Telegram Web Link
#27 ❤️

"ወዳጄ ሆይ ሮማውያን ወታደሮች ጎንጉነው በጌታችን እራስ ላይ እሾህ እዳቀዳጁት ባሰብህ ጊዜ እጅግ ማዘንህ አይቀርም ። ሆኖም አንተም እሾህ የተባለውን አንድ ኃጢአት በሰራህ ቁጥር በጌታችን ላይ የተደፉትን እሾኾች ቁጥር እንደጨመርህ አስብ ።በፈጣሪ የማያምኑት ሮማውያን ወታደሮች ከጎነጎኑት እሾኽ በላይ የጌታችንን እራስ የበለጠ ዘልቆ የሚወጋው ደሙን አፍስሶ ያዳነን እኛ ክርስቲያኖች በኃጢአታችን የምንጎነጉነው የእሾኽ አክሊል ነው ።{ስለመተላለፋችን የቆሰለው አምላክ በመተላለፋችንም ይቆስላል ።!}

{በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን ከሚለው ርዕስ የተወሰደ )

[ ሕማማት]
{በዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ}

መድኃኔዓለም ሆይ አባት ሆይ ይቅር በላቸው በማለት በታላቅ ቃል በመስቀል ላይ ፥ ለተናገረ ቃልህ ሰላም እላለሁ በመስቀል ላይም በሰቀሉህ ጊዜና ጎንህን በጦር በወጉ ጊዜ አንዳችም የተቃውሞ ትንፋሽ ላልተነፈሰ እስትንፋስህም ሰላም እላለሁ ።
መድኃኔዓለም ሆይ ጻድቃንን ያይደለ ኃጥአንን ለማዳን በራሱ ደም ራሱ ለተጥለቀለቀ ስነ መልክህ ሰላም እላለሁ !

( መልክአ - መድኃኔአለም )27

@ortodoxtewahedo
🔴 መድኃኔአለም 🔴
✍️✍️✍️
መድኃኔአለም ማለት አለምን ያዳነ የአለም መድኃኒት ማለት ነው። ሰው በመበደሉ ምክንያት ከክብር ተዋርዶ ይኖር ነበር።ኢየሱስ ክርስቶስ ግን የተዋረደውን ሰው እርሱ በመስቀል ተሰቅሎ ወደ ቀድሞ ክብሩ መለሰው። ምን አይነት ፍቅርነው?????
ወንድሜ /እህቴ አስባችሁታል ግን እኛን ለማዳን ብሎእኮ ነው

የተሰቀለው፡ራቁቱን በመስቀል ምን ያህል
አሳፋሪ እንደሆነ እናውቀዋለን
ጌታ ግን እኛን ለማዳን ብሎ መስቀሉን ናቀው።
በፈጠራቸው ፍጥረት ተተፋበት።
እኛን ትእግስት ሊያስተምረን እነርሱን ማጥፋት
እየቻለ እርሱ ግን

💖በፍቅር እያዩ የማያውቁትን አያውቁምና
አባት ሆይ ይቅር በላቸው ይል ነበር።
ክርስቶስ እኛን ለማዳን ሲሰድበት
አልተሳደበም ሲንቁት አልናቃቸውም
ሲታበዩበት ሁሉ እርስ ግን በትህትና ያያቸው ነበር።

💖ታዲያ እኛ ደግሞ እራሳችንን ለማዳን ሰዎች ሲንቁን ሲሰድቡን ሲታበዩን በፍቅር በዝምታ ማለፍ ይጠበቅብናል።
ይህን ካደረግን የክርስቶስ ደቀ መዝሙር እንባላለን።
በ 5 ችንካር ነበር የቸነከሩት።

በመስቀል የተገኙ ድንግል ማርያም ሐዋርያው ዮሐንስ ነበሩ። አንተም በመስቀሉ ስር
ለመገኘት ከፈለግህ ትእግስትን ፍቅርን ትሕትናን ገንዘብ አድርግ።

መድኃኔአለም በቸርነቱ ይቅር ይበለን።


@ortodoxtewahedo
ሰንበት ተማሪዎች የነገዋ ቤተ ክርስትያን ተስፋዎች ናቸው ።

አቡነ ጎርጎርዮስ

ወጣቱን በቤተ ክርስትያንን ስርዓት ከማስተማር ጀምሮ ተተኪ ካህናትን እያፈሩ አስከ ጵጵስና ድረስ የደረሱ ሰንበት ተማሪዎች አሉ በሰንበት ትምህርት ቤት ያልገባን ልንገባ ያሰብን እንግባ ቤተ ክርስትያንን እንወቃት ክርስትናን እንኑረው ።

@ortodoxtewahedo
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
አሜን

☑️ #አማኑኤል

አማኑኤል ማለት

🎚አማኑ ኤል፣ አማነ ኤል፣ የአምላክ ሰላም፣ የእግዚአብሔር እርቅ፣ የጌታ አንድነት ማለት ነው።

🎚«አማነ»እና «ኤል» ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።

አማኑኤል ማለት

🎚«እግዚአብሔር ከእኛ
ጋር» ማለት ነው።

🎚ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ (በዕብራይስጥ: ישוע ፣ ዮሹዓ) ሲሆን «ዮ» የያህዌህ ምህፃረ ቃል ሲሆን «ሹዓ» ደግሞ «አዳኝ መድኃኒት» ማለት ነው።

🎚ይህም «እግዚአብሔር አዳኝ መድኃኒት ነው» ማለት ነው፤ ክርስቶስ ማለት በግሪክ ቋንቋ
ነው፤ ይህም መሢሕ በዕብራይስጥ ማሺያሕ ወይም«የተቀባ ንጉሥ»ማለት ነው።

🎚ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተጠመቀው በ5531 ዓመተ ዓለም ዘመነ ሉቃስ ማክሰኞ ጥር 11 ቀን ከሌሊቱ በ10ኛው ሰዓት ነበር፡፡
ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 19

🎚በተጠመቀም ጊዜ ዕድሜው 30 ዓመት ከ13 ቀን ነበር፤ ስብሐት ለከ አምላኪየ፤ አምላኬ ሆይ በራስ ፀጉሬ ቁጥር ምስጋና ይገባሃል።

🎚ፈጣሪዬ ሆይ፤ በአጥንቶቼ ቁጥር ምስጋና ይገባሃል፤ ጌታዬ ሆይ በሚታየው ሁሉ ቁጥር ምስጋና ይገባሃል።

🎚ንጉሤ ሆይ፤ በማይታየውም ቁጥር ሁሉ ቁጥር ምስጋና ይገባሃል።

🎚ለሦስትነትህንም ምስጋና ሁልጊዜ አፌ ይናገራል፤ እምኩሉ ይሄይስ፤ ጌታዬ ኢየሱስ ሆይ ከሁሉ ይልቅ በሦስትነትህ መታመን ይበልጣል።

🎚አንተን በወለደችህ በማርያም መማፀን መልካም ዕድል ነው፤ ፈጣሪያ ክርስቶስ ሆይ ከቤተ መንግሥትና ከቤተ ክህነት ወገን የአንተን ሰው መሆን የሚጠራጠር ወይም አምላክ ሰው፤ ሰው አምላክ መሆኑን የሚክድ ቢኖር እመቀ እመቃት መንጸፈ ደይን ወርዶ ይንኮታኮት።

ክብር፣ ኃይል፣ ምስጋናና ውዳሴ ለቅዱስ ስም አጠራሩ ይሁን ነው ለዘለዓለሙ።

In the name of the Father, the Son, the Holy Spirit, the One God
Amen

☑️ #Emanuel

Emanuel means

🎚 Amanu El, Aman El, means God's peace, God's reconciliation, God's unity.

🎚 It is a name based on two words "Amane" and "El".

Emanuel means

🎚 "God from us
"with".

🎚Our Lord and Savior is Jesus Christ (Hebrew: ישוע, Joshua) and "Yo" is the abbreviation of Yahweh and "Shu'a" means "Saviour, Medicine".

🎚 This means "God is the Savior and Medicine." Christ means in Greek
it is; This means Messiah in Hebrew Mashiach or "Anointed King".

🎚 Our Lord and Savior Jesus Christ was baptized in the year 5531 AD Luke on Tuesday January 11th at 10 o'clock in the night.
Justice Article 19

He was 30 years and 13 days old when he was baptized. Good morning worshiper. O God, I thank you for the number of my hairs.

🎚 O my creator; You deserve thanks for the number of my bones. O Lord, you are worthy of praise in every number that appears.

🎚 O my king; You deserve thanks for every invisible number.

🎚 My mouth always speaks thanks to your trinity; This is what I mean. Lord Jesus, it is better to trust in your Trinity than anything else.

🎚 It is good luck to pray to Mary who gave birth to you. Creator Christ, who doubts whether you are human or God-man from the side of the palace and the church; If anyone denies that man is God, let him come down and crush him.

Glory, power, thanks and praise be to the Holy Name forever.

@ortodoxtewahedo
#አማኑኤል 28

#እግዚአብሔር ከኛ ጋር ሆነ

እኛ ከእርሱ ጋር መሆን ቢያቅተን እርሱ ከእኛ ጋር ሊሆን ልዑል ባህርዪን ዝቅ አድርጎ ከእኛ ጋር ሆነ። በባህርያችን ጎስቁለን የተፈጠርንለትን አምላካዊ መልክ ብናጎድፈው የሰውን አእምሮ በሚፈታተን የተዋህዶ ምስጢር እርሱ ሰው ሆነ።

እኛ አምላክን ወደ መምሰል ከፍ ማለት ቢያቅተን ይህን ክፍተት ያደላድል ዘንድ አምላክ ሰው ሆነ። ሰማያትን እንደ መጋረጃ የሚጠቀልላቸው እርሱን በጨርቅ ጠቀለሉት። ከአለት ውሀን ያፈለቀው አምላክ ከእናቱ ጡትን ለምኖ አለቀሰ።

በላይ ያሉ መላእክትን የሚልካቸውን ንጉስ ማርያምና ዮሴፍ ውሀ ለመቅዳት፣እንጨት ለማምጣት ላኩት።እርሱም በፍቅር ተላካቸው። ከመቅደሱ አገልጋዮች ይልቅ የተናቁትን ሰዎች ሐዋርያት አድርጎ መረጣቸው።

ከቀራጮችና ከሐጢአተኞች ጋር ተቀመጠ።ከእነርሱም ጋር በላ ጠጣ። ሰዎች የተፀየፋቸውን በመቃብር ስፍራ የተጣሉት በምህረቱ ጎበኘ። ከሰርገኞች ጋር ተደሰተ።

ከኀዘንተኞችም ጋር አለቀሰ። እስከመጨረሻም ከእኛ ጋር እንደሆነ እንረዳ ዘንድ የእኛን የሞት ፅዋ ተጎነጫት። መስቀል ላይም ከወንበዴዎች ጋር ተቆጠረ።

በሲኦልም አልተወንም።ከእኛው ጋር ነበር።በገነት መቆየት ያልቻለውን አዳም እስከ ሲኦል ተከተለው። ከዚያም አውጥቶ ወደ ቀደመ ክብሩ መለሰው።

"ከፍ ባልሁ ጊዜ ሁሉን ወደ እኔ እስባለሁ" ያለ አምላክ እኛነታችንን ከእርሱ ጋር ከፍ አድርጎ በዘለዓለማዊ ክብር በአብ ቀኝ አስቀመጠው። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ የተባለውም ተፈጸመ።

እኛም ከእርሱ ጋር ለመሆን ያብቃን!!

#መልካም ቀን

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo

📖📖📖📖📖📖📖📖📖
ብፁዕነታቸው ተገድደው እንዲመለሱ ተደርገዋል

"ትኬት አዘጋጅተው ሰጡኝ። በዚህ በመጡበት ኤምሬትስ አየር መንገድ ይመለሱ አሉኝ።" በማለት ብፁዕነታቸው ሒደቱን አስረድተዋል።

የመግቢያ ሰነዳቸው ምንም ጉድለት ሳይኖርበት "የዕድሳት ጊዜው አልፏል። በዚህ መግባት አይቻልም።" የተባሉ ቢኾንም "ገና ኹለት ዓመት ጊዜ አለው እኮ አንብበው" ያሉት የኢሚግሬሽን ኃላፊ "በቃ አይገቡም ይመለሳሉ ከበላይ ታዝዣለሁ" ማለቱ ታውቋል።

ወደ ሀገራቸው በክብር የሚመለሱበት ቀን ግን ሩቅ አይደለም።

@ortodoxtewahedo
ትዕቢት ውድቀትን ትቀድማለች!!!

ጥር በየዓመቱ ቤተክርስቲያን ላይ ብዙ ካርዶች ተመዘዙ ደግሞም የቤተክርስቲያን አምላክ እያከሸፋቸው ነው።

ዛሬ ደግሞ ካርዱ በብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ ላይ ተመዟል። ብፁዕነታቸው ህጋዊ ሰነድ ይዘው፣ የቤተክርስቲያኒቱ መሪ መሆናቸው እየታወቀ፣ የ60 ሚሊዮን ኦርቶዶክሳዊ አባትነታቸው ቀርቶ አረጋዊነታቸው ክብር ሳይሰጠው በጎረምሳ ጉልበት ወደ ሀገራቸው ሳይገቡ እንዲመለሱ ተደርገዋል።

ይህ ሊያሳፍር የሚገባው ተግባር በሆድ አምላኪዎቹ ዘንድ ጮቤ እያስረገጠ ነው።

ይሁንና "ቤተክርስቲያንን ከማሸነፍ ፀሐይን ማጨለም ይቀላል!" እንዲሉ ይህ እብሪት በኦርቶዶክሳዊ ጥብዓት ተመክቶ ይሰክናል።

"የመውጊያውን ብረት ብትረግጥ ለአንተ ይብስብሃል"

#ኢንፈርህሞተ
#ሞትንአንፈራውም

@ortodoxtewahedo
የሐዋ•፱÷፭
የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል ።


“ወደ እናንተ ልንመጣ ወደን ነበርና ... ሰይጣን ግን አዘገየን”
(1ኛ ተሰሎንቄ 2፥18)

የሚዘገይ እንጂ የሚቀር ነገር የለም...!

@ortodoxtewahedo
አንዳንድ ነጥቦች በብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ወደ ሀገራቸው እንዳይገቡ መከልከል ዙሪያ፦

1. ለዚህ አሳዛኝ ድርጊት የተቀነባበረ ሽፋን በቅርብ ሲሰጥ እንደምንሰማ የታወቀ ነው። በመንግሥት አካላት ተደርሶ የሚቀርበው ድራማና ዶክመንተሪ አያልቅምና ያልሠሩትን ወንጀል ሲያሸክሟቸውና ሲያጥላሉዋቸው እንሰማ ይሆናል። ስለዚህም ከሚዲያ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ልሳን የሆኑ ሚዲያዎችን ብቻ እንከታተል።

2. መንግሥት ይህን መሰል አንገት ሰባሪና ድፍረት የተሞላበት ድርጊት ሲፈፅምም ብፁዕነታቸው ያሉበትን ኃላፊነት ከግምት አላስገባም። ክብራቸውን የሚወክሉትን ቤተ ክርስቲያንና ሕዝባቸውን አላከበረም። በዚህ ጸያፍ ድርጊቱ እርሳቸውን ብቻ ሳይሆን መላውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አማኝን እንዳሳዘነ መታወቅ አለበት።

3. ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ፓትርያርኩን ሸክም ጎንበስ ብለው የሚሸከሙ አባት ናቸው። የዛሬው የመንግስት ድርጊት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስን ከሜዳው በማግለል የቅዱስ ሲኖዶስን ማዕከላዊነት የመናድ ሙከራ ነው።

4. ብፁዕነታቸው በእምነታቸው የማይደራደሩ ታላቅ አባት ሲሆኑ እርሳቸውን ወደ ሀገራቸው እንዳይገቡ የማድረግ ርምጃ የቤተ ክርስቲያንን በር የበግ ለምድ ለለበሱ ተኩላዎችና ለእንደ ልቡዎች ክፍት የማድረግ ዕቅድ አካል ነው። ከዚያም ውጪ ሌሎች ውጪ የሚኖሩ አበው ብፁዓን አባቶችንም አፍ የማስያዣ አካሄድ ነው።

5. በሌላ በኩል በውጪ ያሉ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ቁጣቸውን ማሳደር አለባቸው። ምክንያቱም መንግሥትም ሆነ ሕገ ወጥ አካላት በተለያዩ ሚዲያዎች በኩል ይህን ነገር እያራገቡ ጫና ፈጥረው ሌላ ሲኖዶስ እናቋቁም የሚል ሀሳብ እንዲፈጠር መሥራታቸው አይቀርምና በዚህ በኩል ረጋ ብሎ መጠንቀቅ ተገቢ ነው። ተተኪ ጸሐፊ ይመረጥ የሚል ሤራ እንዳይሸርብም ነቅቶ መጠበቅና መሥመር ማስያዝ እንደሚገባው ሳይረሳ!!

6. ይህ ድርጊት ቤተ ክርስቲያንን ለመከፋፈል የታሰበ እቅድ ነው። ስለዚህም እንደ ምእመን በበለጠ የቤተ ክርስቲያን አንድነት ላይ ማተኮርና ቤተ ክርስቲያናችንን በንቃት መጠበቅ አለብን።

7. ይሄ ጉዳይ መሥመር እንዲይዝ የሚያደርጉ አባቶችን በሚያስፈልጋቸው ሁሉ ማገዝና ትዕዛዛቸውንም እንደ ልጅ መፈጸምም ይገባናል።
ልዑል እግዚአብሔር ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ይጠብቅልን

#ኢንፈርህሞተ
#ሞትንአንፈራውም
ብርሃኑ ተ/ያሬድ


@ortodoxtewahedo
- የተወሰነ ቀን ፌስቡክ ላይ እንንጫጫለን
- ፕሮፋይል የሚያማምር ፖስተር ሠርተን እንለቃለን
- ከዛ ሲኖዶስ አነቃቂ ንግግር በተመላ መልኩ መግለጫ ያወጣል
- የተወሰነ አገልጋይ ይታሠራል ከዛ ከርሞ ይፈታል
.... ሁልጊዜ ከፋከራ ያልወጣን ተግባር ላይ ዜሮ የሆን የክፍለ ዘመኑ አሳዛኝ ሆነናል
ገና ያኔ ካህን በአደባባይ በድንጋይ ተቀጥቅጦ ሲገደል ያልነቃን ኤርፖርት ቢከለክሉ አይደንቅም ! እንዲሁ በመግለጫ በፋከራ እንሰነብታለን አንደራጅ አናቅድ በሚዲያ ተጽዕኖ ተጽናንተን ከሳምንት የማናልፍ ሆነናል መሬት የወረደ ሥራ ካልሠራን ከዚህም የባሰ ገና ይጠብቀናል

ኢዮብ ዘገነተ ፅጌ

@ortodoxtewahedo
2024/09/29 23:17:44
Back to Top
HTML Embed Code: