Telegram Web Link
“እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው ሕይወትም ነው።” (ዮሐ. 6፥63)
***
የክርስትና አስተምህሮ አመክንዮአዊ ቀመር እና የቃላት ብያኔ ብቻ አይደለም። ጌታችን እንደነገረን ከዚያ የሚያልፍ መንፈስ ነው፤ ሕይወትም ነው። በመሆኑም አንድ ንባብ በቅዱሳት መጻሕፍት ቢገኝም 'መንፈሱን' ካልተረዳን እንስታለን። ያ አገላለጽ የተነገረው ምንን ለማጠየቅ ነው? ምን ብለን ብንረዳው ደግሞ ስህተት ይሆናል? ብሎ ትውፊታዊ መረዳትን ይጠይቃል። አንዳንዶቹ አገላለጾች ደግሞ እጅግ ትልቅ ቅጥነተ ህሊና ይጠይቃሉ። ከእነዚህ አንዱ 'ፈጣሪ ወፍጡር' የሚለው ትምህርት ነው።
ሁለት ባህርይ የሚሉ ካቶሊኮች እንኳ ክርስቶስን 'በሥጋው ፍጡር' ማለት በትክክለኛ ዓውዱ ከተነገረ ስህተት ባይሆንም ምእመናን እንዳይደናገሩ በነገረ ሃይማኖት ሐተታዎች ውስጥ በብዛት አንጠቀመውም ይላሉ። (Catholic Encyclopedia)
ይህ ጥንቃቄ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ውስጥም ያለ ነው። እኔ እስከማውቀው በአምልኮ መጽሐፎቻችን ውስጥ አይነገርም። እጅግ አልፎ አልፎ የሚገኘው በአንዳንድ ሊቃውንት ድርሳናት ውስጥ ነው። ይህ የሚያመለክተው አገላለጹ በቅጥነተ ህሊና ከነሙሉ ዓውዱ ካልተረዱት ምእመናን 'በሥጋው ፍጡር ስለሆነ በሥጋው አናመልከውም' ብለው እንዳይሰናከሉ ነው።
'ክርስቶስ በሥጋው ፍጡር ነው' ሲባል፦
1. የለበሰው ሥጋ ዘላለማዊ ህልውና ያልነበረው የእኛ የተፈጠረ እውነተኛ ሥጋ ነው ለማለት ነው።
2. የሰው ልጆች ሐዲስ ተፈጥሮ (መታደስ) ከእርሱ የተጀመረበት ዳግማይ አዳም፣ በኲረ ፍጥረታት መሆኑን ለመናገር ነው። ቅዱስ ጎርጎሬዎስ ዘእንዚናዙ እንዳለው ያልነሳውን አላዳነምና።
3. ሌሎችም።
***
ነገር ግን ከነዚህ እሳቤዎች መጠንቀቅ ደግሞ ይገባል፦
1. 'ክርስቶስ በሥጋው ፍጡር ነው' ማለት በሥጋው አምልኮ አይገባውም ማለት አይደለም። የክርስቶስን ሥጋ ከመለኮቱ ለይተን በመለኮቱ ብቻ እናምልክ ካልን የማይከፈለውን አንዱን ክርስቶስን እየከፈልነው ነው፤ ስለ መዳናችን ሰው የሆነውን ክርስቶስን ስለእኛ ሰው በመሆኑ ዝቅ እያደረግነው ነው። ስለ ሕዝቡ ሲል ከአባቱ ዙፋን ወርዶ ሕዝቡ የሚለብሱትን መናኛ ልብስ ለብሶ የሚታደገውን የንጉሥ ልጅ ውለታ ባለመረዳት 'በዚህ ሁኔታ እንደ ንጉሥ አናይህም' ብሎ እንደመሳለቅ ነው።
2. 'ክርስቶስ በሥጋው ፍጡር ነው' ማለት በሥጋው ማኅየዊ (ሕይወትን የሚሰጥ) አይደለም ማለት አይደለም። ይህ ቢሆን ቅዱስ ቄርሎስ እንዳለው ሥጋውን እና ደሙን መቀበል ከንቱ በሆነ!
3. 'ክርስቶስ በሥጋው ፍጡር ነው' ማለት በሥጋው ለአብ ይገዛል ማለት አይደለም። አብ ከፍ ከፍ አደረገው፣ ከስሞች ሁሉ በላይ የሆነ ስምን ሰጠው የተባለ በሥጋው ነው። ታዲያ ይህ ከፍታ ከመገዛት የማያወጣ ከሆነ ከቅዱሳን የጸጋ ክብር በምን በለጠ? ቅዱስ አትናቴዎስ እንዳለው ከፍጡራን ግብርናት እስካልወጣ ድረስ ምን ቢከብር ለእርሱ የሚገባ ክብር አይደለም። በቅዱሳት መጻሕፍት ስለ ክርስቶስ የተነገሩ የትሕትና ንግግሮች ከማዳን ግብሩ እና አርአያነቱ (economy of salvation) አንጻር የምንረዳቸው ናቸው። ካልሆነ ግን በክርስቶስ ዘንድ ሰው ከመሆኑ የተነሣ ዘላለማዊ ተዋርዶ ገብቷል ያስብላል።
በሥላሴ አካላት ዘንድ ከአንዱ ወደሌላው የሚፈስ ዘላለማዊ ክብርና ምሥጋና አለ። ነገር ግን ሰው ከመሆኑ የተነሣ በወልድ ዘንድ የፍጡር አምልኮ ግዴታ አልወደቀበትም። ቅዱስ ጎርጎሬዎስ ዘእንዚናዙ እንዳለው ይህን አብም አይፈልግም፤ ወልድም አይሰጥም።

Bereket Azmeraw
ስብከታችን እኛን ራሳችንን መለወጥ ሳይችል ሌሎችን እንዲለውጥ መመኘት ሞኝነት ነው። መጽሐፋችን በእኛ ላይ መልካም ለውጥን ካላመጣ ሌላው ገዝቶ እንዲያነበው ማስተዋወቅ ከንቱ ድካም ነው። ስብከታችን፣ መጽሐፋችን መጀመሪያ መለወጥ ያለበት እኛን ራሳችንን ነው።

አንድ መጽሐፍ ወይም ስብከት ከሚከተሉት ነገሮች ቢያንስ በአንዱ ሊጠቅመኝ ይገባል።

ጥሩ ስነ ምግባር እንዲኖረኝ ማድረግ
የክህሎት እድገት እንዲኖረኝ ማድረግ
ሃይማኖታዊ ዕውቀት እንዲኖረኝ ማድረግ
ከክፉ ሥራዎች ማራቅ
የሕይወትን መንገድ ማሳየት
መልካምን እንዳስብ ማድረግ

አለበት። እኛ ስድብን ሳንተው ሌላው ሰድብን እንዲተው መስበክ አስቂኝ ነው። እኛ መኖር ያቃተንን ሕይወት ሌሎች እንዲኖሩት አብዝቶ መናገር ከንቱነት ነው። ሌሎች የእኛን ቃል ሰምተው ሊለወጡበት ይችላሉ። እኛ ግን እንደ ገንዳ ሆነን እንቀራለን። የክርስትና ሕይወት በልብ የሚያስቡት፥ በቃል የሚናገሩት፣ በተግባር የሚያሳዩት ሕይወት ነው።

በመንፈሳዊ ሕይወታችን ለማደግ እናንብብ፣ እንማር፣ እንጠይቅ።

© በትረ ማርያም አበባው
ይህ ሰው ድሀ፣ ለማኝ ወይም ቤት አልባ አይደለም ይልቅስ በአለም ስነ-ጽሁፍ ገዝፎ የሚታየው ሊዮ ቶልስቶይ ነው። ቶልስቶይ በሩሲያ ውስጥ ሰፊ መሬት እና ትልቅ ሀብት የነበረው ቢሆንም፤ ሀብቱን ሁሉ ለድሆች፣ ለምስኪኖች፣ ለችግረኞች እና ለቤት ፈላጊዎች በመስጠት የራሱን ህይወት ባልተጋነነ መለኩ የኖረ ሰው ነው።

ታዋቂ ከምንላቸው አባባሎችሁ መኃል፦

"ስለ ሀይማኖት ብዙ አትንገረኝ፣ ነገር ግን በድርጊትህ ውስጥ ሃይማኖትህን እንዳይህ ፍቀድልኝ።"

“ህመም ከተሰማህ በህይወት አለህ፤ የሌሎችን ህመም ከተሰማህ ግን በውኑ አንተ ሰው ነህ”
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"የካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ብዙ ችግር ያመጣባት ከልክ ማለፍ ነው"

"ኦርቶዶክሳዊነት መጠን ነው"

"ከመጠን ያለፈ ነገር ሁሉ ከሰይጣን ነው"

ዲ/ን ያረጋል
በምሥጋና ዐረገ፤ ቤተ ክርስቲያኑንም ከፍ ከፍ አደረጋት።
***
እየታያቸው ከፍ ከፍ አለ፤ የባሕርይ ክብሩን የምታመለክት ደመና ተቀበለችው። በእርሱ ዕርገትም አካሉ የሆነች ቤተ ክርስቲያን በእርሱ ሆና ከፍ ያለች እና በሰማያዊ ሥፍራ የተቀመጠች ሆነች።
የዚህ ዓለም ኃያላን የሚያናንቋት ሐረገ ወይን የተባለች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሥሯ በምድር ቢሆን ቅርንጫፎቿ በሰማይ ናቸው። ይህ ምን ይደንቅ!
አንዳንድ አገልጋዮቿ በሥርዓተ አምልኮዋ በዘፈቀደ እና በቸልተኝነት የምንመላለስባት ቤተ ክርስቲያን በመንቀጥቀጥ የሚያገለግሉ ሰማያውያን መላእክት ጋር ኅብረት ያላት ናት። በላይ በበጉ ዙፋን የምትቀድስ ናት! ለዚህ ጸጋዋ አንክሮ ይገባል!
ይህ ሁሉ የሆነው ግን ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ አባቱ ያቀርበን ዘንድ በእኛ ሥጋ ከፍ ከፍ ብሎ በአብ ቀኝ በመቀመጡ የተሰጠን ጸጋ ነው።
***
"እስከ ቢታንያም አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው።
ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ።
እነርሱም፤ ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፥
ዘወትርም እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እየባረኩ በመቅደስ ኖሩ።"
***
(ሉቃ. 24፥50-53)
ከንቱ ውዳሴን አልወድም ያለ ሰው ሲሰድቡት ከተከፋ በከንቱ ውዳሴ ላይ ውሸታምነትን ደርቦ የያዘ መሆኑን እንረዳለን። ሲሰድቡት ለምን ተሰደብኩ ብሎ ለክብሩ የሚጨነቅ፣ አንድ ሰው ክፉ ቃል ተናገረኝ ብሎ የሚቦልክ ወይም ከጓደኝነት የሚያወጣ ሰው ሐዋርያዊ አይደለም። ሐዋርያት ጌታን ሲከተሉ መጀመሪያ እከብር ባይ ልቡናን ትተው ነው። እውነትን በመናገራቸው የደረሰባቸውን ነቀፋ፣ ስድብ፣ መደብደብ፣ በሰይፍ መቀላት በደስታ ተቀብለውታል እንጂ አላጉረመረሙም። ሐዋርያዊ የሆነ ሰው መሪው ክርስቲያናዊ ዓላማው ነው እንጂ የሰዎች ሙገሳና ጩኸት አይደለም። ከንቱ ውዳሴን አምርረን መጥላት አለብን። መመስገን ያለበት በሁሉ ፍጹም የሆነ እግዚአብሔር ነው። አንድም ተጋድሏቸውን ጨርሰው በአፀደ ነፍስ ያሉ ቅዱሳን ናቸው። ክርስቲያን እንደ ጌታው ከምድር ከፍ ብሎ መውጣት (ማረግ) ይገባዋል። ሐዋርያት የሰውን ሙገሳ ንቀው የኖሩት ከሰው ተለይተው እንደ ጌታቸው ከፍ ከፍ ብለው በመውጣታቸው ነው።

በሰማይ የሀሉ ልብክሙ
በሰማይ የሀሉ ልብነ

© በትረማርያም አበባው
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ "እኔ ሕይወት ነኝ" ብሏል

ክርስቶስ 'እኔ ሕይወት ነኝ' ሲል እውነተኛ ሕይወት በእርሱ ተጀምሯል፣ በእርሱም ትቀጥላለች፣ እናም በእርሱ ያበቃል ማለት ነው። በክርስቶስ አምኖ በእርሱ የሚኖር ሁሉ የዘላለም ሕይወትን ያገኛል፣ እርሱ የማይጠፋ የሕይወት ምንጭ ነውና…

ክርስቶስ ሕይወት ነው ምክንያቱም በኃይሉ ከሞት በመነሣቱ እና በትንሣኤው የዘላለም ሕይወትን መንገድ ስለጠራልን። ከክርስቶስ ጋር ያለን አንድነት ከሕይወት ጋር ያለን አንድነት ነው፣ ዐዲስ እና ክቡር ሕይወት እንድንኖር ብርታት ይሰጠናልና…

በክርስቶስ ያለው ሕይወት እውነተኛ ሰላምና ደስታ የተሞላ ሕይወት ነው። በክርስቶስ ስንሆን፣ ሕይወትን በፍፁም ትርጉሙ፣ ከሞት በላይ የሆነና ጊዜን የሚጋፋ ሕይወት እናገኛለን።

አቡነ ሺኖዳ
“ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል።”
(ያዕ. 4፥8)
***
የመልካም ነገር ጅማሮ ከማን ነው? ከእግዚአብሔር ወይስ ከሰው? የዚህ ጥያቄ መልስ ግልጽ ነው፦ የመልካም ነገር ሁሉ ምንጭ ከእግዚአብሔር ነው። ታዲያ ያዕቆብ በመልእክቱ "ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል፤" ብሎ ሲናገር መቅረብ ከሰው የሚጀምር ይመስል የእኛን ኃላፊነት ቀድሞ መናገሩ ለምንድር ነው? ብለን እንጠይቃለን። መልሱ የሚከተለው ነው፦ እግዚአብሔርማ ሁሉን ፈጽሞ ትቀበለው ዘንድ እየጠበቀን ነው። ከሰው በኩል ግን መቀበል ይገባል። እንዴት ነው የምንቀበለው? በእምነት፣ በንስሐ፣ ከኃጢአት ጋር ተጋድሎ በማድረግ እና በክርስቶስ ትእዛዛት ለመኖር በመጣር ነው። እነዚህ ነገሮች የጸጋ ሁሉ ምንጭ ወደሆነው እግዚአብሔር ለመቅረብ ጽኑ ፈቃዳችን በውስጥም በውጭም የምንገልጽባቸው ናቸው። እግዚአብሔር በእንዲህ ያለ ተግባር ውስጥ ሲያየን በእኛ ጥረት ሊገኝ የማይችለውን ዘላለማዊ ድኅነት ያጎናጽፈናል፤ የጸጋ አማልክት እስክንባል ደርሰን የእርሱ ጸጋ የሞላብን ያደርገናል። በእርሱ ዘንድ በባሕርዩ ያለ ቅድስናን ወደ እርሱ ቀርበን እናገኘው ዘንድ ይሰጠናል። ይህን ሁሉ የምናገኘው ከእኛ ብቃት ሳይሆን ከእሱ ጸጋ ነው፤ ነገር ግን በየጊዜው በምናደርገው የእምነት መታዘዝ እና ተጋድሎ ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ እና እርሱን ለመምሰል ያለነን በተግባር የተፈተነ ጽኑ ፈቃድ እንገልጣለን።
***
“ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል። እናንተ ኃጢአተኞች፥ እጆቻችሁን አንጹ፤ ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ፥ ልባችሁን አጥሩ።
ተጨነቁና እዘኑ አልቅሱም፤ ሳቃችሁ ወደ ኀዘን ደስታችሁም ወደ ትካዜ ይለወጥ።
በጌታ ፊት ራሳችሁን አዋርዱ ከፍ ከፍም ያደርጋችኋል። ...
እንግዲህ በጎ ለማድረግ አውቆ ለማይሠራው ኃጢአት ነው።”
***
(ያዕ. 4፥8-12)

Bereket Azmeraw
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በበዓለ ኀምሳ ምንባብ ላይ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ጰራቅሊጦስ ስለተባለበትና ተስፋ በተሰጣቸው በኀምሳኛው ቀን ወርዶ ስለ ሠራው ሥራ እንዲህ በማለት ያብራራል። ‹‹ወመንፈስ ቅዱስኒ ኢተሰምየ ጰራቅሊጦስሃ ዘእንበለ አመ ይቤሎሙ እግዚእ ኢየሱስ ለአርዳኢሁ እፌኑ ለክሙ ካልአ ጰራቅሊጦስሃ። ጰራቅሊጦስ ብሂል ናዛዚ ብሂል በነገረ ጽርዕ ……መንፈስ ቅዱስም ጌታ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ሌላውን አጽናኝ እልክላችኋለሁ›› ከማለቱ በፊት ጰራቅሊጦስ አልተባለም ጰራቅሊጦስ ማለት በጽርዕ ቋንቋ አጽናኝ ማለት ነው ስለምን አጽናኝ ተባለ ደቀ መዛሙርቱ ወልድ ካረገበት ቀን ጀምሮ ጰራቅሊጦስ እስከ ወረደበት ቀን ድረስ  ያለቅሱ ነበረና ስለዚህም ወልድ መንፈስ ቅዱስን ጰራቅሊጦስ አለው። የስሙ ትርጓሜ ግን አስቀድመን እንደተናገርነው አጽናኝ ማለት ነው። (ዮሐ. ፲፬፥፲፭)
በዓለ ጰራቅሊጦስ የሚከበረው ርደተ መንፈስ ቅዱስን መሠረት በማድረግ በመሆኑ ምክንያት ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ለመቀበል ነው፤ በዕለቱም ኢየሩሳሌም በተባለችው ቤተክርስቲያን ስለመጽናት፤ ከግለኝነት ይልቅ መንፈሳዊ አንድነትን ስለማስቀደም እና ስለመጸለይ  እንማራለን፡፡
በዓለ ትንሣኤውን በቸርነቱ በሰላም እንድናሳልፍ ፈቅዶ እስከ ዛሬ ድረስ ስለ ጠበቀን፣ አሁን ደግሞ በጾም፣ በጸሎት ሆነን እርሱን የምናመሰግንበትን ወቅት ስላመጣልን አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር ስሙ ለዘለዓለሙ የተመሰገነ ይሁን፤ ፆሙን የበረከት የምህረት የቸርነት ያርግልን አሜን፡፡
"የእግዚአብሔር ጸጋ የምትሰጠው እምነታቸውን ለሚናገሩት ሳይሆን እምነታቸውን ለሚኖሩት ነው።"
~ ቅዱስ ጎርጎሪዎስ ነባቤ መለኮት

“በተግባርና በእውነት እንጂ በቃልና በአንደበት ብቻ አንዋደድ።”
  — 1ኛ ዮሐንስ 3፥18
የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትን መስማት ቤተ ክርስቲያንን መስማት ነው ምክንያቱም ሊቃውንት የቤተ ክርስቲያን አንደበቶች ናቸውና
መንፈስ ቅዱስ አስቀድሞ በነቢያት በኋላም በሐዋርያት በኩል እንደተናገረ ዛሬም በተለያዩ መምህራን አድሮ ያስተምራል

በዘመናችን ርቱዕ አንደበት ከዕውቀት ጋር
ትሕትና ከትጋት ጋር
ቅንነት ከሊቅነት ጋር የተባበረላቸው አራት ዓይናው ሊቅ ሊቀ ሊቃውንት ዮሴፍ ደሳለኝ
#ዳቤር በሚል የሚዲያ አማራጭ ከኦሪት ዘፍጥረት እስከ ራእየ ዮሐንስ በተከታታይ ሊያስተምሩን መጥተዋል
ስለሆነም ይህንን ከታች የተያያዘውን ሊንክ በመጫን ወይም ዳቤር ብለን #youtube ላይ #search በማድረግ እና #Subscribe በማድረግ ሊንኩን ለሌሎችም በማጋራት እንድንከታተል ተጋብዘናል ።
ሊቃውንቱን ወደ መገናኛ ብዙኃን መረብ በማምጣት እናበረታታ

https://youtube.com/@yosef-daber?si=-jwo1UTiPZRMfOte
ወላዲተ_አምላክ_በዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ.pdf
352.7 KB
ወላዲተ አምላክ

*እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም "ወላዲተ አምላክ" ትባላለችን? ለምን?

* "ወላዲተ አምላክ" የቃሉ ትርጉም

* የቃሉ ነገረ መለኮታዊ ፋይዳ

* የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክነት በመጽሀፍ ቅዱስ ትምህርት

* የእመቤታችን ወላዲተ አምላክነት-በቀደምት አበው ትምህርት

+++++++++~~~+++++++

ቅዱስ ቄርሎስ ንስጥሮስ “ወላዲተ አምላክ” የሚለውን መቃወሙ በነገረ ክርስቶስና በነገረ ድኅነት ላይ የሚያስከትለው ነገር መሠረታዊ የሆነ ኑፋቄ መሆኑን በሚገባ አስረድቷል፡፡ እነዚህን ነገሮችም እንደሚከተለው በሚገባ ለይቶ አውጥቷቸዋል፡-

ከድንግል ማርያም የተወለደው አካላዊ ቃል የእኛን ባሕርይ ነሥቶ (ተዋሕዶ) ሥግው ቃል ካልሆነና ሰው ብቻ (ዕሩቅ ብእሲ) ከሆነ መዳናችን አደጋ ላይ ይወድቃል፡፡ ምክንያቱም ክርስቶስ የተቀበላቸው ሕማማትና መከራዎች የሥግው ቃል (ሥጋን የተዋሐደውና የእኛን ባሕርይ ባሕርዩ አድርጎ ሰው ሆኖ በሥጋ የተገለጠው አካላዊ የእግዚአብሔር ቃል) ሕማማትና መከራዎች ሳይሆኑ የዕሩቅ ብእሲ (የስው ብቻ) ይሆናሉና፡፡ ፍጡር በሆነ በሰው ብቻ መዳን አይቻልምና ስለዚህ ድነናል ማለት አይቻልም፡፡ ስለዚህ ወላዲተ አምላክ የሚለውን ቃል መካድ የአምላክን ሰው የመሆን ምሥጢር (ምሥጢረ ሥጋዌን) እና የሰውን መዳን መካድ ነው፡፡

እንደዚሁም አካላዊ ቃል አዲሱን ሰው ዳግማዊ አዳምን ለመፍጠር አካላዊ ቃል ከእኛ ባሕርይ ጋር ሊያደርግ የሚያስፈልገው ተዋሕዶ፡ ንስጥሮስ እንዳለው ዓይነት አፍኣዊና የጉርብትና ዓይነት ዝምድና ሳይሆን፣ ውሳጣዊና ባሕርያዊ የሆነ ጥብቅ እና አማናዊ የሆነ ተዋሕዶ ያስፈልገው ነበር፡፡ ይህ አይደለም ከተባለ የባሕርያችን መታደስ፡ በሐዲስ ተፈጥሮ የመዳናችን ነገር ሁሉ ከንቱ ይሆናል፡፡

#መድሎተ_ጽድቅ

#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ
🤑💵 🇫 🇴 🇷 🇪 🇽 𝗧𝗿𝗮𝗱𝗶𝗻𝗴 መማር የምትፈልጉ የሚገርም የ Forex  ቻናል ያውቃሉ

💶  𝗖𝗶𝘁𝘆 𝗙𝗼𝗿𝗲𝘅 𝗘𝘁𝗵𝗶𝗼𝗽𝗶𝗮 💶

@City_Forex_Ethiopia ይባላል ።
ተመዝገባችሁ መማር የምትፈልጉ አናግሯቸው እስከ 𝟰𝟬% Discount የሚደርስ ቅናሽ አድርገዋል !

    ☎️   +251977338586       🇪🇹
    ☎️   +251977338586       🇪🇹


      ይህን ይጫኑት  ይህን  ይጫኑት  ይህን ይጫኑት
      
👇👇 ይህን ተጭነው መመዝገብ ይችላሉ   !👇👇


█▓▒░        ►OPEN◄░►OPEN       ▒▓█
█▓▒░         ►OPEN◄░►OPEN      ▒▓█
█▓▒░         ►OPEN◄░►OPEN      ▒▓█
█▓▒░        ►OPEN◄░►OPEN       ▒▓█
💸💸💸💸💸💸💸💸💸💸💸💸💸💸💸💸💸💸💸



👆 ይህን ይጫኑት  ይህን  ይጫኑት  ይህን ይጫኑት 👆

🇫 🇴 🇷 🇪 🇽    🇹 🇷 🇦 🇩 🇮 🇳 🇬

🇫 🇴 🇷 🇪 🇽    🇹 🇷 🇦 🇩 🇮 🇳 🇬


🎯 𝗔𝗱𝗱 𝗬𝗼𝘂𝗿 𝗖𝗵𝗮𝗻𝗻𝗲𝗹

👇 ምርጥ ምርጥ ቻናሎችን ከፈረጉ ከስር ያለውን ይጫኑ 👇
2024/06/28 09:26:26
Back to Top
HTML Embed Code: