Telegram Web Link
- እንዲህ ነው መውረድ -

|ጃንደረባው ሚዲያ | መስከረም 2016 ዓ.ም.|
ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ እንደጻፉት

ወደ ላይ መውጣትን ማን ይጠላል? ከሁሉ በላይ መሆንንስ የማይሻ ማን ነው? ስለሌሎች መዳን ለሚጨነቁ ሰዎች ካልሆነ በቀር ከልዕልና ወደ ትሕትና መምጣት ከባድ ነው። ዲያብሎስ እንጦርጦስ የወረደው ክብር ቢጎድልበት ነው። አዳም ወደዚህ ዓለም የመጣው ከገነት ቢሰደድ ነው። ናቡከደነፆር በሕይወት ሳለ ዙፋኑን ለልጁ ለዮርማሮዴቅ የለቀቀው ሰው መሆን ቢሳነው ነው ዳን 4÷33። ማንኛውም ሰው ወደ መቃብር የሚወርደው ነፍስ ቢለየው ነው።

ወዶ ፈቅዶ የወረደ ማነው?
መውረዱ ለሌሎች ወደ ላይ መውጣት ምክንያት ይሆን ዘንድ የወረደ ማነው? እንዲህ ያለ መውረድን የወረደ አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው እንጅ ሌላ ማንም የለም። ራሱን በፈቃዱ ዝቅ አደረገ። ከወረደበት ጊዜ ጀምሮ የሰው ባሕርይ በላይ በሰማይ ቦታ አግኝቶ ታየ።

እንዲህ ነው መውረድ!
አንተን ፍለጋ የወረደውን አምላክ ከፍ ካለው ምንጣፍህ ወርደህ ፈልገው። ወደ ታች በወረደ ጊዜ ያገኘው የሰውን ባሕርይ እንጅ የመላእክትን ባሕርይ አልነበረምና ከላይ ያለውን የመላእክትን ባሕርይ ሳይሆን የታችኛውን የሰውን ባሕርይ ተዋሐደ። ወንድሜ! እግዚአብሔር እንዲዋሐድህ ከላይ ልሁን አትበል። ዝቅ ባልህ ቁጥር ለእግዚአብሔር ቅርብ ትሆንለታለህ።

ሙሉውን ያንብቡ
ዘወረደ
ዘማሪ ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ
 ✞ ዘወረደ
"በእርሱ ፍቃድ"

በእርሱ ፍቃድ በአባቱ ፍቃድ
በመንፈስ ቅዱስ ፍቃድ
ከሰማያት ወረደ
ከድንግል ማርያም ተወለደ

ዓለሙን እንዲሁ ወደደና
ከሰማያት በላይ ወረደና
በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት
ተወሰነ አምላከ አማልክት
ከሰማያት የወረደው
ፍቅር ስቦት የመጣዉ
ወልደ አብ ወልደ ማርያም
ኢየሱስ ፈራጅ ነዉ
አዝ
ቅድመ ዓለም ተወልዶ ያለ እናት
ድህረ ዓለምም ያለ አባት
የእግዚአብሔር ልጅ በእርግጥም ሰው ሆነ
ሁሉ በእርሱ ይኸው ተከናወነ
ከሰማያት የወረደው
ፍቅር ስቦት የመጣዉ
ወልደ አብ ወልደ ማርያም
ክርስቶስ አምላክ ነዉ
አዝ
የማይታይ ታየ በምድር
ረቂቁ ገዘፈ ስለፍቅር
ሥጋን ተዋህዶ ሆነልን ፈውስ
አማኑኤል የነገስታት ንጉሥ
ከሰማያት የወረደው
ፍቅር ስቦት የመጣዉ
ወልደ አብ ወልደ ማርያም
እግዚአብሔር እርሱ ነዉ
   
ዲ/ን ቀዳሜጸጋ
ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ በመአልት ላይ ሰልጥኖ ከሚያበራ ፀሐይ ይልቅ ሰባት እጅ ለሚያበራው ስነ ገፅህ ሰላም እላለሁ።
ክቡር አባት ሆይ ምጽዋትን እንደ ዘር የምትዘራ ለጋስ ባለጸጋ ነህና ሙሽራው ድንገት ለሊት በመጣ ጊዜ ከአንተ ጋር መብራት አብርቼ እቀበለው ዘንድ ከትሩፋተ ገድልህ የመብራት ዘይት አካፍለህ ስጠኝ።


ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ ዕውነተኛውን የክርስቶስን ሃይማኖት ላስተማረ አንደበትህና ችግርን ለሚያቃልል ሥልጣነ ቃልም ሰላም እላለሁ።
ክቡር አባት ሆይ መንግስተ ሰማያት ላንተ ፈጽማ የተዘጋጀች ናት በጠላት ዲያቢሎስ ዘንድ እንደ እባብ ብልህ ስትሆንበት በቅዱሳኖቹ በኩል ልክ እንደ ርግብ የዋህ ሆነህ ተገኝተሀልና።

ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ ስንፍናን የሚያመጣ ምድራዊ ኅብስት ያይደለ ሰማያዊ ኅብስት ለተመገበ ከርሥህ ሰላም እላለሁ።
ክቡር አባት ሆይ ሁሉ በግልጽ ያከብርሃል ሁሉ ያደንቅሃል ለዕውራኖች ብርሃናቸው ለሐንካሶች ምርኩዛቸው ለማይሰሙትም የመስሚያ ቃል ሆነሀልና።



እንኳን ለአባታችን ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በዓለ እረፍት በሰላም አደረሳችሁ ።
መዝሙር 63
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ አምላኬ፥ አምላኬ፥ ወደ አንተ እገሠግሣለሁ፤ ነፍሴ አንተን ተጠማች፥ ሥጋዬ አንተን እንዴት ናፈቀች እንጨትና ውኃ በሌለበት በምድረ በዳ።
² ኃይልህንና ክብርህን አይ ዘንድ እንዲሁ በመቅደስ ውስጥ ተመለከትሁህ።
³ ምሕረትህ ከሕይወት ይሻላልና ከንፈሮቼ ያመሰግኑሃል።
⁴ እንዲህ በሕይወቴ ዘመን አመሰግንሃለሁ፥ በአንተም ስም እጆቼን አነሣለሁ።
⁵ ነፍሴ በቅቤና በስብ እንደሚጠግቡ ትጠግባለች፥ ከንፈሮቼም ስምህን በደስታ ያመሰግናሉ።
⁶ በመኝታዬም አስብሃለሁ፥ በማለዳም እናገርልሃለሁ፤
⁷ ረዳቴ ሆነኸኛልና፥ በክንፎችህም ጥላ ደስ ይለኛልና።
⁸ ነፍሴ በኋላህ ተከታተለች፥ እኔንም ቀኝህ ተቀበለችኝ።
በጾማችን የነፍሳችንን ክፉ ልማዶች ካላስወገድን ከሥጋ መከልከላችን ብቻውን ምን ይጠቅመናል? ስንጾም ውለን ጾም ከመግባቱ በፊት እንመገበው የነበረውን ምግብ ለውጠን መናኛ የሆነ የጾም ምግብ በማዕዳችን አቀረብን፡ ሆኖም ግን በጸሙ የምንመገበውን ምግብ እንደ ለወጥን ክፉ ግብራችንን እና ሕይወታችንንስ አብረን ለውጠናል ይሆን? በእውነት እኔ ግን እንዲህ ያደረጋችሁ አልመሰለኝም፡፡ እንዲህ ከሆነ መጾማችሁ ጥቅሙ ምንድን ነው? ስለዚህ ከጾማችሁ ጋር ልማዳችሁንና ሕይወታችሁን ወደ መልካምነት ትቀይሩ ዘንድ በተከታታይ እንድታስቡበት አደርጋችሁ ዘንድ ስለዚህ ነገር እናንተን ማስተማርንና መገሠጽን አላቋርጥም፡፡ (ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ፣ ትምህርት በእንተ ምክንያተ ሐውልታት 4 ቁ 12)
አመጋገብን በተመለከተ የምትከተሉት መመሪያችሁ ይህ ይሁን፣ በጾም ጊዜ ከሚመገቡት የምግብ ዓይነት የተነሣም ብዙዎች ይሰናከላሉና፡፡ ... ከሥጋና ከወይን በመከልከልና እነዚህን በመተው የምንጾመው የረከሱ ነገሮች ናቸው ብለን በመጸየፍ አይደለም፤ ነገር ግን እነዚህን የሚታዩትን ቁሳዊ ነገሮች በመናቅና በመተው መንፈሳዊና ሰማያዊ ተድላ ደስታን እናገኝ ዘንድ ተስፋ በማድረግ ነው እንጂ በጾማችን ሥጋንና ወይንን የምንተወው ሰማያዊ ዋጋን ከእግዚአብሔር ዘንድ እናገኝ ዘንድ ተስፋ ስለምናደርግ ነው፣ በለቅሶ ዘርተን በደስታ እናጭድ ዘንድ ነው እንጂ መዝ. 125፡5 ... ከእነዚህ ነገሮች ራሳችሁን ስትከለክሉና ስትታቀቡ የተጠሉ የረከሱ ነገሮች እንደሆኑ አድርጋችሁ አስባችሁ መሆን የለበትም እንደዚህ የምታስቡ ከሆነ ጾማችሁ ምንም ዋጋ የለውም፡፡ ነገር ግን ሥጋና ወይን በተፈጥሯቸው መልካም ነገሮች ቢሆኑም በፊትህ ስለ ተዘጋጁልህ የበለጡ መንፈሳዊ ነገሮች ስትል በጾም ጊዜ እነርሱን ተዋቸው፡፡" (ቅዱስ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም፡ ትምህርት 4 ቁ. 27)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
So powerful እንዴት ደስ ይላል..

“ጀግና ከሆንህ..”
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"ህይወት የሌለው ጾም ምን ያደርጋል !"
"እጠይቃችኋለሁ ለዝሙትና ለግድያ ራሳቸውን ባስገዙ፣ ስሜታቸውን በሚያመልኩ ፣ ከሥጋቸው በቀር ምንም ነገር መረዳት በማይችሉ ሰዎች የነገረ መለኮት ትምህርት እንዴት ሊተረጎም ይችላል?"[ጎርጎርዮስ ዘእንዚናንዙ]

Gregory Nazianzen,First Theological Oration 27.6,http:/www.newadvent.org/fathers/310227.
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔴 አዲስ ዝማሬ " አኑርልኝ ለአፌ ጠባቂ " ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ @-mahtot

ስሟት 🥰🥰🤗🤗
2024/09/27 00:18:45
Back to Top
HTML Embed Code: