Telegram Web Link
አላህ እንደቀደረብኝ ያንን vpn ካላወረድኩ የኔ ነገር መና ሆኗል ።
አንድ በጣም ትልቅ ቆሻሻ የጫነ ጋሪ የሚገፋ ሰው ወደ ቤትህ መጥቶ "እባክህ በርህን ክፈትልኝና ይህን ቆሻሻ አንተ ቤት ላራግፈው?" ቢልህ፣ "ውይ የሚጥልበት ቢያጣ ነው። ባይቸገር ወደ እኔ አይመጣም ነበር" ብለህ ደጅህን ከፍተህ ታስገባዋለህ? በፍጹም፤ እንደውም "እንዴት ብታስበኝ ነው? ምነው ስታየው ቤት አልመሰለህም? እንዴት ሰው በሚኖርበት ቤት ቆሻሻ ካልደፋሁ ትላለህ? ስትል ለጠብ ትጋበዛለህ። መደፈርህ እያንገበገበህ  "እምቢ!" ብለህ ትቆጣለህ። በእርግጥም ያስቆጣል።

ግን ሌላ የሚከፋ ሽታ ያለው ቆሻሻን ጭኖ ለመጣ ባላጋራ እኮ በፈቃድህ የከፈትከው ቤት አለ። "የምን ቤት?" ብለህ ብትጠይቀኝ "ልብህ ነዋ" ብዬ እመልስልሃለሁ፤ "ማን ይኖርበታል?" ካልኸኝም "እግዚአብሔር ነዋ" እልሃለሁ።

አንተ ለመኖሪያ ቤትህ ጽዳት የምትጠነቀቀውን ያህል የያዕቆብ አምላክ ለሚያርፍበት ኅሊናህ ተጠንቅቀህ ታውቃለህ? ሰይጣን ጭኖ የሚያመጣውን የኃጢአት ቆሻሻ ሁሉ እሺ ብለህ ወደ ልብህ በማስገባት የፈጣሪህን መቅደስ ለምን ታቆሽሻለህ? ንጹሑ እግዚአብሔር የሚያድርበትን ቤት ሊያቆሽሽ በመጣ ሰይጣን ላይ እንዴት አልተቆጣህም? ድፍረቱ ለምን አላብከነከነህም?

እግዚአብሔር አንተ ልትኖርበት ከምትፈልገው ንጹሕ ቤት የበለጠ ጽዱ መቅደስ የማይፈልግ ይመስልሃል?

(Dn Abel Kassahun Mekuria )
ፀሎት አድርጋችሁ ተኙ
ኦ ነዛሕከ ደመ መለኮት ረሡነ
እምነ አድባር አድባረ ወእምነ መካን መካነ
በንዝሐተ ደሙ ለወልድ ይኩኑ ቅዱሳነ
ፈለገ ጥበብ ዑራኤል እንተ ታስተፌሥህ ዓይነ
ክንደፈ መትከፍትከ ረዳኤ ይኩነነ
እንደምን አደራችሁ
መግቢያ በነጻ!

ኑ! መምህራንን በቀጥታ እንጠይቅና የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን መልስ እንስማ!

በ3 ወር አንዴ የሚካሄደው ጉባኤ ቦሩ ሜዳ "የሚመጣው ማነው?" በሚል ዐብይ ጉዳይ ይካሄዳል።

የፊታችን እሑድ ሐምሌ 23/2015 ዓ.ም በጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ ይገኙ።

የእናንተን የፊት ለፊት ጥያቄዎች ለመመለስ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ይገኛሉ።
መሃይም መሆኑን እያወቀ #እየጨመቀ ኢቅራ አለው....
በአደባባያቸው ማክበር አልተቻለም

የሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስ መታሰቢያ በዓል በየዓመቱ ሃውልታቸው በሚገኝበት ፒያሳ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ስር ሲከበር ቆይቷል።

ዘንድሮ ሀምሌ 22-2023 ግን ይህንን "የዝክረ ሰማዕት አቡነ ጴጥሮስን" በዓል በዓደባባይ ለማክበር አልተቻለም። ወይም ባልተገለፀ ምክንያት ክልከላ ተደርጓል።

ይህንን በማስመልከት የቅዱስ ራጉዔል ስብከተወንጌል አገልግሎት መታሰቢያቸውን በቤተክርስቲያኗ አዳራሽ ለማድረግ ከፍተኛ ዝግጅት የተደረገ ስለሆነ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።

"ዝክረ ሰማዕቱ ለአቡነ ጴጥሮስ"
ያኛው ጣሊያን ሲሄድ ሌላ ጣልያን መጥቶ
ጴጥሮስን ማን ይዝከር ከአደባባይ ወጥቶ!
©መምህር ዘላለም
+++ "ልጆቼ ከመሸ ተገናኘን" +++

ያኔ የገዳሙ መጋቢ የነበሩት አባ ተጠምቀ በጭንቀት ተውጠዋል። ከአቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ እግር ስር ወድቀው "ግድ የልዎትም አባ የዛሬው ጉዞ ይቆይዎ። እኔ ጥሩ ሕልም አላየሁም። እባክዎ እግርዎን ከዚህ ቤት አያንሡ፤ እንደው እባክዎ" እያሉ ይለምኗቸዋል። አቡነ ጎርጎርዮስ ግን ወደ መቂ ጊዮርጊስ ለአገልግሎት ለመሄድ ቆርጠው ተነሥተው ነበርና ሳልሄድ አላድርም ብለው እምቢ አሉ። በእርግጥ በዚያች የጉዞ ቀን ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ ቀድመው ሳይረዱት ቀርተው አይመስልም። ምክንያቱም "ዛሬ ጥሩ ሕልም አላየሁምና አይሂዱ" ላሏቸው አባ ተጠምቀ " እኔስ ብሆን አንዳች ምልክት ያላየሁ ይመስልሃል። ዛሬ ጠዋት ሱሬን ስታጠቅ ሰባት ጊዜ መልሶ ሲፈታብኝ ነበር" ሲሉ መልሰውላቸዋል። ይሁን እንጂ በመቂ የሚገኝ እጅግ ሕመም የጸናበት አንድ የሚያውቁት ክርስቲያን ስለ ነበር ከራሳቸው ሕይወት ይልቅ ለዚያ ሰው ነፍስ ዋጋ ሰጥተው "ኸረ ሳላቆርበው እንዳይሞትብኝ" እያሉ አባ ጎርጎርዮስ ወደ መኪናው ፈጥነው ወጡ። ነገር ግን ከዚያ መኪና በሕይወት አልወረዱም። ከአዲስ አበባ ሕዝብ ጭኖ ከመጣ ተሽከርካሪ ጋር እርሳቸው ያሉበት መኪና ተጋጭቶ እሑድ ኃምሌ 22 ቀን ጠዋት አንድ ሰዓት ገደማ እኛ ደግ እና ባለ ብዙ ራእይ አባት አረፉ።

ብፁዕነታቸው ከማረፋቸው ከ15 ቀናት በፊት በአላጌ ሕፃናት አምባ የልጆች ማሳደጊያ ተገኝተው በዚያ ቦታ ለሚሠራ ቤተ ክርስቲያን መሠረት ካኖሩ በኋላ "ሰው የሚፈልገውን ከሠራ የሚጠብቀው ሞቱን ነው" ብለው ተናግረው ነበር። በውስጣቸውም የነበረው የአገልግሎት እሳት ገና እየተቀጣጠለ ቢሆንም በዚህች ምድር የሚቀራቸው የእንግድነት ዘመን ግን ጥቂት መሆኑን ስለተረዱ በዚያ ለነበሩት መንፈሳዊ ልጆቻቸው እየደጋገሙ "ልጆቼ ከመሸ ተገናኘን" ይሏቸው ነበር። ከዚህች ክፋት ከነገሠባት ዓለም ጠልቀው ፈጣሪያቸው ካለበት መንፈሳዊ አገር የሚወጡበት ጊዜ መቃረቡን ቀድመው የተረዱ አባት ነበሩ።

አቡነ ጎርጎርዮስ ከዘመናቸው ቀድመው የኖሩ፣ ትውልዱ ሃይማኖቱን ያቆዩለትን አባቶች እንዲያውቅና የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ እምነቱንም ታሪክ ከመሠረቱ ተረድቶ ቤተ ክርስቲያኑን እንዲያፈቅር በቃልም በመጽሐፍም የተጉ አባት ናቸው። ቅዱስ አባታችን የነበሩበትን ዘመን አልፎ በሚሄደው ተራማጅ አሳቢነታቸውና ለቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ ዕድገት ያሳዩት በነበረው ትጋት አሁን ላይ ላሉትና ወደ ፊትም ለሚነሡ በእውነት ለሚደክሙ ቅን አገልጋዮች ሁሉ ትልቅ አርአያ ይሆናሉ።

የአገልግሎት ድካማቸው በረከት በሁላችን ላይ ይደርብን። እኛንም የአባቶቻችን ልጆች ያድርገን!!!

(*የያኔው አባ ተጠምቀ የአሁኑ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ሣልሳይ የምሥራቅ ሸዋ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ናቸው።)

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
ሐምሌ 22፣ 2014 ዓ.ም.
ዝዋይ (ብፁዕነታቸው ብዙ ሥራ በሠሩበት ክፍለ አገር ሆኜ)
እንዴት ነሽ እህትዓለም ዛሬ 3:00 ላይ ለልባም ሴቶች #ስለነገረ_ተክሊል  የተዘጋጀ ሸጋ ትምህርት አለ 🤩 መማር ከፈለጊ  ከሆነ ከታች ያለውን ሊንክ ተጭነሽ ግቢ ። አትጠራጠሪ ትጠቀሚበታለሽ ።😔 https://www.tg-me.com/lebame_set?livestream=2a59968ca42a697ae4 

🏃‍♀🏃‍♀🏃‍♀🏃‍♀🏃‍♀ ግቢና ተማሪ 😍😍😍😍
ህገወጡ ጳጳስ አደጋ ደረሰበት

ሰሞኑን በታላቋ ገዳም በአክሱም ጽዮን ቤተክርስቲያን ድፍረት በተሞላበት ሁኔታ ጵጵስና ተሹሟል የተባለው ሰው የመኪና አደጋ ደረሰበት የሚል መረጃ ከዚሁ ከማህበራዊ ሚዲያው ሰማው ሁላችሁም ፀልዩለት
👉ንስሃ እንዲገባ
Hadith

"حَدَّثَنَا قُتَيْبَةُ، وَنَصْرُ بْنُ عَلِيٍّ، قَالاَ حَدَّثَنَا سُفْيَانُ، عَنْ عَمْرِو بْنِ دِينَارٍ، عَنْ جَابِرٍ، قَالَ أَطْعَمَنَا رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم لُحُومَ الْخَيْلِ وَنَهَانَا عَنْ لُحُومِ الْحُمُرِ ‏.‏ قَالَ وَفِي الْبَابِ عَنْ أَسْمَاءَ بِنْتِ أَبِي بَكْرٍ ‏.‏ قَالَ أَبُو عِيسَى وَهَذَا حَدِيثٌ حَسَنٌ صَحِيحٌ وَهَكَذَا رَوَى غَيْرُ وَاحِدٍ عَنْ عَمْرِو بْنِ دِينَارٍ عَنْ جَابِرٍ ‏.‏ وَرَوَاهُ حَمَّادُ بْنُ زَيْدٍ عَنْ عَمْرِو بْنِ دِينَارٍ عَنْ مُحَمَّدِ بْنِ عَلِيٍّ عَنْ جَابِرٍ وَرِوَايَةُ ابْنِ عُيَيْنَةَ أَصَحُّ ‏.‏ قَالَ وَسَمِعْتُ مُحَمَّدًا يَقُولُ سُفْيَانُ بْنُ عُيَيْنَةَ أَحْفَظُ مِنْ حَمَّادِ بْنِ زَيْدٍ ‏.‏"
 
Narrated Jabir:
"The Messenger of Allah (ﷺ) allowed us to eat horse meat, and he forbade us from eating donkey meat."

He said: There is something on this from Asma' bin Abi Bakr. Abu 'Eisa said: This Hadith is Hasan Sahih. This is how it was reported by more than one narrator, from 'Amr bin Dinar from Jabir. Hammad bin Zaid reported it from 'Amr bin Dinar from Muhammad bin 'Ali, from Jabir. The narration of Ibn 'Uyainah (no. 1793) is more correct. He said: I heard Muhammad saying: "Sufyan bin 'Uyainah is better at memorizing than Hammad bin Zaid."

Sahih (Darussalam) 

Jami` at-Tirmidhi, 1793
In-Book Reference: Book 25, Hadith 6
English Reference: Vol. 3, Book 23, Hadith 1793
በትግራይ ተጨማሪ ሕገ ወጥ ሢመት ተፈጸመ
++++
አስቀድሞ እንሾማለን ብለው ካሰቡትና ባለፈው ሣምንት ሳይሰየሙ ከቀሩት አራት መነኮሳት መካከል የሦሥቱን ዛሬ ፈጽመዋል። አባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል ብቻ ቀርተዋል። እሳቸውን እዚያው አውስትራሊያ ሄደው ወይም አሜሪካ አስመጥተው ይሾሟቸው ይሆናል።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
Narrated Abu Huraira:The Prophet (ﷺ) said, "When you hear the crowing of roosters, ask for Allah's Blessings for (their crowing indicates that) they have seen an angel. And when you hear the braying of donkeys, seek Refuge with Allah from Satan for (their braying indicates) that they have seen a Satan."

"አቡሁሬራ እንደተከው ፦ ነብዩ (ﷺ) እንዲህ አሉ "አዉራ ዶሮ ሲጮህ ከሰማቹ አላህ እንዲባርካቹ ለምኑት (የእነሱ ጩኸታቸው እንደሚጠቁመው) አዉራ ዶሮው የጮሀው መላዕክን ስላየ ነው፡፡ እና አህያ ሲያናፋ ከሰማቹ ግን አላህን መሽሽጊያ ለምኑት (ማናፋቱ የሚጠቁመው) ስይጣን ስላየ ነው።"

Reference : Sahih al-Bukhari 3303In-book reference : Book 59, Hadith 111USC-MSA web (English) reference : Vol. 4, Book 54, Hadith 522  (deprecated numbering scheme)
2024/09/29 13:24:40
Back to Top
HTML Embed Code: