንደር ዕብናት ወረዳ
2ኛ ደቀ መዝሙር አብርሃም የአቋቋም አድራሽ ሸዋ መርኃ ቤቴ
3ኛ ደቀ መዝሙር መንክር የአቋቋም አድራሽ ይልማና ዴንሣ
4ኛ ደቀ መዝሙር በቃሉ አቋቋም የለዬ ይልማና ዴንሣ
5ኛ ደቀ መዝሙር ኤርምያስ አቋቋም የለዬ ነፋስ መውጫ ወረዳ
6ኛ ደቀ መዝሙር ሳሙኤል የለዬ ሞጣ ነፍጠኛ
7ኛ ደቀ መዝሙር ሕዝቅኤል አቋቋም ጀማሪ ሸቨል ወረዳ ቅኔ ዘራፊ
8ኛ ደቀ መዝሙር ብርሃኑ የለዬ እናርጅ እናውጋ ወርዳ
9ኛ ደቀ መዝሙር ሱቱኤል ጀማሪ ሰሜን ጎንደር ደባርቅ
10ኛ ደቀ መዝሙር ፍሬ ሕይወት ጀማሪ
11ኛ ደቀ መዝሙር ነቢዩ የለዬ ሰሜን ሽዋ መራ ቤቴ
12ኛ ደቀ መዝሙር ዘለዓለም ሞካሪ እናርጅ እናውጋ
13ኛ ደቀ መዝሙር ባርኮት የቍጥር ተማሪ ነፋስ መውጫ
14ኛ ደቀ መዝሙር አእመረ አወቀ.....
15ኛ ደቀ መዝሙር ሰሎሞን ዳዊት ....ናቸው።
[በግምት ከ20 እስከ 45 ዓመት በሚሆን የእድሜ ክልል ውስጥ ይገኛሉ]

➛ ፪ኛ፦ ⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
የካቲት 20 ለ21/2016 ዓ/ም በግምት ከሌሊቱ 6፥30 በሰሜን ጎጃም ሀገረ ስብከት በሰሜን ሜጫ ወረዳ በላይ ጋፊት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በግፍ የተገደሉ የቅኔ ደቀ መዛሙርት ስም ዝርዝር፦
1ኛ.ደቀ መዝሙር ግሩም ዘሰሜን ሜጫ ጭሮ ቀበሌ
2ኛ.ደቀ መዝሙር ጌታሰው ዘዳንግላ
3ኛ.ደቀ መዝሙር አብርሃም ዘዳንግላ
4ኛ.ደቀ መዝሙር ይትባረክ ዘሰሜን አቸፈር ሊበን
5ኛ.ደቀ መዝሙር ዘርዐ ዳዊት ዘሰሜን ሜጫ ሳምሲ በዐታ [በዘመናዊ ዲግሪ ያለው]
6ኛ.ደቀ መዝሙር ኤፍሬም ዘመሸንቲ [በዘመናዊ ዲግሪ ያለው]
7ኛ.ደቀ መዝሙር ስብሐት ዘመሸንቲ
8ኛ.ደቀ መዝሙር ገብረ ማርያም ዘመሸንቲ
9ኛ.ደቀ መዝሙር ሳምናስ ዘሰሜን ሜጫ ዳጋሊ ሚካኤል
10ኛ.ደቀ መዝሙር ቃለ ጽድቅ ዘሰሜን ሜጫ ዳጋሊ ሚካኤል
11ኛ. ደቀ መዝሙር በእውቀት ፍሬው ዘሰሜን ሜጫ ላይ ጋፊት ገብርኤል[የደብሩ መሪጌታ የሥጋ ልጅ]
12ኛ.አቶ እንዳላማው ወርቄ [በአጋጣሚ በአካባቢው የነበረ] ናቸው።[በግምት ከ15 እስከ 30 ዓመት በሚሆን የእድሜ ክልል ውስጥ ይገኛሉ]

➛ከዚህ ጋር ተያይዞ ይህ ጽሑፍ እስከተጻፈበት ቀን እና ሰዐት ደራስ የደብሩ ኃላፊ የሆኑትን ቀሲስ ደጋአረገ አሳየን ጨምሮ የደብሩ አገልጋዮች ወደማይታወቅ አካባቢ ተወስደው ያልተገባ እንግልት እና ድብደባ እየተፈጸመባቸው መሆኑን ከታማኝ ምንጮች መረዳት ችለናል።

➢ፍትህ ለቤተ ክርስቲያን❗️

@ortodoxtewahedo
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን
ሰላም የኔ ተወዳጆች እንደምን አላችሁ?
የጌታችን የእየሱስ ክርስቶስ ፀጋና ሰላም ከሁላችን ጋራ ይሁን አሜን!
አንድነገር ላማክራቹ ስለወደድኩኝ ነው ዛሬ እዚህ የተገኘሁት
በወቻሞ ዩኒቨርሲቲ ዱራሜ ካንፓስ ተማሪዎች ከ8 አመታት በፊት የተመሰረተው ይህ አማኑኤል ቤተክርስቲያን የተቋቋመው
>ከተማሪዎች በሚሰበሰብ አስራት እና
> ከተማሪዎች የሚሰበሰበውን የቁርስ ዳቦ በመሸጥ ነው
ፅላቱን የገባው በቅርቡ ማለትምበ27/08/15 ሲሆን  ግን
አሁንም ቤተክርስቲያኑ ብዙ ነገር ያስፈልገዋል ።
ይህ ቤተክርስትያን በአካባቢው ካሉ ጥቂት ቤተክርስትያኖች አንዱ ነው ስለሆነም በአካባቢው ላሉ ኦርቶዶክሳዊያን፣ለሚመጣውም የጊቢ ተማሪም ሆነ ለተዋህዶ ልጆች  እጅግ አስፈላጊ ነውና
ቤተክርስቲያናችንን አብረን እንስራ ስል በክርስቶስ  ፍቅር እጠየቃለሁ ::

የጊቢ ጉባኤው ደግሞ
        cbe   1000278503732 ዱራሜ ካንፓስ ጊቢ ጉባኤ
   


                 ወስብሀት ለእግዚአብሔር
                  ወለወላዲቱ ድንግል
                  ወለመስቀሉ ክቡር

@ortodoxtewahedo
«ከተወሰኑ ዓመት ወዲህ የተስተዋሉ የቀኖና ጥሰት ፣ ኦርቶዶክሳውያን መከራ፣ እንዲሁም የአብያተ ክርስቲያናት መቃጠል በአጠቃላይ የተከሰቱ ችግሮችን የእግዚአብሔርን ተልእኮ መሠረት በማድረግ ማስተካከልና ማከናወን ካልቻልን የብዙዎች ኢትዮጵውያንን ልብ እናደማለን ከዚህ በላይ ትውልዱም ይጠይቀናል፤ የታሪክ ተወቃሾችም እንሆናለን።»

ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባህርዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በዓለ ሢመት ላይ ካስተላለፉት መልዕክት የተወሰደ

@ortodoxtewahedo
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን

❖❖ታላቅ መንፈሳዊ የንግስ ጉዞ ወደ ምድረ ከብድ አቡነ ገብረ መነሰፈስ ቅዱስ ገዳም❖❖


የተወደዳችው የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንደምን ቆያችሁ እግዚአብሔር አምላካችን የተመሰገነ ይሁን እንደሚታወቀው #መጋቢት_5 ቀን የአባታችን የ እረፍት ክብረ በዓል በደማቅ ሁኔታ ይከበራል ስለዚህም በየአመቱ ማህበራችን ይህን አመታዊ የማይቀር ጉዞ በደማቅ ሁኔታ አዘጋጅቶሎታል ፈጥነው በመደወል የበረከቱ ተካፋይ ይሁኑ!

የጉዞ ቦታ :- ምድረ ከብድ

የጉዞ ቀን ፦  መጋቢት 4 - 5

የጉዞ መነሻ:-  12:00


የጉዞ መነሻ ቦታ:- ፒያሳ ጊዮርጊስ

የጉዞ ዋጋ:- 800 ብር

ጉዞውን ለመሄድና ከበረከቱ ለመሳተፍ ከስር በተጠቀሱት ስልክ ቁጥሮች በመደወል ተመዝገቡ ያለን ውስን ቦታ ስለሆነ....!!!!!!
   
   |➛ +251910455701
   |➛ +251911354174
   |➛ +251961089373
    "ወስብሃት ለእግዚያብሔር ወለ ወላዲቱ ድንግል "
.አዘጋጅ:- ማህበረ እመጓ ዑራኤል ወ አቡነ መልከፀዴቅ
2024/09/29 07:19:42
Back to Top
HTML Embed Code: