Telegram Web Link
ህይወትህን በሙሉ ለምድራዊ ነገር አሳልፈህ ከሰጠህ ምድር መቃብርን ትሰጥሃለች፤ ነገር ግን ህይወትህን ለመንግስተ ሰማያት አሳልፈህ ብትሰጥ ግን መንግስተ ሰማያት ዙፋንን ትሰጥሃለች።

👉 ምክረ አበው

@ortodoxtewahedo
የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻና ግብረ ሰዶማዊነትን አስመልከቶ እየተደረጉ ያሉ ሁለገብ ተጽእኖዎችንና መመሪያ የማስለወጥ ማግባባቶችን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ፤

@ortodoxtewahedo
“ወለእመቦ ዘሰከበ ምስለ ተባዕት ከመ አንስት ርኵሰ ገብሩ ክልኤሆሙ …ወጊጉያን እሙንቱ..ማንኛውም ሰው ከሴት ጋር እንደሚተኛ ከወንድ ጋር ቢተኛ ሁለቱ ጸያፍ ነገር አድርገዋል።
ደማቸውም በላያቸው ነው "(ዘሌ.፳ ፥፲፫)ግብረ ሰዶማዊነት በሕገ ተፈጥሮም ሆነ በሰው ልጅ ሰብአዊ አኗኗር ፈጽሞ ተቀባይነትየሌለው፣ዓለምንበልዩ ጥበብ በፈጠረ አምላክ ፈቃድ፣መለኮታዊ ሥርዓቱ በተገለጠባቸው ቅዱሳት መጻሕፍት ፈጽሞ የተከለከለ፣በቀኖናተ ቤተክርስቲያን፣ በፍትሕ መንፈሳዊና በፍትሐ ብሔር ድንጋጌዎች፣በሥነ ልቦና ደንቦች የተወገዘ፣ሥነ አእምሮዊ ሚዛንን የሚያዛባ፣ግለሰባዊ  ማንነትንና ማኅበራዊ ትሥሥርን የሚያናጋ የረከሰ ተግባር ነው፡፡

ግብረ ሰዶማዊነት በቅዱሳት መጻሕፍት እንደተገለጸው ለአንድ ሀገርና ሕዝብ ከነጎረቤቶቹ መጥፋት ምክንያት የሆነ ተግባር ሲሆን የሰዶምና ገሞራ በመቅሰፍተ እሳት መቃጠል ከእነርሱ መቀጣትም  አልፎ ላለውና ለመጪው ትውልድ አስተማሪ የሆነ ምልክት እንዲሆን ነው።

መጽሐፍ ቅዱስም ግብረ ሰዶማውያን የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም በማለት የግብሩን አስከፊነት፣
በማኅበረ ሰብእ ላይም የሚያመጣውን ጥፋት
በአጽንዖት ይነግረናል: (ሮሜ ፩፳፮ ፩ቆሮንቶስ ፮፱፣I፣)
ይህንንም ግብረ ርኩሰት ቅዱሳት መጻሕፍት በተለያየ ሥያሜ ጠርተውታል፤ከእነዚህም ርኩሰት፣ ጸያፍ፣ ትልቅ ኃጢአት፣ በደልና አመጻ የሚሉት ቃላት ይገኙበታል፡፡ (ዘሌ ፲፰-፳)
የኃጢአተኛውን ሞት የማይሻው እግዚአብሔር ሌሎች ሕዝቦች በሚበድሉበት ጊዜ በዕዶምና በገሞራ የደረሰውን ጥፋት እየጠቀሰ ከጥፋታቸው እንዲመለሱ ማስጠንቀቁን በቅዱሳት መጻሕፍት በሰፊው ተመዝግቦ ይገኛል፡፡(ኢሳ፫÷፱፣ኤር፶÷፵፣ ሰቆ ኤር ፬÷፮፣ ሕዝ ፲÷፵፱፣ አሞ ፬÷፲፩፣ ማቴ ፲÷፲፭፣ ፪ ጴጥ ፪÷፮)በመሆኑም ቅድስት ቤተክርስቲያን ማንኛውም በጾታ ተፈጥሯዊ ስጦታ ላይ የሚሠራ ኃጢአት ሕገ ተፈጥሮን የሚጻረር ጽኑዕ በደል እንደሆነ ታስተምራለች፡የያዕቆብ ወንድም ይሁዳም “እንደ እነርሱ ዝሙትን ያደረጉና ሌላን ሥጋ የተከተሉ ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸውም የነበሩ ከተማዎች በዘላለም እሳት እየተቀጡ ምሳሌ ሆነዋል” በማለት ይህ ተግባር የተወገዘና በዘላለም እሳት የሚያስቀጣ መሆኑን አስረግጦ ይናገራል።

ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ግብረ ሰዶማዊነትን የምትቃወመው ተፈጥሮዋዊ ስላልሆነ ብቻ ሳይሆን በብሉይ  ኪዳንም ሆነ በሐዲስ ኪዳን ትምህርት በእግዚአብሔር ዘንድ የረከሰ፣ተቀባይነት የሌለው፣ ኃጢአት በመሆኑ ነው፡

ጌታችንም ሲያሰተምር “ፈጣሪ በመጀመሪያ ወንድና ሴት አደረጋቸው"በማለት ጾታ የፈጣሪ ሥጦታ መሆኑን እና ይህንም መጠበቅ ግዴታ እንደሆነ ያስረዳል፡ (ማቴ፲፱÷፲፭) ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ግብረ ሰዶማዊነት አጸያፊ ድርጊት መሆኑን
“እግዚአብሔር ለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ሴቶቻቸውም ለባሕርያቸው የሚገባውን ሥራ ለባሕርያቸው በማይገባው ለወጡ እንዲሁም ወንዶች ደግሞ ለባሕርያቸው ሴቶችን መገናኘት ትተው እርስ በርሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ፤ ወንዶችም በወንዶች ነውር አድርገው በስሕተታቸው የሚገባውን ብድራት በራሳቸው ተቀበሉ የሚገባውን እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው"በማለት ገልጾታል፡፡

ቅድስት ቤተክርስቲያንም ጾታዊ ግንኙነት ወይም የተቀደሰ ጋብቻ በተቃራኒ ጾታዎች ብቻ የሚፈጾም እንዲሆን የምታስተምረው ከዚህ የተነሣ ነው፡(፩ ቆሮ ፯፡፪፣ ፩ ጢሞ ፩፡፱)ግብረ ሰዶማዊነት የሰውን ልጅ ተፈጥሯዊ ማንነት የሚንድ፣መሠረተ እምነትንና ቀኖናን የሚሽር፣ማኅበራዊ ዕሴት  የሚያጠፋ፣ ከሥነ ምግባር መገለጫዎች በአሉታዊ ገጽ የቆመ፣ሕሊናን የሚያውክ ለትውልድ ጥፋት፣ለሀገር መውደም ምክንያት የሆነ አጸያፊ ተግባር ነው፡፡

በመሆኑም ቅድስት ቤተክርስቲያን ይህን ተግባር የሚፈጽሙ ሰዎች ወደ ንሥሓና ድኅነት እንዲመጡ፣ ከሥጋና ከመንፈስ ስብራት እንዲፈወሱ ዘወትር ጥሪ ታደርጋለች እንጅ ማንም ሰው የኃጢአቱ ወይም የርኩሰቱ ተባባሪ እንዲሆን
አትፈቅድም።

በ፲፱፻፺፮ በወጣው የሀገራችን የወንጀል ሕግ ክፍል፪ አንቀጽ ፮፻፳፱ ጠቅላላ ድንጋጌ “ግብረ ሰዶምና ለንጽሕና ክብር ተቃራኒ የሆኑ ሌሎች ድርጊቶች, በሚለው ንዑስ አንቀጽ ርእስ ሥር ይህ ድርጊት ወንጀል ስለሆነ በትክክል የሚያስቀጣ መሆኑን አስቀምጧል። በተለይ አንቀጽ ፮፻፴፩ዕድሜያቸው ፲፰ ዓመት ያልሞላቸው ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች ላይ ለሚፈጸም ግብረ ሰዶማዊነት ከ፭ እስከ ፳፭ ዓመታት የሚያስቀጣ መሆኑ በግልጽ ተጽፏል።በተሻሻለውም የሀገራችን የቤተሰብ ሕግ በአንቀጽ 13 መሠረት የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ በሕግ የተከለከለ መሆኑ ተደንግጓል፡፡

ይሁን እንጅ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይህን ተግባር በግልጥ በሕገ መንግሥታቸውና በልዩ ልዩ ማኅበራዊ ድንጋጌዎቻቸው እንደ ጥሩ ነገርእንደ ፍትሐዊነትና አካታችነት በመቁጠር በይፋ የደነገጉ የምዕራቡ ዓለም ሀገራት መኖራቸው ግልጽነው።

እነዚሁ ሀገራት ያላቸውን የፖለቲካና የኢኮኖሚ አቅም መከታ በማድረግ በእምነታቸው፣በባሕላቸው በማኀበራዊ
መገለጫቸው ይህን አጸያፊ ድርጊት ፈጽመው በማይቀበሉ የአፍሪካና የምሥራቁ ዓለም ሀገራት ላይ ቢቻል በማግባባት፣
ካልሆነም የፖለቲካና የኢኮኖሚ ጫና በማሳደር እንዲቀበሉ የጥፋት ልማዳቸውን እንዲጋሩ ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉትን ድብቅና ግልጽ እንቅስቃሴዎች ቋሚ ሲኖዶስ በጽኑ ይቃወማል፡፡

ይህ ግብረ ርኩሰት በዘመናችን ተቀባይነት እንዲኖረው፣
የሚደረጉ ሁለገብ ማግባባቶች፣ተጽዕኖዎችና ተያያዥነት ያላቸው ስምምነቶች በሀገራችን መንግሥት ተቀባይነት አግኝተው እንዳይፈጸሙ ቋሚ ሲኖዶስ በጥብቅ ያሳስባል።

ከመገናኛ ብዙኃንና ከሌሎችም የመረጃ ምንጮች ለማወቅ እንደተቻለው ግብረ ሰዶማዊነትንና ተያያዥነት ያላቸውን ተግባራት የንግድ፣የፖለቲካ፣የኢኮኖሚ፣የፍትሕና የሰብዓዊነት ግንኙነቶች አካል በማድረግ በቃላትና በዓረፍተ ነገሮች ውስጥ አስርጎ በማስገባት አሣሪ ስምምነቶች እንዲፈጸሙ ለማድረግ ያለው ሃደት በአፋጣኝ እንዲፈተሽ የሀገራችን መንግሥት ብሎም የአፍሪካ መንግሥታት የአህጉራችንን ሃይማኖታዊ ማኅበራዊና ሥነ ልቦናዊ ዕሴቶች አስጠብቀው እንዲቀጥሉ ቋሚ ሲኖዶስ ጥብቅ የሆነ የአደራ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

በስምምነቱ ሰነድ ጤናማ መስለው የሠረፁ ዐረፍተ ነገሮች ውስጥ እንደታየው በጾታና ሥርዓተ ጾታ መብት፣ የሥርዓተ ጾታ ትምህርት ጋር በማያያዝ ጾታን በቀዶ ጥገና የመቀየር ውርጃ፣ልቅ የሆነ የተመሳሳይና ተቃራኒ ጾታ ግንኙነትን መፍቀድ፣ግለሰቦችን እና ማኅበረሰብን መረን በማድረግ ውስብስብ ለሆኑ ሃይማኖታዊ፣ ማኅበራዊና ባህላዊ ችግሮች የሚዳርጉ መሆናቸውን ቅዱስ ሲኖዶስያምናል።

በመሆኑም በብዙ መስዋዕትነት ተጠብቆ የቆየው እምነት፣የባህልና የሥነ ምግባር ማኅበራዊ ዕሴት የክብር ስፍራውን ይዞ እንዲቀጥልና በእጅ አዙር ቅኝ ግዛት ኃጢአትንና ርኩሰትን አባብሎ በማስረጽ፣ለዚህ አጸያፊ ድርጊት ትውልዱ እንዳይጋለጥ የሚመለከተው ሁሉ በልዩ ጥንቃቄ እንዲመለከተው ቋሚ ሲኖዶስ ጥሪውን ያስተላልፋል።

ግብረ ሰዶማዊነት በማንኛውም የቃላት አግባብ ተገልጦ በጾታ መብት መካተት የማይችል የመደበኛ ተፈጥሯዋዊ ክስተት ጋር በጭራሽ አቻ የማይሆን በመሆኑናተግባሩንምመቃወም ቤተክርስቲያናችን መንፈሳዊ ተልእኮዋ ስለሆነ ይህን አስመልክተው የሚደረጉ ስምምነቶች የሀገራችንን ሃይማኖታዊ፣ማኅበራዊና ሥነ ልቦናዊ ዕሴት የሚጥሱ መሆኑ ታውቆ ሁሉም ዜጎች እንዲቃወሙት፣የፈዴራል መንግሥትም ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እንዲከታተለው ቋሚ ሲኖዶስ በጥብቅ ያሳስባል፡፡

@ortodoxtewahedo
Forwarded from LikeBot
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን !!!

እንኳን ለቅድስት ሥላሴ በዓል እንዲሁም ለሌሎች ቅዱሳን መታሰቢያ በዓል በሰላም በጤና አደረሳችሁ፤ አደረሰን።

የአብርሐምን ቤት የባረኩ ሥላሴ እኛንም በህይወታችን በኑሮዋጭን በአገልግሎታችን በትዳርአችን በትምርታችን በሥራችን ይባርኩን ።

ሥሉስ ቅዱስ ለሚታምን ሁሉ እምነትን በረከትን ሀገራችን ኢትዮጽያን ሰላም ያድርጉልን አሜን ::

#መልካም እለተ ይሁንልን

#መልካም ቀን

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
.
🌼"ከሄድክ እንጦንስ ትባላላለህ ከቀረህ ደግሞ አባ
እንጦንስ ትባላለህ " 🌼
አንድ ጊዜ አባ እንጦንስ ከቁስጥንጥኒያው ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ቁስጥንጥንያ እንዲመጣ መልዕክት ደረሰው። ልሂድ ወይስ ልቅር በሚለው ሀሳብ ውስጥ እያለ ረድኡን "ምን ትመክረኛለህ" ሲል ጠየቀው። ያም ረድእ "ከሄድክ እንጦንስ ትባላላለህ ከቀረህ ደግሞ አባ እንጦንስ ትባላለህ " አለው።አባ እንጦንስም ምክሩን ተቀብሎ ቀረ።
ክርስቲያን ስትሆን ወንበርህን መለየት ይኖርብሀል ከፌዘኛ ፍልስፍና ወንበር ከዋዘኛ የመናfkan መንበር ከማይጠቅም የእንቶ ፈንቶ ዙፋን መራቅ ይኖርብሀል ከማይመስሉህ ጋር ከሄድክ እገሌ ይሉሀል ብትርቅ ግን አባ ይሉሀል ሰው በጠባዩ ባወቀህ ልክ ይሰለችሀል የክብሩ መጠን ይቀንስበታል ያቀልሀል አንተ በመንበሩ ፊት የምትቆም አገልጋይ እስከሆንክ ድረስ ከመጠንህ ልትወርድ አይገባም መጠንህም ክርስትና ነው ነገር ግን ፌዝና ቀልድ በበዛበት ምግባር በቀለለበት በማይጠቅመው ስፍራ አትሂድ ምክንያቱም "ከሄድክ እንጦንስ ትባላላለህ ከቀረህ ደግሞ አባ እንጦንስ ትባላለህ "
ወንበራቸውን የለዩ ከዋዘኛም ጋር ያልተቀመጡ የደጋግ አባቶቻችንን የደግነት ዜናቸውን አደንቃለሁ ለጊዜያዊ ጥቅም የአላውያንን ዱካ ለሚከተሉ የአበውን እግር ይስጥልን
/ ኢዮብ ዘገነተ ጽጌ /

@ortodoxtewahedo
ᴡᴀᴠᴇ Ғᴏʟᴅᴇʀ መግባት የምትፈልጉ
ቻናላችሁ ከ 10ᴋ በላይ የሆናችሁ ብቻ

Ғᴏʟᴅᴇʀ ʟɪɴᴋ👇👇

https://www.tg-me.com/addlist/kCcqFTaarz0wN2I0
https://www.tg-me.com/addlist/kCcqFTaarz0wN2I0

አናግሩኝ ➛
@Naolviva
ወይዘሮ አስቴር ሰይፉ ያስገነቡት ቤተክርስቲያን ከ23 አመታት በኋላ ተጠናቆ ሊመረቅ ነው።

ታላቅ የምሥራች በመላው አለም ለምትገኙ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በሙሉ።የለኩ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ከ23 ዓመት ድካም በኋላ ተጠናቆ የካቲት 10 ቀን 2016 ዓ/ም ብፁአን አባቶች መዘምራንና ሰባኪያን በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ይመረቃል።

"ይህቺ ሴት ግን ከአቋሟ ሳታፈገፍግ ጸናች። ስንዝር በሆነው ዕድሜዋ አግኝታ ከምትለዬው የልጅ ፍቅር ይልቅ በሰማይ የሚጠብቃት ሙሽራዋ ክርስቶስን አስባ እና ተስፋ አድርጋ ሁሉንም ትታ ቤተክርስቲያኒቷን ማነጽ ብቻ ሐሳቧ አደረገች ።

በትግስት ዓመታትን በተማጽኖ ውስጥ ሆነ ከሰነበተች በኃላ እንደ አጋጣሚ ሀገረስብከቱ የብጽአን አበው ሊቃነጳጳሳት ለውጥ በማድረግ ብጽኡ አቡነ ፋኑኤል ወደ ሲዳማ ሀገረስብከት ይመደባሉ።

ይህቺ ብርቱ ሴት ለዓመታት የተከለከለችውን ህንጻ መቅደስ የማነጽ ቡራኬ እና ፍቃድ ብጽኡ አቡነ ፋኑኤል በቀናት ውስጥ ጨርሰው "አይዞሽ በርቺ" ብለው ሸኝዋት ።

እነሆ ከእዛች ቀን በኃላ 21 ዓመታትን ስለኢየሱስ እያለች በበዓላት በአዘቦት ቀናት ለ21 ዓመታት የአድባራትን ደጅ እየጠናች ከማህበረ ምዕመኑ ባሰባሰበችው ገንዘብ እዚህ ደረጃ ላይ አደረሰች።

ሲቃ ባነቀው እንባ ባጀበው የስስት ምኞቷ "የአምላኬ ስጋና ደም ሲፈተት፣በስፍራው ህጻናት ተሰብስበው ምስጋና ለሥላሴ ሲያቀርቡ፣ቅዱሳን ተወድሰው መላእክት ከብረው የምመለከትበትን ቀን እናፍቃለው" ትለናለች። "

@ortodoxtewahedo
2024/09/29 23:22:38
Back to Top
HTML Embed Code: