“እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።”
— ኢሳይያስ 53፥5
— ኢሳይያስ 53፥5
"ከሙታን ተነሥቶ ሲኦልን ረግጦ በሞቱ ሞትን ደመሰሰው” (መጽሐፈ ኪዳን)
እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሰን!
የተጻፈው ቢነበብ፣
የተነበበው ቢተረጉም፣
በተተረጎመው ምግባር ቢሠራ፣
የዚህ ኹሉ የሃይማኖት ፍጻሜው "ትንሳኤ" ነው። ትንሳኤ ከሌለ፣ሃይማኖት ኹሉ ከንቱ ነው።
የሃይማኖት የመጨረሻ ዋጋው በትንሳኤ ማክበሩ እንጂ በምድር ማቀማጠሉ( መቀማጠሉ )አይደለም።
ሰው የተፈጠረው ለትንሳኤ ነው፤
የሚኖረውም ለትንሣኤ ነው፤
የሚጽናናውም በትንሣኤ ነው።
ጌታችንም፦
ሥጋውን የበላውን፣ደሙን የጠጣውን ሰው፣
ሰለሚሰጠው ዋጋ ሲናገር
'እሾመዋለኁ፣
እሸልመዋለኁ፣
ጤና እሰጠዋለኁ፣
ሀብት አድለዋለኁ፣
...'አላለም‼️
ይልቁንም
"ሥጋዬን የሚበላ፣ደሜን የሚጠጣ፣የዘለዓለም ሕይወት አለው፤እኔም በመጨረሻ ቀን አነሣዋለኁ" ነው ያለው፤
ሌሎች የማያስፈልጉን ኾነው ሳይኾን፣እነዚያ {ሹመት፣ጤና፣...} የፍጡርነት ዋጋ እንጂ፣የሃይማኖት ዋጋ ስላልኾኑ ነው፤ የሃይማኖት ዋጋ በክብር መነሣት ነውና።
የሃይማኖት ዋጋው ትንሳኤ ነው፤
ሃይማኖት ለጤና፣
ሃይማኖት ለፈውስ፣
ሃይማኖት ለሹመት፣
ሃይማኖት ለመብል...
የሚል መርሕ ያላቸው፣ የአነ ሰዱቃውያን ዘመዶች ናቸው።
ዓላማው ትንሣኤ የኾነ ሰው "ምንም የማይገታው ክርስትና" ይሉሃል ርሱ ነው።
( ጸያሔ ፍኖት-መንገድ ጠራጊ፤በአባ ገ/ኪዳን፤ገጽ ፻፶፰/፫፻፶፬/158/354፤ ፳፻፲፩/2011 ዓ.ም.)
ትንሣኤ ልቡናን ገንዘብ የምናደርግበት በዓለ ትንሣኤ ይሁንልን🙏

“እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።”
— ዕብራውያን 12፥1-2
— ዕብራውያን 12፥1-2
ወንድ ልጅ በገጽ፣ ሴት ልጅ በሕይወት ክርስቶስን ይመስሉታል። ወንድ በራስነቱ ሴት ልጅ ይክበር ይመስገንና ወልድ በፈቃዱ ለአብ እንደ ታዘዘ ለባሏ በመታዘዝ ክርስቶስን ትመስለዋለች። ወንድ እንደ ክርስቶስ ሕይወቱን እስከ መስጠት ደርሶ ሚስቱን እንደሚወዳት እርሷም ለእርሱ ለውዷ በሕይወትና በሞት መካከል ሆና ጽኑ ሕማምን ተቀብላ የፍቅራቸው ፍሬ የሆነውን ልጅ በእቅፉ ታኖርለታለች። እርሱ ጌታችን ጽኑ ሕማምን በመቀበል ሕያው በሆነ ሞቱ እኛን ልጆቹን እንደወለደን።(ዮሐ 16:21)
Shimelis Mergia
Shimelis Mergia
ሁሉም_ክርስቲያን_ካህን_ነውን_በዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ.pdf
323.4 KB
ሁሉም ክርስቲያን ካህን ነውን?
* የ1ኛ ጴጥሮስ 2፥9 እንዲሁም የዮሀንስ ራዕይ 1፥6 ማብራሪያ እና ከ ዘጸአት 19፥6 አንፃር
* ክህነትን የተዳፈሩ ሰዎች
* ካህናት ትሆኑ ዘንድ ምን ማለት ነው?
* የክርስቲያኖች ሁሉ አጠቃላይ ክህነት
++++~~ +++++
እዚህ ላይ ጳውሎስ “ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ አቅርቡ” ሲል አሳሰበን። ሰውነት መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርበው እንዴት ተደርጎ ነው? ብሎ የሚጠይቅ ይኖር ይሆናል። ዓይን ክፉ ነገርን አይመልከት፣ እንዲህ ካደረግህ ዓይንህ መሥዋዕት ሆኖ ቀርቧል ማለት ነው፤ እጅህ ሕገ ወጥ የሆነ ተግባርን አያድርግ፣ ይህ ከሆነ የተቃጠለ መሥዋዕት ሆኗል ማለት ነው። ወይም ይህም ብቻውን በቂ አይደለም፣ በዚህ ላይ መልካም ሥራን መሥራትም ይገባናል እንጂ። እጅ ምጽዋትን ይስጥ፣ አንደበት የሚረግሙትን ይመርቅ፣ ጆሮም የቅዱሳት መጻሕፍትን ትምህርትነውርና በመስማት ደስ ይሰኝ። መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርብ ነገር አንዳችም ነውርና ነቀፋ ያለው ሆኖ ሊቀርብ አይችልምና። መሥዋዕት የሌሎች ተግባራት ሁሉ ቀዳምያት ነውና። ስለዚህም ከእጃችንም፣ ከእግራችንም፣ ከአንደበታችንም፣ ከሌላውም አካላችን ሁሉ ለእግዚአብሔር ቀዳምያትን እናቅርብ። ይህ ዓይነቱ መሥዋዕት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ነው። (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
#መድሎተ_ጽድቅ
#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ

++++

ጸሎተ ፍትሐት.pdf
172.3 KB
ጸሎተ ፍትሐት የሚደረግባቸው መሠረታዊ ምክንያቶች
👉እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ ስለ ሆነ
👉የቤተ ክርስቲያን ባሕርይዋና ማንነቷ የሚገለጥበት ስለሆነ
👉ከዕረፍታቸው በኋላም ሕያዋንና አዋቂዎች ስለ ሆኑ
👉አስተምህሯችን፣ እምነታችን፣ ተስፋችን፣ ... የሚገለጥበት ስለ ሆነ
በዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

ነገረ ክርስቶስ ምዕራፍ ፪ ክፍል ፬
#በነገረ #ክርስቶስ #ላይና #በምሥጢረ #ሥላሴ #ላይ #የተነሡ #ሌሎች #ከሓድያን
፩) መነናውያን:- እነዚህ በማኒ ክሕደት ጸንተው የሚኖሩ ናቸው። በትርጓሜ የሚታወቁ ሁለት ማኒዎች አሉ። አንደኛው ማኒ በብሉይ ኪዳን ዘመን የነበረ "ይህች ዓለም መጋቢ፣ አስተዳዳሪ የላትም፣ ክረምትና በጋ መዓልትና ሌሊት በልማድ ይፈራረቃሉ" ብሎ ሀልዎተ እግዚአብሔርን የካደ ሰው ነው። በእግዚአብሔር እንደልቤ የተባለ ነቢዩ ቅዱስ ዳዊት ለእርሱ ምላሽ የሚሆን አንድ አርእስት ጽፎለታል። መዝ. ፬ የተጻፈው ለማኒ ተግሣፅ ነው። ሁለተኛው ማኒ በሐዲስ ኪዳን ዘመን የተነሣ ሲሆን ወልደ እግዚአብሔር ክርስቶስ ሰው መስሎ በምትሐት ታየ እንጂ ሰው አልሆነም ብሎ የካደ ሰው ነው። ምትሐት ማለት መስሎ የሚታይ ግን ያልሆነ ማለት ነው። የሚዳሰስ የሚመስል ግን የማይዳሰስ ማለት ነው። ነገር ግን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መከራን ተቀበለ፣ ተራበ፣ ተጠማ፣ ተሰቀለ ተብሏል (ዮሐ. ፲፱፣፳፰፣ ማቴ. ፬፣፪፣ ማር. ፲፩፣፲፪)። ምትሐት ደግሞ እንደ ጥላ ስለሆነ አይራብም፣ አይጠማም፣ አይሰቀልም። ስለዚህ የመነናውያን ክሕደት በሐዲስ ኪዳን መሠረት የለሽ ነው ማለት ነው። ቅዱስ ቄርሎስም "እስመ ኢይክል ጽላሎት ሐሚመ" ብሎ ተናግሯል (ድርሳነ ቄርሎስ ፲፩)። በዳግም ትንሣኤ ቶማስ እንዲዳስሰው ያደረገውም ምትሐት እንዳልሆነ ለማጠየቅ ነው።
፪) ሐራጥቃ:- እነዚህ ደግሞ ቃል ሥጋ ኮነ የሚለውን የወንጌላዊው ዮሐንስን ጽሑፍ ምክንያት አድርገው ቃል ተለውጦ ሥጋ ሆነ የሚሉ ናቸው። አምላክ ሰው ሲሆን አምላክነቱ ተለውጦ ሰው ሆነ የሚሉ ናቸው። ካለመኖር ወደመኖር (እምኀበ አልቦ ኀበቦ) መጥቶ የተፈጠረ ፍጥረት መለወጥ ይስማማዋል። እግዚአብሔር ግን በዘመን ብዛት የማይለወጥ አምላክ መሆኑን ሐራጥቃዎች አልተረዱም። ራሱ እግዚአብሔር "እኔ እግዚአብሔር አልለወጥም" ብሎ በነቢዩ አድሮ ተናግሯልና (ሚል. ፫፣፮፣ መዝ. ፻፩፣፳፯)። ስለዚህ ትክክለኛው አስተምህሮ ሰው አምላክ ሲሆን ሰውነቱ አልተለወጠም። ከሰውነቱ ሳይለወጥ አምላክነትን ገንዘብ አደረገ እንጂ። አምላክ ሰው ሲሆንም ከአምላክነቱ አልተለወጠም። ከአምላክነቱ ሳይለወጥ ሰውነትን ገንዘቡ አደረገ እንጂ። ዘእንበለ ውላጤ (ያለመለወጥ) እያልን የምናስተምረው ትምህርት ይህንን ነው።
፫) ፎጢኖስ:- የቃል ህልውና ከማርያም ወዲህ ነው ብሎ የካደ ሰው ነው። ይኽውም ወልደ እግዚአብሔር ዓለም ከመፈጠሩ በፊት ያልነበረ ነው። ፍጡር ከሆነች ከድንግል ማርያም የተገኘ ነው የሚል ነው። ነገር ግን ወልደ እግዚአብሔር ቅድመ ተዋሕዶ በቃልነቱ ጸንቶ የኖረና እናቱን ድንግል ማርያምን የፈጠረ አምላክ ነው። ድንግል ማርያምም ፈጣሪዋን በሥጋ የወለደች ናት። "ድንግል ወለደቶ ለገባሪሃ። ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው። ወለሊሁ ፈጠረ ወላዲቶ። እርሱም እናቱን በጥንተ ተፈጥሮ በሐዲስ ተፈጥሮ ፈጠረ። ነሥአ ሥጋነ ዘውእቱ ፈጠረ። ከእርሷ እርሱ የፈጠረውን ሥጋችንን ተዋሐደ" እንዲል (ሃይ.አበ. ፵፯፣፪)። ወልደ እግዚአብሔር ከድንግል ማርያም በፊት እንደነበረ ራሱም ተናግሯል። "ኢየሱስም፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለኹ አላቸው" እንዲል (ዮሐ. ፰፣፶፰)። በተጨማሪም "አሁንም፥ አባት ሆይ፥ ዓለም ሳይፈጠር ባንተ ዘንድ በነበረኝ ክብር አንተ በራስኽ ዘንድ አክብረኝ" ብሏል (ዮሐ. ፲፯፣፭)።
፬) መርቅያን:- ቃለ እግዚአብሔር በአካላዊነት ያለ ሳይሆን ዝርው ነው ያለ ከሓዲ ነው። ይኽውም እንደ እኛ ቃል ያለ ነው። እኛ ስንናገር ድምፃችን አካል ያለው እንዳልሆነ ሁሉ የእግዚአብሔር ቃልም አካል ያለው አይደለም ማለቱ ነው። ነገር ግን የሰውን ቃል (ድምፅ) ካስተዋልነው የሰው ነው እንጂ ሰው አይደለም። የእግዚአብሔር ቃል ግን የእግዚአብሔር ተብሎ የሚነገር ብቻ ሳይሆን ራሱም እግዚአብሔር ነው። "በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ" እንዲል (ዮሐ. ፩፣፩)። የፍጡራን ቃል ዝርው ሲሆን ነው። የእግዚአብሔር ቃል ግን አካላዊ ነው። "ወለዝንቱ ስም ዘውእቱ ቃል ንሌብዎ እምሠለስቱ ቃላት። ይህንን ስም ከሦስቱ ቃላት ለይተን እናውቃለን። እነዚህም አተርጋዎን፣ አአትሪኮን፣ ቦርፎሪኮን ናቸው" እንዲል (ሃይ.አበ.፲፫፣፳፪)። አተርጋዎን የሚባለው የሰው ቃል ነው። ቦርፎሪኮን የሚባለው ነቢያት ከእግዚአብሔር የሰሙት ቃል ነው። ይኽውም ለእነርሱ የተሰማው ድምፅ ዝርው መሆኑን ያሳውቃል። ለእነርሱ የተሰማውን ዝርው ድምፅ (ቃል) የተናገረው ግን አካላዊ ቃል መሆኑን መዘንጋት አይገባም። ይኽውም ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ አካላዊ ቃል ሲሆን ለሐዋርያትና ለሕዝቡ ሲያስተምር የተሰማው ቃሉ (ድምፁ) ግን ዝርው እንጂ አካል ያለው እንዳልሆነ ልብ ማድረግ ይገባል። አአትሪኮን የሚባለው የእንስሳት ድምፅ (ቃል) ነው። ድምፅ የሚባለው የሚሰማው ሲሆን ቃል የሚባለው የድምፁ መልእክት (ፍሬ ነገር) ነው።
፭) አቡሊናርዮስ:- ይህ ደግሞ ለክርስቶስ ሥጋዊ ነፍስና ልቡና የለውም። በሥጋዊ ነፍሱና ልቡ ምትክ መለኮቱ ሆነው ያለ ከሓዲ ነው። አቡሊናርዮስና ተከታዮቹ እንዲህ ያሉት ቃል ሥጋ ሆነ አለ እንጂ ቃል ነፍስን ሆነ አይልም ብለው ነው። ነገር ግን ቅዱሳት መጻሕፍት ሰውን ነፍስም፣ ሥጋም ብለው ይጠሩታል። ሥጋ ሲጠራ ነፍስን ዘንግተው አይደለም። "ለሥጋ ሁሉ ምግብን የሚሰጥ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና" እንዲል (መዝ. ፻፴፭፣፳፭)። መቼም በዚህ ጊዜ ነፍስን ዘንግቶ አይደለም። ምክንያቱም ነፍስ የሌለው ሥጋ መጀመሪያውንም ምግብን አይበላምና ነው። ሬሳ ሲበላ አይተን አናውቅም። ነፍስ ስትጠራም ሥጋን ዘንግተው አይደለም። ለምሳሌ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ "ጥቂቶች ማለት ስምንት ነፍስ በውሃ የዳኑበት መርከብ ሲዘጋጅ፥ የእግዚአብሔር ትዕግሥት በኖኅ ዘመን በቈየ ጊዜ ቀድሞ አልታዘዙም" ብሏል (፩ኛ ጴጥ. ፫፣፳)። መቼም ስምንት ነፍስ የዳነባት ሲል እነኖኅ የዳኑት ከነሥጋቸው ነውና። ይህን የመሰለ ራሱ ክርስቶስም ብዙ ቦታ ተናግሯል። ራሱን ብዙ ጊዜ የእግዚአብሔር ልጅ እያለ ጠርቷል። በዚህ ጊዜ የሰው ልጅ መሆኑንም እያሰበ ተናግሯል። ራሱን ብዙ ጊዜም የሰው ልጅ እያለ ጠርቷል። በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑንም እያሰበ ተናግሯል። ክርስቶስን ነፍስ የለውም ካሉ ፍጹም ሰው አይደለም ያሰኝባቸዋል። ነፍስ የሌለው ሰው የለምና። ክርስቶስ ነፍስ እንዳለው ግን "ነፍሴ እስከ ሞት ድረስ እጅግ ዐዘነች በዚህ ቈዩ፥ ከእኔም ጋራ ትጉ አላቸው" ተብሎ ተገልጿል (ማቴ.፳፮፣፴፰)። ስለዚህ ቃል ሥጋ ኮነ ሲል በሥጋ በጠቅላላው የሰውን ማንነት መግለጥ ስለሆነ ነፍስን አልነሣም አያሰኝም። በነፍሱ ምትክ መለኮቱ ሆነው ለማለት አያስኬድም። ይህንን ትምህርት ውድቅ የሚያደርገው ሌላው ጉዳይ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነፍሱን ከሥጋው በዕለተ ዓርብ መለየቱ ነው። በመስቀል ተሰቅሎ ሞተ በሦስተኛውም ቀን ከሙታን መካከል ተነሣ እንላለን። ሞት ማለት የነፍስ ከሥጋ መለየት ነው። በነፍሱ ምትክ መለኮቱ ነው ካሉ መለኮት ከሥጋ ተለየ ያሰኛል። መለኮት ከሥጋ ከተለየ ደግሞ መለኮት የሌለበት ቦታ አለ ያሰኛል። መለኮት ግን የማይኖርበት ቦታ የለም።

Telegram
በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw
አቀድም አእኵቶቶ ለእግዚአብሔር
፮) መለካውያን ኦርቶዶክስ:- መለካውያን ኦርቶዶክሶች (የግሪክ፣ የሩሲያ፣ የዩክሬን እና ሌሎችም ካሉ) እንደ እኛ እንደ አኃት አብያተ ክርስቲያናት (ኢትዮጵያ፣ አርማንያ፣ ሶርያ፣ ግብፅ፣ ሕንድ፣ ኤርትራ) መንፈስ ቅዱስን ዘሠረፀ እምአብ በማለት አንድ ናቸው። በዚህ አንድ ብንሆንም ክርስቶስን አንድ አካል ሁለት ባሕርይ በማለታቸው ግን እንለያያለን። መለካውያን ኦርቶዶክሶች ከካቶሊክ የተለዩት በ11ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ነው። አንድ አካል ሁለት ባሕርይ በማለት ከካቶሊክ ጋር ተመሳሳይ ናቸው። ይህ ደግሞ ስሕተት እንደሆነ ነገረ ክርስቶስ ምዕራፍ ፪ ክፍል ፫ በሚለው ትምህርታችን ተማምረናል። ካቶሊኮች ግን አንድ አካል ሁለት ባሕርይ በሚለው ክሕደት ላይ መንፈስ ቅዱስን ዘሠረፀ እምአብ ወእምወልድ በማለት ይክዳሉ። አብ ወልድን የወለደው፣ መንፈስ ቅዱስን ያሠረጸው ቅድመ ዓለም ነው። ቅድመ ዓለም ነው ስንል መነሻ አለው ማለታችን አይደለም። ከሰው መታሰብ በላይ ነው ያሰኘው ይህ ነው። ሊቁ በሃይማኖተ አበው "ዘኢየኀልቅ ልደቱ" ያለውም ሁልጊዜም ወልድ ሲባል ይኖራል ለማለት ነው እንጂ ሁልጊዜ ይወለዳል ማለት አይደለም። ዘኢየኀልቅ ልደቱ ሲል ልደት ወልድና ከሚለው ጋር በምሥጢር ይገጥማል።
የዩቲይብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ
https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።
ቀጣይ በክፍል ፭ ቀሪዎቹን እንመለከታለን ይቆየን።

ብዙዎች በሰርጋቸው ቀን "የአገራችን ባሕል ነው" የዘፈን ድግስን ያዘጋጃሉ። ወይም ደግሞ "ቤተሰብ እሺ አይልም" በማለት እንደሚቸገሩ ይናገራሉ። ነገር ግን ይህን የቅዱስ ዮሀንስ አፈወርቅ ቃል ማስታወስ ይገባል
"ጋብቻ ዝሙትን የምናጠፋበት መድኃኒት ነው። ስለዚህ በዲያብሎስ ስራ (በዘፈን) ጋብቻን አናቃልል። ከዚህ ይልቅ አሁን የሚያገቡ ሰዎች በቃና ዘገሊላ እንደ ኾነው ያድርጉ። በመካከላቸው ጌታችን ክርስቶስ እንዲኖር ያድርጉ። "እንዴት ይህን ማድረግ ይችላሉ? ብሎ የሚጠይቅ ሰው ሊኖር ይችላል። ካህናትን በመጥራት! 'እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል' ይላልና (ማቴ 10:40)። ስለዚህ ዲያብሎስን አርቁት። የሴሰኝነት ዘፈኖችን፣ የርኵሰት ዜማዎችን፣ ሥርዓት የለሽ ጭፈራዎችን፣ የሚያሳፍሩ ቃሎችን፣ ዲያብሎሳዊ ትርኢቶችን፣ ሁከቶችን፣ቅጥ ያጡ ሳቆችን፣ ሌሎች እነዚህን የመሰሉ አግባብ ያይደሉ ነገሮችንም አስወግዱ። በእነዚህ ፈንታም የጌታችን ክርስቶስ ቅዱሳን አገልጋዮችን ጥሩ ፣ በእነርሱም በእውነት ያለ ሐሰት ከእናቱና ከወንድሞቹ ጋር በሰርጋችሁ ላይ ይገኛል። " በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ እርሱ ወንድሜ እኅቴም እናቴም ነው" ብሏልና (ማቴ 12:50)።
አንዳንድ ሰዎች እንደዚህ ያሉ ተግሣጻትን ስለምናገርና የጥንት ባሕሎችን ስለማስቀር አሰልቺና አስቸጋሪ እንደ ኾንኩ አድርገው እንደሚያስቡ ዐውቃለው። ነገር ግን እነርሱ ስለ ተቃወሙኝ በፍጹም አልጨነቅም። እኔ የምፈልገው በእናንተ ዘንድ ተቀባይነትን ማግኝት ሳይኾን የእናንተን ጥቅም ነውና። ከዚህ ጥበብ ጥቅምን እንድታገኙ እንጂ እንድታመሰግኑኝ አልፈልግምና። ስለዚህ "ይህ ባሕል ነው" ብሎ አንድ ሰውስ እንኳ አይንገረኝ። ኀጢአት በድፍረት የሚፈፀምበት እስከ ኾነ ድረስ ባሕሉን እርሱት። ክፉ ሣራ የሚሰራባቸው እስከ ኾኑ ድረስ ባህሎቹ የቱንም ያህል ጥንታውያን ቢሆኑ ከእናንተ አስወግዷቸው። ክፉ ስራ የማይሰራባቸው ከኾኑ ግን ያልተለመዱ እንኳን ቢሆኑ ተቀበሏቸው።