Telegram Web Link
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የእወነት አባት
በረከቶ አትለየን ።

“እናንተ ስሜን የምታቃልሉ ካህናት ሆይ፥ ልጅ አባቱን፥ ባሪያም ጌታውን ያከብራል፤ እኔስ አባት ከሆንሁ ክብሬ ወዴት አለ? ጌታስ ከሆንሁ መፈራቴ ወዴት አለ? ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።”

— ሚልክያስ 1፥6


@ortodoxtewahedo
ማን ነው ባለተራ? ማነው ባለሳምንት?

ልክ ከዛሬ ዓመቱ ትግል በኋላ መጀመሪያ አቡነ ናትናኤል ላይ ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ ተደረገ። ከዚያም ቅዱስነታቸው አቡነ ማትያስ ላይ የተቀነባበረው ድራማ ቀጠለ። በሦስተኝነት አቡነ ኤርምያስ አጀንዳ ተደረገው ተብጠለጠሉ። ከሰሞኑ ደግሞ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ላይ ያነጣጠረው ዘመቻ ተከፍቷል።

የነገሮችን አካሄድ በማስተዋል ለመረመረ ሰው ተከታዩን ባለተራ መገመት አይቸግረውም። በቀጣይ ደግሞ ለሴራቸው አልያም፣ አልጨበጥ ያሉት ብፁዕ አቡነ አብርሃም ላይ እንደሚቀጥል ሳይታለም የተፈታ ነው። የመንግሥት ዋና ዓላማ በቅዱስ ሲኖዶስ አባላት መካከል መለያየትና መከፋፈልን መፍጠር፣ በመጨረሻም በኦርቶዶክሳውያኑ ዘንድ የቅዱስ ሲኖዶስን ቅቡልነት ማሳጣት ነው።

በአጠቃላይ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን በማሳዘንና በማስመረር፣ ተስፋ በማስቆረጥ፣ በረጋ ልብ እንዳያገለግሉን፣ በውድም፣ በግድም ተማርረው ራሳቸውን ከኃላፊነት ስፍራ እንዲያነሡ የማድረግ ዕቅድ ያለው ነው። ደግሞም እነዚህ አባቶቻችን በጥቂት ዓመታት ልዩነት ውስጥ ያለዕድሜያቸው አካላቸው እርጅና እንዲጫነው፣ እያየናቸው ሽበት ሲወርሳቸው፣ ገጻቸው ሲሸበሸብና ከባባድ የስጋ በሽታዎች ሲጠቁም እንደ ልጅ ታዝበናል። እንደ ልጅ እኛ ብናዝንም አብረናቸው ብናነባም፣ እነርሱ ግን እስከሰማዕትነትም የቆረጡ ናቸው።

ነገር ግን እንደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጅነታችን ሰፊውን ምስል ማጤን፣ የነገሮችን አካሄድና አንድምታ አርቀን ልንረዳ ያስፈልጋል። አስቀድመንም የቤት ሥራዎችን መሥራት እንደሚጠበቅብን መገንዘብ አለብን። በተለይም ዘመቻው የዩቲዩብ፣ የቴሌግራም፣ የፌስቡክ... በአጠቃላይ በመንግሥት የዲጂታል ቅጥረኞች፣ የፈጠራ (Deep fake)፣ የአርቴፊሻል አስተውሎት የሚዘወር ዓለም ነውና ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ማርከሻ የሚሆኑ ሥራዎችን ከሥር ከሥር መሥራት፣ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያንና ለብፁዓን አባቶቻችን ጥብቅና ብቻ ሳይሆን ዘብ መቆም ይጠበቅብናል።

@ortodoxtewahedo
እየተደረገ ያለው ቤተ ክርስትያንን በየአቅጣጫው የማዳከም ሴራ ላልገባቹ ይሄ ትልቅ ማሳያ ነው ።

አሁንስ ተገለጠልህ?
በተሰጠን አጀንዳ መፍሰሳችንን ስለሚያውቁ፤ መለያ አልብሰው ነጥብ ለማስጣል በሜዳችን ያሰማሩብናል። ይህ እንዲገለጥልህ ነው! ምን ያህል ቤተክርስቲያንን ለመጣል እየታገሉ እንደሆነ አደንዝዘውህ እንደሆን ነቃ ብለህ ተረዳ።
ፎቶ፦ ቤተክርስቲያን አባቶች ወደ ትግራይ ሲሄዱ እና የሌላ ቤተእምነት ሰዎች ወደ ትግራይ ለመታረቅ ሲሄዱ።
እግዚአብሔር አለ ።

ላልነቃቹ የእውነት አምላክ ማስተዋሉን ይስጣቹ በአራቱም አቅጣጫ ያለን ኦርቶዶክሳዊያን አንድ የምንሆንበት ግዜ ቀርባል እውነት ያሸንፋል ምክንያቱም እውነት እግዘብሔር ነው የአገዛዙ ሴራ ግልፅ ነው ።

@ortodoxtewahedo
ዜና አበው

"እኛ የመነኮስነው ለፍትፍት እንጀራ አይደለም።"
"የቤተክርስቲያን ሕይወት በመስቀል ላይ ስለሆነ ፈተና ይበዛበታል።
ስለዚህ ከግል ሕይወታችሁ በላይ የቤተክርስቲያንን አቋም አጠናክሩ።"
"ቤተ ክርስቲያን ሰው የላትም ሰው ሁኑላት የብረት አጥር ሁኗት ቅዱስ ጊዮርጊስን ሁኑላት።"
ቃለ በረከት

ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ
የቅዱስ ፓትያርኩ እንደራሴ
የመላው ሸዋ ሊቀ ጳጳስ
የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የነበሩ።
1932-1982

የወንጌል ገበሬ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን
እንዲህ እንደዛሬ በፈቃዳቸው ያበዱ ውሉደ መርገም በናኙበት
ተፈሪ ተከባሪ ተናጋሪ እውነት መስካሪ በጠፋበት አስመስሎ መኖር
ነውር ክብር በሆነበት ቅዱስ ፓትርያርኩ በገመድ ታንቀው በነፍሰ በላዎች በተገደሉበት ገዳማት በደከሙበት የቤተክርስቲያንን ሲሳይ በነጠፈበት የእናት ጡት ነካሾች በበዙበት
በጨለማው ዘመን አለኝታ መከታ ይሆኗት ዘንድ ለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የተሰጡ ታላቅ ሐዋሪያ የፓሊተከኞችን ሴራ የባለሥልጣናት ግልምጫ የማያስበረግጋቸው ወንጌል የተጫሙ የእውነት የሐቅ ሞጣሕት የደረቡ ለመንጋው ለሾማቸው ጌታ የታመኑ ዜና ሕይወታቸውን በሰማን ቁጥር ልባችን የሚርድ😭😭
ሰርተው የሚያሰሩ መስለው ሳይሆን ኖረው የሰበኩ
የምናኔያቸውን መአዛ የአራት ኪሎ ውሐ ያልቀየረው ተከብሮ አስከባሪው በዝዋይ በረሐ በወባ ትንኝ እየተነደፉ ብዙ ወራዙትን ለቤተክርስቲያን የሰጡ
የካህናቱ ቀጸላ
የሰባክያኑ ጥላ
የምዕመናን ሾላ
ቤተክርስቲያንን ያገለገሏት እንጂ ያልተገለገሉባት
ድንገት ለወንጌል አገልግሎት በሐዋርያት ሲፋጠኑ በመኪና አደጋ ያጣናቸው ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የማይሞት ስምና ታሪክ ባለቤት።
በረከታቸው ይደርብን እንደዚህ ያሉ አበው መድኃኔዓለም አይንሳን የገዳም መአዛ ያልራቃቸው የአበው ረድኤት የረበባቸው መነኮሰ ሞተን በስራ የሚሰብኩ የራስ ቅላቸው ሳይሆን ልባቸው የመነነ የአባታችን የቅዱስ አባ እንጦንስን አሰረ ፍኖት የተከተሉ በአደባባይ እዮኝ እዮኝ የማይሉ ለቤተክርስቲያን በፈረሰባት በኩል የሚቆሙ የታፈሩ የተከበሩ ተሰሚ ቢናገሩ ተልዕኮ የሚያሰምሩ አበው መነኮሳት ያብዛልን እኛንም ከወሬ ይልቅ ካህን ይፍታን ቀጥኖ ከሚያመነምን ዘመን እግዚአብሔር ይታደገን ከታዘዘ መቅሰፍት ከቁጣው ከመከራው ይሰውረን
አሜን አሜን አሜን ::

@ortodoxtewahedo
4_5902366013483123703.pdf
42.2 MB
#ስንክሳር ዘወርሃ የካቲት

ሰው ሁሉ ለመናገር የዘገየ ለመስማት የፈጠነ ይሁን !

(ያዕቆብ 1፥19)

< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >

#መልካም ቀን

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
መሰረቷ ጉልላቷ እሱ ነው ሙሽራዋም መስቀል ላይ የሞተው ዛሬም ነገም ያውነው ለዘላለም አትንገሩን አዲስ ጌታ የለም

#ሊቀ መዘምራን ቴድሮስ ዮሴፍ

ለመቀላቀል
👉 @ortodoxtewahedo

📔📒📕📗📘📙📙📚📔
📖📖📖📖📖📖📖📖📖

🔥"የዲያቢሎስ ውጊያ"🔥

"የዲያቢሎስ ውጊያ የሚበዛብን በዋነኝነት ስለሦስት ነገሮች ነው።

፩- በስንፍናችን - በጎ ነገርን ከመሥራት ወደኋላ በማለታችን!

፪- በትዕቢታችን - ትዕቢት ውድቀትን ቀድማ ስለምትመጣ የልቡና ዓይናችንን በማሳወር ከኩራት ታስጀምረና ለጥፋታችን ታፋጥነናለች!

፫- በዲያቢሎስ ቅናት - ቅዱሳን አበው እንደሚሉት ይኽ ዓይነቱ ውጊያ የበረከት ነው። 🙏🙏የጌታችንንና የመድኃኒታችንን መንገድ ስንከተል ጠላት ይቃወመናል! ሊጣላንም ይመጣል! የጸኑት እንደ ጻድቁ ኢዮብ ድል ይነሡታል!

📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖

@ortodoxtewahedo
መግለጫ

👉"መንግሥት ቤተክርስቲያንን ደፍሯል
ሲኖዶሱ ይህንን ማውገዝ አለበት"

©በሰሜን አሜሪካ ማኅበረካህናት

@ortodoxtewahedo
😭 በአራዳ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክ
የተፈጸመ ነውር 😭
ጥር 30 ዕለተ ሐሙስ ከምሽቱ 6:00 ሰአት ላይ ያለ ማዘዣና ያለ ዕውቅና ሕግን በተላለፈ መልኩ በቤተክርስቲያኑ ቅጥር ግቢ ውስጥ የየፖሊስና የፌደራል ልብስ የለበሱ ጥይት የታጠቁ አካላት ሰተት ብለው በመግባት ድፍረት የተመላበትን ተግባር ፈጽመዋል
👉 የዕለቱን የጥበቃ አካላት በማስፈራራትና በመዛት "በቤተክርስቲያኑ ውስጥ መሳሪያ ተቀምጧል" በሚል የዲያቆናትና ካህናትን ቤት ሕገ ወጥ በሆነ መልኩ እየበረገዱ ሕጋዊ የሆኑ (የቤ/ክ ሎጎ ያለባቸውን) ባንዲራዎች እያወረዱ በመውሰድ እንዲሁም በአካባቢው ምዕመናን የተገዙ ከ250 ሺ ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸውን የቤ/ክ ሎጎ ያለባቸውን ብዛት ያላቸውን ባንዲራዎች : የታቦት ማሳመሪያ የዲኮር ዕቃዎች በእግር እየረገጡ ክብራቸውን ባዋረደ መልኩ ተወስደዋል
👉 የፖሊስና የፌደራል አካል ነን ብለው የመጡት አካላት ግቢውን በሚያውክ መልኩ ስለገቡ በጊዜው የነበሩ አካላት ወደ አስተዳዳሪው በመደወላ እንዲመጡ ለመደረግ የቻለ ቢሆን የሕግ አካላት ነን ያሉት ግን አስተዳዳሪውን በማዋከብና ለብዙ ዓመታት የቤ/ክ እና የሀገር ቅርስ ያለበትን ሙዚየም ክፈቱ እስከማለት ለመጠየቅ ችለዋል የደብሩ አስተዳዳሪ ግን " ሕዝብና አገልጋዮች በሌሉበት ለዚያውም በዕኩለ ሌሊት አልከፍትም" በማለት አቋማቸውን አሳይተዋል
👉 ይህ የቤ/ክን እና የምዕመናንን ክብር ባልጠበቀና እንደ ወንጀለኛ በዕኩለ ሌሊት መፈጸሙ ነውር ሆኖ ሳለ በካህናትና ዲያቆናቱ ላይ የተፈጸመው እንግልት ደግሞ እጅጉን አሳፋሪ ነበር በጊዜውም የነበሩ የአይን ምስክሮች እንደነገሩን አንዳንድ ካህና በተፈጸመው አዝነው አምርረው እስከማልቀስ ደርሰዋል
👉 በቀጣይነትም ዳግም ይህ ነገር ለመፈጸሙ ምንም ዋስትና ስለሌለን የቤ/ክኑ አስተዳደር አካል ; የሰ/ት/ቤቱ አመራር ; የአካባቢው ወጣትና ምዕመናን በጋራ በመሆን ጉዳዩን በባለቤትነት የፈጸሙት አካላት የወሰዷቸውን ንብረቶች እንዲመልሱና የፈጸሙት የቤ/ክንን ክብር የተላለኀ መሆኑን እስከ ሚመለከት አካል ሔደው ሊጠይቁ ይገባል
👉 አሁን ላይ ማንም እየተነሳ መሳሪያ አንግቦ ሕገ መንግስቱን በተጻረረ መልኩ ቤ/ክ ድረስ ገብቶ የፈለገውን ነገር እያደረገ ነገም ካህናት ብቻ የሚነኩትን ቅዱሱን ታቦትና ንዋየ ቅዱሳቱን ላለመንካቱ ምንም ዋስትና የለንም
👉 የደብሩ አስተዳደር የሰንበት ት/ቤቱ አመራርና አባላት የአካባቢው ወጣቶችና ምዕመናን በሀላፊነት ከመላው ምዕመን ጋር የተፈጸመውን ተግባር አውግዘን የተወሰዱ ንብረቶች ተመልሰው የተፈጸመውን ተግባር ልንጋፈጥ ይገባናል

👉 ስለ አራዳ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክ ያገባኛል 💒

@ortodoxtewahedo
2024/09/29 21:24:21
Back to Top
HTML Embed Code: