Telegram Web Link
ኑሃይላ ቤንዚና ባለሂጃቦ ተጫዋች

ሙስሊሞችዬ
#ድምፃችን_ይሰማ በሉ ። በቅርቡ ታላቅ ወንድሟ እግሯን ሊያሳጥረው ይችላል ። 😁
እኔን ካልወደድከኝ እምነት የለህም 😂

ሙሐመድ እስልምናን የፈለሰፈው ራሱን ለማክብር ነው
ወይስ ሰዎችን ከገሃነም ለመጠበቅ

Narrated Anas:
The Prophet (ﷺ) said "None of you will have faith till he loves me more than his father, his children and all mankind."
አናስ እንደተረከው፡-
ነብዩ (ሶለላሁ ​​ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል "ከእናንተ አንዳችሁም ከአባቱ፣ ከልጆቹ እና ከሰዎች ሁሉ በላይ እስካልወደደኝ ድረስ እምነት የውም።
حَدَّثَنَا يَعْقُوبُ بْنُ إِبْرَاهِيمَ، قَالَ حَدَّثَنَا ابْنُ عُلَيَّةَ، عَنْ عَبْدِ الْعَزِيزِ بْنِ صُهَيْبٍ، عَنْ أَنَسٍ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم ح وَحَدَّثَنَا آدَمُ، قَالَ حَدَّثَنَا شُعْبَةُ، عَنْ قَتَادَةَ، عَنْ أَنَسٍ، قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ لاَ يُؤْمِنُ أَحَدُكُمْ حَتَّى أَكُونَ أَحَبَّ إِلَيْهِ مِنْ وَالِدِهِ وَوَلَدِهِ وَالنَّاسِ أَجْمَعِينَ ‏"‌‏.‏
Reference : Sahih al-Bukhari 15
In-book reference : Book 2, Hadith 8
USC-MSA web (English) reference : Vol. 1, Book 2, Hadith 15
(deprecated numbering scheme)
መልካም ፊት ማለቴ ቀን 😁
"ጌታ ሆይ ወርቅ ትሰጠኝ ዘንድ አልለምንህም ሀብት ንብረትም አልለምንህም እነርሱ ድኅነትን የሚያስገኙ አይደሉም። ይቅርታህን ማግኘት ግን ከወርቅ ይልቃል። የኃጢአት ሥርየትን ማግኘትም ከብር ይበልጣል።" (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)
"ቤተክርስቲያን  ወደ እግዚአብሔር እንድንቀርብ የምታደርገን የልዑል እግዚአብሔር ደጅ ናት፡፡"

መጽሐፈ ዲድስቅልያ
ንፋስን የሚፈራው ነብይ 😁😂😂 መሀመድ

Sahih al-Bukhari 1034
Narrated Anas:
Whenever a strong wind blew, anxiety appeared on the face of the Prophet (fearing that wind might be a sign of Allah's wrath).

አናስ እንደተረከው፡-
ነብዩ ( ሶ.ዐ.ወ) ኃይለኛ ነፋስ በነፋስ ቁጥር ጭንቀት በነብዩ ፊት ላይ ይታይ ነበር (ንፋስ የአላህ ቁጣ ምልክት ሊሆን ይችላል በሚል ፍራቻ )

حَدَّثَنَا سَعِيدُ بْنُ أَبِي مَرْيَمَ، قَالَ أَخْبَرَنَا مُحَمَّدُ بْنُ جَعْفَرٍ، قَالَ أَخْبَرَنِي حُمَيْدٌ، أَنَّهُ سَمِعَ أَنَسًا، يَقُولُ كَانَتِ الرِّيحُ الشَّدِيدَةُ إِذَا هَبَّتْ عُرِفَ ذَلِكَ فِي وَجْهِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم‏.‏

Sahih al-Bukhari 1034
Book 15, Hadith 29
Vol. 2, Book 17, Hadith 144

ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ነው ንፋሱ ማዕበሉን የሚታዘዙለት 🥰🥰🥰🥰

መዝሙር 107
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁸ በተጨነቁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፥ ከመከራቸውም አዳናቸው።
²⁹ ዐውሎንም ጸጥ አደረገ፥ ሞገዱም ዝም አለ።
³⁰ ዝም ብሎአልና ደስ አላቸው፤ ወደ ፈለጉትም ወደብ መራቸው።
³¹ ለሰው ልጆች ስላደረገው ተአምራት ስለ ምሕረቱም እግዚአብሔርን ያመስግኑ።

ሉቃስ 8
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²² ከዕለታቱም በአንዱ እርሱ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ታንኳ ገብቶ፦ ወደ ባሕር ማዶ እንሻገር አላቸው፤ ተነሡም።
²³ ሲሄዱም አንቀላፋ። ዓውሎ ነፋስም በባሕር ላይ ወረደ፥ ውኃውም ታንኳይቱን ይሞላ ነበርና ይጨነቁ ነበር።
²⁴ ቀርበውም፦ አቤቱ፥ አቤቱ ጠፋን እያሉ አስነሡት። እርሱም ነቅቶ ነፋሱንና የውኃውን ማዕበል ገሠጻቸው፤ ተዉም፥ ጸጥታም ሆነ።
²⁵ እርሱም፦ እምነታችሁ የት ነው? አላቸው። ፈርተውም ተደነቁ፥ እርስ በርሳቸውም፦ እንዲህ ነፋሳትንና ውኃን እንኳ የሚያዝ ለእርሱም የሚታዘዙለት ይህ ማን ነው? አሉ።
የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልአተ
ጉባኤ ስብሰባ በጸሎት ተከፈተ።
***********

ሐምሌ ፳፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ/ም አዲስ አበባ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በክልል ትግራይ ባሉ አህጉረ ስብከት ለመንፈሳዊ አገልግሎት ተመድበው የነበሩ አራት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ሐምሌ ፲፮ እና ፳፫ ቀን ፳፻፲፭ ዓ/ም በፈጸሟቸው የቀኖና ቤተክርስቲያን እና የሕግጋተ ቤተክርስቲያን ጥሰቶች ዙሪያ ለመወያየትና ሕግጋተ ቤተክርስቲያንን መሠረት ያደረጉ ውሳኔዎችን ለማሳለፍ ጉባኤውን በጸሎት ጀመረ።
ሕገወጥ ድርጊቱ መፈጸሙን ተከትሎ በቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በኩል የተጠራውን አስቸኳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ስብሰባ ለመጀመር ዛሬ ሐምሌ ፳፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ/ም በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ቀኖና ቤተክርስቲያንና ሕገ ቤተክርስቲያን በሚያዘው ሥርዓት መሠረት የመክፈቻ ጸሎቱ ደርሷል።
የመክፈቻ ጸሎቱ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የተመራ ሲሆን በመርሐ ግብሩ ላይ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት ባሉ አህጉረ ስብከቶች ተመድበው የቤተክርስቲያንን አገልግሎት የሚመሩ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተገኝተዋል።
የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ባወጣው የድርጊት መርሐ ግብር መሠረት ዛሬ በጸሎት የተጀመረው የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልአተ ጉባኤ ነገ ሐምሌ ፳፮ ቀን ፳፻፲፭ ዓ/ም ጠዋት ፪ ሰዓት ከ፴ በተያዙት አጀንዳዎች ላይ በመወያየት የቤተክርስቲያናችንን ቀኖናትና ሕግጋት የሚያስከብሩ ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል።
መናፍቃን እና ሙስሊሞች ለመወያየት ስላልቻሉ እኛ ተከታታይ ወይም አጫጭር ትምህርቶችን እንጀምር ወይ ?
*በወንድምህ ላይ የመፍረድ ክፉ ግብር ቢኖርህ*


👉በፈረድክ ቀን በግንባርህ ተደፍተህ በጸሎት ሦስት ነገሮችን መጠየቅ ይኖርብሃል፡፡

👉ጌታ ሆይ ማረው አድነው፤ ጌታ ሆይ ፈራጁን እኔን በኃጢአተኛው ጸሎት ማረኝ በለው፡፡

👉 በሰው ላይ በፈረድክ ሁሉ ጊዜ ይህንን አድርግ፡፡

👉 ይህንን ማድረግ ከተቻለህ እግዚአብሔር ታማኝነትህን ተመልክቶ ከዚህ ዓይነት ኃጢአት ለዘላለም ያወጣሃል፡፡

በዚህ መንገድ ድኅነትን ማግኘት ይቻልሃል፡፡


_/ቅዱስ ባስልዮስ/ _❤️
“፦ይህ ስፍራ እንዴት ያስፈራ፤ ይህ ስፍራ የእግዚአብሔር ቤት ነው እንጂ ሌላ አይደለም፤ ይህም የሰማይ ደጅ ነው።”
— ዘፍጥረት 28፥17

ሊቃውቱም " #አድባራት_ወገዳምት_ከማሃ_ይመስሉ 🥰 #ደብሩሰ_ለሚካኤል_ትመስል_ደብረ_ሲና "🥰 እውነት ነው የሚካኤል ንጉሱ የገነባት ታላቋ ደብር መድኃኒት ሙሴ ቀዳማዊ ህግን የተቀበለባትን ከግርማዋ የተነሳ ህዝበ እስራኤል ይፈሯትን ደብረ ሲናን ትመስላለች ። ለነገሩ ይችስ ትበልጣልች ።ምክኒያቱም በደብረ ሲና በዚያች ተራራ ህግ ቀዳማዊ ህግ እንጂ አማናዊ አልትሰጠችም ኦሪት እንጂ ወንጌል ቅድስት አልተሰጠችም ፤ አንድም በዛች በሲና እግዚኣ ኃያላን ተገለጠ እንጂ አላደረባትም ፤ አንድም በዛች በቀደመችው ሲና ስለስርየተ ኃጢአት ስለዕለት ስርየት የበጎች እና የጠቧቶች ደም ፈሶል በዚች ቤተመቅደስ ግን በግዕ ዘበዓማን ሐጢአት የሚያስተሰርየው መለኮትን የተዋሃደው እራሱ እግዚአብሔር ይሰዋባታል ፤ አንድም የቀደመችው ሴና ተራራ እግዚአብሔር በተግሳፅ የተገለጠባት የምትጨስ ተራራ ናት ለዛ ነው ሊቁ ኤፍሬም "ይጌስፅ ለለእለ ይፈርሁ በፍርሐት ወበርአድ"ያለው ይችኛይቱ ደብረ መድኃኒት ግን እግዚአብሔር በታላቅ እና ግሩም ፍቅር "ሸክማችሁ የከበዳችሁ ወደእኔ ኑ እኔም አሳርፋችኋለሁ" የሚባልባት የፍቅር ደጅናት 🥰 ...ኧረ ይችስ ከሴና ትበልጣለች ።🥰

👉ደብረ መድኃኒት ቤቴ እንኳን ለ110 አመት ህንፀተ ቤትሽ አደረሰሽ 🥰 የትም ብሔድ ከልቤ የማይጠፋ የአፈሩ ትቢያ እንኳን የሚናፍቀኝ መስናኛዬ ነሽና ።

🥰የደሴው መድኃኔዓለም🥰
ቅዱስ ሲኖዶስ ነቶም ቀኖናን ቤተ ክርስቲያንን ብምጥሓስ ክድዓት ዝፈጸሙን ዘይሕጋዊ ተግባራት ዝፍጽሙን ጳጳሳት ካብ ሓድነት ቤተ ክርስቲያን ኮኒኑን ፈሊዩን!

26 ሓምለ 2015 (ኣዲስ ኣበባ)

ቅዱስ ሲኖዶስ ነቶም ቀኖናን ቤተ ክርስቲያንን ብምጥሓስ ክድዓት ዝፈጸሙ ጳጳሳት ብምኹናን ካብ ሓድነት ቤተ ክርስቲያን ፈሊዩዎም፡ ተግባራቶም መናፍቕነት ስለዝኾነ ብህይወት ይኹን ብሞት ኣገልግሎት ቤተ ክርስቲያን ክቕበሉ የብሎምን።

ንጳጳሳት ነበር ኮኒኖም
"ኣባ" ኢሳያስ
"ኣባ" መቃርዮስ
"ኣባ" መርሓክርስቶስ
"ኣባ" ጴጥሮስ ነዚኦምን ነቶም ተሸይምና ዝበሉ መነኮሳትን ኮነኖም።
ኢትዮጵያን "ኤልዛቤል" በማለት የጠራው እና ከቤተክርስቲያን ጋር የዶግማ ልዩነት አለን በማለት የተናገረው መናፍቁ "አባ" ሠረቀብርሃን ወልደሳሙኤል ከቤተክርስቲያን ተወግዞ ተለየ !

ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

እመቤታችን ጥንተ አብሶ አለባት በሚለው ትምህርቱ የሚታወቀው መናፍቁ "አባ" ሠረቀብርሃን ወልደሳሙኤል ከቤተክርስቲያን አንድነት ተወግዞ መለየቱ ተገለጸ።

በቀድሞ ስሙ አባ ሠረቀብርሃን ወልደሳሙኤል የተባለው ግለሰብ በተለያዩ ጊዜያት በምንፍቅና ትምህርቱ የሚታወቀው ፤ በቅርቡ ደግሞ ከቀኖና ውጭ "መንበረ ሰላማ" በሚል በሚጠ'ራው መሠረት አልባ እና ከቤተክርስቲያን ቅዱስ ትውፊት ያፈነገጠ እንቅስቃሴ ጠንሳሽ እና አደራጅ በመሆን እተየተንቀሳቀሰ የሚገኝ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን በግልጽ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጋር የዶግማ ልዩነት አለን በማለት መግለጹ ይታወሳል።

በዚህም መሠረት ቅዱስ ሲኖዶስ ግለሰቡን አውግዞ መለየቱን በዛሬው ዕለት አስታውቋል።
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ።
**********************

በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ አምስትና በሕገ ቤተክርስቲያን አንቀጽ 19 ቁጥር 3 አስቸኳይ ጉዳይ ሲያጋጥም ምልዓተ ጉባኤ እንደሚያደርግ በተደነገገው መሠረት ሐምሌ 26ቀን 2015 ዓ.ም. ባካሄደው አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ በቤተ ክርስቲያናችን ላይ በተፈጠረው ወቅታዊ የዶግማ፣ የቀኖናና የአስተዳደራዊ ጥሰቶችን አስመልክቶ ውሳኔዎች አሳልፏል፡፡
ጥንታዊት፣ ሐዋርያዊትና ዓለም አቀፋዊት የሆነች ቅድስት ቤተክርስቲያን ሕዝብና አሕዛብን፣ ሰውና መላእክትን፣ ፍጡራን እና ፈጣሪን አንድ አድርጋ የሰው ልጆች ሁሉ በቋንቋ፣ በቀለምና በጐሣ ሳይከፋፈሉ ሀብተ ወልድና ስመ ክርስትና አግኝተው ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ከማህፀነ ዮርዳኖስ የተወለዱ በማየ ገቦ ተጠምቀው የቤተ ክርስቲያን ልጆች በመሆን ልዩነት የሌለባትን ዘለዓለማዊት መንግሥተ እግዚአብሔር እንዲወርሱ በደመ ክርስቶስ የተመሠረተች ስትሆን በየዘመናቱ የተነሣባትን ፈተና ሁሉ አልፋ ከእኛ ዘመን ደርሳለች፤ 

  ምንም እንኳ ከኦርቶዶክስ ትምህርተ ሃይማኖት ፈጽሞ በተለየ ሁኔታ ቤተ ክርስቲያንን በጐሣና በቋንቋ የመለየት ሂደት በዓለም አቀፍ ደረጃ እንግዳ ክስተት ቢሆንም ቤተ ክርስቲያን ከሃይማኖታዊና መንፈሳዊ ጠባይዋ በተለየ፣ ታሪኳንና ሥርዓቷን በማይመጥን፣ ከሕግ መንፈሳዊ፣ ከሕግ ጠባይአዊ እና ከሕገ አእምሮ በወጣ መልኩ የደረሰባት የዶግማ፣ የቀኖናና የአስተዳደር ጥሰት ቅዱስ ሲኖዶስን እጅግ አሳዝኖታል፤ 

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለሀገር አንድነት፣ ለፍትሕ፣ ለጥበብ፣ ለሕዝብ ትስስር፣ ለማኅበራዊ ዕድገት፣ ለጤና፣ ለሥነ-ምግባር መሠረትና ዐምድ፤  ሆና በዓለም አቀፍ ደረጃ የተፈራች፣ የተከበረችና የተወደደች፤ ዕሴቷ እና ዕምቅ የዕውቀት ሀብቷ በምሁራን የታወቀ፣ በትምህርተ ዓለም ሳይቀር የተቀረጸ፤ በእውነተኛ ሊቃውንት የተመሠከረ፣ ቅርሶቿ የተመዘገቡላት ስትሆን፤ ከፍተኛውን ሐዋርያዊ ተልእኮ እንዲወጡ አደራ በተሰጣቸው ሊቃነ ጳጳሳት በማኅበረሰብ ዕድገትና አስተዳደር ውስጥ ከሕዝብ ጋር በቆመች፣ ከፖለቲካ በጸዳች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ መንፈሳዊና ሕዝባዊት ተቋምነቷን በመካድ ከፍተኛ የሆነ ሕገ ወጥ ድርጊትና ተቋምን የመናድ እንደሁም መዋቅሯን የማፍረስ ተግባር ተከናውኗል፡-  

በዚሁ መሠረት፡-

ሐምሌ 16 እና 23 ቀን 2015 ዓ/ም በክልል ትግራይ በማእከላዊ ዞን አክሱም ሀገረ ስብከት በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ማርያም ገዳም ውስጥ የተፈጸመውን ሕገወጥ የሆነ አስነዋሪ፤ የቀኖና ቤተ ክርስቲያን ጥሰት አስመልከቶ ቅዱስ ሲኖዶስ ሐምሌ 26ቀን 2015 ዓ/ም አስቸኳይ ምልዐተ ጉባዔ አድርጓል፤ 

   ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በደመ ክርስቶስ ከተመሠረተችበት ጊዜ ጀምሮ ያለፈተና የኖረችበት ጊዜ እንደሌለ ቅዱሳት መጻሕፍትና የታሪክ መዛግብት ሲመሰክሩ በዘመነ ሐዋርያት ቢጽ ሐሳውያን፣ በዘመነ ሊቃውንት የተለያዩ መናፍቃን፣… በየጊዜው እየተነሡ ሲፈታተኗት ኑረዋል፡፡ አሁንም በግልጽ እንደሚታየው ከውጭም ከውስጥም በተደራጁ ምንደኞች በመፈተን ላይ ትገኛለች፡፡ ይህንኑ በመረዳትም ቅዱስ ሲኖዶስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት አስተዳደር ጉባዔ፣ የሊቃውንት ጉባኤ፤ የሕግ አገልግሎት መምሪያና የህግ ባለሙያዎች አቢይ ኮሚቴ፤ የውጪ ግንኙነት መምሪያ፣ ካቀረቡት ዶግማዊ፣ቀኖናዊ፣ታሪካዊና ትውፊታዊ ሰነዶች በመነሣት የቤተ ክርስቲያንን ልዕልና ለማስከበር ያስችል ዘንድ ጥልቅ ውይይት አድርጓል፡፡
  
  በዚህም መሠረት ሐምሌ 16 እና 23 ቀን 2015 ዓ.ም. በክልል ትግራይ በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ገዳም ውስጥ በትግራይ ክልል በሚገኙ ሊቃነ ጳጳሳት፡-

1. አባ ኢሳይያስ
2 አባ መቃርዮስ
3. አባ መርሐ ክርስቶስ
4 አባ ጴጥሮስ  መሪነት እጅግ አሳዛኝ ኢ-ሲኖዶሳዊ የሆነ አስነዋሪ፣ ሕገ-ወጥ፣ የቀኖና ቤተ ክርስቲያን ጥሰት በመፈጸም 10 መነኮሳትን በእጩነት በመምረጥና ለዘጠኙ ህገወጥ ሲመት በመፈጸም፣ ሥርወ ትውፊት ዘሐዋርያት የሆነውን የኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሐዋርያዊ መንበር በመካድ "መንበረ ሰላማ" የሚባል ህገወጥ መንበር በመሠየምና በህገወጥ መንገድ የሾሟቸውን ግለሰቦች ሊቃነ ጳጳሳት በሚመሯቸው በሀገር ውስጥና በውጪ በሚገኙ አህጉረ ስብከት በሕገ ወጥ መንገድ በመመደብ ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን ጥሰት አልፎ አንዲት ኩላዊትና ዓለም አቀፋዊት የሆነችውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን የሚከፋፍል፤ የሀገር አንድነትን የሚሸረሽር እና የሚያፈርስ፣ ምእመናንን ከምእመናን፣ ካህናትን ከካህናት፣ ሊቃውንትን ከሊቃውንት ወጣትን ከወጣት የሚያጋጭ ሰላም የሚያናጋ መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ተገንዝቧል። በመሆኑም፤ 


- የቤተ ክርስቲያን መንበር ሐዋርያዊ ነው፡፡ ሐዋርያዊ መንበር ጌታችን አስተምሮ ከሾማቸው ከዐሥራ ሁለቱ ከሐዋርያት የወጣ አይደለም፤ ሥልጣነ ክህነት የሚተላለፍበት፣ የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ትምህርተ ሃይማኖት እና ቀኖና ምንጩ ወይም ሥሩ የሚነገርበት፣ የሐዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን አማናዊና ሐዋርያዊ ታሪክ፣ ሃይማኖታዊና ቀኖናዊ ትውፊት የሚጀመርበት መነሻ ነው፡፡ 


- ቤተ ክርስቲያን የምትመራው በሐዋርያት ሥልጣነ ክህነት ነው፤ ይኽንን ሥልጣን ማንም እንደፈለገው ሊከፋፍለው አይችልም፤ በየትም ቦታ ያሉ ጳጳሳት ከቅዱስ ሲኖዶስ እና ከቅዱስ ፓትርያርክ ዕውቅና ውጭ እንደፈለጉ በቡድኑ እየሆኑ መንበር አቋቁመናል ሊሉ አይችሉም፤ ይህ ከቤተ ክርስቲያን ትውፊትና ታሪካዊ ቅብብል ውጭ የሆነ መናፍቅነት ነው፡፡ ከቅዱስ ሲኖዶስ ሕግ እና ሥርዓት ውጭ መውጣት ሕገ ወጥነት፣ ቀኖናን መሻር፣ ኃይማኖትን ማፍረስ ነው፡፡ የገቡትን ቃል መጣስ ነው፤ ከጥንት ጀምሮ መንበር ያለ ፓትርያርክና ከሀገሪቱ ርእሰ ከተማ ውጭ  የማይሰየም መሆኑ እየታወቀ መንበር አቋቁመናል ማለት የፓትርያርክን እና የሲኖዶስን ሥልጣን መቃወም፤ ከሃይማኖትም፣ ከቀኖናዊ ትውፊትም፣ ከአስተዳደራዊ መዋቅርም መውጣትና ራሳቸውን ከቤተ ክርስቲያን መንበር የለዩ በመሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ ድርጊቱን አውግዟል፡፡  

  ይህን ህገወጥ ተግባር ለመፈጸም በሀገራችን ተከስቶ የነበረው ጦርነት እንደ ምክንያት የተጠቀሰ ቢሆንም ቤተክርስቲያን ከጦርነቱ በፊት ጦርነት እንዳይከሰት ያደረገችውን ጥረት በጦርነቱ ወቅት ለተደረጉ ድጋፎችና ከጦርነቱ በኋላ ለተደረጉ የእንወያይ ጥረቶች እንዲሁም በቤተክርስቲያን በኩል የተዘረጋውን የሰላምና የእርቅ በር ይልቁንም ለሰላም ሲባል በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ የተጠየቀውን ይፋዊ ይቅርታ በመግፋት የተደረገ ኢ-ክርስቲያናዊ ተግባር ነው።
  
  በመሆኑም

•  በሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 16 ንዑስ ቁጥር 30 የአጲስ ቀጶሳት መሾም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ፣ በቤተ ክርስቲያን ቀኖና መሠረት እንዲመረጡና እንዲሾሙ የመወሰን ሥልጣን የቅዱስ ሲኖዶስ መሆን የሚደነግገውን ክፍል በግልጽ የጣሰ በመሆኑ

•  በሕገ ቤተክርስቲያን አንቀጽ 31 ንዑስ ቁ 1 እና 3 የቅዱስ ፓትርያርኩን የመዓርግ ስምና መንበር በተመለከተ የተደነገገውን ድንጋጌ የሚያፋልስ ህገወጥ ተግባር የተፈጸመ በመሆኑ
 
• በሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 37 ንዑስ ቁ.1 የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ የሚፈጸመው ኤጲስ ቆጶሳት እንዲሾሙ አስፈላጊ መሆኑ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሲታመንበትና ሲወሰን ብቻ እንደሚፈጸምና መደንገጉ፤ 

• በሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 18 ንዑስ ቁጥር 5 የቤተ ክርስቲያንን ሃይማኖታዊ ሕግጋትንና ቀኖናን የሚያፋልስ ሊቀ ጳጳስ /ኤጲስ ቆጶስ/ ከአባልነት እንደሚሰረዝ በመደንገጉ፤ 
• በአጠቃላይ የተፈጸመው ሕገ ወጥ ተግባር በሕገ ሰብእም ሆነ በሕገ እግዚአብሔር ሚዛን የተወገዘ ከመሠረተ እምነት የተለየ፣ በአበው ቀኖና፣ በሕገ ቤተ ክርስቲያን እና በቤተ ክርስቲያን አስተዳደር  ተቀባይት የሌለው ነው፡፡ ስለዚህ
1ኛ. በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ንኡስ አንቀጽ 138 መሠረት ሐምሌ 16 እና ሐምሌ 23 ቀን 2015 ዓ.ም በክልል ትግራይ በማዕከላዊ ዞን አክሱም ሀገረ ስብከት በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ቤተክርስቲያን ውስጥ 

1. ብፁዕ አቡነ ኢሳይያስ የመቀሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የእንቅስቃሴው ሰብሳቢ

2. ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ በክልል ትግራይ የማዕከላዊ ዞን አክሱም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

3. ብፁዕ አቡነ መርሐ ክርስቶስ የአዲግራት ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

4. ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የሽሬ እንዳሥላሴ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

   የቤተ ክርስቲያንን ቀኖና በመጣስ ባልተሰጣቸው ስልጣን 9 ኤጴስ ቆጰሳትን ሾመናል፤ ሲኖዶስ አቋቁመናል በማለት በተለያዩ ሚዲያዎች በሰጡት መግለጫና በክልሉ መንግሥት ሚዲያ በተላለፈው የቀጥታ ስርጭት የተረጋገጠ በመሆኑ በዚሁ ድርጊታቸው በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭው ዓለም የሚኖረውን ሕዝበ ክርስቲያንን በማታለል የክህደት እና የኑፋቄ ተግባር በመፈጸማቸው በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አውግዞ፤ ከቤተ ክርስቲያን የተሰጣቸውን ከዲቁና ጀምሮ ያለው ሙሉ ሥልጣነ ክህነት በመሻር አውግዞ ለይቷቸዋል፡፡
  በመሆኑም፡- 

ሀ. ሥልጣነ ክህነታቸውና የማዕረግ ስማቸው በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ውሳኔ የተነሣ ስለሆነ ከዛሬ ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በቀድሞ ዓለማዊ ስማቸው እንዲጠሩ፤

ለ. በቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ አገልግሎት ዙርያም በሕይወትም ሆነ በሞት ማናቸውንም መንፈሳዊ አገልግሎት እንዳያገኙ ቅዱስ ሲኖዶስ አውግዞ ከቤተ ክርስቲያን ለይቷቸዋል፡፡

• ይሁን እንጅ ከላይ በስም ተጠቅሰው የተወገዙት ግለሰቦች በሠሩት የቀኖና ጥሰት ተጸጽው ይቅርታን ቢጠይቁ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን የምህረት ደጆች ሁል ጊዜ ክፈት መሆናቸውና በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት የምንቀበላቸው መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳውቃል፤  
  
2ኛ. የቅዱስ ሲኖዶሱንና የቤተ ክርስቲያኒቱን ልዕልና በመዳፈር እና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በመጣስ በተነሳሱ ግለሰቦች አማካኝነት የኤጲስ ቆጶስነት ሹመት አግኝተናል፤ ተሹመናል እያሉ የሚገኙ 9 መነኮሳት

፩. አባ ዘሥላሴ ማርቆስ

፪. አባ ኃይለ ሚካኤል አረጋይ

፫. አባ እስጢፋኖስ ገብረ ጊዮርጊስ

፬. አባ መሓሪ ሀብቶ
  
፭. አባ ኤልያስ ታደሰ ገብረ ኪዳን

፮. አባ ጽጌ ገነት ኪዳነ ወልድ

፯. አባ ዘርአ ዳዊት ብርሃነ

፰. አባ ዮሐንስ ከበደ

፱.  አባ የማነ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል
በሕገ ወጥ መንገድ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንንን ጥሰው የተገኙ በመሆኑ አስቀድሞ ከቤተ ክርስቲያን የተሰጣቸው ከዲቁና ጀምሮ ያለው ሙሉ ሥልጣነ ክህነት ተሽሮ ከዛሬ ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ አገልግሎት ዙርያ በሕይወትም ሆነ በሞት ማናቸውንም መንፈሳዊ አገልግሎት እንዳያገኙ ቅዱስ ሲኖዶስ አውግዞ ከቤተ ክርስቲያን ለይቷቸዋል፡፡
  
3ኛ. ይህ ህገወጥ ሢመት እንዲፈጸም ከመጀመሪያው ጽንሰ ሀሳብ ጀምሮ መሪ ተዋናይና ቀስቃሽ በመሆን ኢትዮጵያን ኤልዛቤል በማለትና ስሟን የሚጠራ የተረገመ ይሁን በማለት እንዲሁም ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጋር የዶግማ ልዩነት አለን በማለት የኑፋቄ ትምህርት በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን የተናገሩትና በህገወጥ ሢመቱ ላይም በእጩነት ተመርጠው በሂደት ላይ ያሉት አባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤልና ሂደቱን በዋና አስፈጻሚነት በመምራትና መግለጫ በመስጠት ላይ ያሉት መ/ር ተስፋዬ ሐደራ ከዛሬ ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተወግዘው ከቤተክርስቲያን ተለይተዋል።

ከላይ በስም ተጠቅሰው የተወገዙት ግለሰቦች በሠሩት የቀኖና ጥሰት ተጸጽው ይቅርታን ቢጠይቁ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን የምህረት ደጆች ሁል ጊዜ ክፈት መሆናቸውና በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት የምንቀበላቸው መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳውቃል።

4ኛ. “መንበረ ሰላማ” የሚለው ሕገወጥ ሥያሜን በተመለከተ በቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ትውፊትም ሆነ በቀደምት አብያተ ክርስቲያናት ትውፊት የማይታወቅ፣ ሃይማኖታዊ መሠረት የሌለው፣ ከቀኖና የወጣ፣ አስተዳደራዊ መዋቅርን የሚያዛባ በመሆኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አትቀበለውም፤ በተጨማሪም ከአንዲት፣ ቅድስት፣ ሐዋርያዊትና ዓለም አቀፋዊትየሆነች የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ መንበር መሠረተ እምነት፣ ታሪክና ቀኖና፣ ከአስተዳደር እና ሕግ ባፈነገጠ ሁኔታ ትውፊትን በመዳፈር ጎሣን መሠረት አድርጎ የተፈጠረ ሕገ ወጥ አደረጃጀት በመሆኑ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አውግዞታል፡፡ ይሕንንም የክርስትናን ትውፊት እና ሐዋርያዊ መሠረት የሚዛባና ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን የማይወክል መሆኑ ታውቆ በመላው ዓለም ለሚመለከተው ሁሉ በደብዳቤ እንዲገለጽ እንዲደረግ፤

6. በየደረጃው የሚገኙ የቤተ ክርስቲያኒቱ የሥራ ኃላፊዎች፤ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፤ መነኮሳት፤ አገልጋይ ካህናት፤ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች፤ ልዩ ልዩ የቤተ ክርስቲያኒቱ መንፈሳዊ ማህበራት እና ምእመናን እና ምእመናት ይህን ሕገ ወጥ አድራጎት ከመከላከል እና የቤተ ክርስቲያናችሁን ደህንነት ከመጠበቅ በተጨማሪ ለዚህ ሕገ ወጥ አድራጎት ልዩ ልዩ ድጋፍ የሚያደረግ ተቋማት እና ግለሰቦችን አስፈላጊውን ክትትል እና ቁጥጥር በማድረግ የመከላከል ሥራችሁን እንድትወጡ ዘንድ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

8. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስምን ከፊትም ሆነ ከኃላ በመጨመር እና በመቀነስ በከፊልም ሆነ በሙሉ መጠቀም፤ ዓርማዋን፤ አድራሻዋን፤የአምልኮ እና የሥርዓት መፈጸሚያ የሆኑ ንዋያ ቅዱሳትንና አልባሳት እንዲሁም መጻሕፍት መገልገል የማይችሉ መሆኑ ታውቆ ይህንን ጉዳይ በየደረጃው ያሉ መንግሥታዊ አካላት እና የቤተ ክርስቲያኒቱ  የሥራ ኃላፊዎች ተከታትለው እንዲያስፈጽሙ ቅዱስ ሲኖዶስ የወሰነ ሲሆን በተጨማሪም ይህን ውሳኔ ተላልፈው በሚገኙ ማናቸውም ግለሰቦች እና ተቋማት ላይ ተገቢውን ሕግ አግባብ ተከትሎ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ዓለማት የሚያስፈጽም ዓለም አቀፍ እና ሀገር አቀፍ የሕግ ባለሙያዎች በመመደብ ተገቢውን ሁሉ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በኩል እንዲፈጸም ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

9. በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ የሚገኙ መንግስታዊም ሆነ መነግስታዊ ያልሆነ ተቋማት፤ አኃት አቢያተ ክርስቲያናት፤ የምሥራቅ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት፤ የሮም ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እና ሌሎች አብያተ ክርስቲያናት፤ የዓለም አቢያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት፤ የመላው አፍሪካ አብያት ክርስቲያናት ጉባዔ እና ሌሎች የአብያተ ክርስቲያናት እና የሃይማኖት ጉባኤዎች በሙሉ እነዚህ የተወገዙት ግለሰቦች የኢትዮጵያ ኦርቶደክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የማይወክሉ እና ምንም አይነት የሥራ ግንኙነት የሌላቸው መሆኑ ታውቆ ማናቸውም ግንኙነት በቤተ ክርስቲያኑቱ ስም እንዳያደርጉ በጽሑፍ አንዲገለጽ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
2024/09/29 15:28:45
Back to Top
HTML Embed Code: