Telegram Web Link
የዐብይ ጾም ሳምንታት።

#ዘወረደ ብለን የጀመርንውን ፆም #ሆሳዕና ብለን እንድንጨርስ የእግዚአብሔር  ቅዱስ ፍቃድ ይሁንልን አሜን!

ይህ ጾም ከእህል እና ውሃ የምንቆጠብበት ሳይሆን ለቤተክርስቲያናችን ለሃገራችን እና ለህዝቦቿ ምህረትን፣ ሰላምንና ፍቅርን የምናስገኝበት የቀድሞ አንድነቷ የሚመለስበት ከተፈራው ከሚወራው ሃገራችንና ህዝቦቿን የምንታደግበት ጾም ያድርግልን።

የታወረ አይነ ልቦናችን የሚገለፅበት፣ ሰላም የሚወርድበት፣ ሃጢአታችን የሚደመሰስበት፣የጠፋነው የምንገኝበት፣ እርስ በእርሰ ከመበላላት የምንፋቀርበት በዘር በሃይማኖት ተከፋፍለን በዲያብሎስ አይን ከመተያየት አንድ የምንሆንበት ጾም ያድርግልን አሜን ::

#አንድ_ሲኖዶስ
#አንድ_ፓትሪያሪክ
#አንዲት_ቤተክርስቲያን

@ortodoxtewahedo
@ortodoxtewahedo
@ortodoxtewahedo
"በዓቢይ ጾም ሕይወቱን ያልቀየረ ክርስቲያን በሌሎች አጽዋማት ይቀይራል ለማለት ይከብዳል "

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ

@ortodoxtewahedo
Audio
ፍቅርና ትሕትና /ዘወረደ/ 
                                                  
Size:- 26.9MB
Length:-24:56
       
     በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

@ortodoxtewahedo
መጋቢት ሁለት

በዚህች ዕለት ኦርቶዶክሳውያን ታላቁን ዓቢይ ጾም የሚጀምሩባት የተባረከች ዕለት ነች እና እንኳን በሰላም አደረሰን ያደረሰን አምላክ ከጾሙ ረድኤት በረከት የምናገኝበት ያድርግልን ያጣነውን ሰላም ይመልስልን ።

መጋቢት 2 ታሪክ ሲታወስ በዚህች ዕለት ታላቁ ንጉሠ ኢትዮጵያ አፄ ዮሐንስ ስለ ሀገር ክብር ስለ ዳርድንበር መጣስ ስለ ኢትዮጵያውያን መጠቃት ዘምተው በውጉያ መሀል ሰማዕት ሆነዋል። ዕለቱን ስናስብ ጀግናውን ንጉስ እናስባለን ነፍሰቸውን አምላካችን ከቅዱሳን ማኅበር ይደምርልን ።

@ortodoxtewahedo
ያልመነኑ ሰዎች ከመነኮሱ፤ ክርስቲያን ያልሆኑ ሰዎች ከቀሰሱ፤ እግዚአብሔርን የማያውቁት ሰዎች ካስተማሩ፤ ደመወዝ፣ቤትና መኪና የሚያጓጓቸው ሰዎች ከጰጰሱ፤ ፍትፍት ያልሰለቻቸው ሰዎች ባሕታውያን ከሆኑ፤ የዘር ዛር ያልለቀቃቸው ሰዎች የሁሉ አባት ከተባሉ፤ ከራሳቸው ጋር ያልታረቁ ሰዎች ለታራቂነትና አስታራቂነት ከተቀመጡ፤ የቤተክርስቲያን ፈተናዋ የሀገርም መከራዋ ገና ይቀጥላል።


@ortodoxtewahedo
@ortodoxtewahedo
@ortodoxtewahedo
"ክቡር ሞቱ ለጻድቅ በቅድመ እግዚአብሔር"
" የቅዱሳኑ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው፡፡"
{መዝ 111:-15}

❖ እንኳን ለጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡
☞ጻድቁ አባታችን ሀገራቸው ንሒሳ/ግብፅ/ ሲሆን አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌሲያ ይባላሉ፡፡
ልጅ አጥተው 30 ዘመን ሲያዝኑ ኖረዋል አንድ ቀን አቅሌሲያ ቤተ
እግዚአብሔር ገብታ ከስዕለ ስላሴ ስር ወድቃ ስትማፀን "ክብሩ ከሰማይ
ከፍታ የሚበልጥ ልጅ እንኪ ተቀበይ" የሚል ድምፅ ሰማች፡፡
በዚህም መሠረት አባታችን መጋቢት 29 ቀን ተጸንሰው ታህሳስ 29 ቀን
ተወለዱ፡፡በተወለዱም ጊዜ አፈፍ ብለው ተነስተው "ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ዘአውጻዕከኒ እም ጽልመት ውስተ ብርሃን" ብለው በማመስገናቸውና ኃላም ምድራዊ መብል መጠጥ ሳይመገቡ ሳይጠጡ ለምስጋና ተግተው በመኖራቸው መላእክትን ይመስላሉ፡፡

☞ ሦሰት ዓመት ሲሆናቸው ቅዱስ ገብርኤል ከእመቤታችንና በገነት ካሉ
ቅዱሳን ዘንድ አስባርኮ ገዳማውያን ካሉበት ምኔት ወስዶ ከበሩ አኖራቸው፡፡
አበምኔቱ አባ ዘመደ ብርሃን ምልክት ተነግሮት ቢሄድ ፍሱሃ ገጽ ሆነው
አግኝቷቸዋል፡፡ አሳድጎ አስተምሮ ከማዕረገ ምንኩስና አድርሷቸዋል፡፡
ከዚህ በኃላ ሀብተ ፈውስ ተሰጥቷቸው በአንድ ቀን እልፍ እውራንና ሀንካሳን ፈውሰዋል፡፡

☞ ከዚህ በኃላ ቅዱስ ገብርኤል በክንፉ ነጥቆ ከጌታ ፊት አቀረባቸው፡፡ "
በገድልህ በትሩፋትህ ከሞተ ነፍስ ከርደተ ገሃነም የሚድኑ ብዙ ነፍሳት አሉና ከሰው ተለይተህ ወደ ጫካ ግባ ኑሮህም ከ60 አናብስትና ከ 60 አናምርት ጋር ይሁን አላቸው፡፡ ጌታዬ ምን ተመግበው ይኖራሉ? አሉት፡፡ የረገጥከውን ትቢያ ልሰው ምግብ ሆኗቸው ይኖራሉ ብሏቸው ገዳም ገብተው ከአናብስትና አናምርት ጋር ይኖሩ ጀመር ይታዘዟቸውም ነበር፡፡

☞ በዚህ መልኩ 30 ዓመታት ከቆዩ በኃላ ጌታ በአንድነት በሦስትነት ተገለጾ ምን ላደርግልህ ትሻለህ? አላቸው፡፡ መጀመሪያ ላሉበት መጸለይ ይገባልና የምድረ ገቦታን ሰዎች ማርልኝ አሉት፡፡
3000 ኃጥአንን ከሲዖል አውጥቶ ገነት አስገብቶላቸዋል፡፡ ከዚህ በኃላ ወደ ኢትዮጵያ ሂድ አላቸው፡፡ ቅዱስ ገብርኤል በሰረገላ ነፋስ ጭኖ ምድረ ከብድ አድርሷቸዋል፡፡
ዳግመኛም ወደ ዝቋላ/ደብር ቅዱስ/ ወስዷቸው ከዚያ ሆነው በንፅሐ ልቦና የኢትዮጵያን ሕዝብ ኃጢአት አይተው ከባሕሩ በራሳቸው ቆመው ይጸልዩ ጀመር፡፡

☞ አርባ ቀን ሲሆናቸው መልአኩ መጥቶ "ዝክርህን ያዘከረ ስምህን የጠራ እምርልሃለሁ" ብሎሀል አላቸው፡፡
መላ ኢትዮጵያን ካልማረልኝ አልወጣም ብለው 100 ዓመት ሲጸልዩ ኖረዋል፡፡ ከ100 ዓመታት በኃላ ጌታ "ኢትዮጵያን ምሬልሃለሁ ውጣ" ብሏቸው ወጥተዋል፡፡
ከዚህ በኃላ ምድረ ከብድ ወርደው ከምድር በላይ ከሰማይ በታች ሆነው 7 ዓመት አይናቸውን ሳይከድኑ ጸልየዋል፡፡ ሰይጣን ለምቀኝነት አያርፍምና ቁራ መስሎ መጥቶ አይናቸውን አንቁሮ አሳወራቸው፡፡
ሁለት ሱባዔ ሲፈፅሙ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል መጥተው እፍ
ብለው አድነዋቸዋል፡፡

☞ ከዚያ በዝቋላና በደብረ ቅዱስ/ ምድረ ከብድ/ በንፅህና ፣ በቅድስና፣ በጾም ፣ በጸሎት ፣ በስግደት ተወስነው 262 ዓመታት በኢትዮጵያ ኖረው በተወለዱ 562 ዓመታቸው በተስፋቸው ያመነውን በኪዳናቸው የተማጸነውን ጌታ ከመከራ ስጋ ከመከራ ነፍስ ሊምርላቸው ተስፋቸውን ተቀብለው መጋቢት 5 ቀን በዕለተ እሁድ አርፈዋል፡፡
.
.
❖ የጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ረድኤት በረከት ምልጃ ጸሎት ከሁላችን ሕዝበ ክርስቲያን ከሀገራችን ከኢትዮጵያ ጋር ለዘለዓለም ይኑር አሜን፡፡
<<ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>

@ortodoxtewahedo
Audio
አትፍሩ፤ ልባችሁም አይደንግጥ
        
Size:-18.2MB
Length:-52:09

በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

@ortodoxtewahedo
2024/09/29 07:19:17
Back to Top
HTML Embed Code: