ጥምቀት | በጥምቀት ዙሪያ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ | ክፍል - 1 | በሊቀ ሊቃውንት ስምዐኮነ መልአክ | Feleg...
https://youtube.com/watch?v=WxDdsIFWb-w&si=teKtyPhZgZn3eX-B

YouTube
ጥምቀት | በጥምቀት ዙሪያ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ | ክፍል - 1 | በሊቀ ሊቃውንት ስምዐኮነ መልአክ | Felege Genet Media | 2021
በጥምቀት ዙሪያ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ክፍል-1| Ethiopian Orthodox Tewahdo Church 2021 | Ethiopian Orthodox Tewahdo Church : Felege Genet Media - ፈለገ ገነት ሚዲያ | በጥምቀት ዙሪያ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ | Ethiopian Orthodox Tewahdo special program 2021 | Felege Genet Media | New EOTC Video…
"ብዙ መሠዊያዎች" ነገር ግን አንድ መሠዊያ
***
ብዙ አብያተ ክርስቲያናት (ሕንጻዎች እና የአጥቢያ ምዕመናን) ቢኖሩም የቤተ ክርስቲያን የማኅበሯ ፍጻሜ ግን አንዲት ናት። በየ አብያተ ክርስቲያናቱ 'ብዙ መሠዊዎች' ቢኖሩም ክርስቶስ ራሱን የሠዋበት ሰማያዊ መሠዊያ አንድ ነው። ብዙ ሲመስሉን አንድ ናቸው፤ በሁሉም ላይ የሚቀርበው አንዱ ክርስቶስ ነውና። ብዙ ቦታዎች ላይ በተለያዩ ጊዜያት ቅዱስ ቁርባን ይፈተታል፤ ነገር ግን በሁሉም ያለመከፋፈል የሚፈተተው ያው አንዱ የክርስቶስ ቅዱስ ሥጋ እና ክቡር ደም ነው። ይህ ራሷ ከሆነ ከክርስቶስ አካሉ ለሆነች ለቤተ ክርስቲያን የተሰጣት ከጊዜ እና ቦታ ከፍ ያለ መንፈሳዊ አንድነት ነው።
ይህን የተረዳ እና ለሰዎች ማስረዳት የቻለ እውነተኛውን የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አንድነት ተረድቷል። የቅዱስ ቁርባን የአንድነት ሥርዓትም የዚህ መሠረት ነው።
***
"በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት፤" የሚል ድንቅ የአብ ድምፅ ለተሰማበት፣ ወልድ በለበሰው ሥጋ ተጠምቆ ውሆችን ለቀደሰበት እና መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ወርዶ በክርስቶስ ላይ ሲኖር ለታየበት የቅድስት ሥላሴ የመገለጥ በዓል (በዓለ አስተርእዮ) እንኳን በሠላም አደረሰን!
(በረከት አዝመራው)

አዋልድ መጻሕፍት የሚባሉ መጻሕፍት የትኞቹ ናቸው? በዘመናችን የሚወጡ አዳዲስ መንፈሳዊ መጻሕፍት ሁሉ…
ማኅበረ ጽዮን
አዋልድ መጽሐፍ የሚባሉት የትኞቹ ናቸው ?
በዘመናችን የሚወጡ አዳዲስ መጽሐፍ አዋልድ ይባላሉን?
አዋልድ ለማለት መለኪያችን ምንድን ነው ?
በዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
በዘመናችን የሚወጡ አዳዲስ መጽሐፍ አዋልድ ይባላሉን?
አዋልድ ለማለት መለኪያችን ምንድን ነው ?
በዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
"የክርስቶስን አካል ልታከብሩት ትወዳላችሁን? መልሳችሁ አዎ ከሆነ ራቁቱን ሆኖ እያያችሁት አትለፉት፣ በየመንገዱ ራቁቱን ሆኖ በብርድ እየተሰቃየ አለና፤ ራቁቱን ሆኖ በብርድ እየተሰቃየ አልፋችሁት መጥታችሁ እዚህ ከቤተ መቅደስ በብርና በወርቅ ላስጊጥህ አትበሉት፡፡ "ይህ ሥጋዬ ነው" ብሎ የተናገረው ክርስቶስ ራሱ "ተርቤ አይታችሁኝ አላበላችሁኝም" ያለው እንዲሁም "ከእነዚህ ከታናናሾች ወንድሞቼ ለአንዱ ያደረጋችት ለእኔ አደረጋችሁት" ያለውም ያው እርሱ ራሱ ነውና፡፡ ወንድምህ በረሃብ እየተሰቃየና እየሞተ ቅዱስ ደሙ የሚቀዳበት ጽዋ በወርቅ ቢለበጥና ቢንቆጠቆጥ ጥቅሙ ምን ላይ ነው? አስቀድመህ የወንድምህን ረሃብ በማጥገብና ጥሙን በማርካት ጀመር፤ ከዚያ በኋላ በተረፈህ ገንዘብ ቤተ መቅደሱንና ንዋያተ ቅድሳትን እንዲህ ማስጌጥ ትችላለህ፡፡"
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
▫ ጌታዬ አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የውስጤን የሚረዳልኝ እንዳንተ ያለ ማንንም አላገኝም፤ ከአንተ ጋር ስሆን ብቻ ደህንነት ስለሚሰማኝ ለአንተ ለአምላኬ ልቤን ከፍቼ ምሥጢሬን አዋይሃለሁ።
▫ ቃልህን የምሰማ ነገር ግን የማላስተውል ደካማ ነኝና፣ ናፍቆቴን ቢገልፅልኝ እንባዬን በፊትህ አፈሰዋለሁ፤ ልቤን ከሚያጸናውና በሃይሉ ከሚደግፈኝ ጋር እንደሆንኩ አውቃለሁና ከአንተ ጋር ብቻ ስሆን ብቸኝነት አይሰማኝም፤ ያለ አንተ ግን ባዶነቴ ያስጨንቀኛል።
▫ ከእኔ ጋር የሆንክ አማኑኤል አምላኬ ሆይ ነፍሴ ከዓለምና በዓለም ካሉት ከቁሳዊ ነገሮች ይልቅ የአንተን ሁሉን ቻይነት ትናፍቃለች፤ ውስጤ የማትወሰን አንተን ተጠምቷል፤ ከአንተም በቀር ይህን የሚረዳኝልኝ ከቶ የለም"
[ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ]

“#ማግባት_ለሚሹ”
የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ምክር
ከምንም በፊት የጋብቻ ዓላማን ማወቅ አለባችሁ፡፡ በሕይወታችን ለምን ጋብቻ እንደሚያስፈልገን መረዳት አለባችሁ፡፡ ከዚህ ውጪ ሌላ ነገርን አትጠይቁ፡፡ እናስ የጋብቻ ዓላማው ምንድነው? ለምንድነው እግዚአብሔር ጋብቻን የሰጠን? ብጹዕ ጳውሎስን እናድምጠው፤ እንዲህ ያለውን፦ "ስለ ዝሙት ጠንቅ ለእያንዳንዱ ለራሱ ሚስት ትኑሮው፤ ለእያንዳንዲቱ ደግሞ ለራሷ ባል ይኑራት" (1ኛ ቆሮ.7፥2)። "ከድህነት ይወጣ (ትወጣ) ዘንድ" ነው የሚለውን? ወይስ "ሀብት ለማግኘት ሲባል" ነው የሚለውን? አይደለም፡፡ ታዲያ ምንድነው የሚለው? ከዝሙት እንጠበቅ ዘንድ፤ ራሳችንን መቆጣጠር እንችል ዘንድ፤ ንጽህናን ገንዘብ እናደርግ ዘንድ፤ በትዳር አጋራችን ደስ ተሰኝተን እግዚአብሔርን እናመሰግን ዘንድ፡፡ አያችሁ ይኼ ነው የጋብቻ ስጦታው ይኼ ነው የጋብቻ ፍሬው፤ ይኼ ነው የጋብቻ ጥቅሙ፡፡
ስለዚህ #ልጆቼ! እማልዳችኋለሁ ትልቁን ጥቅም ዘንግታችሁት ዓይናችሁን በትንሹ ላይ አታሳርፉ፡፡ የትዳር አጋርን ስትመርጡ የሀብት ጉዳይ የእናንተ ትልቅ አጀንዳ ሊኾን አይገባም፡፡ ስለ ሀብት ብሎ የትዳር አጋርን መምረጥ ድንቁርና ነው፤ ሀብት ነገ ሊጠፋ ይችላልና፡፡ ስለዚህ ለትዳር የምትመርጡት ሰው ከምንም በላይ መንፈሳዊ ሀብቱን ተመልከቱ፡፡ በዚህም ዓለም በወዲያኛውም ዓለም ይበልጥ የሚጠቅማችሁ ይኼ ነውና፡፡
#አባቶች_ሆይ! አብርሃምን ምሰሉት፡፡ አብርሃም ለልጁ ለይስሐቅ ሚስትን ሲፈልግለት፦ ሀብትን አላየም፤ የንጉሣውያን ቤተሰብን አልተመለከተም፤ አፍአዊ ውበትን መመዘኛ አላደረገም፤ ወይም ይህን የመሰለ ሌላ መስፈርትን አልደረደረም፡፡ የነፍስ ንጽህናን እንጂ፡፡
#እናቶች_ሆይ! ሴት ልጆቻችሁን እንደ ርብቃ አሳድግዋቸው፡፡
እናንተ ማግባትን የምትሹ #ወጣቶች_ሆይ! ይስሐቅን ምሰሉት፦ ዘፈንን፣ ዳንኪራን፣ ሳቅና ስላቅን፣ የከበሮንና የዋሽንት ጫጫታን፣ ሌላውንም የዲያብሎስ ትርኢት በሰርጋችሁ ቀን አታስቡ፡፡ ከዚህ ይልቅ በምታደርጉት ኹሉም ላይ እግዚአብሔር እንዲቀድማችሁ ለምኑት፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ ትዳራችሁ ፍቺ፣ ዝሙት፣ ቅናት፣ ጭቅጭቅ፣ ንትርክ የሌለበት ኾኖ ይፀናላችኋል፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ፥ ሌላው በረከትም ተትረፍርፎ ይመጣላችኋል፡፡ የአውሎ ነፋስ ዓይነት በዙሪያችሁ ቢነፍስም፥ አትነዋወፁም፡፡
#እናንተ_ልጃገረዶች_ሆይ! ርብቃን ምሰሏት፡፡ የትዳር አጋራችሁን ፍጹም ለማፍቀር የተዘጋጃችሁ ኹኑ፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ ቤታችሁ ፍጹም ሰላማዊ ባሎቻችሁ የምትልዋቸውን የሚያደርጉና በፍቅራችሁ የሚንበረከኩ ይኾናሉ፡፡ ትዳር እንዲህ ኾኖ ሲጀመር፥ እግዚአብሔርንና ወላጆቹን ደስ የሚያሰኝ ልጅ ይገኝበታል፡፡
የቤት ዕቃዎችን መግዛት ስንፈልግ፥ በጣም እንጠነቀቃለን፡፡ የሻጮቹን ማንነት አይተን፣ የዕቃዉንም ጥንካሬ አገላብጠን ተመልክተን ነው የምንሸምተው፡፡ ሚስት ስናገባም ከዚህ የበለጠ ልንጠነቀቅ ይገባናል፡፡ የገዛነው ዕቃ ችግር ቢኖርበት ለሸጠልን ሰው መመለስ እንችላለን፡፡ ሚስት ስናገባ ግን ወደ ቤተሰቦቿ መመለስ አንችልም፤ እስከ ዕድሜአችን ፍጻሜ ድረስ ከእኛ ጋር ነው የምትኾነው፡፡ ክፉ ናት ብለን ብንመልሳት፥ በሕገ እግዚአብሔር መሠረት አመንዝራ እንኾናለን፡፡ ስለዚህ፥ ሚስት ስትመርጡ የሀገራችሁን ሕገ መንግሥትን ብቻ አታንብቡ፤ ከኹሉም በፊት ሕገ ቤተ ክርስቲያንን አንብቡ እንጂ፡፡

ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ህትመት የየትኛው ዓ.ም ነው?
https://youtu.be/fOgqgsFPZA4
https://youtu.be/fOgqgsFPZA4
YouTube
ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ህትመት የየትኛው ዓ.ም ነው?
✝️✝️✝️የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ በጸሎት ያግዙን✝️✝️✝️አዲሱን የማኅበራችንን የዩቱዩብ ቻናል +++SUBSCRIBE +++ እያደረጋችሁ ትምህርቶችን እና መዝሙሮችን እንዲደርሶት እና ለሌሎች እንዲደርሳቸው ሼር በማድረግም ይተባበሩን::
ከዚህ በፊት የተለቀቁ ትምህርቶችንና ዝማሬዎችን ለማግኘት ከስር የሚገኘውን ሊንክ ይጠቀሙ
https://www.youtube.com/channel/UCol_BHX6I…
ከዚህ በፊት የተለቀቁ ትምህርቶችንና ዝማሬዎችን ለማግኘት ከስር የሚገኘውን ሊንክ ይጠቀሙ
https://www.youtube.com/channel/UCol_BHX6I…
ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ህትመት የየትኛው ዓ.ም ነው?
ማኅበረ ጽዮን
ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ህትመት የየትኛው ዓ.ም ነው?
በዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
በዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
ፍኖተ ሕይወት ሣምንታዊ ሴቶች በቤተክርስቲያን
https://youtube.com/watch?v=CZHAAem9YVM&si=rB3v7vycKG28ezJI

†
[ 🕊 ሕይወት እናት ሞት ! 🕊 ]
🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒
❝ የአምላክ እናት ሆይ ጌታን በመውለድሽ ምክንያት ድንግልናሽን እንዳልተውሽ በመሞትሽም ይህንን ዓለም አልተውሽውም:: የሕይወት እናት ነሽና ዛሬ ወደ ሕይወት ተሻገርሽ:: በአማላጅነትሽም ነፍሳችንን በኃጢአት ከመሞት ታደጊ"
‹ ሌሎች በድንግልና የኖሩ ሴቶች 'ለሞት የሚሆኑ ልጆችን አንሰጥህም" በማለት ሞትን ተቃወሙት፡፡ ድንግል ማርያም ግን አንድ ልጅ በመውለድ በልጅዋ ሞት ራሱ እንዲሞት አደረገችው፡፡ ከዐለት ጋር እንደተጋጨ የተፈረካከሰው በማሕፀንዋ ፍሬ ነውና ሞት ወደ እርስዋ ሲቀርብ ተብረከረከ ❞
[ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ]
❝ ልጃቸው ተሰብስበው ወዳሉበት መጥታለችና አዳምና ሔዋን ዛሬ ደስ አላቸው … በዚህች ቀን ታላቁ ዳዊት በራሱ ላይ የተዋበ አክሊል የደፋችለትን ሴት ልጁን አይቶ ደስ አለው … በዚህች ቀን ነቢዩ ኢሳይያስ ትንቢት የተናገረላት ድንግል ወደ ሙታን ሥፍራ ልትጎበኘው መጥታለችና ደስ አለው … በዚህች ቀን ብርሃን ሲበራባቸው አይተዋልና ነቢያት ሁሉ ከመቃብራቸው ራሳቸውን ቀና አደረጉ … አርያም በጣፋጭ የመላእክት ዝማሬ ተሞላ ፣ ምድር ደግሞ ኀዘንን በተሞሉ በሐዋርያት ለቅሶ ተሞላች፡፡ ሙታንም ሕያዋንም ትርጉሙን ሊገልጹት በማይችሉት [የተለያየ] ዜማ ሰውና መላእክት በዚያች ዕለት አብረው ጮኹ ❞
[ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ] (Homily on the Dormition)
❝ በእርሱ ምክንያት ሰማይ ተብላ የተጠራችበት የሚመስለው የሌለ የማሕፀንዋ ፍሬ ለመሞትና ለመቀበር ፈቃደኛ ከሆነ ያለ ዘር የወለደችው እናቱ እንዴት ሞትን ትፈራለች ? ❞
[ ቅዱስ ዮሐንስ ዘደማስቆ ] (The life of Virgin Mary)
❝ የቃሉ አገልጋዮችና ምስክሮች የነበሩት ሐዋርያት በሥጋ የወለደችውን የእናቱን ዕረፍትና እርስዋን የሚመለከቱ የመጨረሻዎቹን ምሥጢራትም ማየት ነበረባቸው፡፡ ይህም የሆነው የክርስቶስ የዕርገቱ የዓይን ምስክሮች እንደሆኑ ሁሉ የወለደችውም እናቱ ወደዚያኛው ዓለም ለሸጋገርዋ ምስክሮች መሆን ስላለባቸው ነው ❞
[ ቅዱስ ዮሐንስ ዘደማስቆ ] (aka Doctor of Dormition)
† † †
💖 🕊 💖

† 🕊 [ አስተርዮ ማርያም ] 🕊 †
💖
በዘመነ አስተርዮ የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ የሆነበትና የአምላካችን አንድነትና ሦስትነት የተገለጠበት ብቻም ሳይሆን በጥር ፳፩ የከበረች እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም የዕረፍት ቀን በመሆኑ “አስተርዮ ማርያም” በማለት በዓልን አናደርጋለን፡፡
የአምላክ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ምድር ላይ ፷፬ ዓመታትን ከኖረች በኋላ መንፈስ ቅዱስ ባስገነዘባት መሠረት በክብር ዐርፋለች፡፡ የዚህን ዓለም መከራና ሥቃይ ለሰዎች ድኅነት የተቀበለችው ክብርት እናታችን በሥጋ ብትሞትም እንደ ልጇ ደግሞ በትንሣኤዋ ተነሥታለች ፤ ይህም የሆነው በተቀደሰች ዕለት ነሐሴ ፲፮ ነው፡፡
እመ ብርሃን ከእናትና ከአባቷ ጋር ሦስት ዓመት ፣ በቤተ መቅደስ ፲፪ ዓመት ፣ ከተወዳጁ ልጅዋ ጋር ፴፫ ዓመት ከሦስት ወር ፣ ከጌታችን ዕርገት በኋላ ከወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ጋር ፲፭ ዓመት ፣ በድምሩ ፷፬ ዓመት በዚህ በኃላፊው ዓለም ኖራ ጥር ፳፩ ቀን በ፵፱ ዓመተ ምሕረት በክብር ዐርፋለች፡፡
ክርስቲያኖች በሙሉ ይህንን በዓል ልናከብር ይገባልና ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓትን ሠርታልናለች፡፡ “አስተርዮ ማርያም” በሕዝበ ክርስቲያን ዘንድ የሚከበር በዓል በመሆኑ በሀገራችን ኢትዮጵያ እና በመላው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ማኅበረሰብ ዘንድ በድምቀት ይከበራል፡፡ በዓሉን የምናከብረውም የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ከዚህ ዓለም ድካም ማረፍ በማዘከር ብቻ ሳይሆን አማላጅነቷና ተረዳኢነቷን በማሰብና ተስፋ በማድረግ ነው፡፡
ስለዚህም እመ ብዙኃን እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዐሥራት ሀገሯን ኢትዮጵያን እንድታስባት ፣ ለእኛም ለሕዝቦቿ ሰላምን ፣ ፍቅርንና አንድነትን ታሰጠን እንዲሁም ለነፍሳችን ድኅነትን ትለምንልን ዘንድ ዕረፍቷን መዘከር ይገባል፡፡
የአምላካችን እግዚአብሔር ቸርነት ፣ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነትና ተረዳኢነት አይለየን ፤ አሜን !!!

🕊
[ ዮም በፍሥሐ ለማርያም እምነ ፤ አስተርእዮ በሰማይ ኮነ ]
እንኳን አደረሳችሁ።
----------------------------------------
" አስደናቂው የእመቤታችን እረፍት "
[ " አቤቱ ፥ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ ፥ አንተና የመቅደስህ ታቦት።" [ መዝ.፻፴፪፥፰ ]
💖 ድንቅ ትምህርት 💖
[ በዲ/ን ብርሃኑ አድማስ ]
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

👇