Telegram Web Link
#ክፉን_በመልካም_እንዴት_መቃወም_ይቻላል ?

የምታስፈራዋን የፍርድ ቀን እንባህን በማፍሰስ አስብ። ተስፋህ በእርሱ ዘንድ የቀና የጸና ይሆን ዘንድ የፈጣሪህን መልካም ተስፋውን ስበክና መስክር። መቀባጠር የሚያበዙትን በአርምሞህ ጸጥ አሰኛቸው ፤ ሐሜተኞችን በትዕግሥትህ ገሥጻቸው ፤ እንቅልፋሞችን በትጋትህ አንቃቸው ፤ ሀጥአንን አጽናናቸው ፤ የተዋረዱትን ራስህን በማዋረድ በትሕትና አረጋጋቸው ፤ ገንዘብ በማጠራቀም የበለጸጉትን ናቃቸው። ከዓለም የተለየህ ሁን ፤ የዓለም ፍቅሯና ትርፏ ፍርድን እደሚያመጣ እወቅ። ከዚህች ዓለም ትሸሽ ዘንድ ፍጠን ተሽቀዳደም ። ነፍስህንም ከመቀባጠር ፤ ጥቅም ከሌለው ከንቱ ጨዋታና ዋዛ ፈዛዛ አሳርፋት ።ይልቁንም የተሠወረውን ለሚያውቅ  እግዚአብሔር ምስጋና አቅርብ እንጅ። ድኽነትን እንደ ወርቅ ውደዳት።

📖መፅሐፈ ወግሪስ
ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

ቸር እደሩልኝ🤗
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"📖አሐቲ ድንግል"
ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

ከመፅሐፏ ምርቃት የተቀነጨበች ንግግር 🤗

''1 በር ነው ያለው እሱም ክርስቶስ ነው
ቅዱሳኑ ደሞ ወደክርስቶስ በር ነት መርተው የሚያደርሱ ናቸው ''

🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
በዚኽ ዓለም ስንኖር በምንም ነገር እርግጠኞች መኾን አንችልም። ሐብታም ልንኾንም ላንኾንም እንችላለን። ባለሥልጣኖች ልንኾንም ላንኾንም እንችላለን። ግን በአንድ ነገር ብቻ እርግጠኛ ነን።

ሟ ቾ ች ነን!

መምህር ኢዮብ ይመኑ

ቸር ዋሉልኝ🤗
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
‹‹ ቤተክርስቲያንን ከክርስቶስ የሚለይ የለም ክርስቶስ ከቤተክርስቲያን እንደማይለይ ቃል ገብቷልና ስለዚህ ማንኛውም የጉዞ አቀበትና ቁልቁለት ቢያጋጥማትም ከክርስቶስ ጋር ያለች ቤተክርስቲያን አትደነግጥም በካታኩንቦ ብትቀድስም በወርቅ በተለበጠ በሐር በተንቆጠቆጠ ቤተመቅደስም ብትቀድስ ቤተክርስቲያን የክርስቶስ ናት፡፡ ››

ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ

በቸር ዕደሩልኝ🤗
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
በሥጋ ደመና ተጭኖ መመላለስን እንማያውቅ፤
ወደ ግብጽ ምድር ሲወርድ ደክሞ አላበው፤
የአበባ  ከንፈሮቹ ውበትም በፀሐይ ሐሩር ጠወለገ፤
መከታ የሆኑ የእናቱን ጡቶች ለመጥባት በወደደ ጊዜ! ወተት አጥቶ እንደሕፃናት አለቀሰ፤
ስለወልድ እንባ መፍሰስ የእኔም እንባ ይፍሰስ፡፡
....
ያንጊዜ በስደቱ ከእሱ ጋር ብኖር፤
እሱን በጀርባዬ ማዘልን በተመኘሁ ነበር፤
የእግሩንም ትቢያ በምላሴ እልስ ዘንድ፤
በዐለት ላይ የተሳለ የእጁን ምልክትም በአፌ እስም ዘንድ፤
የዮሴፍ በትር በተተከለበትም ከእሱ ጋር አርፍ ዘንድ፤
በማርያም ልጅ የፍቅር ጦር ልቤ ቆሰለ፡፡

ሰቆቃወ ድንግል

#ለሌሎች_ተደራሽእንዲሆን_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ👇👇
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ኤጲስ ቆጶስ የሚለው ማዕረግ በጥንቱ የሮማ ቤተሰባዊ መዋቅር ውስጥ 'አንድ ሮማዊ ጌታ በሚያስተዳድረው ቤት ውስጥ የሚሠሩ አገልጋዮች አለቃ - master of slaves' የሚጠራበት ስም ነበር። ክርስቲያኖች ስሙን ከዚያ ነበር የወሰዱት። በእግዚአብሔር ቤት ካሉ አገልጋዮች መሀከል አንዱ ግን ታላቁ አገልጋይ ስም ኤጲስ ቆጶስ መባሉ የጥንቶቹ ተምኔት ምን እንደሆነ በግልጥ ያሳያል። ዛሬ ይኼ የአገልጋይነት መንፈስ የሚገኘው የት ይሆን? የሚለው የእኛ የቤት ሥራ ነው። አገልግሎትን በተመለከተ የተወያየነውን እንደ ወትሮው እንድታዳምጡ፣ አሳባችሁንም እንድታጋሩን ግብዣችን ነው።

https://youtu.be/-M_tj2UM-oE?si=45QsJ9fFkpY9620M

“እግዚአብሔር ሰንበትን እንደ ሰጣችሁ እዩ።”
— ዘጸአት 16፥29

https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
ሕማሜን በሕማምህ አድን፤ በቁስልህም ቁስሌን ፈውስ፡፡ ደሜን ከደምህ ጨምር፤ ሕይወት የሆነ የቅዱስ ሥጋህን መዓዛም በሥጋዬ ጨምር፤ በጠላቶች /በአይሁድ/የጠጣሃው ከርቤም ክፉ ሐሞትን የጠጣች ነፍሴን ያጣፍጣት፡፡ በሰፊው መስቀል ላይ የተዘረጋው ሥጋህም ሕሊናዬን ወደ አንተ ያድርገው:: በጠላት /በዲያብሎስ ድል ተነስቻለሁና። በመስቀል ላይ የዋለው ራስህ በርኩሳን ዘንድ የተቀጠቀጠ ራሴን ከፍ ያደርገው፡፡ በከሀድያን የተቸነከሩ ቅዱሳት እጆችህም ወደ አንተ ይንጠቁኝ፡፡

በወንጀለኞች ምራቅንና ጉስቁልናን የተቀበለ ፊትህ በኃጢአት የጐሰቆለ ፊቴን ያብራልኝ፡፡ የተሰቀለች ሰውነትህም ወደ አባትህ ዐረገች:: ጸጋህም ወደ አንተ ታድርሰኝ፡፡ አቤቱ ለመማጸን ዕንባ የለኝም፡፡ ለመለመንም ያዘነ ልብ የለኝም፡፡ ልጆችህን ወደ ርስታቸው የሚሰበስብ ንስሐና ኀዘንም የለኝም። ከጥፋት ብዛት የተነሣም ሕሊናዬ ጠቆረ፡፡ በእነዚህና በመሳሰሉትም ልቡናዬ ተሸፈነ፡፡ ወደ አንተ እመለከት ዘንድም ኃይል የለኝም፡፡ ከክፋት የተነሣም አዕምሮዬ ቀዘቀዘ፡፡ በተቃጠለ ፍቅር ዕንባን ማፍሰስም ተሳነው፡፡

የመልካም ነገር ሁሉ መዝገብ ክርስቶስ ሆይ፤ አንተን ለመፈለግ በፍቅር እወጣ ዘንድ ፍጹም ንስሐንና ትጉ ልቡናን ስጠኝ፡፡ ስለ አንተም ከሁሉ የተለየሁ ሆንሁ: ቸር ሆይ፣ ከባሕርዩ የወለደህ ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞም በባሕርዩ የነበርህ የአብን ጸጋ ስጠኝ፡፡ አርአያህና አምሳልህም ውስጤን ያድሰው:: እነሆ ተውሁህ፤ አንተ ግን አትተወኝ፤ ወደ አንተ መጣሁ፤ አንተም እኔን ለመፈለግ ውጣ፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
(ውዳሴ አምላክ ዘሐሙስ)

የክርስቶስን ፍቅር በማሰብ ቸር ዋሉልኝ🤗
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ሰላም የችግሮች አለመኖር ሳይሆን በፈተናዎች(በችግሮች) ውስጥ ከእግዚአብሔር ጋር የመሆን ውጤት ነው።

እግዚአብሔር የሚሰጠውን ሰላም የትኛውም ኃይል ሊወስደው አይችልም!

ዲ/ን አቤል ካሳሁን

“ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም።” ዮሐንስ 14፥27
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
"When a bad or gloomy thought, fear or temptation threatens to afflict you, don’t fight it to try and get rid of it. Open your arms to Christ’s Love and He will embrace you, then it will vanish by itself.”

+ St Porphyrios of Kavsokalyvia

"መጥፎ ወይም ጨለምተኛ ሀሳብ፣ ፍርሃት ወይም ፈተና ሊያስጨንቅህ በሚችልበት ጊዜ፣ እሱን ለማስወገድ አትዋጋው፣ እጆቻችሁን ለክርስቶስ ፍቅር ክፈቱ እና እሱ ያቅፋችኋል፣ ያኔ በራሱ ይጠፋል።"

+ የካቭሶካሊቪያ ቅዱስ ፖርፊሪዮስ

“ ኢየሱስ ክርስቶስን አስብ፤”2ኛ ጢሞ 2፥8
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ከእርሱ ጋር ኀብረት ፍጠሩ!

እግዚአብሔርን ለማወቅ ለመውደድ ከእርሱ ጋር መተባበር አለባችሁ። ንባብ ብቻውን በቂ አይደለም። ንባብ የሚከፍትላችሁ መዝጊያውን ብቻ ነው። ከዚህ በኋላ እናንተ ትገቡና ከእግዚአብሔር ጋር ትኖራላችሁ ከዚያም ከእርሱ ጋር መኖር ጣፋጭ መሆኑን እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ።

ስለሆነም ከእግዚአብሔር ጋር የሚሆን ሕይወትን ትሞክሩታላችሁ እርሱ በሁሉም ነገር ውስጥ ተካፋይ እንዲሆንም ትፈቅዳላችሁ።

እንደ ባልጀራችሁ አድርጋችሁ ልትወዱት ሞክሩ አሳቦቻችሁንና ሚስጥሮቻችሁን ለእርሱ ንገሩት። ከዚህ በኋላ የሚሆነውን ጠብቁና እርሱ ምን ያህል ከእናንተና ለእናንተ እንደሚሰራ ታያላችሁ። ከዚህ በተጨማሪ በአሳቦቻችሁና በተሰጥኦዎቻችሁ ከመተማመን የበለጠ በእርሱ ላይ መተማመንን ታውቃላችሁ።

[ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ ]

#ለሌሎች_ተደራሽእንዲሆን_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ👇
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ነገረ አበው (Patrology) 


ክፍል አንድ


"Patrology" የሚለው ቃል "pater" ከሚለው የመጣ ሲሆን "አባቶችን ማጥናት" ማለት ነው። በአጠቃላይ ይህ የሥነ መለኮት ዘርፍ የሚያጠናው ስለ አባቶች ሕይወት እና ትምህርት ነው።

  
የቤተ ክርስቲያንን አባቶች በምን እናውቃለን?

አንድ አባት የቤተ ክርስቲያን አባት ለመባል የሚከተሉትን መሥፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል።

1. ኦርቶዶክሳዊ ሕይወት ሊኖረው ይገባል
2. የቅድስና ሕይወት ሊኖረው ይገባል
3. የቤተ ክርስቲያንን ማረጋገጫ ማግኘት ይኖርበታል

 
የቤተ ክርስቲያን ሐኪሞች

እነዚህ ከቤተ ክርስቲያን አባቶች ውስጥ በቅድስናቸው ቤተ ክርስቲያንን ከመናፍቃን በመጠበቅ አና በሌሎች ነገሮች ከሌሎች የጎሉ ናቸው። እነዚህም ቅዱስ ባስልዮስ፣ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ፣ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ፣ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ፣ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ወዘተ ይጠቀሳሉ።

 
የነገረ አበው ጥቅም አና ዓላማ

ነገረ አበውን ማጥናት ዋነኛው ጥቅሙ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ለመረዳት ነው፤ ምክንያቱም እነዚህ አባቶች የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ምንጭ ስለሆኑ ነው።

ዓላማው ደግሞ እነዚህን አባቶች በማጥናት የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት መረዳት አና ከቅድስና ሕይወታቸው ለመማር ነው።
 
የነገረ አበው ትምህርት ክፍፍል

የመጀመርያው የነገረ አበው ትምህርት በቋንቋ ሊከፋፈል ይችላል። ይህም የጽርዕ፣ የላቲን፣ የሱርስት፣ የቅብጥ፣ የግእዝ ወዘተ እያልን መከፋፈል እንችላለን።

ሁለተኛው እከፋፈል በዘመን ሲሆን የመጀመሪያዎቹ ማለትም ፩ኛ እና ፪ኛ መቶ ክፍለ ዘመን አባቶች፣ የወርቃማው ዘመን አባቶች፣ የኋለኛው ዘመን አባቶች ተብለው ይከፈላሉ።

አስቀድመን ግን ወደ ነገረ አበው ትምህርት በደንብ ከመግባታችን በፊት ስለ ቤተ ክርስቲያን ባሕርያት ማወቅ ይኖርብናል።
• ቤተ ክርስቲያን አንዲት ናት፤ ማለትም ክርስቶስን ያመኑ እና በጥምቀት የተባበሩ ሁሉ አንድ ናቸው።
•  ቤተ ክርስቲያን ቅድስት ናት፤ ማለትም የክርስቶስ አካል ስለሆነች ንጽሕት ቅድስት ናት።
•  ቤተ ክርስቲያን ኩላዊት ናት፥ ማለትም የመሬት አቀማመጥ፣ ቋንቋ ወይም ብሔር አይገድባትም።
•  ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊት ናት፤ ማለትም ሐዋርያዊ እምነት አላት።


የቤተ ክርስቲያን መከፋፈል

ከጉባኤ ኤፌሶን በኋላ (431 ዓም) Assyrian Church of the East, The East Syrian Church እና Chaldean Church of the East የንስጥሮስን ትምህርት እንቀበላለን በማለት ከቤተ ክርስቲያን ወጡ።

ከጉባኤ ኬልቄዶን በኋላ (451 ዓም) ኬልቄዶናውያን የሆኑ እና ኬልቄዶናውያን ያልሆኑ በመባል በድጋሚ ቤተ ክርስቲያን ለሁለት ተከፍላለች።

በድጋሚ በ1054 ዓ.ም በኬልቄዶናውያን መካከል የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እና የምሥራቅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን (Eastern Orthodox) በመባል ለሁለት ተከፍለዋል። ይህም መከፋፈል "The Great Schism" በመባል ይታወቃል።


Oriental Orthodox vs Eastern Orthodox

Oriental Orthodox የምንላቸው አብያተ ክርስቲያናት የኬልቄዶንን ነገረ መለኮት (ማለትም የሁለት ባሕርይ ትምህርትን) የማይቀበሉ የቅዱስ ቄርሎስን የአንድ ባሕርይ ትምህርትን የሚቀበሉ ናቸው። እነዚህም the Coptic Orthodox Church of Alexandria፣ the Syriac Orthodox Church of Antioch፣ the Malankara Orthodox Syrian Church፣ the Armenian Apostolic Church፣ the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church እና the Eritrean Orthodox Tewahedo Church ናቸው።

🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
☝️የቀጠለ......

"የሐዋርያነ አበው" ዘመን የሚባለው ከ70 ዓ.እ(AD)-160 ዓ.እ(AD) ያለው ነው። (ዓ.እ:- ዓመተ እግዚእ)

በመስኩ ጥናት ያደረጉ ሊቃውንት እንዲሁም የቤተክርስቲያን የታሪክ መጻሕፍት እንደሚናገሩት በዚህ ዘመን ከሚመደቡት አበው ውስጥ:-

* ቅዱስ ቀሌምንጦስ ዘሮም(St. Clement of Rome)

*ቅዱስ አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ (St. Ignatius of Antioch )

*ቅዱስ ፖሊካርፐስ ዘሰርምኔስ(St. Polycarp of Smyrna)

*ፓፒያስ ሊቀ ጳጳሳት ዘሄራሊስ (Papias of Hierapolis)

*በርናባስ (ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ)

* ሔርማ ኖላዊ( Hermas the shepherd) ይገኙበታል።

እነዚህ ሐዋርያውያን አበው በተለያየ አገር የኖሩ ይሁኑ እንጂ በመልእክቶቻቸው ያንጸባረቁት አስተምህሮት ግን ተመሳሳይ እና ከአንድ ምንጭ የተቀዳ ነው። ይህም ነገር የቤተክርስቲያንን ኩላዊነት/Catholicity/ የሚያሳይ ቀዳማዊ ማስረጃ ነው።

📖(አባቶችህን እወቅ(ነገረ አበው) ፣ ዲያቆን አቤል ካሳሁን)

#ለሌሎች_ተደራሽእንዲሆን_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ👇
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
☝️የቀጠለ.......

ለመሠረታዊ ትምህርተ ሃይማኖት "በዋናነት" የሚጠቀሱ አባቶች

1.ቅዱስ አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ (50-117 ዓ.ም) :- የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ደቀመዝሙር የነበረ፣ የአንጾኪያ ቤተክርስቲያን 3ተኛው ጳጳስ ነበር ከጴጥሮስ እና ከኢቮዲየስ ቀጥሎ

2.ቅዱስ ፖሊካርፐስ (69-156 ዓ.ም) የነበረ አባት ነው ከቅዱስ አግናጥዮስ ምጥው ዘአንበሳ ጋር ባለንጀራ ነበሩ ቅዱስ ፖሊካርፐስም የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ደቀመዝሙር ነበር

3.ቅዱስ ሄሬኔዎስ:- የቅዱስ ፖሊካርፕ ደቀመዝሙር ነበር(130 ዓ.ም ወይም 142- 202 ዓ.ም)

4.ቅዱስ ቆጵርያኖስ ሰማዕት (St. Cyprian of carthage) ከ200 - 258 ዓ.ም

5.ቅዱስ አቡሊዲስ (170 -236 ዓ.ም )

6.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ(298 - 373 ዓ.ም)

7.ቅዱስ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም( 315 - 386 ዓ.ም)

8.ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ (330 - 379 ዓ.ም)

9.ቅዱስ ጎርጎሪዮስ ዘእንዚናዙ(329 - 390 ዓ.ም)

10.ቅዱስ ጎርጎሪዮስ ዘኑሲስ (330 - 395 ዓ.ም)

11.ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ(347 - 407 ዓ.ም)

12.ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ( 315 - 403 ዓ.ም)

13.ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ (376 - 444 ዓ.ም)

14.ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ( 459 - 538 ዓ.ም)

15.ቅዱስ ያሬድ (505 - 571 ዓ.ም)

(መድሎተ ጽድቅ ፣ ቅጽ 1 ፣ ዱያቆን ያረጋል አበጋዝ )

"የከበሩ የአባቶቻችን ልጆች ልትሆኑ ከወደዳችሁስ እነርሱ የጻፉትን እንጂ ምንም ምን ሌላ አትመኑ"

       ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ

#ለሌሎች_ተደራሽእንዲሆን_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ👇👇
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
የሚለቀቁትን በማንበብ ትምህርት እያገኛችሁባቸው ነው ተወዳጆች በዚው እንቀጥል🤔?
Anonymous Poll
92%
አዎ በብዙ አትርፈናል
8%
በጥቂቱ አትርፈናል
0%
እየተከታተልን አይደለም ከስረናል?
ክርስትናን በትክክል ለመረዳት፣የክርስቶስን ቤተክርስቲያን ለማወቅ እና በዛች ቅድስት ቤተክርስቲያን ውስጥ ለመኖር እነዚህ ነገሮች ያስፈልጋሉ።

   1. Mind of the church(phranema)
   2.patristic view
   3. reading with the apostolic fathers

   4. Reading with the church

እነዚህ አገላለጾች ሁሉም አንድን ነገር ያሳያሉ እሱም "ኦርቶዶክሳዊ አስተሳሰብ" ይሄንን ኦርቶዶክሳዊ አስተሳሰብ ለማግኘት እና በዛ መነጽር ነገሮችን ለማየት እና ለመረዳት ደግሞ ሐዋርያዊ የሆኑ አባቶች አስተሳሰብን ማወቅ እና መረዳት የግድ ነው። አስተሳሰባችን ኦርቶዶክሳዊ ሲሆን ቤተክርስቲያን ውስጥ ያለውን ህይወት እና ቅዱሳት መጻሕፍትን እንረዳለን መለኪያ እና ሚዛንም ይሆነናል። እውነተኛውን ከሃሰተኛው ለመለየት አንቸገርም ግራም አንጋባም በስሜትም አንመራም ስለዚህ አባቶቻችንን ማወቅ አለብን።

“የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፥ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው።”
    ዕብራውያን 13፥7

#ለሌሎች_ተደራሽእንዲሆን_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ👇
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

ከተገኙ ብታነቡ መፀሐፍት📖 ጥቆማ👇
ልክ እንደዚህ የተለያዩ አባቶችን ሕይወት እና ትምህርት ላይ የተጻፉ መጽሐፎች አሉ ከእነዚህ ጀምሩ እና ሌሎቹንም እየገዛችሁ አንብቡ pdf እንለቃለን ሌሎች ፅሁፎችንም እናተ ለሌሎች ተደራሽ እያረጋችሁም ጠብቁ🙏
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
             †             
[ ኦርቶዶክሳዊ እይታ ምልከታ ማለት !

ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
2024/11/15 12:28:20
Back to Top
HTML Embed Code: