Telegram Web Link
"Those who come close to people in pain naturally draw near to God, because God is always by the side of His children who are in pain."

+ St Paisios of Mount Athos
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኤልያስ ሽታሁን
ፍቅር ስለሆነ .......
#ለሌሎች_ተደራሽእንዲሆን_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ👇👇
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
"አንዳንድ ፍሩሃነ ንሥሐና እኩያነ ምግባር የሆኑ ሰዎች ከክፋታቸው ሳይመለሱና ንስሐ ሳይገቡ በድፍረትና በማን አለብኝነት መንፈስ አንድ ቀን በቅዱሱ በዓል ስለመጡ ፣ ቦታውን ስለረገጡና የተቻላቸውን ስላደረጉ "ቦታህን የረገጠውን ፣ እንዲህ ያደረገውን .....እምረዋለሁ" የሚለውን ብቻ በመስማት በእግዚአብሔር የማዳን ሥራ እንዳይዘብቱ አስጠንቅቆ መንገሩና ወደ ንስሐ እንዲመለሱ ፣ በጎ ሥራ እንዲሰሩና ክፋታቸውን እንዲተው ማስተማር ያስፈልጋል ። እግዚአብሔር ለሰሎሞን ያለውን ማሰብ ያስፈልጋል ።

1ኛ ነገሥት 9
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³ እግዚአብሔርም አለው፦ በፊቴ የጸለይኸውን ጸሎትህንና ልመናህን ሰምቻለሁ፤ ለዘላለምም ስሜ በዚያ ያድር ዘንድ ይህን የሠራኸውን ቤት ቀድሻለሁ፤ ዓይኖቼና ልቤም በዘመኑ ሁሉ በዚያ ይሆናሉ።
⁴ ዳዊትም አባትህ በየዋህ ልብና በቅንነት እንደ ሄደ አንተ ደግሞ በፊቴ ብትሄድ፥ ያዘዝሁህንም ሁሉ ብታደርግ፥ ሥርዓቴንም ፍርዴንም ብትጠብቅ፥
⁵ እኔ፦ ከእስራኤል ዙፋን ከዘርህ ሰው አታጣም ብዬ ለአባትህ ለዳዊት እንደ ተናገርሁ፥ የመንግሥትህን ዙፋን በእስራኤል ላይ ለዘላለም አጸናለሁ።

ምክንያቱም እግዚአብሔር ለዳዊት የገባውን ቃል ኪዳን ያጸናው ወይም የሚጠብቀውም ሰሎሞን በትእዛዘ እግዚአብሔር ሲኖር ነውና። "ዳዊትም አባትህ በየዋህ ልብና በቅንነት እንደሄደ አንተ ደግሞ ብትሔድ" የሚለው ይህን ያስረግጥልናል።

ስለዚህ በዓላትን እንደ ክርስትያን ማክበር የሚለው በቤተክርስቲያን ተሰባስቦ በመማር ፣ በመጸለይ ፣ በማስቀደስና ሥጋውን ደሙን በመቀበል ሊሆን እንደሚገባ ማስተዋል ያስፈልጋል ።

(በዓላት ምን ? ለምን ? እንዴት ? ፣ ዲያቆን ብርሃኑ አድማስ ፣ ገጽ 162-163)

#ለሌሎች_ተደራሽእንዲሆን_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ👇👇

⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
"በእርግጥ ሕዝቡ ለበዓላት ትርጓሜ ስንሰጥ ባየንበት መንገድ እግዚአብሔርን በሆታና በእልልታ የሚያመሰግንበት ፣ ደስታውንም የሚገልጽበት በዓል ነው። ስለዚህ እነዚህን በዓላት ከዚህ ባለፈ ማክበር እንዲገባ የጻፈ የለም። አንድ ሰው ይኸን ማድረግ ሳይችል ፣ ወደ ቤተክርስቲያን ሳይሄድ ፣ እግዚአብሔርን ሳያመሰግን ፣ ሳያስቀድስ ፣ ቃለ እግዚአብሔር ሳይማር እቤቱ በመቀመጡ ብቻ በዓሉን አክብሯል ሊባል አይችልም። ምክንያቱም በዓል ማክበር ሥራ ፈትቶ በሐሜት ፣ በጸብ ፣ በክርክርና በአሉባልታ የሚያሳልፉት ነገር አይደለምና ። ስለዚህ በዓላቱን እናከብራለን የሚሉ ሰዎች አስቀድመው ማድረግ ያለባቸውን ግዴታ አውቀውና ተረድተው መወጣት ይጠበቅባቸዋል። ሥራ መተው የሚያስፈልገውም ለማስቀደስ ፣ ለመጸለይ ፣ ቃለ እግዚአብሔር ለመስማትና ፣ በማኅበር እግዚአብሔርን ለማመስገንና ለማገልገል እንጂ ለዋዛ ለፈዛዛ ጉዳይ አይደለም ።"

(በዓላት ምን? ለምን ? እንዴት? ፣ ዲያቆን ብርሃኑ አድማስ ፣ ገጽ 169 -170)

#ለሌሎች_ተደራሽእንዲሆን_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ👇👇
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
✞✞✞ እናታችን ቅድስት አርሴማን በምን እንመስላታለን? እርሷ በአድማስ ላይ ተቀምጦ እንደሚያበራ እንቁ ናትና ክብሯ ብዙ ነው:: መድኃኒታችን ክርስቶስ በወንጌል እንዳለው "በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሠወር አይቻላትምና" ማቴ 5÷14 በክርስቶስ የማዳን ተራራነት የሰማዕቷ ሕይወት በፊታችን እንደ ብርሃን ተገልጦ ይታያል።

በዚህች ዕለት እናታችን ቅድስት አርሴማ ተጋድሎዋን በክብር የፈጸመችበት ቀን ነው። በጸሎቷ ይማረን በረከቷም ይደርብን!🤲🤲🤲አሜን🙏🙏🙏

#ለሌሎች_ተደራሽእንዲሆን_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ👇👇

⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
የፍቅር መለኪያው ምን ያህል ነው? ትሉኝ እንደሆነ

ያለ ልክ እንዲሁ መውደድ ነው እላቹሃለው።

ቅዱስ አውጉስቲን

'' እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።”
  ዮሐንስ 3፥16


#ለሌሎች_ተደራሽእንዲሆን_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ👇👇
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
'' በጎ ነገር አግኝተህ እንደ ሆነ እግዚአብሔርን አመስግን ያም በጎ ነገር ከአንተ ጋር ጸንቶ ይኖራል። በጎ ያልሆነ ነገር ደርሶብህ እንደሆነም እግዚአብሔርን አመስግን ያም በጎ ያልሆነ ነገር ወደ በጎ ነገር ይቀየራል።''

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

#ለሌሎች_ተደራሽእንዲሆን_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ👇👇
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
''ጌታ ሆይ ፥ ወደ ማን እንሄዳለን ? አንተ የዘላለም ሕይወት ቃል አለህ ፤''

ዮሐንስ 6፥68

#ለሌሎች_ተደራሽእንዲሆን_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ👇👇
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
“ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን🤲፥ ለእርሱም ይሰጠዋል።”
ያዕቆብ 1፥5

#ለሌሎች_ተደራሽእንዲሆን_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ👇👇
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
የ 'አሁን'ነት ሃይል (The Power of Now ) ከሚለው የ:-አፈወርቅ በቀለ  ትርጉም መፅሐፍ ላይ እንዲ የምትል ሃሳብ 🤔💭አገኘው

'' ዕውቀት ሊከሰት የሚችለው ታዋቂውን በማስተዋል ብቻ አይደለም ። አዋቂው ራሱ አድራጊ ሆኖ መገኘትና መቅረብ ይኖርበታል ''
ሃሳቡን ለቁሱ ዓለም ማብራሪያነት ቢያቀርበውም እደቀልድ ግን ዘልዬው ልሄድ አልተቻለኝም ሃሳቡን ወደዚህ አምጥተን እንዲህ ብናስበውስ👇

ብዙ ጊዜ ክርስትያኖች የተለያዩ አይነት እውቀቶችን በጉባኤ ፣ በሰንበት ት/ቤት ፣ በንስሃ አባቶች ተምረን ነገሮችን አውቀናቸው ሊሆን ይችላል ! ለምሳሌ :- ሚስጢራትን መፈፀም ስለሚስጢራት ብዙ እውቀቶችን ሰብስበን ልንተነትን እንችላለን እንፈፅማቸዋለን ወይ ነው ? ጥያቄው መፅሐፍ ቅዱስን አገላብጠን ማንበብ ችለን በቃልም እናነበንበው ይሆናል ኑረነዋል ወይ ነው ጥያቄው ? የማንፈፅማቸው ከሆነ አዋቂዎችም ልንሰኝ አይገባም ማለት ነው ።

ለምሳሌ ያክል አንድ ሙያ(የየራሳችሁን ትምህርት ከታቹ አስቡልኝ) የሚማር ሰው ትምህርቱን እስካልጨረሰ የሚማርበትን  ስያሜ ሊያገኝ አይችልም ማለትም ዶ/ር ፣ ኢንጂነር ወዘተ..... ተምሮ ጨርሶ መኖር ሲጀምር ግን መጠሪያውን ያነግባል አወቀ ተብሎ ስለሚታመን  ልክ እንዲሁ ክርስትያንም  ክርስትያን ሊያሰኘው የሚችለው ወደ ተግባረ ዕውቀት ከፍ ያለ እለት ነው ።

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ''ቅዱሳት መፃሕፍትን የማያነብ የማይኖር ክርስትያን ክርስትያን ተብሎ ሊጠራ አይገባውም'' ይለናል

ወደ ተግባር ዕውቀት ያሸጋግረን ዘንድ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ያፀናን ዘንድ በፀሎት እንትጋ🥰🥰🥰

ሃሳቧ ግን ከዚህም በላይ ስለምታስኬድ አስብልኝ እያልኩ ስጋብዝ በሌላም እይታ የሚያስቀምጥ ካለ ከታች 👇 አስፍሩልን🤗

https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ☝️
ቅዳሴ (liturgy)

"ቅዳሴ የምትቀድስ ቤተክርስቲያን "
"A Church that celebrates the Divine liturgy"

እኛም ቤተክርስቲያናችንን ምን ብለን እንደምንገልጽ ስንጠየቅ መመለስ ካለብን መልሶች አንዱ ይሄ ነው ☝️☝️ከዚ ውጪ ህይወት የለም እና🤗

ፎቶው የተነሳው ከአኮቴተ ቁርባን መጽሐፍ ላይ ነው 📖

ሰንበቶሙ ይእቲ ለጻድቃን ትፍሥሕት፤ሰንበቶሙ ይእቲ ለኃጥአን ዕረፍት፤ኅቡረ ንትፈሳሕ በዛቲ ዕለት፡፡ፅሩይ ዕምዕንቈ ባሕርይ፤ ዐክሊለ ፅጌ ማርያም ቀፀላ መንግሥቱ

#ለሌሎች_ተደራሽእንዲሆን_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ👇👇

🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ስለ " ቅዳሴ" መሰረታዊ እና መታወቅ ያለባቸው ነገሮች

1⃣. ቅዳሴ ምንድነው ? What is "Liturgy"?

"ቅዳሴ" ማለት "ቀደሰ" ከሚለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ የምሥጋና ቃል ነው ። አመስጋኙ የሰው ልጅ ሲሆን ተመስጋኙ ፈጣሬ ዓለማት ( የዓለማት ፈጣሪ ) የሆነው ቅዱስ እግዚአብሔር ነው እርሱ  የሚመሰገነው በሰው ብቻ ሳይሆን በፈጠራቸው ፍጥረታት ሁሉ ነው ። ( ኢሳ 6:3 ፣ ራዕ 4:8 ፣ ሉቃ 2:13 - 14 ፣ ሐዋ 16:25 ..........) 

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን "ቅዳሴ" የሚለው ቃል ቅዱስ ቁርባን የሚከብርበትን አገልግሎት ሲያመለክት "ምስጋና" የሚለው ትርጉሙ ደግሞ (ጽርእ) ቃል  "ኤቭኻሪስቲያ" (Thanksgiving) አቻ ነው ። ከምስጋና ባሻገር "ቅዳሴ" የሚለው ቃል "ቅድሳት" በመባል የሚታወቀውን የጌታን ሥጋውንና ደሙን ተቀብለው ካህናቱና ምእመናኑ የሚያገኙት የቅድስና ሕይወትን ያመለክታል ።  

ቅዳሴ እና ቅዱስ ቁርባን ስለማይለያይ "ቁርባን" ምን ማለት እንደሆነ እንይ እና ወደሌላው እንቀጥላለን

ቁርባን :- የሱርስት ቃል ሲሆን ፍቺውም መባእ እና ስጦታ አምሀ ማለት ነው ። በመስቀል ላይ የተሰጠን ሥጋና ደም ሳይገባን በነጻ በችሮታ የተሰጠን ስለሆነ ነው ስጦታ የተባለው ። ምሥጢረ ቁርባንን የመሰረተው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ። የመሰረተውም በጸሎተ ሐሙስ ዕለት ነው። በማስተማር ዘመኑም ሥጋዬን የበላ ደሜን የጠጣ የዘለዓለም ሕይወት አለው ብሎ አስተምሯል ( ዮሐ 6:56 ፣ ማቴ 26:26 ) በዚሁ አምላካዊ ትምህርት ክርስትያን የሆነ ሁሉ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን መቀበል ይኖርበታል ። በዚህ አምኖ ያልተቀበለ ርስተ መንግሥተ ሰማያትን አያገኝም ፣ አይድንም ።


2⃣ . በቤተክርስቲያናችን ስንት አይነት ቅዳሴዎች አሉ ?

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከተመሠረተችበት ጊዜ ጀምሮ ለትምህርተ ሃይማኖትና ለጸሎት እንደዚሁም ለአምልኮተ እግዚአብሔር ከምትገለገልባቸው ቅዱሳት መጻሕፍት አንዱ አሥራ አራቱ መጻሕፍተ ቅዳሴ ነው ። 

ይህ መጽሐፈ ቅዳሴ በቁጥር 1⃣4⃣ ሲሆን በሥርዓት አፈጻጸሙ ግን ሦስት ክፍሎች አሉት ።

እነሱም ⤵️⤵️⤵️
 
ሀ) ሥርዓተ ቅዳሴ (የዝግጅት ክፍል ወይም ግብዓተ መንጦላዕት ) :- Preparation service

"ኦ እኁየ ሀሉ በዝንቱ ልቡና....." ከሚለው ጀምሮ
" ሚ መጠን ግርምት ......." እስከሚለው ያለው ነው ።

ለ) ጸሎተ አኮቴት (የትምህርት ወይም የንባብ ክፍል) :- Didactic service

" ሚ መጠን ግርምት ....." ከሚለው ጀምሮ
" ፃኡ ንዑሰ ክርስትያን " እስከሚለው ድረስ ያለው ክፍል ነው ።

ሐ) አኮቴተ ቁርባን ( ፍሬ ቅዳሴ) :- Eucharistic service

"ፃኡ ንዑሰ ክርስትያን" ከተባለ በኋላ ያለውን ክፍል ነው። 

👉 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሥጋውና ደሙን የምታከብርባቸው 1⃣4⃣ ቅዳሴያት አሏት ።

እነሱም ⬇️⬇️⬇️

1⃣.ቅዳሴ ሐዋርያት ( Anaphora of the Apostles)

2⃣.ቅዳሴ እግዚእ (Anaphora of the Lord)

3⃣.ቅዳሴ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ (Anaphora of st. John the son of thunder)

4⃣.ቅዳሴ ማርያም( Anaphora of st.mary)

5⃣.ቅዳሴ ሠለስቱ ምዕት(Anaphora of the 318 Orthodox fathers)

6⃣.ቅዳሴ አትናቴዎስ( Anaphora of Athanasius)

7⃣.ቅዳሴ ባስልዮስ(Anaphora of Basil)

8⃣.ቅዳሴ ጎርጎርዮስ(Anaphora of Gregory of Nyssa)

9⃣.ቅዳሴ ኤጲፋንዮስ( Anaphora of Epiphanius)

🔟.ቅዳሴ ዮሐንስ አፈወርቅ(Anaphora of John chrystosom)

1⃣1⃣.ቅዳሴ ቄርሎስ(Anaphora of Cyril)

1⃣2⃣.ቅዳሴ ያዕቆብ ዘሥሩግ(Anaphora of Jacob of sarug)

1⃣3⃣.ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ(Anaphora of Dioscoros)

1⃣4⃣.ቅዳሴ ጎርጎርዮስ ካልዕ(Anaphora of Gregory of Nazianzus )
ይህ ታላቅ ምሥጢር የሚፈጸምበት አገልግሎት ከልዑል እግዚአብሔር ለሰው ልጆች የተሰጠ የፍቅር ስጦታ ነው። ስለሆነም ቅዳሴ የክርስቶስን ሕማም ሞትና ትንሣኤ እያሰብን እግዚአብሔር አብ በአንድ ልጁ ሞት ላሳየን ዘለአለማዊ ፍቅር ምስጋና የምናቀርብበት አምልኮ ነው ።

#ቅዳሴ የአዲስ ኪዳን መሥዋዕት የሚቀርብበት ዐቢይ ሥርዓተ አምልኮ ነው ።

*ቅዳሴ የክርስቶስን የማዳን ሥራ እውን የሚያደርግልን የምስጋና አገልግሎት ነው።

*ቅዳሴ በምድር ላይ ያለ ሰማያዊ አገልግሎት (Heaven on earth service) ነው ።

*ቅዳሴ የሰማያዊው አምልኮ ነጸብራቅ ነው።

*ቅዳሴ በደስታና በሐሴት የሚከናወን አምልኮ ነው።

(አኮቴተ ቁርባን ፣ቀሲስ ዶ/ር መብራቱ ኪሮስ ፣ ገጽ 3)


➡️ዋቢ መጻሕፍት 👇

"አኮቴተ ቁርባን" በቀሲስ ዶ/ር መብራቱ

ፅጌም አይደል በአበባዎች እያሸበረቅን እናስባት🥰
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
በዚህኛው የበእንተ ወንጌል ቆይታችን በዮሐንስ ወንጌል ላይ ካሉ ዐበይት ታሪኮች ውስጥ አንዱ የሆነውን ጌታችን ከሣምራዊቷ ሴት ጋር ያደረገውን ንግግር ቃኝተናል።

በውይይታችን ውስጥ እነዚህን ሦስት መሠረታዊ ነጥቦችን አንስተናል።

1) ይህንን የወንጌል ክፍል ለመረዳት አስፈላጊ የሆነውን አይሁዳውያን ከሣምራውያን ጋር የነበራቸውን ግንኙነት ሰፋ ባለው ታሪካዊ አውዱ ለማንሳት ሞክረናል።

2) የዚህ ታሪክ መሠረታዊ ነገረ ቤተክርስቲያናዊ ጭብጥ አንስተናል።

3) በዚህ ታሪክ ላይ ፈጽሞ ታሪካዊ አውዱንም ሆነ የወንጌሉን መሠረታዊ ጭብጥ ያልተገነዘቡ ፣ በዘመናችን ከሉ ሊቃውንትም ሆነ ከአበው ምስክርነት የማይገኝላቸውን ወፍ ዘራሽ "ትርጓሜዎች" ሞግተናል።

መልካም ቆይታ።

https://youtu.be/f2aunKpPPBY?si=NhrzAV9-_TZj6ifC
ሰዎች ውስጣቸው ክርስቶስ ባለመኖሩ ባዶ ሲሆኑ ብዙ ሺ ነገሮች መጥተው ይሞሏቸዋል: ቅናት፣ ሃሜት፣ ጥላቻ፣ ድብርት፣ ጥልቅ ኅዘን፣ እልህ፣ ዓለማዊ ዕይታ፣ ምድራዊ ደስታ ወዘተ... ነፍሳችን ባዶ እንዳትሆን ነፍሷ የሆነው ክርስቶስን አንከልክላት🤲

ማቴዎስ 11
²⁸ እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።
²⁹ ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤

#ለሌሎች_ተደራሽእንዲሆን_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ👇👇
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

ቸር ዋሉልኝ🤗
+++++++#በበጎነት_መጽናት#+++++++++

ማር ወግሪስ እንዲህ ይላል፦ "ዳግመኛም ስማኝ ልንገርህ! ለዘለዓለም ላንተ ይብስብሃልና ባደርክበት ኹሉ ቃልህን አትለውጥ። በሰዎች መካከል ጥልን አትዝራ፤ አነዋወርህ ኹሉ በሰላም ይኹን፤ ወደ ልቡናህም ቍጣን አታስገባ፤ ወንድምህ የበደለህን ከቶ አታስብ። የቍጡ ሰው ድካሙ ኹሉ በዐይን ጥቅሻ በከንፈር ንክሻ ፈጥኖ ያልፋልና። ቂምን በልቡናው የሚያኖር ሰው የሰይጣን ደቀ መዝሙሩ ነው፤ የዘለዓለም ሕይወትንም አያያትም። ማንንም ማንን አትማ፤ ከማንም ጋር አትከራከር፤ የባልጀራህን ንብረት አትመኝ የሌላውንም አትቀማ።

ሐሜተኛ ሰው የእግዚአብሔር ጠላቱ ነው። በጠላትህ ውድቀትና ሞት ደስ አይበልህ፤ ባዘኑት ላይ አትሣለቅ፤ ለዕውሩ መሰናክል አታኑርበት። ስትጸልይ ለመቀመጥ አትቸኩል፤ ለጸሎት ዝግጁ ኾነህ በቆምክበት ቦታ ኹሉ አትነቃነቅ፤ በመካነ ጸሎትህ ላይ አዘውትረህ ቆመህ ተገኝ። ለለመነህ ኹሉ ስጥ፤ ከሌለህ ደግሞ እግዚአብሔር ይስጥህ ካለው ያድርስህ ብለህ በለዘበ ቃል ተናገር። የምትሠራውን ሥራ ኹሉ ፊት አይተህ አድልተህ አትሥራ። የደረሰብህን ኹሉ እግዚአብሔርን አመስግነህ ተቀበል። ይህንን ያደረግህ እንደ ኾነ በእግዚአብሔር ትእዛዛትና ሕግጋት አንተ በእውነት ፍጹም ነህ። እኔስ በእውነት የእግዚአብሔርን ጥበብ አደንቃለሁ።" እንዲል። (አባ ገብረ ኪዳን ግርማ ፣ የአራቱ ጉባኤያት የምስክር መምህር)፣ መጽሐፈ ወግሪስ፣ 2013 ዓ.ም፣ ገጽ 51)።

የሕይወት መርሐችን ከላይ በተገለጸው መሠረት ቢኾን በበጎ መጽናት እንችላለን። ክፉ ነገር በሕሊናች ውስጥ በመጣ ጊዜ ወዲያው አስወግደን ብናስወጣው እና ሕሊናችን ውስጥ የእግዚአብሔርን ቃል ኹል ጊዜ ብናስቀምጥ፥ በዚያም ቃል ብንመሰጥበት ሕይወታችን የተስተካከለ ይኾናል። ድንገት ስሜታዊ ኾነን ወደ ክፉ ልንሳብ ስንል ራሳችንን የምንቆጣጠርበት የእግዚአብሔር ቃል ውስጣችን ሊኖር ይገባል። በእርግጥም የሕይወት መርሐችንን በቃለ እግዚአብሔር እያደረግን ስንሄድ ስሜታችን በራሱ በቃለ እግዚአብሔር እየተገራ ይሄዳል። ውስጣችንም በቃለ እግዚአብሔር መመራትን እንደ ግዴታ መቀበል ይጀምራል። እንዲህ ሲኾን ብንጣላ ወዲያው ይቅር እንባባላለን፥ ቢበድሉን እንታገሳለን፥ ቢሰድቡን ስድብ የሚገባን ኃጥእ እንደ ኾን አድርገን እንቀበላለን፣ ቢንቁንም የክፉ ሥራችን ውጤት መኾኑን አምነን ያለተቃውሞ እንቀበላለን። እንዲህ በበጎ እየጸናን ስንሄድ የሚረብሸን ነገር በእኛ ላይ ኃይሉን እያጣ ይሄዳል፤ ሕይወታችንም በፍጹም ሰላምና ዕረፍት ይመላል።

እንግዲህ ምክንያታዊ ነኝ ብለን ከምናስበው አጸፋዊ መልስ ኹሉ እየራቅን እንሄዳለን። እንዲህ ያደረግኹት እንዲህ ስላደረገችኝ/ገኝ ነው እያሉ ከመናገር ኹሉ ነጻ እንወጣለን። በሕይወታችን የሚገጥሙንን ችግር የምንላቸውን ነገሮች ኹሉ የመጋፈጥና የማሸነፍ ብርታታችን ታላቅ ይኾናል። የብዙ ዓመታት ሕማም ቢኾን፣ ወይም የገንዘብ እጦት ችግር ቢኾን፣ ወይም ከሰዎች ዘንድ ፍቅር አጣኹኝ ብሎ የማሰብ ፈተናም ቢኾን እንሻገረዋለን። መጀመሪያ መስተካከል ያለበት አስተሳሰብ እና ነገሮችን የምንረዳበት መንገድ ነው። ሲቀጥልም የመኖር ትርጒሙና ዓላማው ግልጽ ኾኖ ሊገባን ያስፈልጋል። ይህ በትክክል ሲገባን ያን መፈጸም ዋና ዓላማችን እየኾነ ይመጣል። ስለዚህ ሰይጣን ሊጥለንና ጥቅም አልባ ሊያደርገን የሚፈጽምብን ጥቃት ኹሉ ይከሽፋል። በበጎነት ጽናታችንም ድል ይነሣል። ስለዚህ ስንኖር ለምንድን ነው የምኖረው? እንዴትስ እንድኖር ነው ፈጣሪ የሚፈልገው? ፈጣሪስ እንደሚፈልገው መኖር ያልቻልኩት ለምንድን ነው? ለመኾኑ በበጎነት ጸንቼ እንዳልኖር የሚከለክለኝ ምንድን ነው? የሚሉ ጥያቄዎችን ለራሴ እየጠየኩ ሕይወቴን እያስተካከልኹኝ ልኖር ይገባኛል። በምን መመሪያ እንዳንል ከላይ ማር ወግሪስ ያስቀመጠልን ድንቅ የሕይወት መመሪያ አለልን።
ዲ/ን ዮሐንስ ጌታቸው

ለመኖር የተፃፈ📜

#ለሌሎች_ተደራሽእንዲሆን_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ👇👇
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
እንኳን ለጻድቁ አባታችን ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ እረፍት ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

#ዋኖቻችሁን_አስቡ። ዕብ 13:7

ይህን ኃይለ ቃል ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለጊዜው ለዕብራውያን ሰዎች የተናገረው ሲሆን ፍጻሜው ግን በክርስቶስ ክርስቲያን ለተሰኘን ለኛ ለምዕመናን ሁሉ ነው።

ዋኖቻችን እነማን ናቸው ቢሉ ሐዋርያው «የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሯችሁ» በማለት መልሶልናል። እነርሱም ከቀደምት አበው ጀምሮ ነቢያት ሐዋርያት ጻድቃን ሰማዕታት በሙሉ ቅዱሳን ናቸው።

ጻድቁ ገብረ መንፈስ ቅዱስም ገብረ ሕይወትም ይባላሉ።በ562 ዓመታት ሕይወታቸው እንደ ሐዋርያት ከምድረ ግብፅ እስከ ኢትዮዽያ ወንጌልን ሰብከዋል። በዚህም በሚሊየን (አእላፍ) ለሚቆጠሩ ነፍሳት የድኅነት ምክንያት ሆነዋል። “በሕይወት ሆነን ብንኖር ለጌታ እንኖራለንና፥ ብንሞትም ለጌታ እንሞታለን። እንግዲህ በሕይወት ሆነን ብንኖር ወይም ብንሞት የጌታ ነን።” ሮሜ 14፥8 እዳለው ቅዱስ ጳውሎስ ሕይወታቸውን ለክርስቶስ የሰጡ ወንጌልን(የእግዚአብሔርን ቃል) በቃላቸው የሰበኩት ብቻ ሳይሆን አካል አልብሰው ሚዳሰስ ሚታይ አድርገው የኖሩት የዕምነትን ፍሬ ያስመሰከሩ ታላቅ ቅዱስ የቤተክርስቲያናችን አባት ናቸው የንሒሳው ኮከብ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለኢትዮጵያ ልዩ ፍቀር አላቸው። ስለ ሃገሪቱና ሕዝቧ ፍቅር ሲሉ ለ100 ዓመታት በደብረ ዝቋላ መከራን ተቀብለዋል። ምሕረትን ሲለምኑ ሥጋቸው አልቆ በአጥንታቸው ቁመው ነበርና ሃገራችን አሥራት ሆና ተሰጠቻቸው። በ8ኛው ክ.ዘ አካባቢ የተወለዱት አባታችን ያረፉት በ14ኛው መቶ ክ.ዘ አካባቢ ነው። ፍጥረታትን ሁሉ አዘው መጋቢት 5 ቀን ሲያርፉ ግሩማን መላእክት ገንዘው አካላቸውን ሠውረዋል። ጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እረፍታቸው መጋቢት 5 ቀን ነው ይህ ደግሞ በታላቁ ዓብይ ጾም ወቅት ነው ፍትሃ ነገስት አንቀጽ 15 ላይ በዓብይ ጾም በዓል ማክበር ይከለክላል የሀዘን ወቅት ነውና ከበሮ አይመታም እልልታና ጭብጨባ የለም ፍጹም ሀዘን እንጂ የመጋቢት 27 ስቅለት ጥቅምት 27 ቀን እንደሚከበረው ሁሉ ወደ ጥቅምት 5 ቀን ተዛውሮ እንዲከበር ተደረገ፡፡

በመጨረሻም ሐዋርያው እንዳለን ቅዱሳኑን አስበን የነርሱን አሰረ ፍኖት ተከትለን በምግባር በሃይማኖት እንድንመስላቸው አምላካችን በቸርነቱ ይርዳን። እመ አምላክ ወላዲተ አምላክ ሰዓሊተ ምሕረት ፍቅሯን በልባችን ጧዕሟን በአንደበታችን ታኑርልን። የጻድቁ የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን።

መልካም በዓል🤗!

#ለሌሎች_ተደራሽእንዲሆን_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ👇👇
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://youtu.be/UJqDe2vd4N0?si=E8kJBnxk9BUpMwot

ዘመኑን የበከለ ክርስትያኑን ተዓምር ወዳጅ ከድህነት ይልቅ ጊዜያዊ (ስጋዊ) ፈውስ ላይ ብቻ ያተኮረ እዲሆን እና እረኛ እዳጣ መንጋ ከአንዱ ወደአንዱ እዲቅበዘበዝ ያደረ በሽታ ነው እጅግ ሊታሰብበት የሚገባ ትምህርት ነው ተከታተሉልኝ ታተርፉበታላችሁ🤗🤗🤗

“ነገር ግን መናፍስት ስለ ተገዙላችሁ በዚህ ደስ አይበላችሁ፥ ስማችሁ ግን በሰማያት ስለ ተጻፈ ደስ ይበላችሁ።”
— ሉቃስ 10፥20
“ ኢየሱስ ክርስቶስን አስብ፤”2ኛ ጢሞቴዎስ 2፥8

ቸር ዋሉልኝ🤗
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
2024/11/15 14:25:43
Back to Top
HTML Embed Code: