Telegram Web Link
Audio
🎧አንተ እና የሰዎች ተቃውሞዎች🎧

🎤 #በሐና ማርያም🎤
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"ለምን ተስፋ ትቆርጣለህ ?"

1ኛ ቆሮ 8÷6 '' ለእኛስ ነገር ሁሉ ከእርሱ የሆነ እኛም ለእርሱ የሆንን አንድ አምላክ አብ አለን ነገር ሁሉም በእርሱ በኩል የሆነ እኛም በእርሱ በኩል የሆንን አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አለን።''🥰
አንድ አባት ምን ብለው ሲያስተምሩ ሰማሁ..

እውነተኛ ጉዋደኛ ማለት አንተን ከፍ የሚያደርግህ እንጂ ወደ ታች የሚጥልህ አይደለም.. ከፍታ ደግሞ ኢየሱስ ነው እናም ለአንተ እውነተኛ ጉዋደኛ ወደ ኢየሱስ የሚያቀርብህ ነው.. ወደ ሰይጣን የሚያቀርብህ እርሱ ጉዋደኛህ አይደለም..

ትልቁ ቁም ነገር:- አንተም እውነተኛ ጉዋደኛ ከሆንህ እንግዲያውስ ጉዋደኛህን ወደ ኢየሱስ ከፍ አድርገው.. ሃረቄ ቤት ምናምን ሳይሆን ቅዳሴ ውሰደው.. ይሄ እህቶችንም ይመለከታል ያው..

@Apostolic_Answers
ሰይጣን ተስፋ አይቆርጥም

ሰይጣን አሉኝ በሚላቸው ፈተናዎቹ ሁሉ ጌታን ፈትኖ ከጨረሰ በኋላ ድል እንዳላደረገው ባየ ጊዜ እስከጊዜው ከእርሱ ተለየ ሉቃ.4፥14 
ሰይጣን ለጊዜው ተስፋ ቢቆርጥም እንደቆረጠ አይቀርም በሌላ መንገድ እስኪ መጣ ለጊዜው ተወው ኋላግን በይሁዳ በአይሁድ አድሮ እስኪያሰቅለው ድረስና ሰይጣን ተሸነፍሁ ብሎ መሸነፉን በእለተአርብ እስኪያውቅ ድረስ ከእርሱ ተለየ
ሰይጣን ዛሬም ከእኛ ዘንድ በጾም በጸሎት  ድል ተነስቶ ቢሄድ መንገድ ቀይሮ ይመጣል እንጂ ከዚህ ዓለም እስክንለይ ድረስ እኛን ከማሳሳት እኛን ከመፈተን ወደኋላ አይልም ምክንያቱም
ለዛሬው ቢሸነፍ ለነገው
ሰይጣን ተስፋ አይቆርጥምና
#የእግዚአብሔር_ልጆች_ነን!
.
የሰውን የቀደመ የእግዚአብሔር አርአያና አምሳል ይመልስ ዘንድ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ አለም መጣ!

ለሰው የተደረገው የእግዚአብሔር ስጦታ "የእግዚአብሔር ልጅ" ተብሎ መጠራቱ ነው።
(አቡነ ሽኖዳ ሳልሳዊ)

#እግዚአብሔር_ይክበር_ይመስገን! #አሜን
ሁልጊዜ ሦስት ነገሮችን በሕሊናችሁ ትይዙ ዘንድ እመክራችኋለሁ፡፡
እነርሱም፡-
           ✞ ክፉ ከመናገር መከልከልን
           ✞ ማንንም ሰው እንደጠላት ከማየት መቆጠብንና
           ✞ እንደልምድ አደርጋችሁ ከያዛቸሁት መሐላ ትርቁ ዘንድ፡፡

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
who is jesus chrisit

jesus christ is the only true God
creater of everything


ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ አምላክ የሁሉም ፈጣሪ ነው!........
ገሃነም መግባት እንድትፈሩ የሚያደርጋችሁ ምንድር ነው..??

የሚፋጅ እሳት..??
የማያንቀላፋ ትል..?? ሎል

በጣም የሚያስፈራው ጋይስ.. ኢየሱስን ሙሉ በሙሉ ማጣታችን ነው.. ወይኔ አስባችሁታል ኢየሱስን ዳግም ላናገኘው ስናጣው..?? ማለት አሁን እኮ እበድለዋለሁ ምናምን እኮ ግን የፈለገ ቢሆን ኢየሱስን በቃ አጥተኸዋል ካሁን በኋላ ምንም እድልም የለህ ስባል.. በስምአብ የምር በጣም ያስፈራል.. የኔ ኢየሱስ የኔ ጌታ የኔ አባት የኔ ተስፋ..

ጌታ እዚህ የሰጠንን እድል ተጠቅመን በንስሐ ወደ እርሱ እንድንቀርብ ይርዳን.. የሚታገሰንም ለዚሁ ነው በነገራችን ላይ.. ጴጥሮስ እንዲህ እንዳለ:

2ኛ ጴጥሮስ 3
9፤ ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፥ ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል።

@Apostolic_Answers
በቤተ ክርስቲያን ያለ ማንኛውም ሰው ቢሆን የክርስቶስ መጋቢ እንጂ ክርስቶስን የሚወክል አይደለም፡፡ ድግስ የደገሰ ሰው ሁሉን ነገር ካዘጋጀ በኋላ እርሱ ለጠራቸው እንግዶቹ ያዘጋጀውን ነገር በየጊዜው ይሰጡለት ዘንድ አሳላፊዎችን (አስተናጋጆችን) ይሰይማል፡፡ መጋቢ ወይም አስተናጋጅ ቢያበላሽ ያ ጥፋት የመጋቢው እንጂ የድግሱ ባለቤት አይደለም፡፡ እርሱማ ሁሉን እንደሚገባ ስጡልኝ ብሎ ነበር አደራ የሰጣቸው፡፡ ሰዎች ግን አደራቸውን ላይወጡ ይችላሉ፡፡ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎትም እንዲሁ ነው፡፡ ክርስቶስ ራሱን መሥዋዕት አድርጎ ሠርጉን አዘጋጅቶአል፡፡ ማቴ፳ ፪፥፩-፲ ፬ ይህን በቤተ ክርስቲያን በኩል የሚሰጠውን የእርሱን ጸጋ የሚመግቡ ካህናትን በተዋረድ ከሐዋርያት ጀምሮ ይሾማል፡፡ሆኖም መጋቢዎች ሁለት ዓይነት፡- አንዱ ታማኝ፣ ሌላው ደግሞ ክፉ መሆናቸውን ራሱ ጌታችን አስተምሯል፡፡ ማቴ፳ ፬፥፵ ፭-፶ ፩፡፡ መልካም የሆነውም መጋቢ ዋጋውን ከባለቤቱ ይቀበላል፤ ክፉውም እንዲሁ ፍዳውን ይቀበላል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም «ሰው እኛን እንደ ክርስቶስ ሎሌዎችና እንደ እግዚአብሔር ምስጢር መጋቢዎች ይቁጠረን›› ያለው ለዚህ ነው፡፡ ፩ ቆሮ.፬፥፩-፪፡፡ ከሐዋርያት ጀምሮ ያሉ ሁሉም አገልጋዮች (ሎሌዎች)ና መጋቢዎች ብቻ ናቸው፡፡
ስለዚህም መንጋውንና እረኛውን፣ ጌታችንንና አገልጋዮቹን፣ ሰውንና እግዚአብሔርን ማደባለቅ የለብንም፡፡ የሰው ጥፋት የሰው እንጂ የእግዚአብሔር አይደለም፡፡ የሰዎች አለማመን የእግዚአብሔርን አምላክነትና ታማኝነት ሊያስቀር እንደማይችል ሁሉ የሰው ጥፋትም በእግዚአብሔር ላይ የሚሳበብበት፣ ሰዎች ስላላስደሰቱን በእግዚአብሔር ላይ የምናኮርፍበት ምክንያት ሊኖር አይገባም፡፡ «እስመ አንተ ትፈድዮ ለኩሉ በከመ ምግባሩ - አንተ ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው ፍዳውን ትሰጣለህና›› ተብሏልና፡፡መዝ.፷ ፩፥፲ ፪፡፡ እንዲሁም «እስመ ኩሉጾሮ ይጸውር - ሁሉም የየራሱን ሸክም ይከማል›› እንደተባለ፡፡ የክርስትና ሕይወት ለሰዎች በውክልና የምንሰጠውና ከእነርሱ የምንጠብቀው ሳይሆን እያንዳንዳችን ራሳችን የምንኖረው ሕይወትና የምንወጣው ድርሻ ነው፡፡ ሌሎች ‹‹ለምን እንዲህ አላደረጉም?››ብለን የምንቆጣበት ሳይሆን ‹‹እኔ ለምን እንዲህ አላደረግሁም?›› ብለን ራሳችንን የምንወቅስበት ነው፡፡ እግዚአብሔርም የሚፈርድብንና የሚጠይቀን ‹‹እገሌ ለምን እንዲህ አላደረገም ወይም ለምን እንዲህ አደረገ?››ብሎ ሳይሆን «አንተ ለምን ይህን አደረግህ ወይም ለምን ይህን አላደረግህም?» ብሎ ነው፡፡ ‹‹እያንዳንዳችን ስለ ራሳችን ለእግዚአብሔር መልስ እንሰጣለን› ተብሏልና፡፡ሮሜ፲ ፬፥፲ ፪። ስለሆነም በቤተ ክርስቲያን ስንኖር ከተለያየ አቅጣጫ ፈተና እንደሚኖር ተረድተን ነገር ግን በፈተናዎች ተስፋ ሳንቆርጥ ክርስቶስ ከደቀ መዛሙርቱ- ከቅዱሳኑ ጋር ከሚገኝባት ታንኳ (ቤተ ክርስቲያን) እንውረድ ሳንል አብረን እንጓዝ፡፡ ትኩረታችንም ሌሎች የድርሻቸውን ስለመሥራታቸውና ሓላፊነታቸውን ስለ መወጣት አለመወጣታቸው ሳይሆን፤ በመጀመሪያ እኛ የራሳችንን ድርሻ ስለ መወጣታችን፤ ራሳችንን እንጠይቅ፡፡ አንዱ ስለሌላው አለመሥራት እያወራና በሌላው እያመካኘ ቤተ ክርስቲያን ከእርሱ የምትጠብቀውን ድርሻ የማይወጣ ከሆኑ አጠቃላይ የሆነ የአለመሥራት አዙሪት ውስጥ እንገባለን፡፡ ነገር ግን እያንዳንዱ የራሱን ድርሻ ከሠራ፤ በመጨረሻ ላይ ሲደመር ሁሉም ሥራ ተሠርቶ ይገኛል፡፡ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎትና ዕድገት የተሟላ፣ አስደሳችና ውጤታማ የሚሆነው እንዲህ ሲሆን ነው፡፡

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
The Release of the Spirit.pdf
1.4 MB
The Release of the Spirit by Pope Shenouda III

መልካም ንባብ
በኦሪቱ እግዚአብሔር ደግሞ ደጋግሞ የሚናረው ነገር ነበር፡፡ እርሱም «አንተ ግን ከእግዚአብሔር ጋር ተጣበቅ የሚለው ነበር።እኛም ምንም ይሁን ምን ከእግዚአብሔር ጋር እንጣበቅ፡፡ ሐዋርያት በባሕር ላይ ስንጓዝ የገጠማቸውን ፈተና ያለፉት ከታንኳው በመውጣትና ከክርስቶስ በመለየት አይደለም፡፡ እዚያው በማዕበል ከሚጨነቀው ታንኳ ውስጥ ሆነው «ጌታ ሆይ አድነን ጠፋን» እያሉ ማዕበሉን በቃለ ኃይሉ በቅጽበት ጸጥ ሊያደርግ ወደሚችለው ወደ አምላካቸው ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ጸለዩ እንጂ፡፡ እርሱም ልመናውን ሰምቶ የነፋሱንና የባሐሩን ማዕበል በአምላክነቱ ገሠጸው ወዲያውኑም በቅጽበት ታላቅ ጸጥታ ሆነ፡፡ጭንቀታቸው ተወገደ፡፡ በፈተና ምክንያት ከቤተ ክርስቲያን መውጣት ከክርስቶስ መለየት ነው፥ በፈተናው ድል መሆንና መሸነፍ ነው፡፡ ጌታችን «እስከ መጨረሻ የሚጸና እርሱ ይድናል» ያለው ለዚህ ነው፡፡ ማቴ ፳ ፬÷፲ ፫። እስከመጨረሻ መጽናት አስፈላጊ መሆኑን አስቀድሞ የነገረን ለፈተናዎች ራሳችንን እንድናዘጋጅ ነውና፡፡ የሌላውም ኃጢአት ለእኛ ኃጢአት ምክንያት ሊሆነን አይችልም፡፡ የሌላው ሰው ስንፍና ለእኛ ስንፍና ምክንያት ወይም ሽፋን ሊሆነን፣ በፍርድ ቀንም አስተያየት ሊያስደርግልን አይችልም፡፡ በኖኅ ዘመን የነበሩ ሰዎች ከኖኅ በስተቀር ሁሉም ኃጢአተኞች ሆነው ቢገኙ፤ ሁሉም በጥፋት ውኃ ጠፉ እንጂ ስለ ብዛታቸው ወይም ሁሉም ኃጢአተኞች በመሆናቸው የተደረገላቸው አስተያየት አልነበረም፡፡ ዛሬም ወደፊትም የሚሆነው ይኸው ነው፡፡ ስለዚህ በትንሹ የዚህ ዓለም የሕይወታችን ዘመን ፈተናዎችን ተቋቁመን ከክርስቶስ ጋር በቤተ ክርስቲያን ጸንተን ኖረን «በትንሹ ታምናችኋልና በብዙ እሾማችኋለሁ ወደ ጌታችሁ ደስታ ግቡ»ለመባል ያብቃን፡፡
ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
በየጥቂቱ ማደግ .pdf
149.4 KB
በየጥቂቱ ማደግ
በዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
ጌታችን በተግባር እንዳስተማረን መንፈሳዊ ሕይወት በትንሹ ተጀምሮ ከዚያ ቀስ በቀስ እያደገና እየጠነከረ የሚሄድ እንጂ በአንድ ጊዜ ተጀምሮ በቅጽበት ፍጹም የሚሆንበት አይደለም፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያትን ከተለያየ ሁኔታና ሕይወት ከጠራቸው በኋላ ወዲያውኑ ዕለቱን ወደ ፍፁምነት ደረጃ አልደረሱም፡፡ ብዙ ድክመቶች ነበሩቸው። እርሱ ስለ ሰማያዊ መንግስት ሲነግራቸው ስለ ምድራዊ መንግስት የሚጠይቁበት ጊዜ ነበር።የሚነገራቸውን ባለማስተዋላቸው፣ ለእርሱ የቀኑና የተቆረቆሩ ምስሎአቸው እሳት ከሰማይ ወርዶ እርሱን ያልተቀበሉትን ሰዎች እንዲያጠፋቸው በመጠየቃቸው፣ ስለ ሞቱና መከራው ሲነግራቸው “አትሙትብን” በማለታቸው ÷ ስለ እምነት ማነስ ሁሉ ብዙ ጊዜ ተገሥጸዋል፡፡ እነርሱም ከዚህ የተነሳ “ጌታ ሆይ እምነት ጨምርልን” እስከማለት ደርሰዋል ። ጌታችንም ብዙ ጊዜ ይገስጻቸውና ስሕተታቸውን እንዲያስተካክሉ በአባትነቱ ይመክራቸው ነበር፤ ሦስት ዓመት ከእርሱ ጋር ከዋለበት እየዋሉ ካደረበት እያደሩ በቃልም በተግባርም ተምረው እንኳ ፍጹማን መሆን አልቻሉም ነበር። ጌታችን በሰጣቸው ተስፋ መሰረት መንፈስ ቅዱስን ሲቀበሉ ነበር ፍጹማን የሆኑት። እንግዲህ ሐዋርያት በእንዲህ ዓይነት ሂደትና ውጣ ውረድ ውስጥ ያለፉ ከሆነ ወደ ፍጹምነት ደረጃ መድረስ በአንድ በኩል በራስ ጥረት በዋናነትም በእግዚአብሔር ቸርነት በሂደትና ቀስ በቀስ እንጂ በአንድ ጊዜ በቅጽበት የሚሆን ነገር አይደለም ማለት ነው፡፡ በክርስትና የሕይወት ጉዞ ውስጥ የሕይወትን አካሄድ÷ ስልትና ዘዴ ማወቅ በጣም ወሳኝ ነው፡፡ የጉዞውን ርዝመትና ጠባይ እንዲሁም በሂደቱ ውስጥ ያሉና ሊገጥሙ የሚችሉ ነገሮችን አስቀድሞ ሳያውቁ የሚጀመር ጉዞ መሰናሎች ሲገጥሙት የመውደቅ ዕድሉ የሠፋ ነው፡፡ ከዚህም አንዱ የአካሄድን ፍጥነት መወሰን ነው፡፡ አንዳንዶች ክርስትና በተወሰነ ጊዜ ተሰርቶ ማለቅ እንዳለበት የሥራ ዕቅድ (ፕሮጀክት) ወዲያውኑ እንደ ጀመሩ አካሄዳቸው የጥድፊያና የችኮላ ይሆናል፡፡ ሰውነቱ ጾምን በሚገባ ሳይለማመድ እስከ ማታ ድረስ በመጾም ይጀምራል። «የክርስቶስ ክቡር ደም በፈሰሰባት ምድር በጫማ አልሄድም» እስከ ማለት ይደርሳል፡፡ ይህን ዓለም በሙሉ የመጸየፍና የምናኔ ነገር ብቻ ይታሰበዋል። ሌሎች ሰዎች ኀጢአተኞችና ደካሞች ሆነው ይታዩታል። አንዳንዶች ሥራቸውን እስከ መተው ደርሰው በየገዳማት መዞርን ብቻ ስራዬ ብለው ይይዛሉ:፡ በአጠቃላይ ነገሮችን ሁሉ እንዳይሆን እንዳይሆን አድርገው ይይዟቸዋል፡፡ በየቦታው በመዞር ብቻ በረከትና ጽድቅ የሚገኝ ይመስለዋል። ከትምህርት ቤት ወደ ትምህርት ቤት እየተዘዋወረ መምህር ሲያማርጥና የተመቸ ሁኔታን ሲፈልግ አንድ ቁም ነገር ሳይማር ጊዜውን የሚያጠፋውን ተማሪ አበዉ ’እግረ ተማሪ’ ይሉታል፡፡ዛፍ እንኳን ፍሬ የሚያፈራው ከተተከለበት ቦታ ሲኖር ነው:: ነገር ግን በየጊዜው እየተነቀለ የሚተከል ከሆነ ወይ ይደርቃል፤ ባይደርቅ እንኳ ፍሬ ማፍራት አይችልም።ጊዜውን በዙረት ብቻ የሚጨርስ ሰውም ፍሬ ማፍራት አይቻለውም፡፡ ቢያፈራም እንኳ በአንድ ቀን በቅላ በአንድ ቀን አብባ በአንድ ቀን ታፈራለች እንደምትባለው ዕፀ ከንቱ÷ ፍሬው ምትሐታዊ ይሆንና ከመታየቱ ወዲያውኑ ይረግፋል። በእንዲህ ያለ ሕይወት የሚጓዙ ሰዎች የማይመች አካሄድ ውስጥ ይወድቃሉ፡፡ ይህ ዓይነት ሕይወት ብዙ ችግሮችን ሊያስከትል የሚችል አስቸጋሪ አካሄድ ነው፡፡
....................

ክርስትና የክርስቶስ ፍቅር እንደ ተረዳውና እንዳከበረው መጠን ከውስጥ በሚመነጭ ፍቅር የሚመሠረት እንጂ በተጽዕኖ ከውጭ የሚጫን ሸክም አይደለም። ሐዋርያው «የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናል» አለ እንጂ ሌላ ማንም ያስገድደናል አላለም። በሰዎች ላይ ከባድና እስቸጋሪ ሸክም የሚጭኑ ጸሐፍትንና ፈሪሳውያንን ጌታችን እንዲህ በማለት ገሥጾአቸዋል « ከባድና አስቸጋሪ ሸክም ተብትበው በሰው ትከሻ ይጭናሉ፥ እነርሱ ግን በጣታቸው እንኳ ሊነኩት አይወዱም»:: ማቴ 23÷4። እንዲህ በሌሎች ላይ መጫን ገድልና ትሩፋት መስሎ የሚታያቸው ሰዎች ሁሉን ከሚያውቅና ሁሉን በጊዜው ከሚያደርግ ጌታ ጋር ያሉትን ቅዱሳን ሐዋርያትን የግድ፥ እንዲጸሙ ለማደረግ ወደ ጌታችን ቀርበው: « እኛና ፈሪሳውያን ብዙ ጊዜ የምንጾመው ደቀ መዛሙርትህ ግን የማይጸሙት ስለ ምንድነው?» እስከማለት ደርሰዋል፡፡ ለጾም ከራሱ ከባለቤቱ የበለጠ ተቆርቋሪዎች በመምሰል በሌሎች ላይ ለመወሰን ቀረቡ፡፡ ማቴ.9÷14። አባቶቻችን ሐዋርያትንም እንጀራ ሲበሉ፡ “እጃቸውን አይታጠቡም በሰንበት ቀን እሸት ቆርጠው በሉ» ወዘተርፈ እያሉ ይከሷቸውና ይነቅፏቸው ነበር:: ጌታችን ከሰው የሚፈልገው ግን ከባድና አስጨናቂ የሆኑ ነገሮችን አይደለም፤ « እናንተ ደካሞች፥ ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ ወደ እኔ ኑ እኔም አሳርፉችኀለሁ… ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና» በማለት የእርሱ ቀንበር ቀላልና የማይጎረብጥ መሆኑን ነገረን። የተለያዩ ሰዎች መጥተው ምን አናድርግ?» እያሉ በጠየቁት ጊዜ ዮሐንስ መጥምቅ የነገራቸዉ በዚያው በአቅማቸው ሊሠሩት የሚችሉትን እንጂ ከባድ የሆኑ ነገሮችን አላዘዛቸውም ሉቃ.3፥10-14:: ምክንያቱም ገና በመንፈስ ያላደጉ ስለነበሩ ከበድ ያለ ነገር ቢነግራቸው አይችሉትምና፡፡ ጌታችንም፦ «ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ሁሉ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉላቸው፤ ሕግም ነቢያትም ይህ ነውና በማለት ለሁሉም በሚቻልና በማይከብድ ሁኔታ አዘዘ ማቴ.7÷1። ሌሎች ለእኛ ሊያደርጉልን የምንወደውን ነገር እኛም ያንን ለሌሎች ማድረግ እንችላለንና። ሌሎች እንዲያደርጉልን ከምንፈልገው ነገር እኛ ለሌሎች ማድረግ የማንችለው ካለ ከሌሎች የምንፈልገው እኛ የማንችለውን ነው ማለት ነው። እኛ የማንችለውን ከሌሎች መጠበቅ ደግሞ ተገቢ አይደለም፡ እንዲሁም ራሳችን ከሌሎች የምንፈልገውን ጠንቅቀን እንደ ምናውቅ ሁሉ ሌሎች ከእኛ የሚፈልጉትንም በእኛው ፍላጎት አንጻር በቀላሉ ማወቅ እንችላለን፡ ስለዚህ ይህን ማወቅም ሆነ መፈጸም ከባድ አይደለም።
...................

ወደ ክርስትና የገቡት አይሁዶች እንኳ ኦሪታዊ ልማዳቸው አልተዋቸው ብሎ ከቤተ አሕዛብ እያመኑ ወደ ክርስትና የሚመጡትን አማንያን «ያንኑ የኦሪቱን ሕግና የሙሴን ትእዛዛት በሙሉ ሊጠብቁ ይገባል» እያሉ ስላስቸገሩ በዚህ ምክንያት የመጀመሪያው የቤተ ክርስቲያን ጉባኤ በኢየሩሳሌም ተደርጓል። በዚህ ጉባኤም ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ «እንግዲህ አባቶቻችንና እኛ ልንሸከመው ያልቻልነውን ቀንበር በደቀዛሙርት ጫንቃ ላይ በመጫን እግዚአብሔርን አሁን ስለምን ትፈታተናላችሁ?» በማለት የጉባኤ መግቢያ ሐሳብ ተናገረ። ከዚያም ቅዱሳን ሐዋርያት ከተወያዩ በኋላ፦ ለጣዖት ከተሰዋ ከደምም ፥ከታነቀም፥ ከዝሙትም ትርቁ ዘንድ ከሚያስፈልገው በቀር ሌላ ሸክም እንዳንጭንባችሁ እኛና መንፈስ ቅዱስ ፈቅደናልና ክዚህ ሁሉ ራሳችሁን ብትጠብቁ በመልካም ትኖራላችሁ» ሲሉ በአንድነት ወሰኑ። የሐዋ. 15፥29።

#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ

#በየጥቂቱ_ማደግ

ሐመር መስከረም/ጥቅምት ፲፱፻፺፰ ዓ.ም
ምሳሌ 10
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ የሰሎሞን ምሳሌዎች። ጠቢብ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፤ ሰነፍ ልጅ ግን ለእናቱ ኀዘን ነው።
² በኃጢአት የተገኘ መዝገብ ጥቅም የለውም፤ ጽድቅ ግን ከሞት ያድናል።
³ እግዚአብሔር የጻድቁን ነፍስ አያስርብም፤ የኀጥኣንን ምኞት ግን ይገለብጣል።
⁴ የታካች እጅ ችግረኛ ታደርጋለች፤ የትጉ እጅ ግን ባለጠጋ ታደርጋለች።
⁵ በበጋ የሚያከማች ልጅ አስተዋይ ነው፤ በመከር የሚተኛ ግን እርሱ ራሱን ያስነውራል።
⁶ በረከት በጻድቅ ራስ ላይ ነው፤ የኀጥኣንን አፍ ግን ግፍ ይከድነዋል።
⁷ የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው፤ የኀጥኣን ስም ግን ይጠፋል።
⁸ በልቡ ጠቢብ የሆነ ትእዛዝን ይቀበላል፤ በከንፈሩ የሚሰንፍ ግን ይወድቃል።
⁹ ያለ ነውር የሚሄድ ተማምኖ ይሄዳል፤ መንገዱን የሚያጣምም ግን ይታወቃል።
¹⁰ በዓይኑ የሚጠቅስ መከራን ያመጣል፤ ደፍሮ የሚገሥጽ ግን ሰላምን ያደርጋል።
¹¹ የጻድቅ አፍ የሕይወት ምንጭ ናት፤ የኀጥኣንን አፍ ግን ግፍ ይከድነዋል።
¹² ጥል ክርክርን ታስነሣለች፤ ፍቅር ግን ኃጢአትን ሁሉ ትከድናለች።
¹³ በብልሃተኛ ከንፈር ጥበብ ትገኛለች፤ በትር ግን አእምሮ ለጐደለው ሰው ጀርባ ነው።
¹⁴ ጠቢባን እውቀትን ይሸሽጋሉ፤ የሰነፍ አፍ ግን ለጥፋት ይቀርባል።
¹⁵ የባለጠጋ ሀብት ለእርሱ የጸናች ከተማ ናት፤ የድሆች ጥፋት ድህነታቸው ነው።
¹⁶ የጻድቅ ደመወዝ ለሕይወት ነው፤ የኀጥእ ፍሬ ግን ለኃጢአት ነው።
¹⁷ ተግሣጽን የሚጠብቅ በሕይወት መንገድ ይሄዳል፤ ዘለፋን የሚተው ግን ይስታል።
¹⁸ ጥልን የሚከድን ሐሰተኛ ከንፈር አለው፤ ሐሜትንም የሚገልጥ ሰነፍ ነው።
¹⁹ በቃል ብዛት ውስጥ ኃጢአት ሳይኖር አይቀርም፤ ከንፈሩን የሚገታ ግን አስተዋይ ነው።
²⁰ የጻድቅ ምላስ የተፈተነ ብር ነው፤ የኀጥኣን ልብ ግን ምናምን ነው።
²¹ የጻድቅ ከንፈሮች ብዙ ሰዎችን ይመግባሉ፤ ሰነፎች ግን ከልባቸው ጕድለት የተነሣ ይሞታሉ።
²² የእግዚአብሔር በረከት ባለጠጋ ታደርጋለች፥ ኀዘንንም ከእርስዋ ጋር አይጨምርም።
²³ ክፉ ነገር ማድረግ ለሰነፍ ሰው ጨዋታ ነው፤ እንዲሁም ጥበብ ለአስተዋይ ነው።
²⁴ የኀጥእ ሰው ፍርሃት በላዩ ይመጣበታል፥ ለጻድቃንም ምኞታቸው ትሰጣቸዋለች።
²⁵ ዐውሎ ነፋስ ሲያልፍ ኀጥእ አይገኝም፤ ጻድቅ ግን የዘላለም መሠረት ነው።
²⁶ ሆምጣጤ ጥርስን፥ ጢስም ዓይንን እንደሚጐዳ፥ እንዲሁም ታካች ለላኩት።
²⁷ እግዚአብሔርን መፍራት ዘመንን ታረዝማለች፤ የኀጥኣን ዕድሜ ግን ታጥራለች።
²⁸ የጻድቃን አለኝታ ደስታ ነው፤ የኀጥኣን ተስፋ ግን ይጠፋል።
²⁹ የእግዚአብሔር መንገድ ያለ ነውር ለሚሄድ አምባ ነው፥ ጥፋት ግን ክፋትን ለሚያደርጉ።
³⁰ ጻድቃን ለዘላለም አይናወጡም፤ ኀጥኣን ግን በምድር ላይ አይቀመጡም።
³¹ የጻድቅ አፍ ጥበብን ይናገራል፤ ጠማማ ምላስ ግን ትቈረጣለች።
³² የጻድቅ ከንፈሮች ደስ የሚያሰኝ ነገርን ያውቃሉ፤ የኀጥኣን አፍ ግን ጠማማ ነው።
2024/11/15 12:43:45
Back to Top
HTML Embed Code: