Telegram Web Link
ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን
ዝማሬ ዳዊት On Telegram
ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን

ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን 
ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን
ውስተ አፍላገ ባቢሎን
ህየ ነበርነ ወበከይነ
እንዚራቲነ ሰቀልነ ውስተ ኲሓቲሃ

ባሰብናት ጊዜ ጽዮንን
ባሰብናት ጊዜ ጽዮንን
በባቢሎን ወንዞች አጠገብ
ተቀምጠን አለቀስን
መሰንቆአችንን ሰቀልን በዛፎቿ ላይ
አዝ
ፅኑ መከራን ተቀበልን ተጨነቅን በፈተና
የደዌ ሞት በላያችን እንደዝናብ ወርዷልና
አሕዛብም ዘበቱብን እንዲህ ብለው በየተራ
ዘምሩለት ለአምላካችሁ ቢያድናችሁ ከመከራ

እግዚአብሔር ጽዮንን በመንግስቱ መርጧታል እና
ማደሪያው ትሆነው ዘንድ ወዷታል እና
ጽዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
ጽዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
አንቺን ብንረሳ ቀኛችን ትርሳን
አዝ
የማረኩን በጦራቸው በኃይላቸው የተመኩ
በጽዮን ደጅ ያለፍርሃት የጽዮንን ክብሯን ነኩ
ይህን ያየ ከላይ ሆኖ በደመና ተሸፍኖ
ባቢሎንን አሻገረ የማረኩንን በትኖ

እግዚአብሔር ጽዮንን በመንግስቱ መርጧታል እና
ማደሪያው ትሆነው ዘንድ ወዷታል እና
ጽዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
ጽዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
አንቺን ብንረሳ ቀኛችን ትርሳን
አዝ
ስጋችንን ሊገንዘን የሞት ጥላ ቢያጠላም
እናልፋለን ሁሉን ባንቺ
የአምላክ እናት ድንግል ማርያም
ቅድስት ሆይ ከባረክሽን
እንድናለን ከደዌያችን
ለስጋና ለነብሳችን መድኃኒት ነሽ እናታችን

እግዚአብሔር ጽዮንን በመንግስቱ መርጧታልና
ማደሪያው ትሆነው ዘንድ ወዷታልና
ጽዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
ጽዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
አንቺን ብንረሳ ቀኛችን ትርሳን
"ኢየሱስ ክርስቶስ መካከለኛ ስለሆነ ሌላ አማላጅ አያስፈልግም!"
***
በእግዚአብሔር እና በሰው መካከል ያለ (እግዚአብሔርም ሰውም የሆነ) አንድ መካከለኛ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ታዲያ የቅዱሳን ምልጃ ለምን ያስፈልጋል? ፍጹም የሆነ አንድ አስታራቂ ካለ ሌሎች ተጨማሪዎች ለምን ያስፈልጋሉ? የሚል ጥያቄ ይዘወተራል። ጉዳዩን ለየት የሚደርገው ደግሞ አንድ ፍጹም የሆነ አስታራቂ እንዳለ የሚያምኑ ጥንታውያን ክርስቲያኖች በቅዱሳን ምልጃም ሳይጣላባቸው የሚያምኑ መሆኑ ነው፤ እስከ 16ኛው መ/ክ/ዘመን የተሐድሶ ዘመን ድረስ ከክርስቲያን ሊቃውንት መካከል የክርስቶስን መካከለኝነት (አስታራቂነት) ከቅዱሳን ምልጃ ጋር አጋጭቶ የተቃወመ አላየንምና።
ወደ ጉዳዩ ስንመለስ የቅዱሳን ምልጃ ከክርስቶስ መካከለኝነት ጋር የሚጋጭ ሳይሆን የዚያ አካል ነው። ቅዱሳን የክርስቶስ አካል ብልቶች ናቸውና። የቅዱሳን ምልጃ ኃይሉን የሚያገኘው በክርስቶስ የማዳን ሥራ ነው፤ በክርስቶስ ካልሆነ በቀር ለእግዚአብሔር የሚቀርብ ስሙር ጸሎት የለምና። እግዚአብሔር ሰዎች ሁሉ እንዲድኑ ይፈልጋል፤ ቅዱሳንም የክርስቶስ ልብ ስላላቸው ይህን ይሻሉ። መሻታቸውም በጸሎት በተግባር ይገልጣሉ። ምልጃ የዚህ መሻታቸው ተግባራዊ መገለጫ ነው። በክርስቶስ ሕያው ሆነው የሚኖሩ ቅዱሳን ይህን ባያደርጉ ነበር የሚገርመው! ግን በምልጃ ብቻ ዓለም ሊድን አይችልም። ስለዚህ ያለ ክርስቶስ መካከለኝነት (አስታራቂነት) ጸሎታቸው ኃይል አይኖረውም ነበር። እነርሱም የሚማልዱት የክርስቶስን ጸጋ ተማምነው ነው፤ ካልሆነማ ቅዱሳን አይባሉም።
በመሆኑም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መካከለኛ መሆን ለቅዱሳን ምልጃ አስቻይ እና ኃይል እንጂ ተቃራኒ አይደለም። ቅዱሳን ራሱ የሚማልዱት የክርስቶስ አካል ስለሆኑ እና የእርሱ የፍቅር ልብ ስላላቸው ነውና። ይህንም ውብ እና ጥልቅ ሕይወት ቅዱስ ጳውሎስ ጠቅልሎ እንዲህ ተናግሮታል፦ "እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው። አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።" (1ኛ ጢሞ. 2፥1-4) ወዳጄ፥ ጳውሎስ በእግዚአብሔር እና በሰው መካከል ያለው መካከለኛው ክርስቶስ እንደሆነ በተናገረበት በዚህ መልእክቱ ስለ ሰዎች ሁሉ ጸሎትና ምልጃ እንዲደረግ ማዘዙን አስተዋልህን? ለሐዋርያት ያልተቃረነው ለእኛ ለምን ይቃረናል? ይህች ኅሊና የምታስቸግረን ከሆነ ግን ምናልባት ሁሉ ይድኑ ዘንድ የሚሻ የክርስቶስ ልብ ጎድሎን እንዳይሆን ለራሳችን እንሥጋ።
Dn Bereket Azmeraw
ኢየሱስን አንዲት ነገር ለመንሁት እርሷንም እሻለሁ..

በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በአካሉ ማለትም በቤተ ክርስቲያን እኖር ዘንድ.. እርሱን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ.. ራስ የሆነውን እርሱንም እመለከት ዘንድ


እግዚአብሔርን የማፍቀርና የመፍራት ውሎ ይሁንላችሁ
1ኛ ጢሞ 2፡5)
‹‹አንድ እግዚአብሔር አለና በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው (1ኛ ጢሞ. 2፡5)›› የሚለውን ቃል ይዘው ‹‹ኢየሱስ ክርስቶስ አማላጃችን ነው›› የሚሉ ወገኖች አሉ፡፡ ሐዋርያው የተናገረው ቃል ኦርቶዶክሳዊው አስተምህሮ ግን እንደሚከተለው ነው፡፡
ቅዱስ ጳውሎስ በዚህ አንቀጽ ላይ መግለጽ የፈለገው አንድ እግዚአብሔር አለና ማለቱ በስልጣን፣ በአገዛዝ፣ በፈቃድ አንድ የሆነ እግዚአብሔር (የዓለም ጌታ) አለ ማለቱ ነው፡፡ በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው ማለቱ በአንድነት እግዚአብሔር ተብለው ከሚጠሩት ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ ፍፁም አምላክ ፍፁም ሰው(ማዕከላዊ) የሆነው ማለቱ ነው፡፡ አንድ አለ ብሎ መካከለኛው አንድ ብቻ መሆኑን መግለፁ በተለየ አካሉ ፍፁም አምላክ ፍፁም ሰው የሆነው ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ በመሆኑ ነው፡፡
ምክንያቱም እግዚአብሔር አብ መካከለኛ አይባልም፡፡ ለምን ቢባል ፍፁም አምላክ ብቻ ነው እንጂ ፍፁም ሰው አልሆነም፡፡ ወደፊትም አይሆንምና፡፡ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስም መካከለኛ አይባልም ምክንያቱም ፍፁም አምላክ ብቻ ነው እንጂ ፍፁም ሰው አልሆነም፡፡ ወደፊትም አይሆንምና፡፡ እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን መካከለኛ ይባላል ምክንያቱም ፍፁም አምላክ ሆኖ ሳለ አምላክነቱን ሳይለቅ ፍፁም ሰው ሆኗልና፡፡ አምላክነትን ሰውነትንም የያዘ ከሁለት አካል አንድ አካል ከሁለት ባህሪ አንድ ባህሪ በተዋህዶ የከበረ ነው፡፡ ስለዚህ በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ያለው መካከለኛው ሲል ፍፁም አምላክ ፍፁም ሰው የሆነው ማለቱ ነው፡፡
ቅዱስ ጳውሎስ ኢየሱስ ክርስቶስን መካከለኛ ነው ካለ በኋላ ወረድ ብሎ ከቁጥር 6 – 7 እንዲህ ይላል፡፡ ራሱን ለሁሉ ቤዛ ሰጠ ይህም በገዛ ዘመኑ ምስክርነቱ ነበረ በማለት ጌታ በሥጋ ማርያም ተገልፆ በምድር ይመላለስበት በነበረበት በገዛ ዘመኑ ማለትም በሥጋው ወራት ስለሁላችን ራሱን ቤዛ አድርጎ እንደሰጠ ሐዋርያው ተናገረ፡፡በሌላም ቦታ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መካከለኛነት ሲገልጽ እንዲህ አለ፡፡ ዕብ. 9፡15 የፊተኛው ኪዳን ሲፀና ሕግን የተላለፉትን የሚቤዥ ሞት ስለሆነ የተጠሩት የዘላለምን ርስት የተስፋ ቃል እንዲቀበሉ እርሱ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ነው፡፡ የተጠሩት ሰዎች የዘላለምን ርስት የተስፋ ቃል እንዲቀበሉ ማለትም መንግስተ ሰማያት ትወርሳላችሁ የዘላለምን ሕይወት ታገኛላችሁ የሚለውን የተስፋ ቃል እንዲይዙ እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ የሐዲስ ኪዳን መካከለኛ ነው፡፡ ማለትም የዘላለም የተስፋን ቃል(አዲሱን ኪዳን) የተቀበልነው በፍጡር ሳይሆን በፈጣሪ መካከለኛነት ወይም በኢየሱስ ክርስቶስ ፍፁም አምላክ ፍፁም ሰው ሆኖ ነው ማለቱ ነው፡፡ በዚህ መሰረት ፍፁም አምላክ ፍፁም ሰው በመሆን አዲሱን ኪዳን ለሰው ልጆች የሰጠ በመሆኑ ማዕከላዊ (መካከለኛ) ተብሏል፡፡
ጸጋ ብቻ ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
ማኅበረ ጽዮን
ጸጋ ብቻ
በ ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
እጅህ ላይ ባለው ነገር ከታመንህ እግዚአብሔር አምላክ በእጁ ውስጥ ያለውን ነገር ይሰጥሃል።

በውስጥህ ያለውን አቅም መጠቅም ከቻልህ እግዚአብሔር የአንተ ያልሆነ ተጨማሪ አቅም ይሰጥሃል።

ከእግረኞች ጋር ሳትደክም እኩል መራመድና መቅደም ከቻልህ እግዚአብሔር ፈረስን ለውድድር ይሰጥሃል። ኤር. 12፥5

የሚታዩ ኃጢአቶችን ለመዋጋት ታምነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር የተሸሸጉና የማይታዩ ኃጢአቶችን ድል እንድትነሣ ይሾምሃል።

በሕፃንነትህ በልጅነትህ ለእግዚአብሔር የታመንህ ሆነህ ከተገኘህ እርሱ በወጣትነትህ በምታደርገው ውጊያ ውስጥ ታማኝነትን ያድልሃል።

ልያን ለመቀበል ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር ራሔልን ሚስት አድርገህ ታገባት ዘንድ ይሰጥሃል። ዘፍ. 29፥27

በሲና ምድረ በዳ ለመቀመጥ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር አምላክ የተስፋይቱን ምድር ከንዓንን ያወርስሃል።

በዚህ በተወሰነና አጭር ሕይወት ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር መጨረሻ የሌለውን ዘላለማዊ ሕይወት ያድልሃል።

ትልቁ ቁም ነገር በእጅህ ውስጥ የገባው ነገር ትንሽም ይሁን ጥቂት በእርሱ መታመን መቻልህ ነው። ስለሆነም ባለህ አንድ መክሊት ታምነህ ስትገኝ እግዚአብሔር አምስት መክሊቶችን በአደራ ይሰጥሃል።

አንተ በሚታዩት ነገሮች ላይ ታማኝ ሆነህ ስትገኝ እርሱ በማይታዩት ነገሮች ላይ ይሾምሃል።በመሆኑም ዓይን ያላየችውን ጆሮ ያልሰማውን በሰው ልብ ያልታሰበውን መንግሥቱን ያወርስሃል። 1ኛ ቆሮ 2፥9

(#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ - #መንፈሳዊው_መንገድ መጽሐፍ #አያሌው_ዘኢየሱስ እንደተረጎመው።)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔴 አዲስ ዝማሬ " አኑርልኝ ለአፌ ጠባቂ " ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ @-mahtot
"ክርስትና:ሰው:የመሆን:ሙሉ:በሙሉ አዲስ:መንገድ:ነው"።ቅዱሳን ማክስሞስ ተናዛዡ
ሃሌ ሉያ እመቦ ብእሲ እምእመናን ዘቦአ ቤተክርስቲያን በጊዜ ቅዳሴ ወኢሰምዐ መጻሕፍተ ቅዱሳተ ወኢተዐገሠ እስከ ይፌጽሙ ጸሎተ ቅዳሴ(ወ) ወኢተመጠወ እምቁርባን ይሰደድ እምቤተክርስቲያን እስመ አማሰነ ሕገ እግዚአብሔር ወአስተሐቀረ ቁመተ ቅድመ ንጉሥ ሰማያዊ ንጉሠ ሥጋ ወመንፈስ ከመዝ መሐሩነ ሐዋርያት በአብጥሊሶሙ።

ትርጉም
ሃሌ ሉያ በቅዳሴ ጊዜ ከምእመናን ወገን ወደ ቤተክርስቲያን የገባ ሰው ቢኖር ቅዱሳት መጻሕፍትን ሰምቶ የቅዳሴውን ጸሎት እስኪጨርሱ ባይታገሥ ከቁርባንም ባይቀበል ከቤተክርስቲያን ይለይ። የእግዚአብሔርን ሕግ አፍርሷልና የነፍስና የሥጋ ንጉሥ በሚሆን በሰማያዊ ንጉሥ ፊት መቆምንም አቃሏልና። ሐዋርያት በሲኖዶሳቸው እንዲህ አስተማሩን።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የመጽሀፍ ቅዱስ ትርጏሜ ያስፈልጋል ወይስ አያስፈልግም ?

በዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
††† እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል: ቅዱስ ዮሐንስ ዘቡርልስ እና አቡነ ስነ ኢየሱስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት †††

††† በቤተ ክርስቲያን ክቡር ከሆኑ ሊቃነ መላእክት አንዱ የሆነው ቅዱስ ገብርኤል ብዙ የክብር ስሞች አሉት:: በተለይ ግን:-
*ሊቀ አርባብ:
*መጋቤ ሐዲስ:
*መልአከ ሰላም:
*ብሥራታዊ:
*ዖፍ አርያማዊ:
*ፍሡሐ ገጽ:
*ቤዛዊ መልአክ:
*ዘአልቦ ሙስና . . . እየተባለ ይጠራል::

በብሉይ ኪዳንም ሆነ በሐዲስ ኪዳን ስሙ በብዛት ተጠቅሷል:: ስለ ረዳትነቱና አማላጅነቱም ቤተ ክርስቲያን በስሙ ታቦት ቀርጻ: መቅደስ አንጻ በሥርዓት ክብሩን ትገልጻለች::

ከእነዚህም አንዱ ሠለስቱ ደቂቅን እንዳዳነ የሚታሰብበት አንዱ በዓሉ ዛሬ ነው::
"ለዝንቱ ዜናዊ መልአከ ኃይል::
በዛቲ ዕለት ከመ ይትገበር በዓል::
መምሕራን አዘዙ ወሠርዑ በቃል::" እንዲል:: (አርኬ)

ንጉሡ ከምርኮ ወጣቶች ለቤተ መንግስት ሲመርጥ ሦስቱ ቅዱሳንና ዳንኤል ተመርጠው የምቾት ሕይወት ተዘጋጅቶላቸው ነበር:: ነገር ግን በምግብና በአምልኮ ከአሕዛብ ጋር መተባበርን አልፈለጉምና ምርጫቸው ጾምና ጸሎት ከቆሎ ጋር ሆነ::

ምንም እንኳ በቤተ መንግስት ውስጥ ቢኖሩ: ምንም የነገሥታት ልጆች ቢሆኑ ለእነርሱ ከእግዚአብሔር ፍቅር የተሻለ አልነበረምና በጥሬ ቆሎ ተወስነው ኖሩ::

አምላካቸው ከሃሊ ነውና በውበትም ሆነ በጥበብ በባቢሎን ምድር ከነርሱ የሚደርስ አልተገኘም:: ንጉሡም በባቢሎንና በአውራጃዋ ላይ ሾማቸው:: ስማቸውንም በአማልክቱ ስም ሲድራቅ: ሚሳቅና አብደናጐ አላቸው::

ከነገር ሁሉ በኋላ አሕዛብ ቀንተውባቸዋልና የክፋት አዋጅን አሳወጁ:: ናቡከደነጾር 60 ክንድ ቁመት ያለውን የወርቅ ምስል አቁሞ ስገዱ ቢላቸው አይሆንም በማለታቸው ተቃጥለው እንዲሞቱ እሳት ተፈረደባቸው:: ነበልባሉ ከጉድጓዱ ወደ ላይ 49 ክንድ ቢነድም ቅንጣት ያህል ፍርሃት አልጎበኛቸውም::

ወደ እሳቱም ሲጥሏቸው መልዐከ አድኅኖ ቅዱስ ገብርኤል ደርሶ አዳናቸው:: ከሆነው ነገር የተነሳ አሕዛብ አፈሩ:: ናቡከደነጾር ግን ከዙፋኑ ተነስቶ የቅዱሳኑን አምላክ እግዚአብሔርን ባረከ::

ቅዱሳኑን ያዳነ ቅዱስ መልአክ እኛንም ያድነን ዘንድ እንደ አባቶቻችን
"አድኅነኒ ዘአድኃንኮሙ በአክናፊከ ምንትው::
አመ ውስተ እሳት ተወድዩ ሠለስቱ እደው::" እያልን እንለምነው:: (መልክዐ ገብርኤል)

††† ቅዱስ ዮሐንስ ዘቡርልስ †††

††† ይህ ቅዱስ አባት ስም አጠራሩ የከበረ ነው:: ሊቅም: ጻድቅም: ጳጳስም: ገዳማዊም ነው:: ከሁሉም በላይ ግን ዛሬም ድረስ ቤተ ክርስቲያን በተድላ ለምትጠቀምባቸው መጻሕፍት (ስንክሳር: ግጻዌ እና ሃይማኖተ አበው) መሠረትን የጣለ ቅዱስ ሰው ነው::

ቅዱስ ዮሐንስ በትውልዱ ግብጻዊ ሲሆን ጊዜውም 5ኛው መቶ ክ/ዘ ነው:: ወላጆቹ ክርስቲያኖች: በዚያውም ላይ ሞልቶ የተረፋቸው ባለ ጠጐች ነበሩ:: እንደ ሕጉ ወጣት እስኪሆንና ራሱን እስኪችል ድረስ አሳደጉት::

ከዚያ ግን ድንገት አባቱና እናቱ ተከታትለው ዐረፉ:: ከቁጥር የበዛ ሃብትን የግሉ ያደረገው ቅዱስ ዮሐንስ ምን እንደሚያደርግበት ጨነቀው:: አንድ ትልቅ ነገር ግን ከማይሆን ጐዳና ጠበቀው::

ወላጆቹ ሁሌም መዝገብን በሰማያት ያገኙ ዘንድ ለነዳያን ይራሩ ነበርና ይህንኑ ለመቀጠል ወሰነ:: መልካም ፍሬ ከመልካም ዛፍ ነውና (ማቴ. 7:16) ወላጅ ለልጁ ማውረስ ያለበት ምድራዊ ሃብትን ሳይሆን በጐ ሕሊናን ነው:: ሳይሠሩ ያገኙት ሃብት ብዙዎችን አጥፍቷቸዋል::

ለዛም ይመስላል ዛሬ አንዳንዶቻችን በቤተሰቦቻችን ሃብት ከእኛ አልፈን ትውልዱን እየገደልንበት ያለው:: ለዚህ ደግሞ እግዚአብሔር ንስሃ ካልገባን ይመጣብናል:: መቅረዛችን (ሕይወታችንም) ከእኛ ላይ ይወስዳል::

ፍርድ የሚሆነው በክፉው ትውልድ ላይ ብቻ አይደለም:: ይህንን ትውልድ በፈጠርነውና መልካሙን መንገድ ባልመራነው በሁላችንም ላይ እንጂ:: (ራዕ. 2:5)

ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ቅዱስ ዮሐንስ በወላጆቹ ሃብት የእንግዶች ማረፊያ የሚሆኑ ቤቶችን አንጾ ነዳያንን ይንከባከብ ገባ:: ሙሉውን ቀን ለነዳያን ሲራራ ይውላል:: አመሻሽ ላይ እንግዶችን ተቀብሎ: አብልቶ ያሳርፋል::

ከዚያም ፈጣሪውን ያመሰግናል:: በእንዲህ ያለ ሕይወት ዘመናትን ካሳለፈ በኋላ አንድ እንግዳ መነኮስ ወደ ቤቱ መጣ:: አስተናግዶት ሲጨዋወቱ አደሩ:: ሌሊት ላይ ግን ስለ ምንኩስና ሕይወትና ስለ ክብሩ ነግሮት ነበርና ልቡ ተመሰጠ::

መነኮሱን ከሸኘው በኋላም ይመንን ዘንድ ቆረጠ:: ነዳያንን ሰብስቦ ሃብቱን አካፈላቸው:: ከዚያም ወደ ገዳመ አስቄጥስ ሒዶ የታላቁ አባ ዳንኤል ደቀ መዝሙር ሆነ:: በትሕትና ለአባቶች እየታዘዘ ከቆየ በኋላ በጭንቅ ደዌ ተያዘ:: ሰይጣን በቅንዓት ገርፎት ነበርና::

እርሱ ግን በደዌው ምክንያት ለዓመታት መሬት ላይ ወድቆ ቢቆይም ፈጣሪውን ፈጽሞ ያመሰግን ነበር:: እግዚአብሔር ደግሞ በፈውስና በኃይል አስነሳው::

በጊዜው የቡርልስ ጳጳስ ዐርፎ ነበርና አባት ፍለጋ ወደ አስቄጥስ ገዳም መጥተው ነበር:: መንፈስ ቅዱስ መርጦታልና አበው ቅዱስ ዮሐንስ ጳጳስ ይሆን ዘንድ አስገደዱት:: እርሱም የፈጣሪ ፈቃድ መሆኑን ስላወቀ ሔደ::

በዚያም (በሃገረ ቡርልስ) ታላቁን ገድል ተጋደለ:: ወደ ከተማዋ ሲገባ ብዙ ነገሮች ከሚገባው ሥርዓት የወጡ ነበሩ:: ብዙ ሰው የእግዚአብሔርን ድምጽ ከመስማት ይልቅ ባላስፈላጊ ነገሮች ላይ ተጠምዶ ነበርና መንጋውን ያድን ዘንድ ተጋ::

ሳይሆኑ "ባሕታዊ": "አጥማቂ" ነን እያሉ ሕዝቡን የሚያሳስቱ ተኩላዎችንም አስወገደ:: ለሕዝቡ አጉል ሕልም: ሟርትን የሚያስተምሩትን ገሠጸ:: አንመለስም ያሉ መናፍቃንን እሳት ከሰማይ ወርዳ በላቻቸው::

ቅዱስ ዮሐንስ ከቅድስናው ብዛት ዘወትር ሲቀድስ መድኃኒታችንንና አእላፍ መላእክትን ያይ ነበር:: ከከዊነ እሳት ማዕረግ በመድረሱም አካሉ በመፈተት ሰዓት እንደ እሳት ይነድ ነበር:: እንባውም እንደ ውኃ ይፈስ ነበር::

ቅዱስ ዮሐንስ ከዚህ ጐን ዛሬም ድረስ የሚታወቅበትን ታላቅ ሥራም ሠርቷል:: መንፈስ ቅዱስ አነሳስቷቸው ቅዱሱና የሃገረ አትሪብ ጳጳስ የነበረው ሊቁ አባ ሚካኤል መጽሐፈ ስንክሳርን : መጽሐፈ ግጻዌንና ሃይማኖተ አበውን ለመጀመሪያ ጊዜ አዘጋጅተዋል::

"ስንክሳር" የቅዱሳንና የፈጣሪን ነገር በየዕለቱ የሚዘግብ መጽሐፍ ሲሆን "ግጻዌ" የየዕለቱን በዓላት ከምስባክና ምንባባት ጋር አስማምቶ የያዘ መጽሐፍ ነው:: "ሃይማኖተ አበው" ደግሞ የዶግማ መጽሐፍ ሆኖ ከሐዋርያት እስከ ሊቃውንት ድረስ የጻፉትን የያዘ ነው:: ሦስቱን የሚያመሳስላቸው "ስብስብ / እስትጉቡዕ / Collection" መሆናቸው ነው::

ቅዱሱ ዮሐንስ በሃገረ ቡርልስ በከፍተኛ ድካም ይህንን ፈጽሞ በዚህች ቀን ዐርፏል::

††† አቡነ ስነ ኢየሱስ ጻድቅ †††

††† ጻድቁ በመካከለኛው (የብርሃን) ዘመን የነበሩ ኢትዮጵያዊ::
*ከምድረ ሽዋ ወደ ታች አርማጭሆ የሔዱ መናኝ:
*ጭው ባለ በርሃ ለቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ ገዳምን ያነጹ አባት:
*ብዙ አርድእትን ያፈሩ መናኝ:
*ብዙ ተአምራትን የሠሩና ወንጌልን ያስተማሩ መነኮስ ናቸው::
በደመናም ይጫኑ ነበር:: ገዳማቸውም (ታች አርማጭሆ: ከሳንጃ ከተማ የ3 ሰዓት መንገድ ይወስዳል) ድንቅና ባለ ብዙ ቃል ኪዳን ነው:: መልአከ ሞት መስከረም 1 ቀን ቢመጣ "የቅዱስ ገብርኤልን በዓል ሳላከብርአይሆንም" ብለው ለ3 ወራት በበራቸው አቁመውታል:: ታኅሣሥ 19 ቀንም ዐርፈዋል::

††† አምላከ ቅዱሳን በመልአኩ ረድኤት ጠብቆ ለጻድቃኑ በረከት ያብቃን::

††† ታኅሣሥ 19 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ዮሐንስ ዘቡርልስ
3.አቡነ ስነ ኢየሱስ ጻድቅ

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት
2.አቡነ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ
3.አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም
4.ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ

††† ". . . በአምላኬም በእግዚአብሔር ፊት ስለ ተቀደሰው ስለ አምላኬ ተራራ ስለምን: ገናም በጸሎት ስናገር አስቀድሜ በራእይ አይቼው የነበረው ሰው ገብርኤል እነሆ እየበረረ መጣ:: በማታም መሥዋዕት ጊዜ ዳሰሰኝ:: አስተማረኝም . . ." †††
(ዳን. ፱፥፳)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
https://www.tg-me.com/zikirekdusn
2024/11/15 18:33:22
Back to Top
HTML Embed Code: