This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
†
[ ኦርቶዶክሳዊነት ማለት ! ]
† † †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
[ ኦርቶዶክሳዊነት ማለት ! ]
† † †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
ኑፋቄ (በዲያቆን ያረጋል አበጋዝ) (1).pdf
330.5 KB
ኑፋቄ
* ኑፋቄ ምንድን ነው?
በዘመናት የነበሩ ዋና ዋና መናፍቃንና ኑፋቄያቸው በአጭሩ
* ግኖስቲኮች/ ኖስቲኮች
* አርዮስ
* ንስጥሮስ
* ሄልቪዲየስ
* ጆቪኒያን
* ቪጂላንቲየስ
* አርዮስ ዘቴባስቴ
* ማርቲን ሉተር
#መድሎተ_ጽድቅ
#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ
* ኑፋቄ ምንድን ነው?
በዘመናት የነበሩ ዋና ዋና መናፍቃንና ኑፋቄያቸው በአጭሩ
* ግኖስቲኮች/ ኖስቲኮች
* አርዮስ
* ንስጥሮስ
* ሄልቪዲየስ
* ጆቪኒያን
* ቪጂላንቲየስ
* አርዮስ ዘቴባስቴ
* ማርቲን ሉተር
#መድሎተ_ጽድቅ
#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ
የአውስትራሊያው ታዋቂ የአሦሪያ ጳጳስ የግድያ ሙከራ፣ መ*ና*ፍ*ቁ ንስጥሮስ እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች (እንደወረደ)
++++++
(ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ)
ሀ/ መነሻ
የሰኞ የብዙዎች መነጋገሪያ ርዕሰ ጉዳይ የነበረው በአውስትራሊያ የሚገኙ የአሲሪያ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ ላይ በቤተ መቅደሳቸው እንዳሉ የተፈጸመባቸው የመግደል ሙከራ ነው። ጳጳሱ በቀጥታ ሥርጭት በሚተላለፈውና በመላው ዓለም ያሉ በሺህዎች የሚቆጠሩ ተመልካቾቻቸው በሚከታተሉት ዝግጅት ላይ ነው በስለት የመግደል ሙከራ የተደረገባቸው። አንድ በወጣትነት ዕድሜ ላይ የሚገኝ ሰው ጳጳሱን በስለት ደጋግሞ ሲወጋቸው በቪዲዮው ይታያል። ከእርሳቸውም በተጨማሪ በቤተ መቅደሱ የነበሩ ሌሎች ሰዎች አደጋ ደርሶባቸዋል::
እኒህጳጳስ በፌብርዋሪ ወር 2024ም ተመሳሳይ በስለት የመግደል መኩራ ተደርጎባቸው ተርፈዋል፡፡ በፊብሩዋሪ ወንጀሉን የፈጸመው የ 15 ዓመት ወጣት እንደነበር መገለጹ ይታወሳል።
ዛሬ የተፈጸመባቸው የመግደል ሙከራ በጣም አሳዝኖኛል፣ አስደንግጦኛልም:: በርግጥ ወንጀሉን የፈጸመው ሰው ማንነት ግልጽ ባይሆንልኝም ከሊበራሉ ዓለም እስከ አክራሪ ጽንፈኞች ድረስ ጥቃት ሊያደርሱባቸው የሚችሉ ሰዎች እንዳሉ መገመት ይቻላል። በትምህርታቸው ጠንካራነት ምክንያት። በቅርቡ እንኳን እሥራኤል በጋዛ ፍልስጥኤማውያን ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት የተቃወሙበትን ንግግር ተመልክተናል። ይህንን ጽሑፍ እስከጻፍኩበት ሰዓት ድረስ የአውስትራሊያ ፖሊስ ወንጀሉን የፈጸመውን ሰው ማንነት እና ወንጀሉን ለመፈጸም የገፋፋውን ምክንያት አልገለጸም።
ለሁሉም ግን እንኳን እግዚአብሔር አተረፋቸው፡፡ አሁንም ቶሎ አገግመው ወደር ወደሚወዱት አገልግሎት እንዲመለሱ ምኞቴ ነው።
++++
ለ/ ጳጳሱ ማር ማሪ ኢማኑኤል (Bishop Mar Mari Emmanuel) ማን ናቸው?
----------
ማር ማሪ ኢማኑኤል በአውስትራሊያ የሚገኘው የ"Assyrian Church" ሊቀ ጳጳስ ሲሆኑ መልካም እረኛ ቤተ ክርስቲያን (Christ The Good Shepherd Church) በተባለ ሥፍራ ያገለግላሉ። በ2009 (እ.አ.አ) ቅስናን፣ በ2011 ደግሞ ጵጵስና መቀበላቸውን ታሪካቸው ያሳያል።
ጳጳሱ ማር ማሪ ኢማኑኤል በስብከቶቻቸው የሚያነሧቸው ጉዳዮች በብዙ ሰው ዓይን ውስጥ እንዲገቡ ያደረጋቸው ይመስላል። በዘመነ ኮሺድ በመላው ዓለም የተጣለውን ከቤት ያለመውጣት እግድ በጽኑዕ በመቃወማቸው ይታወቃሉ። ከዚያም ቀጥሎ በአሜሪካ እና በሩሲያ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ የሚሰጧቸው ሐሳቦች በተለይም በሊበራሉ ዓለም "አክራሪ" አሰኝቷል። የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባይደን "የተመረጡት በሕቡዕ ቡድኖች ይሁንታ ነው" ማለታቸው እንዲሁም "ግ*ብ*ረ ሰ*ዶ*ማ*ዊነት"ን በጽኑዕ መቃወማቸው ጠላት ያፈራባቸው ይመስላል።
ታዋቂነታቸው ከእንግሊዝኛ ተናጋሪው አልፎ ወደ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ኦርቶዶክሳውያን ዘንድም ደርሷል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ስለ ጳጳሱ ያወቅኹት ስለ ቤተ ክርስቲያኒን ጠንካራ ትችት ያቀረቡበትን እና ቤተ ክርስቲያን "ንስሐ ግቢ" የሚል መንፈስ ያለው አጭር ቪዲዮ አይቼ ነው። "እንዴ!!! ቤተ ክርስቲያን ኃጢአት የማይስማማት የክርስቶስ አካሉ መሆኗን የደፈጠጠ የምዕራቡ ዓለም ፕሮ*ቴስ*ታን*ቲዝም ትምህርት የሚናገር ጳጳስ ከየት ተገኘ?" ብዬ ተገርሜ ነበር። የግብጽ/ቅብጥ ጳጳስ መስለውኝም ነበር። ኋላ ነው የአሦር ኦርቶዶክስ ጳጳስ መሆናቸውን የተረዳኹት። ብዙ ኦርቶክሳውያን የተዋሕዶ ልጆች ስብከቶቻቸውን ሼር ሲያደርጉ "የተዋሕዶ ጳጳስ መስለዋቸው ይሆን?" እል ነበር።
+++++
ሐ/ ስለ ምሥራቅ አሦሪያ ቤተ ክርስቲያን በመጠኑ
---------
1/ ሙሉ ስማቸው:-
## The Assyrian Church of the East (ACOE)፤
## የፓትርያርኩ መቀመጫ (መንበረ ፓትርያርኩ) ሰሜን ኢራቅ ኢርቢል (Erbil) ነው።
2ኛ/ ሌሎች ሰዎች "ንስጥሮሳዊት ቤተ ክርስቲያን" (the Nestorian Church) ይሏቸዋል። በኤፌሶን ጉባዔ የተወገዘውን የንስጥሮስን አስተምህሮ የሚቀበሉ ቢሆንም ንስጥሮሳውያን መባል አይፈልጉም። ከጽርፈት (ስድብ) ይቆጥሩታል።
3ኛ/ ራሳቸውን "ኦርቶዶክስ" ብለውም አይጠሩም:: በየትኛውም ጽሑፋቸው ላይ "ኦርቶዶክስ" የሚል ቃል አይጠቀሙም። ነገር ግን ብዙ ሰዎች የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት በተለይም የተዋሕዶዎቹ "የኦሪየንታል አብያተ ክርስቲያናት" አካል አድርገው ይቆጥሯቸዋል። ስሕተት ነው።
4ኛ/ Assyrian Church of the East (branch of Syriac Christianity) ከሚባሉት ውስጥ በ1870 የተለዩት/ የተገነጠሉት "The Chaldean Catholic Church" ከሮማ ካቶሊክ ጋራ ውሕደት ፈጽመዋል። በ1994 ባደረጉት ውሳኔ በነገረ ክርስቶስ ላይ ያላቸውን አስተምህሮም ከሮማ ካቶሊክ ጋራ አንድ አድርገዋል። መንበረ ፓትርያርካቸውም ኢራቅ ባግድዳ ነው። የቅዳሴ ቋንቋቸው ግን ልክ እንደሌሎቹ የሲሪያክ ይትበሐል አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሁንም "አራማይክ" ነው።
መ/ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶዎቹ የሦሪያ ክርስቲያኖች
—-------------
ሙሉ ስማቸው The Syriac Orthodox Church ይባላል፤
West Syriac Church ወይም West Syrian Church ይባላሉ፣
በመደበኛው (official) አጠራራቸው ደግሞ the Syriac Orthodox Patriarchate of Antioch and All the East ይባላሉ፤
በኢመደበኛ (informal) አነጋገርም ቢሆን (the Jacobite Church) ያዕቆባዊት ቤተ ክርስቲያን ይባላሉ። በትምህርቱ እና በተቀበለው ሰማዕትነት ቤተ ክርስቲያኗን በተዋሕዶ እምነቷ ባጸናት በሊቀ ጳጳሱ በቅዱስ ያዕቆብ ዘእልበረዲ (Jacob Baradaeus ወይም Jacob bar Addai) ስም ይጠራሉ።
የቅዳሴ ቋንቋቸው አራማይክ ሆኖ ይትበሐሉ ግን "የምዕራብ አራማይክ (West Syriac)" ነው።
ንስጥሮሳውያኑ "የምሥራቅ አራማይክ" ይትበሐል ተከታዮች መሆናቸውን ከላይ መግለጻችንን ልብ ይሏል።
የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶዎች የነዚሁ የያዕቆባውያን ኦርቶዶክሶች አካል ናቸው።
++++++
ሠ/ መ*ና*ፍ*ቁ ንስጥሮስ እና የኤፌሶን ጉባኤ (431 ዓ.ም)
—------
ጉባኤ ኤፌሶን በ431 ዓ.ም በኤፌሶን ከተማ በ200 ሊቃውንት የተካሄደ ታላቅ ጉባዔ ነው፡፡ የስብሰባው መሪ ቅዱስ ቄርሎስ ነበር፡፡
የስብሰባው ዋና ምክንያት የንስጥሮስ ክህደት ነው፡፡
የንስጥሮስ ክህደቱም "ቃል ከሥጋ ጋር አልተዋሐደም። ሰው አልኾነም። አምላክም ሰው የሆነው በኅድረት ነው፡፡ ኅድረት ማለትም እመቤታችን የወለደችው ሰውን ብቻ ነው፡፡ ማርያም በወለደችው ሰው ላይ የእግዚአብሔር ቃል አደረበት (ሕድረት)፤ ስለዚህ እርሷም ወላዲተ አምላክ አትባልም" የሚል ነው፡፡
ንስጥሮስን ተከራክሮ የረታውና መልስ ያሳጣው እስክንድርያዊው ሊቀ ጳጳስ ቅ/ቄርሎስ ነው፡፡
የንስጥሮስን የክህደት ትምህርት በመሠረዝ እመቤታችን "እመአምላክ ወላዲተ አምላክ፣ እመ እግዚአብሔር (Mother of God, Theotokos)" መሆኗን እናምናለን፣ እናሳምናለን፣ እናስተምራለን።

ንስጥሮሳውያን እና የነርሱን ትምህርት የሚከተሉ አንዳንድ ፕ*ሮ*ቴስ*ታንቶች ዛሬም ድረስ Mother of Jesus እንጂ Mother of God አይሉም።
* ቅዱስ ቄርሎስ ለንስጥሮስ ሲመልስ፦ "ወልድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማይመረመር ተዋሕዶ ሰው የኾነ አምላክ ነውና ቀዳሚ ሲኾን ከዘመናት አስቀድሞ ከአብ የተወለደ ነው! ዳግመኛም ከድንግል ማርያም በሥጋ የተወለደ ነው" ብሏል /ሃይማኖተ አበው 73፣4 ገጽ 271)
+++++
ረ/ ቃል ሥጋ ሆነ፤ ዘእንበለ ሕድረት (ያለማደር)
==============
የንስጥሮስ ክህደት የሆነው "ሕድረት" የሚለው ነው።
ሕድረት ማለት አንድ አካል በሌላ አካል ውስጥ ገብቶ ማደር ማለት ነው። ለምሳሌ መጽሐፍ ማሕደር ውስጥ ያድራል፤ ሰይፍ ሰገባ ውስጥ ያድራል።
በሕድረት ጊዜ አዳሪውና ማደሪያው በባሕርይ አይዋሐዱም።
ቃል ሥጋ የሆነው ግን በሕድረት አይደለም። ቃል ሥጋ ውስጥ አደረ ከተባለ ሥጋ ለቃል ማሕደሩ፤ ልብሱ፤ መቅደሱ ሆነ እንደማለት ነው። ይህ ማለት ደግሞ ባሕርያዊ ተዋሕዶ አልተፈጸመም እንደማለት ነው።
ቃል ግን ሥጋ ሲሆን የቃል ገንዘቡ ሁሉ ለሥጋ፤ የሥጋም ገንዘብ ሁሉ ለቃል ሆኗል። ስለዚህም ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በፍጹም ተዋሕዶ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ ሆነ እንላለን።
ሰ/ የኢንተርኔት ላይ ክርስትና
—-----
ኢንተርኔቱ በጠቅላላው በተለይ ማኅበራዊ ሚዲያው ሃይማኖታችንን ለማወቅ፣ ለመጠበቅና ለማስፋፋት ይረዳል። ነገር ግን በነባራዊው ዓለም እንዳለው ሕይወታችን ተመልካች፣ መሪ፣ ተቆጪ፣ ተጠያቂ ስለሌለበት ለሃይማኖታዊ ፈተና ሊያጋልጠን ይችላል። ኑ*ፋ*ቄዎች ትክክለኛ ትምህርት፣ የተሳሳቱ መምህራንም ቀና እምነት የሚያስተምሩ መስለው ብዙዎችን ሲያሳስቱ እናያለን። ስለዚህ ራሳችንን ከቀጥተኛዋ የተዋሕዶ ትምህርት ውጪ ሆነን እንዳናገኘው ጥንቃቄ እናድርግ።
ይቆየን!!!

ይሄን እያዬ የሚከራከር ካለ ጤንነቱ 😁ያሳስበኛል ይሄን ሰውዬ መናፍቅ አይደሉም የሚል
ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ_ህይወቱና_ትምህርቱ_በዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ.pdf
214.8 KB
ወደ ቤተ ክርስቲያን ስላልመጡ ምዕመናን
የሚያስጨንቅህ የዚህ ዓለም ጉዳይ አለብህ? እዚህ በምታሳልፈው ጊዜ የእግዚአብሔርን ርዳታና ምሕረት ታገኝ ዘንድ፣ በመረጋጋትና በመጽናናት መንፈስ ሆነህ ትሄድ ዘንድ ስለዚህ ምክንያት ወደዚህ ና፡፡ እርሱ ኃይልሀና ጋሻህ ይሆን ዘንድ፣ በሰማያዊ ሥልጣን በመጠበቅ ለጠላቶችህ ለአጋንንት የማትሸነፍ ትሆን ዘንድ ወደዚህ ወደ ጸጋው ዙፋን ና፡፡ በአባቶች ከሚደርሰው ጸሎት ሱታፌ ካለህ፣ በማኅበር ጸሎት ከተሳተፍክ፣ ቅዱስ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል ከሰማህ፣ የእግዚአብሔርን ርዳታ ካገኘህ፣ እነዚህን መሣሪያዎች ከታጠቅህ የትም ብትሄድ እንዳንተ ያሉ ሥጋ የለበሱ ጠላቶችህ ክፉዎች ሰዎች ይቅርና ዲያብሎስ ራሱ ፊትህን ማየት አይችልም፡፡ ነገር ግን ከቤትህ እንደ ተነሣህ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሳትመጣ ወደ ገበያ፣ ወደ ሥራ፣ ወዘተ ብትሄድ ብቻህን ያለ ምንም መንፈሳዊ ትጥቅና ጸጋ እግዚአብሔር ስለምትሆን ሁሉም ነገር በአንተ ላይ ይበረታብሃል፤ ጠላቶችህም በቀላሉ ያጠቁሃል
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ_ህይወቱና_ትምህርቱ

የእግዚአብሔር ምሕረት ያስደንቃል። ያደረግነውን ብቻ አይደለም ይቅር የሚለን። የማይገባንን ገነትም ይሰጠናል!!!
ለካህን_መናዘዝና_ቀኖና_መቀበል_ለምን_በዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ.pdf
333.1 KB
ለካህን መናዘዝና ቀኖና መቀበል ለምን?
* የተሐድሶዎች ትምህርት ለካህን ስለመናዘዝና ቀኖና ስለመቀበል
* በዚህ ጉዳይ ላይ የተሐድሶዎች መሠረታዊ ስህተቶች
* ለንስሐ አባት መናዘዝና ቀኖና መቀበል በመፅሀፍ ቅዱስ ትምህርት
* ቀኖና የሚሰጥባቸው ምክኒያቶች
* ንስሐ አባትና ቀኖና በአበው ትምህርት
“ነቢዩ ናታን ንጉሥ ዳዊትን ኃጢአቱን ከነገረው በኋላ ወዲያውኑ ኃጢአቱን እንዳመነ አጽናንቶት ነበር፡፡ ሆኖም ብፁዕ ዳዊት ግን ምንም እንኳ እግዚአብሔር ደግሞ ኃጢአትህን አርቆልሃል፡ ኣትሞትም' (2 ሳሙ. 12፡13) የሚለውን የነቢዩን ቃል የሰማ ቢሆንም ንስሐ ከመግባት ግን አልተመሰለም፡፡ ንጉሥ የነበረ ቢሆንም በልብሰ መንግሥት ፋንታ አመድ ለበሰ በወርቅ ዙፋን ላይ በመቀመጥ ፋንታ በመሬት ላይ፣ ያውም በአመድ ላይ ተቀመጠ፡፡ በአመድ ላይ የተቀመጠ ብቻ ሳይሆን አመድንም ምግቡ አደረገ፤ እርሱ ራሱ “አመድን እንደ እህል ቅሜያለሁና፣ መጠጤንም ከእንባዬ ጋር ቀላቅያለሁና” (መዝ 101፡9) ብሏልና፡፡ ወደ ኃጢአት የተመለከተው ዓይኑ በዕንባ እስኪሟሟ ደረሰ፤ “ሌሊቱን ሁሉ አልጋዬን አጥባለሁ፣ በዕንባዬም መኝታዬን አርሳለሁ፤ ዓይኔ ከቍጡ ዕንባ የተነሣ ታወከች” እንዳለ፡፡ መዝ. 6፡6-7 መኳንንቱ እህል እንዲቀምስ በለመኑት ጊዜ እንኳ አልሰማቸውም፡፡ ጾሙን እስከ ሰባት ሙሉ ቀናት አራዘመ፡፡ ንጉሥ የነበረው እርሱ እንዲያ ባለ ሁኔታ ንስሐ ከገባ ተራ ግለሰብ የሆንከው አንተ ንስሐ ልትገባና ልትናዘዝ አይገባህምን?” (ቅዱስ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም፣ ትምህርት 2 በእንተ ንስሐ ወሥርየተ ኀጢአት፣ ቁ 12)

#ዘወረደ_ብለን_ጀምረን ሆሳዕና ብለን እንድንጨርስ የፈቀደልን እግዚአብሔር ይመስገን ቀሪዎችን ቀናት ባርኮልን ለብርሀነ ትንሳኤው በሰላም ያድርሰን 🤲
#ሆሳዕና_በአርያም እንኳን አደረሳችሁ
#ሆሳዕና_በአርያም እንኳን አደረሳችሁ
🔴New | ሕማማት ለምን እና እንዴት | እጅግ ድንቅ ትምህርት በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን ግርማ Aba Ge...
https://youtube.com/watch?v=vfav25bXykE&si=PUdcXZ-Km0WarUd5

YouTube
🔴New | ሕማማት ለምን እና እንዴት | እጅግ ድንቅ ትምህርት በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን ግርማ Aba Gebrekidan Sibket #viral
በሕማማት የሚደረጉ እና የማይደረጉ ነገሮች
ኢሳይያስ 53
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ የሰማነውን ነገር ማን አምኖአል? የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገልጦአል?
² በፊቱ እንደ ቡቃያ ከደረቅም መሬት እንደ ሥር አድጎአል፤ መልክና ውበት የለውም፥ ባየነውም ጊዜ እንወድደው ዘንድ ደም ግባት የለውም።
³ የተናቀ ከሰውም የተጠላ፥ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው፤ ሰውም ፊቱን እንደሚሰውርበት የተናቀ ነው፥ እኛም አላከበርነውም።…
ኢሳይያስ 53
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ የሰማነውን ነገር ማን አምኖአል? የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገልጦአል?
² በፊቱ እንደ ቡቃያ ከደረቅም መሬት እንደ ሥር አድጎአል፤ መልክና ውበት የለውም፥ ባየነውም ጊዜ እንወድደው ዘንድ ደም ግባት የለውም።
³ የተናቀ ከሰውም የተጠላ፥ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው፤ ሰውም ፊቱን እንደሚሰውርበት የተናቀ ነው፥ እኛም አላከበርነውም።…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልዓክ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ማማተብ ይቻላል ? በሰሙነ ሕማማት ☑️
ሊቀ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
ሊቀ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
👆 እዚጋ ሊቀ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን ግርማ ላይ እደተሰጠው ኮመንት አይነት አንዳንድ ሰው '' እገሌ እንዲህ ይላል እገሌ እንዲህ ይላል የቱ ነው ልክ ግራ ተጋባን እኮ የሚል '' አይነት ነገር ይስተዋላል
እንዲህ አይነቱ ጥያቄ ግን ሚመጣው መሰረቱ ምን ላይ እደሆነ እና የክርስትናን መሰረታዊ አስተምህሮ ( ስለቤተክርስትያን) ምንነት ያልተረዳ እና ያልገባው አይነት ሰው ነው እዲህ አይነቱ ሰው ደሞ ከባዱ ችግር የመጣውን ትምህርት ሁሉ አግበስብሶ በመቀበል (የቤተክርስትያን አስተምህሮ ነው በማለት) ወደ ህመም (ኑፋቄ ) ይመራዋል (ወደ አላስፈላጊ ውዝግብ እና እምነቱን ተጠራጥሮ እስከመካድ ድረስ )
ስለዚህ እደአጠቃላይ እገሌ ምን አለ እገሌ ምን አለ እያሉ ከመወዛገብ ትክክለኛው ልባም ክርስትያን ጥያቄውን መልስ ሚያገኘው ቤተክርስትያን (ጉባኤው ) ምን ትላለች? በማለት ነው ይህም
የቤተክርስትያናችን ራስ ጌታ ክርስቶስ ኢየሱስ ምን አለ ? -> ሐዋርያት ምን አሉ -> ሐዋርያነ አበው ምን አሉ -> ሊቃውንት ምን ብለው አስተማሩ -> መፅሐፍት ምን ይላሉ -> ሕሊናዬ ምን ይላል ሚለውን መረዳት ትክክለኛ የክርስቲያን አረዳድ ነው
❗️በተለይ ዶግማ በሆኑ አስተምህሮዎች ላይጥንቃቄን ይሻል ❗️