Telegram Web Link
ኪዳነ ምሕረት

በድንቅ ጥበቡ እግዚአብሔር አምላክ ዓለምን ያደነው እጅጉን መሐሪ ስለሆነ ነው፡፡ የቀደሙት የብሉይ ኪዳን ኪዳናት ሕዝቡን ከሲኦል መታደግ አልቻሉም ነበር፡፡ ፍጹም የሆነው ኪዳን የተደረገው በሰባተኛው ኪዳን ይህም ለሰው ዘር ምሕረትን ባስገኝች በንጽሕት ቅድስት ድንግል ማርያም ነው፡፡  
 
የምሕረት ቃል ኪዳን የተሰጠችውን እናታችንንም ‹‹ኪዳነ ምሕረት›› እያልን የምንማጸናት ለዚህ ነው፡፡ ለአዳም የተገባለት የምሕረት ቃል በእርሷ ተፈጽሟልና፡፡ እመቤታችን አምላክን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና ወልዳዋለችና፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መከራን ተቀብሎ እንዲሁም በመስቀል ተሰቅሎ ዓለምን ያዳነው ከእርሷ በነሣው ሥጋና ነፍስ ነውና፡፡  
 
በነገረ ማርያም ተጽፎ እንደምናገኘው ከጌታችን ከመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገት በኋላ እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ልጇ መቃብር ቦታ ጎልጎታ እየሄደች ትጸልይ ስለ ነበር  በየካቲት ፲፮ ቀን በጸለየችው ጸሎት ቃል ኪዳን ገብቶላታል፡፡ ጸሎቷም እንዲህ የሚል ነበር፤ ‹‹ልጄ ወዳጄ ሆይ፥ ከሥጋዬ ሥጋ ከነፍሴ ነፍስ ነሥተህ ሰው በመሆንህ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በቻለችህ ማኅፀኔ ከአንተ ጋር ሀገር ለሀገር ስለ መሰደዴ መጥተህ ልመናዬን ትሰማኝ ዘንድ እለምንሃለሁ፡፡››
 
ጌታችንም ምን ሊያደርግላት እንደምትሻ ሲጠይቃት በስሟ ለሚማጸኑ፣ መታሰቢያዋን ለሚያደርጉ፣ ለችግረኛ ለሚራሩ፣ በስሟ ቤተ ክርስቲያን ለሚያንጹ፣ ዕጣን፣ ዘይትና መብአ ለቤተ ክርስቲያን ለሚሰጡ ምሕረትን እንዲያደርግላቸው ጨምራ ጠየቀችው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በየካቲት ፲፮ ዕለት የገባላትን ቃል ኪዳን እንዲህ በማለት በመሐላ አጽንቶታል፡፡  ‹‹መሐልኩ ለኪ በርእስየ ወበአቡየ ወበመንፈስ ቅዱስ ሕያው፤ በራሴ፣ በአባቴ እና በመንፈስ ቅዱስ ማልኩልሽ፡፡›› 
የምሕረት ቃል ኪዳን የተሰጠበት ይህ ዕለት ታላቅ ነውና ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በድምቅት ታከብረዋለች፡፡ ቀድሞ ለነበሩ ኪዳናት ማለትም ኪዳነ አዳም፣ ኪዳነ ኖህ፣ ኪዳነ መልከ ጸዴቅ፣ ኪዳነ አብርሃም፣ ኪዳነ ሙሴና ኪዳነ ዳዊት መደምደሚያ ነውና፡፡ ዘለዓለማዊ ስለ ሆነው የማያልፍ የምሕረት ቃል ኪዳን እየታሰበም በመዝሙር፣ በማኅሌትና በቅዳሴ ይከበራል፡፡
 
በክርስቶስ ክርስቲያን ለምንባል ለእኛ የሐዲስ ኪዳን የቤተ ክርስቲያን ልጆችም ይህ አዲስ ውል የተደረገልን ለነፍሳችን ድኅነት በመሆኑ በስሟ እየተማጸንን እንዲሁም መታሰቢያዋን እያደረግን ለተራቡት ማብላት፣ ለተጠሙት ማጠጣትና ችግረኛ መርዳት ይገባናል፡፡  

የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ጸሎት፣ አማላጅነትና ተረዳኢነት አይለየን፤ አሜን! 
ጾመ ነነዌ

ወደ ከተማችን አንድ ሰባኪ ሊሰብክ መጣ ፣ የመጣው ለመስበክ ፈልጎ አልነበረም እኛን ለማዳን ጉጉት አድሮበት ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ሊያሰማን ጓጉቶ አልነበረም  በግድ ተገፍትሮ ፣ ተተፍቶ ፣ ተወርውሮ የመጣ ዓይነት ሰው ነበር ወደ መሃል ከተማም አልገባም የከተማችን አንድ ሦስተኛውን ብቻ ከተጓዘ በኋላ ስብከቱን ጀመረ፡፡ የሰበከው ስብከት  ሰላምታ የለውም ፣ መግቢያ የለውም ፣ መውጫም የለውም ፣ ማጽናኛም የለውም ፣ ‹ንስሓ ግቡ› የሚል አዋጅ የለውም፡፡ በጩኸት የተናገረው አንድ አስደንጋጭ ዐረፍተ ነገር ብቻ ነበር ‹‹በሦስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገለበጣለች!!›› ከነነዌ ነዋሪዎች አንዱ የነነዌን ታሪክ ቢጽፈው የሚጽፈው እንዲህ ነበር፡፡ 

የነነዌ ሰዎች እግዚአብሔርን የማያውቁ አሕዛብ ናቸው፡፡ ዮናስ ደግሞ እነርሱ የማያውቁትን አምላክ የሚያመልክ ነቢይ ነው፡፡ ዮናስ ወደ እነርሱ የመጣው የማዳን ተልዕኮ ይዞ አልነበረም፡፡ ወደ አሕዛብ መላኩ አላስደሰተውም፡፡ ዮናስ ወደ ነነዌ የመጣው እንደ ሌላ ሰባኪ በየትኛውም ትራንስፖርት ተጉዞ ሳይሆን በዓሣ አንበሪ ወደ ነነዌ ተተፍቶ ነው፡፡ የተተፋ ሰባኪ እንዴት ደስ ብሎት ይሰብካል? እንኳን ስብከት ይቅርና ማንኛውም ሥራ ያለ ፍላጎት እንዴት ሊሳካ ይችላል? ዮናስ የነነዌ ሕዝብ እንዲድን ፍላጎትም አልነበረውም፡፡ እንዲያውም ከመጀመሪያውም ፍርሃቱ ‹ትጠፋላችሁ› ብሎ ተናግሮ ሳይጠፉ ቢቀሩስ የሚል ነበር፡፡ 

ዮናስ ወደ ከተማይቱ  ዘልቆ ሲገባም በፍላጎት አልሰበከም ፤ የሰበከው ስብከት ተስፋ የሚያስቆርጥ ፣ እንደ ሰይፍ የሚቆራርጥ ነበር፡፡ የነነዌ ሰዎች የማያውቁትን አምላክ እንዲያውቁ ዕድል የሚሠጥ ትምህርት አልተሠጣቸውም፡፡ ዮናስም እንደ ኖኅ ‹ይኼንን ያህል ዘመን ተሠጥቷችኋል ተመለሱ› ብሎ አልሰበከም፡፡ መርከብ ሠርቶ ግቡም አላላቸውም፡፡ ‹በሦስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገለበጣለች› ብሎ ጮኸ፡፡

የነነዌ ሰዎች ግን ‹ማን ነው የሚገለብጣት?› ‹ለምን ትገለበጣለች?› ‹ለመሆኑ አንተ ማን ነህ?› ‹ዝም ብሎ ትገለበጣላችሁ ይባላል? መጀመሪያ ትምህርት አይቀድምም?› አላሉም፡፡ራሳቸውን እንጂ ሰባኪውንና ስብከቱን ለመገምገም ጊዜ አልነበራቸውም፡፡ ‹‹እግዚአብሔርን አመኑ ለጾም አዋጅ ነገሩ ከታላቁ ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ›› 

አንድ ላይ ኃጢአት መሥራት ቀላል ነው ፤ አንድ ላይ ንስሓ መግባት ግን ይከብዳል፡፡ በሀገር ደረጃ ንስሓ መግባት ግን እጅግ ያስደንቃል፡፡ ‹ነነዌ የምትገለበጥ ከሆነ ሀገር እንቀይር› አላሉም ፤ ሀገር ከመቀየር ይልቅ ራሳቸውን መቀየር እንደሚሻል ተረድተው ነበር፡፡ ሁሉም እኩል ልቡ ተሰበረ ፤ ሁሉም ማቅ ለበሰ፡፡

የሰባኪው ስብከት ጣዕም የለውም ብለው አላማረሩም ፣ ‹ተስፋ የሚሠጥ ስብከት መቼ ሰማን› አላሉም፡፡ ሰባኪው እያዋዛ አላስተማራቸውም ፣ ምሳሌ አልነገራቸውም ፣ ቅኔ አልተቀኘላቸውም ፣ ቅዱስ ኤፍሬም እንዲህ ይላል ‹‹የተላከላቸው ጨካኝ ሐኪም ነበር ፤ የያዘው መድኃኒትም የሚያቃጥል ነበር ፤ እንደ ሰይፍ የሚቆራርጥ ቃል ተናገራቸው ፤ እነርሱ ግን አቁስሏቸው ተፈወሱ››    

የነነዌ ሰዎች ንስሓ ከላይ እስከታች ነበር፡፡ ነገሥታቱ ሳይቀር ማቅ ለበሱ፡፡ ‹‹ነነዌ ትገለበጣለች› ብሎ ሲናገር ንጉሡ ወታደሮች ልኮ ዮናስን ማሰር ይችል ነበር፡፡ ‹‹ምን በሀገራችን ላይ ታሟርታለህ? ›› ብለው አፉን አላፈኑትም፡፡ መፍትሔውን ንገረን ያለውም የለም ፤ ችግሩ እነርሱ ናቸውና መፍትሔውንም ያውቁታል፡፡ ስለዚህ ራሳቸውን መውቀስ ወደዱ፡፡

ሀገሪቱ በአንድ ልብ አለቀሰች፡፡  ንጉሡ ፡- ሰዎችና እንስሶች አንዳች አይቅመሱ! ብሎ አዋጅ አስነገረ፡፡ ከቤተ መንግሥት ጾም የሚታወጅባት ነነዌ እንዴት የታደለች ናት? ‹‹መኳንንቶችሽ ማልደው የሚበሉ አገር ሆይ ወዮልሽ›› ተብሎ ከተጻፈ መኳንንቶችዋ የሚጾሙላት ሀገር እንዴት የታደለች ትሆን? (መክ. 10፡16) መቼም ሕዝብ ብቻ መጾሙ ነገሥታት ቢበሉ የተለመደ ነው፡፡ ነገር ግን እየበሉ የሚጾምን ሕዝብ መምራት እንዴት ይቻላል? ሲጠጡ እያደሩስ ሲጸልይ የሚያድርን ሕዝብ መምራት እንዴት ይቻላል?

ንጉሥሽ ላንቺ ማቅ ለብሶ ያለቀሰልሽ ፣ እንስሳት ሳይቀር የጾሙልሽ ነነዌ ሆይ ምንኛ የታደልሽ ነሽ? ሕዝብሽ ጾም ሲታወጅ የማያላግጡ ፣ ‹እኔ በፈለግሁበት ጊዜ ነው የምጾመው› ብለው የማይመጻደቁ ፣ እንኳን ከቤተ ክህነት ይቅርና ከቤተ መንግሥት የታወጀን ጾም በትሕትና የሚጾሙብሽ ነነዌ ሆይ ምንኛ የታደልሽ ነሽ? የዋሐን ሕጻናትን ጡት ከልክለው የፈጣሪን ርኅሩኅ ልብ የሚያስጨንቁ ፣ እንስሳትን ከውኃ ከልክለው ለምህላ የታጠቁ የነነዌ ሰዎች ምንኛ ድንቅ ናቸው፡፡

ቅዱስ ኤፍሬም ያቺን ከተማ በዓይነ ሕሊናው በጎበኛት ጊዜ እንዲህ ብሏል ፡-
‹‹የንጉሥ ቤት ግብዣ ተቋረጠ ፣ ንጉሥ ማቅ ለበሰ ፤ ንጉሥ ማቅ ከለበሰ ደግሞ የጌጥ ልብስ ይለብሳል፡፡ በዚያን ጊዜ በነነዌ ወርቃችሁን ብትጥሉ ማንም አይሰርቀውም፤ ሀብታችሁ ያለበትን ቤት ክፍት ትታችሁ ብትሔዱ ማንም ዘው ብሎ አይገባም፡፡ ወንዶች ወደ ሴቶች በምኞት አይመለከቱም ፤ ሴቶችም የሚያያቸውን ለመማረክ ጌጦቻቸውን አላደረጉም፡፡ ከልጆቻቸው ጋር አብረው ወደ መቃብር ሊወርዱ ነውና አረጋውያን በላያቸው አመድን ነሰነሱ፡፡ ወላጆች በልጆቻቸው ጥያቄ ተጨነቁ ፤ አብርሃም ልጁ ይስሐቅ ‹የመሥዋዕቱ በግ ወዴት ነው› ሲለው የተጨነቀው ጭንቀት በነነዌ ወላጆች ተደገመ››    

‹‹የነነዌ ንጉሥ ወታደሮቹን ሰብስቦ እንዲህ አላቸውም ፡- ይህ ድል እንደተጎናጸፍንባቸው ውጊያዎቻችን አይደለም ፤ ከባዕድ ሀገር በተሰማው ዜና ኃያላኖቻችን ሳይቀሩ ተብረክርከዋል ፤ አንድ ዕብራዊ መጥቶ በቃሉ አብረከረከን፡፡ የጀግኖች እናት ነነዌ አንድን ለብቻው የመጣ ደካማ ሰው ቃል ፈርታለች፡፡ ስለዚህ ወገኖቼ ፤ የማይፈርስ አጥር እንገንባ ፤ ይህች አጥር ንስሓ ናት ፤ ሥውር ጦርነት ታውጆብናልና ራሳችንን ሥውር መሣሪያ እናድርግ!!››

ዮናስ በነነዌ መመለስ ደስ አልተሰኘም ፤ ትንቢቱ ስለማይፈጸምለት ብቻ አይደለም፡፡ ‹‹የእስራኤል ሽማግሌዎች በሚቀማጠሉባት ሰዓት የነነዌ ሽማግሌዎች ሲያለቅሱ አየ ፤ ጽዮን በዝሙት እንደ ሰም ስትቀልጥ ነነዌ ታነባ ነበር›› እስራኤል ከፈጣሪ በራቁበት ሰዓት አሕዛብ የንስሓ ዕንባ ሲታጠቡ ሲያይ ክብር ከእስራኤል መልቀቁን አይቶ ተከፋ፡፡  ዮናስ እስከመጨረሻው ሰዓት የነነዌን መጥፋት ይጠባበቅ ነበር፡፡ ዮናስ ነነዌ የምትገለበጥበትን ቀን ሲቆጥር ነነዌ ደግሞ ኃጢአትዋን ትቆጥር ነበር፡፡ 
ዮናስ ስለ ነነዌ እንደ ሙሴ ‹እነርሱን ከምታጠፋ እኔን አጥፋኝ› አላለም ፤ በተቃራኒው ‹እነርሱን ካላጠፋህ እኔን አጥፋኝ› እስከማለት ደረሰ፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም ነነዌን ወከሎ ነቢዩን እንዲህ ይለዋል ፡- ‹‹አንተ ዕብራዊ ሆይ ሁላችን ብንጠፋ ምን ይጠቅምሃል? አንተ ሰባኪ ሆይ በሁላችን መሞትስ ምን የተሻለ ነገር ይገኛል? የማቴ ልጅ ሆይ ወደ መቃብር በጸጥታ ብንወርድ ምን ታገኛለህ? በቃልህ ፈውሰኸን ልናመሰግንህ ስንመጣ ለምን ታዝናለህ? ዕጣህ ነነዌን ተናግሮ ያጠፋት ከመባል ይልቅ ተናግሮ ያተረፋት መባል ቢሆን አይሻልህም? መላእክት በሰማይ ሲደሰቱ አንተ ለምን ታዝናለህ? ዮናስ ሆይ ከእንግዲህ በስምህ የምትጠራ ናትና ነነዌን አመስግናት›› በእርግጥም ዮናስ በሽተኛ አክሞ ስለዳነለት የሚበሳጭ ሐኪም ሆነ፡፡ የነነዌ ሰዎች ግን የሰባኪው ማንነት ፣ የስብከቱ ውበት አልባነት ፣ የአነጋገሩ ለዛ ምክንያት ሳይሆናቸው ተስፋ በማይሰጥ ስብከት ተሰብረው ራሳቸውን አዳኑ፡፡ ብዙ ስብከት አልፈለጉም ፤ ክፋትን ለመተው እና ይቅር በለን ለማለት የተሰበረ ልብ እንጂ በእውቀት መሞላት አያስፈልግም፡፡ ኃጢአታችን ከነነዌ ሰዎች ከበለጠ ቆየ ፤ የጋራ ክፋታችንን በጋራ ንስሓ እንጠበው፡፡

https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
ወንድማችሁን ለመግፋት ሳይሆን...
ወንድሞቼ! ከእናንተ መካከል አንድ አይነ ስውር ሰው ወደ ጉድጓድ ገብቶ ሊወድቅ ሲል እጁን ዘርግቶ የማይደግፈው ማን ነው? የታዲያስ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በልቡናቸው ታውረው ወደ ሲኦል ጉድጓድ ለዘለአለም ሲወድቁ እንደ ምን እጃችን የበለጠ አይዘረጋም? ወገኖቸ! በነፍስም በሥጋ የታመመ ሰውን ስታዩ <ይህ የእኔ ስራ አይደለም ፤የቀሳውስትና የመነኮሳት ስራ እንጂ። ምክንያቱም ሚስት አለችኝ፤ልጆችንም አሳድጋለሁ> አትበል። እስኪ ምሳሌ መስዬ ልጠይቃችሁ ፤እናንተም መልሱልኝ። አንድ ትልቅ በወርቅ የተሞላ ሳጥን ወድቆ ብታዩ <ይህ እኔን አይመለከተኝም ፤ሌሎች መጥተው ያንሱት እነጂ>ትላላችሁ? ግራ ቀኛችሁን አይታችሁ በፍጥነት የምታነሱት አይደለምን?
ይህ ወደ ዘለአለም ጉድጓድ እየወደቀ ያለው ወንድማችሁም ከዚያ ወርቅ በላይ ውድ የእግዚአብሔር ሀብት ነውና አንሱት እንጂ የበለጠ እንዲወድቅ አትግፉት። እግዚአብሔር ይህን በተመለከተ በአፈ ያዕቆብ እንዲህ ብሏልና፦<ወንድሞቻችን ሆይ!ከእናንተ ወገን ከጽድቅ ወጥቶ የበደለ ቢኖር መክሮ አስተምሮ ከበደሉ የመለሰው ቢኖር ራሱን አንድም ወንድሙን ከሞት እንዳዳነ ይወቅ። የራሱን አንድም የወንድሙን ብዙ ሀጢአቱን አንዳስተሠረየ ይወቅ። አንድም የወንድሙን ነፉስእንዳዳነ ይወቅ።/ያዕ፡5፥19/✞✞✞✞✞

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
በምጽአት ቀን ሕይወትን ልናገኝ እንዲሁም መንግሥተ ሰማያትን ልንወርስ ይገባናል፡፡

አምላካችን እግዚአብሔር ጸሎታችንን ሰምቶ፣ ልመናችንን ተቀብሎና ጾማችንን አስቦ ምሕረትን ያድርግልን፤ አሜን!!!
ያዕቆብ ለራሔል ስለነበረው ፍቅር መጽሐፍ ሲናገር እንዲህ ይላል

ኦሪት ዘፍጥረት 29
20፤ ያዕቆብም ስለ ራሔል ሰባት ዓመት ተገዛ፤ እርስዋንም ይወድዳት ስለነበረ በእርሱ ዘንድ እንደ ጥቂት ቀን ሆነለት።

ሰባት ዓመት ሙሉ ራሄልን ስለማግኘት ለላባ(ለራሔል አባት) ተገዛ.. በእርግጥ ሌላም ተጨማሪ ሰባት ዓመት ተገዝቷል.. እና በጣም የሚያስገርመው ግን ሰባት ዓመት መገዛቱ ሳይሆን "እርስዋንም ይወድዳት ስለነበረ በእርሱ ዘንድ እንደ ጥቂት ቀን ሆነለት።" መባሉ ነው..

ሰው ጌታችን ኢየሱስን አብዝቶ ሲያፈቅር ከእርሱ ጋር መኖርን እያሰበ ብዙ የዝች ዓለምን ውጥንቅት ይታገሳል.. ከእርሱ ጋር ስለመኖር ራሱን ይገዛል.. እና ፍቅሩ ስለሚኖር መከራው ቀላል ይሆንለታል

@Apostolic_Answers
ለድላቸው እግዚአብሔርን ለሽንፈታቸው ከእግዚአብሔር መለየታቸውን ማውሳት የቀደምት ኢትዮጵያውያን አባቶች ጠባይዕ ነው።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጾምን ቀድሱ፥ጉባኤውንም፡ዐውጁ፤ሽማግሌዎችንና በምድር የሚኖሩትን ዅሉ ወደ አምላካችኹ፡
ወደ እግዚአብሔር ቤት ሰብስቡ፥ወደ፡እግዚአብሔርም ጩኹ።
-ትንቢተ ኢዮኤል 1:14
2024/11/15 09:07:10
Back to Top
HTML Embed Code: