ቅዱስ ጳውሎስን ስለመረዳት
***
ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቶቹ (በተለይ በሮሜ፣ ገላትያ እና 2ኛ ቆሮንቶስ) ስለ "የእግዚአብሔር ጽድቅ" እና በሥራ ሳይሆን "በእምነት ስለ መጽደቅ" ደጋግሞ ይናገራል። ይህም በ16ኛ መ/ክ/ዘመን የፕሮቴስታንት ተሐድሶ እንቅስቃሴ በእግዚአብሔር ፊት ለመጽደቅ ሥራ አያስፈልግም (Sola Fide እና Sola Gracia) የሚል ትርጉም ተሰጥቶታል። ከዚያም በክርስትናው ዓለም መነጋገሪያ ሆኖ ባጅቷል።
በዋናነት ከ20ኛው መ/ክ/ዘመን መጀመሪያ ጀምሮ በተደረጉ ቅዱስ ጳውሎስን ከሮም ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እና ከተሐድሶ አራማጆች ውዝግብ ዓውድ አውጥቶ በመጀመሪያዎቹ የክርስትና ዘመናት ከነበረው የአይሁድ ትውፊት እና ከቅዱስ ጳውሎስ ልዩ ተልእኮ (የአሕዛብ ሐዋርያ ሆኖ መመረጥ) አንጻር የመረዳት እንቅስቃሴ መልካም ፍሬዎችን አፍርቷል። በዚህም መሠረት የሚከተሉት ጉዳዮች በብዙ ሊቃውንት (በዚህ እንቅስቃሴ ውስጥ ግንባር ቀደም የሆኑ ብዙ ኘሮቴስታንት ሊቃውንትን ጨምሮ) ተቀባይነት አግኝተዋል፦
1. ቅዱስ ጳውሎስ "የእግዚአብሔር ጽድቅ" እያለ የሚጠራው ጠቅለል ባለ ሁኔታ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ የተሰጠውን መዳን ነው። ይህ መዳን ሥርየተ ኃጢአትን ይጨምራል፤ ነገር ግን ያ ብቻ አይደለም። ከኃጢአት ባርነት ወጥቶ በክርስቶስ ጌትነት በማመን ለእርሱ በመታዘዝ ለመኖር ከእግዚአብሔር ኃይል ማግኘትን ይጨምራል። "በወንጌል አላፍርምና፤ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው፥ ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን ነውና። ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎ እንደ ተጻፈ የእግዚአብሔር ጽድቅ ከእምነት ወደ እምነት በእርሱ ይገለጣልና፤" ብሎ የእግዚአብሔርን የማዳን ኃይል በእምነት ከተገለጠው የእግዚአብሔር ጽድቅ ጋር አንድ ያደርገዋልና። (ሮሜ. 1፥16-17) በመሆኑም የእግዘብሔርን ጽድቅ "ኃጢአትህ ተትቶልሃል፤ ኃጢአተኛ ብትሆንም ክርስቶስ በአንተ ፈንታ ስለሞተ የእርሱ ጽድቅ ለአንተ ተቆጥሮልሃል" ብሎ ብቻ መተርጎም ቀናሽ (reductionist) በመሆኑ ስህተት ነው። በእኛ ውስጥ ለጽድቅ የሚሠራ የእግዚአብሔር ኃይል መኖሩን እና እኛም በዚህ እየታገዝን ከክርስቶስ አካልነት እና ከመንፈስ ቅዱስ ኅብረት (እነዚህ አገላለጾች ቅዱስ ጳውሎስ በእኛ ያለውን ለጽድቅ ሕይወት የሚሆን የእግዚአብሔር የማዳን ኃይል የሚገልጽባቸው የተለመዱ 'participatory' አገላለጾቹ ናቸው) እንዳንወጣ መጋደል ይገባናልና።
2. ቅዱስ ጳውሎስ የአሕዛብ ሐዋርያ ነው። በመሆኑም ትልቁ ትኩረቱ አሕዛብ ክርስቲያኖች ሲሆኑ ከአይሁድ ከመጡት ክርስቲያኖች ጋር ቀውስ እንዳይፈጠር ማድረግ ነው።“የእግዚአብሔር ጸጋ እንደ ተሰጠኝ መጠን እንደ ብልሃተኛ የአናጺ አለቃ መሠረትን መሠረትሁ፥ ሌላውም በላዩ ያንጻል። እያንዳንዱ ግን በእርሱ ላይ እንዴት እንዲያንጽ ይጠንቀቅ፤” ያለው ለዚህ ነው። (1ኛ ቆሮ. 3፥10) እርሱ ዋናው መሠረት ላይ ነው ይሠራ የነበረው። ቅዱስ ጳውሎስን ለመረዳት ይህ ዋናው ዓውድ ነው! ከዚህ ይልቅ የ16ኛው መ/ክ/ዘመን ውዝግብን ጳውሎስን ለመረዳት ዋና ማድረግ ለማሳሳት መፍቀድ ነው።
3. ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክታቱ "በእምነት ስለ መጽደቅ" ሲናገር ዋናው ጉዳዩ ከአይሁድ ሆነ ከአሕዛብ ወደ ክርስትና ስለ መግባት ነው። ሊቃውንቱ እንደሚሉት 'በእምነት መጽደቅ (justification by faith)' ክርስቲያን ወደመሆን ስለመቀየር የሚናገር 'transfer term' ነው። ('Jutification by faith' is not Paul's basis to teach Christian ethics; his basis to teach Christian ethics is being 'in Christ' and 'in the Spirit'. When you sin, you are separating yourselves from the body of Christ in which you are a member. Being 'in Christ' includes living according to His commandments.)
ቅዱስ ጳውሎስ የሚለው ለአይሁድም ሆነ ለአሕዛብ ወደ ክርስትና ለመግባት (በተገለጠው የእግዚአብሔር ጽድቅ ለመጽደቅ) የጋራ መነሻ ሊሆን የሚችለው እምነት ነው፤ ሥራ ከሆነ እሱ ሐዋርያ ሆኖ የተላከላቸው አሕዛብ ክርስቲያኖች ሊሆኑ አይችሉምና። በመሆኑም "በእምነት ጸድቀናል" ሲል በዋናነት "በእምነት ክርስቲያኖች ሆነናል" እያለ ነው። ይህ ሁሉም የሚቀበለው እውነት ነው። በእኛ ኃጢአተኝነት በእግዚአብሔር አዳኝነት አምነን ስንጠመቅ ከኃጢአታችን እንታጠባለን፤ በክርስቶስ ማዳን እንዲሁ በጸጋ የተሰጠንን ጽድቅ እንለብሳለን። (ስንጠመቅ እኛ ብቻ ሳንሆን አብረው የሚቆሙ ምእመናን ጭምር የሚለብሱት ነጭ ልብስ የዚህ ምልክት ነው።) ከዚያ በኋላ ግን ለክርስቶስ እየታዘዙ መኖር ግድ ነው። ለክርስቶስ የማይታዘዝ ከክርስቶስ አካል (ከመንፈስ ቅዱስ ኅብረት)ውጭ ይሆናል፤ ከክርስቶስ አካል ውጭ ሆኖ ደግሞ ጽድቅም ድኅነትም የለም።
4. በብሉይ ኪዳን ጽድቅ በቃል-ኪዳን (Covenant) ላይ የተመሠረተ ነበር። በኪዳኑ የጸና ጻድቅ ይባላል። እግዚአብሔር ሁልጊዜም ጻድቅ ነው። ሰው ግን ከጽድቅ ቢጎድልም በንስሐ እና በመሥዋዕት እየታገዘ በኪዳኑ ይቆያል። የእግዚአብሔር ጽድቁ ሕዝቡን ማዳኑ፣ መባረኩ፣ ከእነርሱ ሳይለይ መጠበቁ፣ ንስሐ ሲገቡ ይቅር ማለቱ እና በመጨረሻም በእውነት መፍረዱ ነው። የሕዝበ እስራኤል ጽድቃቸው ደግሞ እግዚአብሔር በሰጣቸው ዘርፈ ብዙ ሕጋት መኖር፣ ሲበድሉ ደግሞ ንስሐ ገብተው እንደ ሕጉ መሥዋዕት አቅርበው መመለስ ነው። በዚህ የማይኖር ግን ከኪዳኑ ውጭ ይሆናል። አሁን በዚህ አንጻር የቅዱስ ጳውሎስን ትምህርት እንየው። ኪዳኑ በክርስቶስ ክቡር ደም የተመሠረተው አዲስ ኪዳን ነው። የእግዚአብሔር ጽድቅ የማዳኑ ወንጌል ነው። በእምነት ሆነን ራሳችን ወደ ማዳኑ ስናቀርብ አጽድቆ እና ቀድሶ ወደ ኪዳኑ ያስገባናል።ከሥጋው ከደሙ ያካፍለናል። (ይህ በኪዳን ውስጥ የመኖር መገለጫ ነው፤ ክርስቶስ ለሐዋርያት ጽዋውን ሲሰጣቸው ደሙን አዲስ ኪዳን እንዳለው ልብ ይሏል። (ሉቃ. 22፥20)) በእኛ በኩልስ ኪዳኑን እንዴት እንጠብቃለን? ኪዳን በሁለቱም በኩል ሊጠበቅ ይገባልና። እኛ በኪዳኑ ውስጥ ለመኖር የእግዚአብሔርን ጽድቅ በተቀበልንበት ምነት መጽናት ይገባናል። በዚህ መሠረት ላይ በክርስቶስ ሆኖ ለኃጢአት ዘወትር መሞት እና ከመንፈስ ቅዱስ ኅብረት ላለመውጣት መጋደል ያስፈልጋል። (ሮሜ. 6፣ ዕብ. 3፥6-19፣ ቆላ. 3፥1-17፣ 1ኛ ቆሮ. 6፥9-20) የሕግ ሁሉ ፍጻሜ የሆነውን ፍቅርም ልንጠብቅ ይገባል። (ሮሜ. 13) ኃጢአት ሥንሠራ ቅዱሱን ኪዳን ስላፈረስን እና የእግዚአብሔርን ልጅ ሞቱን ስላቃለልን አዝነን ንስሐ ልንገባ ይገባል። ይህ ሁሉ የሚሆነው ግን በክርስቶስ ሕግ (ትእዛዝ) ስንኖር ነው፤ ሕግ በሌለበት ኃጢአትም ተጋድሎም የለምና። በክርስቶስ መኖር በፍቅሩ መኖር ነው፤ በፍቅሩ ለመኖር ደግሞ በትእዛዙ መኖር ይገባል። (ዮሐ. 14፥21-23) ጸጋው ርካሽ አይደለም፤ ኪዳኑም በእኛ በኩል የሚጠበቅ ግዴታ የሌለበት አይደለም።
Dn Bereket Azmeraw

1ኛ ዮሐንስ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁹ እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን🥰።
²⁰ ማንም፦ እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል?
²¹ እግዚአብሔርንም የሚወድ ወንድሙን ደግሞ እንዲወድ ይህች ትእዛዝ ከእርሱ አለችን።

የጌታችን በዐለ ልደት መቼ .pdf
192 KB
የጌታችን በዐለ ልደት መቼ? ለምን?
መድኃኒታችን የተወለደበት ቀን ይታወቃልን? የልደት በዐል የሚከበርበት ቀንስ በምዕራባውያንና በእኛ ቤተክርስቲያን ለምን ተለያየ?
የእኛ ቤተ ክርስቲያን ልደትን ለምን ታኅሣሥ ፳፱ ታከብራለች? ምዕራባውያንስ የልደትን በዐል ለምን December 25 ያከብራሉ?
በዲ/ን ያረጋል አበጋዝ

ስለ ጌታችን የልደት በዓል የቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናንዙ ስብከት
ክርስቶስ ተወልዶል፥ ምስጋናን አቀርቡ፤
ክርስቶስ ከሰማይ ነው፥ እሱን ለማግኘት ሂዱ፤
ክርስቶስ ምድር ላይ ነው፤ ቀና ያላችው ሁኑ፤
ምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር አዲስ ምስጋናን ታቅርብ፤ (መዝ 96፥1)
ሰማያት ደስ ይበላቸው ምድርም ሐሴትን ታድርግ፤ (መዝ 96፥12)
ሰማያዊው አሁን ምድራዊ ሆኗልና። (1ቆሮ 15፥47)
ክርስቶስ ሥጋን ለብሧልና፥ በመፍራትና በመንቀጥቀት በደስታ አመስግኑት፤(መዝ 2፥11)
መፍራትና መንቀጥቀጡ በኀጢአት ምክንያት፥ ደስታው ደግሞ በተስፋ ምክንያት ነው።
ክርስቶስ ከድንግል ተወለደ፤
ስለዚህም ሴቶች ክርስቶስን ትወልዱ ዘንድ ድንግልናን ተለማመዱ።
ከሁሉ በፊት አስቀድሞ የነበረውን የማያመልክ ማን ነው? (1ኛ ዮሐ 1.1)
የሁሉ መጨረሻ የሆነውንስ የማያገን ማን ነው? (ራእ 1፥17፤ 2፥8)
እንደገና ጨለማ ፈረሰ፤ እንደገና ብርሃን ተቋቋመ፤ (ዘፍ 1፥3-4)
እንደገና ግብጽ በጨለማ ተቀጣች፤(ዘጸ 10፥21-22)
እንደገና እስራኤል በእሳት ዓምድ አበራች፤ (ዘጸ 13፥21)
ባለማወቅ ጨለማ ውስጥ የተቀመጡ ሰዎች ሁሉ ታላቁን የእውቀት ብርሃን ይመልከቱ፤(ኢሳ 9፥2)
ያረጁት ነገሮች አልፈዋል፤ አሁን ሁሉም አዲስ ሆንዋል።(2 ቆሮ 5፥17)
ፊደል ወደኋላ ያስቀረራል መንፈስ ግን ወደፊት ያስቀድማል፤ (2ቆሮ 3፥6)
ጥላዎች ተገፈዋል፥ እውነት እሱን ተከትሎ ገብቷል፤
መልከ ጻዴቅ ተፈጽሟል፥ እናት የሌለው አሁን አባት የሌለው ስለሆነ ተፈጽሟል፤
በመጀመሪያ እናት አነበረውም፥ በሁለተኛው አባት የለውም፤ (ዕብ 7፥3)
የተፈጥሮ ባህሪይ ሕጎች ቀለጡ።
ክርስቶስ አዟል፥ አንቃወም፤
ሕዝቦች ሁሉ እጃችሁን አጨብጭቡ፤ (መዝ 47፥1)
ለእኛ ሕጻን ተወልዶልናልና፥ ልጅም ተሰጥቶናልና፥ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ነው፦ ከመስቀሉ ጋር ከፍ ከፍ ብሏልና፥ ስሙም የአብ ድንቅ መካር ተብሏልና።(ኢሳ 9፥6)
ዮሐንስ የጌታን መንገድ አዘጋጁ እያለ ያውጅ፤ (ማቴ 3፥3)
እኔ ራሴ የዚህችን ቀን ኃይል እናገራለው፤
ሥጋ የሌለው ሥጋን ወሰደ፣ ቃል ተዳሰሰ፣ የማይታየው ታየ፣ የማይነካው ተነካ፣ ከጊዜ በላይ የሆነው ጀመረ፣ የእግዚአብሔር ልጅ የሰው ልጅ ሆነ።
ኢየሱስ ክርስቶስ ትላንት ዛሬም ነገም እስከዘለዓለም አንድ ነው። (ዕብ 13፥8)
አይሁድ ያጉረምሩሙ፥ ግሪኮችም ያፊዙ፤
መናፍቃንም ምላሳቸው እስኪያማቸው ያውሩ፤
ወደ ሰማይ እያረገ ሲያዩት ያምናሉ፤ (ዮሐ 6፥62)
በዚህ ካላመኑ ግን ከሰማይ ሲመጣ እንደፈራጅም ሲቀመጥ አይተው ያምናሉ፤ (ማቴ 25፥31)
እነዚህስ በኋላ የሚመጡ ናቸው፤ አሁን ግን የመገለጥ(አስተርእዮ) በዓል ነው፥ የልደትም በዓል ነው፤ በዓሉን በሁለቱም ስሞች እንጠራዋለን፥ ለአንዱ እውነታ ሁለቱ ስሞች ተሰይመውለታልና፤
እግዚአብሔር በልደቱ ለሰው ልጆች ተገልጧልና ነው፤
በአንድ በኩል እሱ ነው(he is)፤ እሱም ከዘለዓለማዊው አማናዊ ኋኝ(Being) ለዘለዓለም ከሁሉ ምንጭ ከሁሉ መርህ በላይ የሆነ ነው፤ ከአማናዊው መርህ በላይ የሆነ መርህ ስለልለ።
በሌላ በኩል ለእኛ መሆንን የሰጠን እሱ በደህና መሆንን ይሰጠን ዘንድ ስለኛ ወደ ኋኝነት(being) መጣ፤
ይህም ከደህና መሆን በክፋት ወድቀናልና በሥጋዌው እንደገና ወደራሱ ያመጣን ዘንድ ነው።
ስሙ አስተርእዮ ነው፥ ስለተገለጠ፤
ስሙ ልደት ነው፥ ስለተወለደ፤
ይህ የእኛ በዓል ነው፥ እኛ ወደ እግዚአብሔር እንድንጓዝ ወይም እንድንመለስ እግዚአብሔር ከሰው ልጆች ጋር ሊኖር በመምጣቱ ዛሬ የምናከብረው ይህ በዓል ነው፤
ይህን እንዲህ ብሎ መናገር ይበልጥ ትክክል ነው፦ በአዲስ ሰውነት እንሸፈን ዘንድ አርጌውን ሰውነታችንን እናስወግድ፤(ኤፌ 4፥22) እናም በአዳም እንደሞትን በክርስቶስ እንኖር ዘንድ ከክርስቶስ ጋር እንወለድ ከእሱ ጋርም እንሰቀል፥(1ኛ ቆሮ 15፥22)(ገላ 2፥19) ከእሱ ጋርም ተቀብረን ከእሱ ጋር እንነሳ፤
ለእኔ በመልካሙ ለውጥ ማለፍ የተገባ ነውና፤
ደስ ከሚሉ ነገሮች የሚያሳምሙ ነገሮች እንደሚመጡ፥ ከሚያሳምሙ ነገሮች ደስ የሚሉ ነገሮች ይመጣሉ፤
ኃጢአት በበዛበት ቦታ ሁሉ ጸጋ ይበልጥ በዝቶ ይገኛል፥(ሮሜ 5፥20) ስለዚህ የእጸ በለስ ቅምሻ የሚያስፈርድ ከሆነ፥ የክርስቶስ ሕማም ምንኛ ያጸድቅ ይሆን?
ስለዚህ በዓልን አረማውያን እንደሚያከብሩበት አናከብረውም፤ አምላካዊ በሆነ መንገድ ነው እንጂ፤ በዓለማዊ መንገድ አናከብረውም፤ ከዓለም በላይ በሆነ መንገድ ነው እንጂ....
ታድያ ይህ እንዴት ነው? ክብ የአበባ ጉንጉን በራችን ላይ አናስቀምጥ ወይም ዳንሰኞችን አንሰብስብ ወይም መንገዶችን አናጊጥ፤ ዓይናችንን አናስደስት፣ ጆሮዎችንን አናስመስጥ፣ የማሽተት ሕዋሳችንን አናለስልስ፣ መቅመሳችንንም ልክ ባልሆነ መንገድ አናስገዛ፣ መዳሰሳችንንም የሚያረካ አናድርግ እነዚህ የተዘጋጁ የክፋት መንገዶች የኃጢአት በሮች ናቸውና፤ በውድና በስሱ በተሸመነ ልብስ አንሸነፍ፤ እነዚህ ልብሶች ውበታቸው የማይጠቅም ነው አልያም ውበታቸው በድንጋዮች ማብረቅረቅ አልያም በወርቅ ማብራት አልያም በአርቴፊሻል ቀለሞች የተገኘ ነው፥ እነዚህ ግን ተፈጥሯዊ ውበትን የሚሸፍኑ ከመለኮታዊ መልክ በተቃራኒ የሚቆሙ ናቸው። ወይም ከመጥፎ አስተማሪ መጥፎ ትምህርት ከመጥፎ ዘር መጥፎ ፍሬ እንደሚወጣ ከዝሙትና ፍትወት ጋር በሚገኙ ስካርነና በመጠጥ በተማላ ጭፍራ አንሸነፍ፤.....እርስ በርሳችን ኢ-ምግባራዊ በሆነ መንገድ ለመያዝ(ለማሳለፍ) አንስራ፤ ምክንያቱም ምንም ነገር ከበዛና ከሚያስፈልገን በላይ ከሆነ ኢ-ምግባራዊ ነውና። ሌሎች እንደኛው ሸክላ(አፈር) የሆኑና ተመሳሳይ አሰራር ያላቸው ሰዎች በተራቡበትና የእኛ ርዳታ በሚያስፈልጋቸው ወቅት (እንደዚህ ማክበር) ኢ-ምግባራዊነት ነው።
ትርጉም ዮሐንስ ሙሉጌታ 2015 ዓ.ም
Festal Orations: Oration 38 On the Nativity of Christ.

ጾሙስ አበቃ.....?
(#በአባ_ገብረ_ኪዳን)
ጾሙስ አበቃ የነፍስ ረሃባችን መቼ ያበቃ ይሆን? ነፍሳችን ሥጋውን ደሙን እስከመቼ ነው የምትጾመው? ጾሙስ ተደመደመ። የእኛ በደል መቼ ይሆን የሚቋጨው? ስግብግብነታችን መቼ ነው ዳር የሚደርሰው? በዚህ ጾም መጨረሻ የአብ አንድያ ልጁ ተወልዶ መለያየት ተወገደ ሰውና መላእክት አንድ ሆኑ፤ መቼ ይሆን ጎጠኝነታችን የሚጠፋው? መቼ ይሆን ሰማያዊ ዘመድ የምናበጀው። ጾም ተፈጽሟልና ለሥጋ ሥጋ ተገዛለት። ለዚህ ጾሞ ፋሲካ ለነፍስ ምን ቅመም ተቀመመላት? ምን ንብረት ተመደበላት? ምን ሙክት ተገዛላት? ምን ወይን ተጠመቀላት? ምን ልብስ ተሠራላት? ምን ድግሥ ተደገሠላት? እነማንን ድግሥ ጠራንላት? አጋንንትን ወይስ መላእክትን? ዛሬ ዛሬ የጾም መግቢያና መውጫ ይገርማል። የጾም መግቢያ ሥጋ ይበላል የጾም ፍጻሜ ሥጋ ይበላል። በሥጋ ጀምረን በሥጋ መጨረስን ተያይዘነዋል! ሥጋው በደል ሆኖ አይደለም መጀመሪያችን መፈጸሚያችን የሥጋ ብቻ መሆኑ ግን የነፍስ ያለህ ያሰኛል!
አንዳንድ ሰው የዘንድሮው በዓል ልዩ የሚያደርገው ዓመቱ መሆኑ ይመስለዋል። ልዩ የሚያደርገው ከአምናው በተለየ ነፍስ ያገኘችው ነገር ሲኖር ነው። ለሥጋ ተበድሮ ሳይቀር ይደገሳል። ቢያንስ ድኃ ቢያጣ ያለችውን አጥቦ ለብሶ ከጎረቤት ሥጋ እየሸተተው ይውላል። ነፍሳችንስ ቢያንስ የሚቆርቡትን እያየች የክርስቶስ መዐዛ ቢናፍቃትም ባይሆን ተናዝዘን ታጥበን ብንውል ምን አለ?
የጸሎት ረሀብ መቼ ነው የምንፈስከው? የንጽሕና ረሀብ መቼ ነው የምንገድፈው? መፈሰክ ማለት መሻገር ነው? ዝሙትን የተሻገርን ዕለት ያን ጊዜ ነበር ፋሲካ!
ሱባኤው ደረሠ ቀጠሮው ተፈጸመ ጌታ ተወለደ። የእኛ ቀጠሮ መቼ ነው የሚደርሰው? በዚህን ጊዜ...ን አደርጋለሁ ብቻ! ጸሎቱ ቀጠሮ ጾሙ ቀጠሮ ትጋቱ ቀጠሮ አሥራቱ ቀጠሮ ኑዛዜው ቀጠሮ መታረቁ ቀጠሮ ቁርባኑ ቀጠሮ ሁሉ ቀጠሮ!ማን አለ የእኛስ ቀጠሮ ቢደርስ ምን አለ ጽኑዕ ቀጠሯችን ሳይደርስ እኛ የቀጠርነውን ጽድቅ ብንጀምረው! ምን አለ የእኛም ሱባኤ አብቅቶ የእግዚአብሔርና የቅዱሳን ልጆች ሆነን በምግር ብንወለድ!
የጾመ ነቢያት ፍጻሜ ጌታ ተወለደ። እኛም ከንስሐ ማኅፀን እንድንወለድ ይርዳን። ከጾሙ መጨረሻ ክርስቶስ ከእነርሱ በሥጋ መጣ። ከጾማችን ፍጻሜ ጌታ በሰውነቴችን እንዲያድር ንስሐ ብንገባ ይህ ነው የጾም ፍጻሜ። ጌታ ሲወለድ አሮጌው ዘመን አበቃ። ሐዲስ ሕይወት፡ ተወጠነ። እኛም ኃጢአታችን በንስሐ አልቆ አዲስ ከዘንድሮው ልደት ጀምሮ አዲስ ሕይወት ለመኖር ያብቃን። ኃጢአታችን ይለቅልን!

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
The Eucharist service is our chance ...
Archpriest Theodore Gignadze
Archpriest Theodore Gignadze
እስኪ ንገረኝ! ምንስ ታስባለህ? በነፍሱ መከራ የሚቀበለው የትኛው ነው፡- የተሳደበ ሰው ወይስ የተሰደበ ሰው? የተሳደበ ሰው እንደ ኾነ ግልጽ ነው፡፡ ምክንያቱም አስቀድሜ እንደ ነገርኩህ አንድን ሰው ኃጠአተኛ የሚያሰኙት ከውስጥ ከሰውዬው የሚመነጩ ክፋቶች እንጂ ከአፍአ የሚመጡ አይደሉምና ከድርጊቱ ራሱ የታወቀ ነው - “ስሜት” መባሉም ለዚህ ነውና፡፡ ዳግመኛም በተሳዳቢው ላይ በሚፈጥሩት ነገር የታወቀ ነው፡፡ ተሳዳቢው ሲቈጣ ዓይነ ልቡናው ይታወራልና፤ አእምሮው ይታወካልና፤ [የጤና መታወክ ሳይቀር] ሌሎች ስፍር ቊጥር ጉዳትም ይደርስበታልና፡፡ ስለዚህ መከራ እየተቀበለ ያለው ተሰዳቢው ሳይኾን ተሳዳቢው መኾኑን መረዳት ይቻለናል፡፡
ምናልባት “እርሱ ልጄን ሞኝ ብሎ ተሳድቦአል” ልትለኝ ትችላለህ፡፡ እኔም እልሃለሁ፡- መሳደብ ራስን መጉዳት እንደ ኾነ ነግሬሃለሁ፤ ስለዚህ ሰውዬው ደካማ ኾኖ ስለ ተሳደበ አንተም እርሱን መስለህ ደካማ ኾነህ የስድብ አጸፌታ አትስጥ፡፡ እስኪ ልጠይቅህ! አንተም መልስልኝ! ይህ ሰው ልጅህን በመሳደቡ መልካም ነገር አደረገን? መቼስ “አዎ መልካም አድርጓል” አትለኝም፡፡ እንግዲያውስ አንተም እርሱ የፈጸመው መልካም ያልኾነን ግብር አታድርግ፡፡ ልጅህ በተሰደበ ጊዜ ወይም በእንደዚህ ዓይነት ሌሎች ኹኔታዎች ውስጥ በልብህ ሊፈጠር የሚችለውን ስሜት እረዳለሁ፡፡ ኾኖም እርሱን [ተሳዳቢውን] ባለመምሰል በራስህ ላይ መከራን ከማምጣት ተከልከል እልሃለሁ፡፡
ምናልባት “እንደዚህ በማድረጌ እንዳሸነፈኝ ቈጥሮ ቢንቀኝስ? ይህ ሳይበቃውና ከልጄም አልፎ እኔንም ጭምር ቢሰድበኝስ?” ብለህ ትጠይቀኝ ይኾናል፡፡ እኔም፡- “እንዲህ ያደረገውን ሰው በተሳሳተ መንገድ እየኼደ እንደ ኾነ በትሕትና ገሥጸው፣ ራሱን ከመጉዳት በቀር እርሱ አንተን በፍጹም ሊጎዳህ እንደማይችል ምከረው” ብዬ እመክርሃለሁ፡፡ በየውሃት፥ በልብ ውስጥ ያለውን የቊጣ ስሜት መፈረካከስ ይቻላልና፡፡ ስለዚህ በየውሃት ወደ ተሳዳቢው ኺድና ገሥጸው፡፡
ሰዎች እኛን ሲጎዱን ወደ እነርሱ የምንኼደው ግን እኛ እንደ ተጎዳን ለመናገር እንዳልኾነ በደንብ አስተውል፡፡ የምንኼደው ተጎጂዎቹ እነርሱ ራሳቸው ስለ ኾኑና ስለ እነርሱ መዳን ስንል ነው፡፡ ስለዚህ አንተም ወደ ተሳደበው ሰው ስትኼድ ልጅህ በመሰደቡ ምክንያት ወይም አንተ ራስህ እንደ ተሰደብክ በመቁጠር አይኹን፡፡ ተሳዳቢው ሰው አንተን ንቆህ አጥቅቶህ ሊኾን ይችላል፡፡ ነገር ግን ልጄ ተሰደበ ወይም እኔ ተናቅሁ ተጠቃሁ ብለህ አትኺድ፡፡ መኼድ ያለብህ ተሳዳቢው ሰው ራሱን እየጎዳ እንደ ኾነ አስበህና ስለ እርሱ መዳን ብለህ ነው፡፡ ስለዚህ እንደ ሰይፍ የሰላውን የቊጣ ሰይፍህን መልሰው፤ ወደ ሰገባውም ክተተው፡፡
(ነገረ መከራ - ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው #ገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ እንደተረጎመው)

✞ አባቶቻችን እንዲህ አሉ
"እሳትና ውኃን ማዋሐድ እንደ ማይቻል በሰው ኃጥያት መፍረድም በራስ ኃጥያት ከመፀፀት ጋር አብሮ አይሄድም" [ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው]
"የማያማትብ እጅ ቀኙም ግራውም አንድ ነው" [አባ ፓስዮስ ዘደብረ አቶስ]
"እግዚአብሔር ለኃጥያተኛ ሰው ያለው ፍቅር ፃድቅ ሰው ለእግዚአብሔር ካለው ፍቅር ይበልጣል" [አባ አርሳኒ]
"ዕለትን የሰጠህ እርሱ ለዕለት የሚበቃህንም ይሰጥሀል" [ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ]
"ለኃጥያተኛ ክንፍህን ዘርጋለት። ኃጥያቱን ልትሸከምለት ባትችል እንኳን ሸፍንለት" [ቅዱስ ይስሐቅ ሶርያዊ]
"ይቅር ካላልክ ገነትም ይቅርብህ" [አባ ኤፍሬም አረጋዊ]
"እጅግ ምርጡ ፀሎት "ጌታ ሆይ አንተ ሁሉን ታውቃለህ የፈቀድከውን አድርግልኝ" ማለት ነው"[ባህታዊ ቴዎፋን]
"እንግዲህ እንደ እግዚአብሔር ምርጦች ቅዱሳን ሆናችሁ የተወደዳችሁም ሆናችሁ÷ ምሕረትን÷ ርኅራሔን÷ ቸርነትን÷ ትሕትናን÷ የዋሕነትን÷ ትዕግሥትን ልበሱ"። [ቆላስይስ፫÷፲፪]

MK TV || ሕግና ዕቅበት እምነት || ሁሉን ሃይማኖት አንድ ነው ማለት ራሱ ሃይማኖት ነው።
Mahibere Kidusan
ሁሉን ሃይማኖት አንድ ነው ማለት ራሱ ሃይማኖት ነው
በዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
በዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
የቀደሙት ሰዎች በሰናዖር ከምድር እስከ ሰማይ፣ እስከ አምላክ ማደሪያ የሚደርስ ግንብ ሊሠሩና ስማቸውን ሊያስጠሩ ተነሡ። ነገር ግን በትዕቢታቸው ጠፉ። እነዚህ የባቢሎን ሰዎች ምንኛ ችኩሎች ሆኑ?! ጥቂት ዘመን ቢታገሱ ኖሮ ራሱ አምላክ ከእነርሱ እንደ አንዱ ሰው ሆኖ በግርግም ተኝቶ ያገኙት አልነበር?!
እነዚህ የሰናዖር ሰዎች ትንሽ ቢታገሱ ኖሮ ከምድር ወደ ሰማይ መሻገሪያ የምትሆን በእግዚአብሔር እጅ የታነጸች ታላቋን የብርሃን ድልድይ ድንግል ማርያምን ያገኙዋት ነበር። በዚህችም የብርሃን ድልድይ (መሰላል) እነርሱ ብቻ ሳይሆኑ የሰው ልጆች ሁሉ ስም እንደ ተጠራ አይተው ደስ ይሰኙ ነበር።
====
አቤቱ ጾም፣ ጸሎት፣ መንፈሳዊ ትሩፋቶቻችን የአንተ ረድኤት የሌለባቸው በትዕቢት ያቆምናቸው የሰናዖር ግንቦች አይሁኑብን። እንዲህም ከሆኑ፣ በሥራዬ እያለ ልባችን እንዳይኮራ፣ ዓይናችንም ወደታች እያየ ወዳጆቹን እንዳይንቅ ወደ አንተ የማያደርሱንን እነዚህን የሐሰት ግንቦች አፍርስልን። በእነርሱም ፈንታ በትሕትና እና በፍቅር ያጌጡ ውብ ግንቦችን እናንጽ ዘንድ ረድኤትህን ላክልን።
እንኳን አደረሳችሁ!
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://www.tg-me.com/Dnabel
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg

|| በፊቴ አልቅሰሃልና ሰምቼሃለው || ለነፍስ የሆነ ትምህርት ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ መደመጥ ያለበት…
ቤተ-ጊዮርጊስ- Bete Georgis
በፊቴ አልቅሰሃልና ሰምቼሃለው
ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
🛑🛑የምስራች እንኳን ደስ አላችሁ የተዋህዶ ልጆች አክሊል ሚዲያ ተተኪ ዘማርያን የምናፈራበት መዝሙራት ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች ወቅታዊ የቤተክርስቲያን መረጃዎች የተለያየ መንፈሳዊ አገልግሎቶች የሚተላለፍበት መንፈሳዊ ሚዲያ ተከፈተ አሁኑኑ ሰብስክራይብ ያድርጉ ለሌሎችም ሼር ያድርጉ ለነፍስዎ ብዙ ነገር ያተርፋሉ@aklil media
https://youtu.be/-S_ZG86A9Bc?si=0HlMPv5UnuqJ9Vv4

YouTube
🛑New mezmur የቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ ዝማሬ በዘማሪት ቃልኪዳን///ውዳሴ ማርያም እጮሀለሁ@AklilMedia
#orthodox #ተዋህዶ #መዝሙር #viral #ውዳሴ ማርያም #YouTube #ኢትዮጵያ
አክሊል ሚዲያ መዝሙራት ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች :ብሂለ አበው:ወቅታዊ የቤተክርስቲያን መረጃዎች ተተኪ ዘማርያን ዝማሬ የሚያቀርቡበት የተለያዩ መንፈሳዊ አገልግሎቶች የሚተላለፍበት መንፈሳዊ ሚዲያ
ቻናሉን ሰብስክራይብ በማድረግ ያበረታቱን

#ጥር_10
#ጾመ_ገሃድ
ጥር አስር በዚህች ዕለት ምንም ምን መብልን ሰይቀምሱ ምእመናን ሁሉ እስከ ምሽት ይጾሙ ዘንድ ከእኛ አስቀድመው የነበሩ ታላላቅ ሊቃውንት የቤተ ክርስቲያን መምህራን ሥርዓትን ሠሩ በምሽትም ቢሆን በታላቁ ጾም ከሚበላው በቀር ጥሉላትን እንዳይቀምሱ። በዚች ዕለት ምእመናን እስከ ምሽት እንደመጾሙን ያዘዙበት ምክንያቱ ይህ ነው የልደትና የጥምቀት በዓል በዓል በረቡዕ ወይም በዓርብ ቀን ቢሆን በበዓለ ኃምሳ የሚበላውን የጥሉላት መብል በጥዋት በመብላት ምእመናን ሁሉ በዓሉን እንዲአከብሩ የከበሩ አባቶቻችን ሐዋርያት አዝዘዋል እሊህ ሁለቱ የእግዚአብሔር ታላላቅ በዓላቶቹ ናቸውና።
እኛ በዚህ በኅላፊው ዓለም ተድላ ደስታ ደስ የሚለን ለሌሎች እንዳይመስላቸው እንደ አይሁድና እንደ አረማውያን በዓል በመብልና በመጠጥ ብቻ እንዳናደርግ ስለዚህ ከልደትና ከጥምቀት በዓል በዋዜማ ያሉትን ሁለቱን ዕለታት እንድንጾም አዘዙን የልደትና የጥምቀት በዓል በረቡዕና በዓርብ ላይ በሚሆን ጊዜ በረቡዕና በዓርብ ፈንታ እንድንጾማቸው ይገባልና በዚህም ሁለት ሥራ ይፈጸምልናል የጾም ሥራና የበዓል ማክበር ሥራ ነው። እንዲሁም በግብፃውያን አብያተ ክርስቲያን የተሠራ ነው።
በይረሙን በእሑድ ወይም በአይሁድ ሰንበት ቀን ቢሆን ይህም ጌታ የተገለጸበት ጥር ዐሥራ ቀን ነው በዋዜማው ዐርብ እስከ ምሽት ይጹሙ አስቀድመን እንደተናገርን ጥሉላት አይብሉ የልደትና የጥምቀት በዓልም ሰኞ ቀን ቢሆን በሰንበት ቀን ይጾም ዘንድ አይቻልም ነገር ግን ጥሉላትን ከመብላት ይጠበቁ።
በጥምቀትም ዕለት ከእኵለ ሌሊት በፊት ተነሥተው በውኃው ላይ ይጸልዩና ይጠመቁ ሕፃናትም በሚጠመቁ ጊዜ በውኃ እንዳይገድፉ ካህናቱም ከመንጋቱ በፊት ቀድሰው ቊርባኑን ያሳርጉ እጅግም ማልደው በጥዋት ከቤተ ክርስቲያን ይውጡ በከበረ ሥርዓታቸው ጌቶቻችን ሐዋርያት እንዳዘዙ።
የመለካውያን ወገኖች ግን የልደትና የጥምቀት ዋዜማ በቅዳሜ ቀን ወይም በእሑድ ቀን ቢሆን በሦስት ሰዓት ይቀድሳሉ ከወደዱም የተባረከ ኅብስት ተመግበው ውኃ ይጠጣሉ ከዚህም በኋላ ካህናቱ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሁነው በየሰዓቱ በመጸለይ ለበዓሉ የሚገባውን የነቢያትን ትንቢቶች ያነባሉ በዚያች ቀን በምሽት ይኸውም ጥር ዐሥር ነው በውኃው ላይ ይጸልያሉ ይህም አባቶቻችን ሐዋርያት እንዳዘዙት አልሆነም። እርሳቸው የኤጲፋንያን በዓል እንዲአክብሩ አዘዋል ይኸውም መድኃኒታችን የተገለጠበት ካኑን በሚባል በሮም ሁለተኛ ወር በሰባት ይህም ጥር ዐሥራ አንድ ቀን ነው።
መለካውያን ግን የከበሩ አባቶች የቤተ ክርስቲያን መምህራን ያዘዙትን ይተላለፋሉ በልደትና በጥምቀት በዓል ዓርብም ረቡዕም ቢሆን አስቀድመው በርሱ ፈንታ ሳይጾሙ በጥዋት ተነሥተው ይበላሉና። እኛንም ከበደላችን ያነጻን ዘንድ በዮርዳኖስም ወንዝ እንደ ተገለጸ የጌትነቱን ክብር በልቡናችን ይገልጥልን ዘንድ የክብር ባለቤት የሆነ ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን እንለምነው።
ጌትነት ክብር ስግደት ለእርሱ ይገባልና ከቸር አባቱ ጋር ይቅር ባይ ከሆነ መንፈስ ቅዱስም ጋር ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥር)