Telegram Web Link
ከዛሬው የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርስቲ ተመራቂዎች መሓል የምንኩስና ሕይወቷን በመንፈሳዊ እውቀት ለማጠንከር በማዕረግ የተመረቀች መነኮሳይት።
ሲኖዶስን እንደ መጅልሱ የጎሣ ማድረግና ከቀኖና ውጭ የፖለቲካ አገልጋይ ማድረግ ከትልቁ የዓለም አቀፍ ሤራ ጋር ትሥሥር ይኖረው ይሆን? ያድምጡት https://fb.watch/lGDtZnbMNY/?mibextid=WPBo4E68yvx9pgQK
እማሆይ ዜና ማርያም 💚💛

በመንፈሳዊ ትምህርት የቅኔ መምህርነት አስመስክረዋል ፣ አቋቋም ተምረዋል ፣ በረካታ የቤተክርስቲያን ትምህርቶችን ተምረዋል። ከልጅነት እስከምንኩስና በርካታ የችግር ጊዜዎችን አልፈዋል። እማሆይ ዜና ማርያም በዲማ ጊዮርጊስ ቅኔ ተምረዋል ፣ በባህርዳር የአብነት ትምህርት ቤት አቋቋም ተምረዋል። በዘመናዊ ትምህርት የመጀመርያ ድግሪ ተምረው ተመርቀዋል ፣ በዚህ አመት በ2014 ደግሞ በከፍተኛ ማዕርግ የማስተር ድግሪያቸውን ይዘዋል። በአሁኑ ሰዓት በቅድስት ሰላሴ መንፈሳዊ ዩኒበርስቲ በማስተማር ላይ ይገኛሉ።

እማሆይ ዜናማርያም በልጅነታቸው ከሰንበት ትምህርት ቤት የጀመራቸው የእግዚአብሔር ቃልና ለእግዚአብሔር ራስን የመስጠት ፍቅር እንዲሁም በእግዚአብሔር ቃል የመጠራት ጥበብ በሴትነታቸው የደረሰባቸውን ባህላዊና ቤተሰባዊ ጫና በትዕግስትና በእግዚአብሔር ጥበብ በማለፍ ለዚህ ክብር የበቁ እናት ናቸው። በታላቁ ገዳም በደብረ ሊባኖስ የምንኩስናን ተቀብለው የመንፈሳዊ ህይወት ሰባኪ ሆነው ቀጥለዋል።

እማሆይ ዜናማርያም ለሴቶች የሚከብድ የሚመስለውን ህይወት ኖረው አሳይተዋል እየኖሩትም ነው። የዕማሆይ ፅናታቸውና እምነታቸው ገራሚ ነው። በወጣትነታቸው የገቡበትን መንፈሳዊ ህይወትና ውጣ ውረድ አልፈው በሁለት የተሳለ ሰይፍ የመሆን ምስጢርን አሳይተዋል።
+++ ኦርቶዶክሳውያን ለቅዱሳን ለምን ይዘምራሉ? +++

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን ካሏት ብዙ መገለጫዎች አንዱና ዋነኛው ‹ምስጋና የሚገባውን› እግዚአብሔርን ሳታቋርጥ የማመስገን አገልግሎትዋ ነው፡፡ እግዚአብሔርን ለማመስገን ለዓመታት የዜማ ስልት ተምረው የተመረቁ የስብሐተ እግዚአብሔር ሊቃውንት ያሏት ይህች ቤተ ክርስቲያን ዝማሬዋ ፣ ማሕሌትዋና ቅዳሴዋ የሃያ አራት ሰዓታት ጊዜ የማይበቃው ፣ ለሰዓት ሲባል በንባብ እየተባለ ፣ ዜማው እያጠረ የሚተው በመሆኑ ፀሐይ በማይጠልቅበት በዘላለማዊው መንግሥት ለማመስገን ዝግጁ ሆና የምትጠባበቅ ቤተ ክርስቲያን ያሰኛታል፡፡ ከዚህ እንደ ባሕር ጥልቅ ከሆነው ስብሐተ እግዚአብሔር ጋር የእግዚአብሔር ቅዱሳንንም በሰፊው ታመሰግናቸዋለች፡፡

በዚህች አጭር ጽሑፍ ምስጋና የባሕርይ ገንዘቡ የሆነው እግዚአብሔር ከሆነ ፍጡራን ለሆኑ ለቅዱሳን ሰዎች ፣ ለቅዱሳን መላእክትና ለድንግል ማርያም የሚዘመረው መዝሙርና የሚቀርበው ውዳሴ ምን ያህል ተገቢ ነው? ለቅዱሳን መዘመር ከመጽሐፍ ቅዱስ አንጻር ተገቢ ነው ወይ? የሚለውን እንመለከታለን፡፡

ይህንን ጥያቄ ለመመለስ ሳስብ በመጽሐፍ ቅዱስ ወደር ያልተገኘለትን ዘማሪ ለመጠየቅ ወደድኩ፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ በስሙ መቶ አምሳ መዝሙራት የተጻፉለት ፣ ራሱ ሰማኒያ ሰባት መዝሙራትን የዘመረና በሥሩ ያሉ መዘምራን ደግሞ አብረውት ብዙ መዝሙራትን የዘመሩበት የዝማሬ ባለ ጠጋ ንጉሥ ዳዊትን ‹‹እውነት ለፍጡራን ምስጋና ይገባል ወይ?›› ብዬ ልጠይቀው አስቤ ወደ መዝሙረ ዳዊት ገሰገስኩ፡፡

ፈጣሪ እንደ ልቤ ያለው ዳዊት የልቤን ማን እንደነገረው እንጃ የእኔን ጥያቄ ለመመለስ ቸኩሎ ጠበቀኝ፡፡ ገና የመጀመሪያው መዝሙሩን ‹‹ምስጉን ነው በክፉዎች ምክር ያልሔደ ፣ በኃጢአተኞች መንገድ ያልቆመ ፣ በዋዘኞች ወንበር ያልተቀመጠ›› ብሎ ጀምሮት አገኘሁት፡፡ (መዝ. 1፡1) ዳዊት በዚህ ዝማሬው ‹ምስጉን ነው› ያለው ፈጣሪን ነው ወይንስ ፍጡርን? እግዚአብሔርን ነው እንዳልል ‹በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል› ይላል፡፡ ስለዚህ ዳዊት ዝማሬውን የጀመረው ‹በክፉዎች ምክር ያልሔደ ፣ በኃጢአተኞች መንገድ ያልቆመ ፣ በዋዘኞች ወንበር ያልተቀመጠ›ን ሰው በማመስገን ነው፡፡

ወደ መዝሙሩ ስገባ ዳዊት ምስጋናውን ሰፋ አድርጎ ‹ለቅኖች ምስጋና ይገባቸዋል› ‹ለችግረኛ የሚያስብ ምስጉን ነው› ‹አንተ የመረጥከው በአደባባዮችህም ለማደር የተቀበልከው ምስጉን ነው› ‹እግዚአብሔር አምላኩ የሆነ ሕዝብ ምስጉን ነው› ‹እልልታን የሚያውቅ ሕዝብ ምስጉን ነው› ብሎ ከግለሰቦች አልፎ ሕዝብን ሲያመሰግን አገኘሁት፡፡ ከሁሉ ያስደነቀኝ ግን ‹‹መተላለፉ የቀረችለት ፣ ኃጢአቱ የተከደነችለት ሰው ምስጉን ነው›› የሚለው ዝማሬው ነው፡፡ ኃጢአቱን እግዚአብሔር ይቅር ያለውና በደሉን ፈጣሪ የሸፈነለት ሰው በታላቁ ዘማሪ በዳዊት አንደበት መዝሙር ከተዘመረለት በሃሳብዋ እንኳን ኃጢአትን ስላልሠራችው ድንግል ምን ዓይነት መዝሙር ይዘመርላት ይሆን?

ንጉሥ ዳዊት ሕይወት ላላቸው ሰዎች ብቻ ዘምሮ አላቆመም ፤ ለማትናገረውና ከእንጨት ከድንጋይ በሰው እጅ ለተሠራችው ከተማው ለጽዮን የእግዚአብሔር ማደሪያ በመሆንዋ ዝማሬን አዝንሞላታል፡፡
‹‹እግዚአብሔር ጽዮንን መርጦአታል ፤ ማደሪያው ትሆነው ዘንድ ወድዷታል፡፡ እንዲህ ሲል ይህች ለዘላለም ማረፊያዬ ናት ፣ መርጫታለሁና በእርስዋ አድራለሁ››
‹‹እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወድዳቸዋል ፤ የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ በአንቺ የከበረ ነገር ይባላል››
‹‹በባቢሎን ወንዞች አጠገብ በዚያ ተቀመጥን ፤ ጽዮንን ባሰብናት ጊዜ አለቀስን ፤ የማረኩን በዚያ የዝማሬን ቃል ፈለጉብን ፤ የእግዚአብሔርን ዝማሬ እንዴት በባዕድ ምድር እንዘምራለን? ኢየሩሳሌም ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ ፤ ባላስብሽ ምላሴ ከጉሮሮዬ ጋር ይጣበቅ ፤ ከደስታዬ ሁሉ በላይ ኢየሩሳሌምን ባልወድድ›› ብሎ ስለ ቅድስቲቱ ከተማ ሲዘምር አገኘሁት፡፡ ከራሱ አልፎም በዙሪያው ላሉት በመዝሙሩ እንዲህ ሲል ጥሪ አቀረበ ‹‹ጽዮንን ክበቧት በዙሪያዋም ተመላለሱ ፤ ግንቦችዋን ቁጠሩ ፤ በብርታትዋ ልባችሁን አኑሩ ፤ ለሚመጣው ትውልድ ትነግሩ ዘንድ›› የእግዚአብሔር ከተማ ጽዮንን ለማይወድዱ ደግሞ በመዝሙሩ ‹‹ጽዮንን የሚጠሉ ሁሉ ይፈሩ ወደ ኋላቸውም ይመለሱ›› ብሎ ዘምሮአል፡፡

ዳዊት ስንት ኃጢአተኛ ሲራኮት ለሚውልና ለሚያድርባት ከተማ የእግዚአብሔር ማደሪያው እንድትሆን እንደ መረጣት አውቆ እንዲህ ሲዘምር ማየቴ ‹መንፈስ ቅዱስ ይጸልልሻል የልዑል ኃይልም ያድርብሻል› ለተባለችዋ ቅድስት ድንግል ማርያም ‹የጌታዬ እናት ፣ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ፣ የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ› ብዬ ለመዘመር እንድችል ኃይል የሚሠጥ ሆነልኝ፡፡ ባቢሎን በተባለ በኃጢአት ሥፍራ ሆኜ ድንግልን ባሰብኳት ጊዜ እንዳለቅስና ‹‹ድንግል ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ ባላስብሽም ምላሴ ከጉሮሮዬ ይጣበቅ›› ብዬ እንድዘምርላት ድፍረት ሠጠኝ፡፡

የዳዊት ሲደንቀኝ ልጁ ሰሎሞን ደግሞ ‹ከመዝሙራት ሁሉ የሚበልጥ የሰሎሞን መዝሙር› (መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን) በተባለ ውብ ድርሰቱ ከአባቱ የባሰ የመዝሙር ቅኔን ሲቀኝ አገኘሁት፡፡ በዚህ ዝማሬው ላይ በፍቅረኛሞች መካከል የሚደረግን የፍቅር ቃል ልውውጥ ሰበብ አድርጎ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ሙሽራው ስላደረጋትና እርስዋም ‹ውዴ› ብላ ስለምትጠራው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ውብ ስንኞችን ጽፎ አገኘሁት፡፡

በዚህ ዝማሬው ላይ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ውድዋ የሆነውንና ነፍስዋ የወደደችውን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስን ስትፈልገው ፣ በከተማ የሚጠብቁ ጠባቂዎች የተባሉ መላእክትን ስትጠይቅ ፣ ቤተ ክርስቲያን በቀዳም ስዑር የምትዘምረው ‹እርሱ እስኪፈልግ ድረስ ፍቅርን እንዳታስነሡት› ብላ አልጋ በተባለ መቃብር ስለ ሰው ልጅ ፍቅር የተኛውን ክርስቶስን እርሱ ወድዶ ሞትን ድል አድርጎ እስከሚነሣ በእምነት እንዲጠብቁ ስትናገር ፣ ውዴ ወደ ገነቱ ወረደ ብላ ነፍሳትን ይዞ ወደ ገነት ስለ መውጣቱ ስትዘምር በሰሎሞን ዝማሬ ውስጥ አገኘሁ፡፡ በዚህ ዝማሬ ላይ ሙሽራው ስለ ሙሽራዪቱ ቤተ ክርስቲያን ቅድስናና ውበት ፣ ጡቶችዋ ስለተባሉ የቃሉ ወተት ስለሚፈስስባቸው ብሉይና ሐዲስ ኪዳን ማማር ፣ ድንቅ ቅኔ ሲዘምር አገኘሁት፡፡

በሰሎሞን መዝሙር ላይ ‹ወዳጄ ሆይ ነይ ውበቴ ሆይ ተነሽ› ‹ወዳጄ ሆይ ሁለንተናሽ ውብ ነው ነውርም የለብሽም› የሚሉት ውብ ዝማሬዎች ለፍጡር እንጂ ለፈጣሪ የቀረቡ ምስጋናዎች አይደሉም፡፡ ለዚህም ነው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይህንን ውብ ዝማሬ ሁለተናዋ በቅድስና ለተዋበችው ድንግል ማርያም መዝሙር አድርጋ የምትዘምረው፡፡ አባቱ ዳዊት ‹ልጄ ሆይ ስሚ እዪም ጆሮሽን አዘንብዪ› ብሎ ለጠራት ድንግል ልጁ ሰሎሞን ‹እኅቴ ሙሽራ ሆይ› ብሎ መዘመሩን የምንቀበለውም ከዚህ ተነሥተን ነው፡፡

ቅዱሳንን ማመስገን በዳዊትና በሰሎሞን አላበቃም ፤ መላእክትም ለቅዱሳን ሲዘምሩ ታይተዋል፡፡ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ‹ጸጋ የሞላብሽ ሆይ ደስ ይበልሽ አንቺ ከሴቶች ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ› ብሎ ለድንግል ማርያም ያቀረበው ሰላምታ ‹ከእንዴት ውለሻል› ሰላምታ ያለፈ ምስጋና አይደለምን? ለዘካርያስ ‹አንተ ከካህናት ተለይተህ የተባረክህ ነህ› ያላለው ይህ መልአክ ለድንግል ለይቶ ያቀረበው በእርግጥም ምስጋና ነበር፡፡ ስለሆነም የገብርኤልን ሰላምታ ተውሰን ድንግሊቱን ለዘወትር እናመሰግናታለን፡፡ ገብርኤል ያቀረበውን እኛ ማቅረብ አያስፈልገንም የሚሉ ሰዎች ይኖራሉ፡፡
ሆኖም ድንግሊቱ ‹ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ያመሰግኑኛል› ብላ መናገርዋ ለማመስገናችን ምክንያት ነው፡፡ ‹ትውልድ ሁሉ› አለች እንጂ ሰው ሁሉ አላለችምና ከየትውልዱ የማያመሰግኗት ቢገኙ አይደንቅም ፤ ከእኛ የሚጠበቅብን እንደ ኖህ ‹በትውልዳችን ጻድቅ› ሆኖ መገኘት ብቻ ነው፡፡ መልአኩ ገብርኤል ‹ደስ ይበልሽ› ቢላትም እኛ ‹ደስ ይበልሽ› አንላትም የሚሉ ሰዎች መላእክት ‹ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ› የሚሉትን እግዚአብሔርም ‹ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ› ለማለት እንዴት ፈቃደኞች ሊሆኑ ይችላሉ?

ለቅዱሳን የሚቀርበው ምስጋና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ያለው መሆኑን የምንደመድመው መድኃኔዓለም ክርስቶስ ራሱ ለመጥምቁ ዮሐንስ የተናገረው ምስጋና ነው፡፡ ‹‹ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይን? አዎን እላችኋለሁ ከነቢይም የሚበልጠውን … እላችኋለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ ማንም የለም›› (ሉቃ. 7፡26-28) ከዚህ በላይ ምስጋና ከየት ይመጣል? በዜማ መሆኑ ከሆነ ችግሩ በንባብ እንለዋለን።

የመጥምቁ ምስጋና በቅዱስ ገብርኤልም አንደበት ተነግሮ ነበር፡፡ ቅዱስ ገብርኤል የዮሐንስን ልደት ሲገልጥ ‹‹በመወለዱ ብዙዎች ደስ ይላቸዋል›› ብሎ ነበር ፤ ወደ መዝሙር ሲለወጥ ‹ዮም ፍስሓ ኮነ በእንተ ልደቱ ለዮሐንስ› እንደማለት ነው፡፡

አባቱ ዘካርያስ ደግሞ ‹‹አንተ ሕፃን ሆይ የልዑል ነቢይ ትባላለህ›› ብሎ ነበር ይህም ‹ወአንተኒ ሕፃን ነቢየ ልዑል ትሰመይ ፤ አርኩ ለመርአዊ ትሰመይ›› የሚለው መዝሙር ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ለቅዱሳን ስትዘምር ቃላትና ግጥም የምትዋሰው ከመጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡

‹‹ሐውፅ እምሰማይ ተክለ ሃይማኖት ፀሐይ›› (ፀሐይ ተክለ ሃይማኖት ሆይ ከሰማይ ሆነህ ጎብኝ)
የሚል መዝሙር ቢዘመር ‹‹ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ያበራሉ›› የሚለውን የተስፋ ቃል ይዞ ነው፡፡ (ማቴ. ፲፫፥፵፫)

‹‹ጊዮርጊስ ኃያል ኮከበ ክብር›› ተብሎ ቢዘመር ‹‹ብዙዎችን ወደ ጽድቅ የሚመልሱ እንደ ከዋክብት ለዘላለም ይደምቃሉ›› የሚለውን ይዞ ነው፡፡ (ዳን. 12፡3)

‹‹አቡነ አረጋዊ ሆይ ነፍሴ ዛሬ በአንተ ፊት የከበረች ትሁን!›› ‹‹ትክበር ነፍስየ በቅድሜከ ዮም ፤ ወባርከኒ አባ አረጋዊ›› ተብሎ ሲዘመር ብንሰማ አንድ የመቶ አለቃ በነቢዩ ኤልያስ ፊት ተንበርክኮ ‹‹የእግዚአብሔር ሰው ሆይ ነፍሴ አሁን በፊትህ የከበረች ትሁን›› ብሎ ካቀረበው ልመና ተወስዶ ነው፡፡ (2ነገሥ. 1፡13)

በአንዳንድ ሥፍራ ለቅዱሳን በሚቀርቡ ምስጋናዎች ላይ ለፈጣሪ የቀረቡ የምስጋና ቃላት ተወስደው ለቅዱሳን ሲቀርቡ ይታያል፡፡ ይህንን የሚያዩ ሰዎች ቅዱሳን የተመለኩ ፣ የፈጣሪ የባሕርይ ክብሩ ለቅዱሳን የተሠጠ መስሏቸው ይተቻሉ፡፡ በዚህ ምክንያት ለቅዱሳን በሚዘመሩ መዝሙራት ሁሉ ላይ የሚታረም ነገር አያጡም፡፡ ሆኖም ይህንን ዓይነት እርማት ላድርግ ብሎ የሚነሣ ሰው መጽሐፍ ቅዱስንም ማረም ሊኖርበት ነው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ ለእግዚአብሔር የተነገረን ቃል ለቅዱሳን ሲሠጥ በተደጋጋሚ እናገኘዋለን፡፡

ጥቂት ምሳሌዎችን እንመልከት ፡-

‹‹ገብረ መንፈስ ቅዱስ የዓለም ብርሃን ናቸው›› ሲባል ‹‹የዓለም ብርሃን ክርስቶስ ብቻ ነው›› ብሎ የሚቃወም ቢኖር ራሱ ክርስቶስ ለሐዋርያቱ ‹‹እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ ፤ ብርሃናችሁ በሰው ፊት ይብራ›› ብሏል፡፡ የእርሱ ብርሃንነት የባሕርይው የቅዱሳን ብርሃንነት ግን ከእርሱ የተሠጠ ነው ብለን እንከፍለዋለን እንጂ የቅዱሳንን ብርሃንነት አንክድም፡፡ (ማቴ. 5፡14)

አንዳንድ ምእመናን ስለ ድንግል ማርያም አማላጅነት ሲመሰክሩ ‹‹ለእመቤቴ የሚሳናት ነገር የለም›› ሲሉ የሚሰማ ሰው ራሱን እየነቀነቀ ‹የእኛ ሰው Bible ላይ ብዙ ይቀረዋል› ብሎ ሊመጻደቅ ይችላል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን የሚያውቅ ከሆነ ግን ‹‹እምነት ቢኖራችሁ የሚሳናችሁ ነገር የለም›› የሚለውን የጌታ ቃል ፣ ‹‹ኃይልን በሚሠጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ›› የሚለውን የጳውሎስ ቃል በሰማበት ጆሮው ‹ያመነችው ብፅዕት› ‹የልዑል ኃይል ያደረባት› ድንግል ‹የሚሳናት የለም ሲባል ከመቆጣት ይልቅ ለምእመናን የተሠጠውን እምነትና ማስተዋል ያደንቃል፡፡ (ማቴ. 17፡20 ፣ ፊል. 4፡13 ፣ ሉቃ.1፡35፣45)

ለእግዚአብሔር የተነገሩ ቃላት ለቅዱሳን ተደግመው ብናገኛቸው እንኳን ትርጉሙን እንረዳለን እንጂ የእግዚአብሔርን ክብር ቅዱሳን ወሰዱ አንልም፡፡ ለምሳሌ ጌታ መጥምቁ ዮሐንስን ‹የሚያበራ መብራት ነበር ፤ በብርሃኑ ደስ ሊላችሁ ወደዳችሁ› ሲለው ወንጌላዊው ደግሞ ‹‹እርሱ ስለ ብርሃን ሊመሰክር መጣ እንጂ ብርሃን አልነበረም›› ብሎታል፡፡ የማንን እንቀበል? የጌታችንን ንግግር ወይስ የወንጌላዊውን? ዮሐንስ ብርሃን ነው ወይንስ አይደለም? መልሱ ግልጥ ነው ዮሐንስ ብርሃን ነው ፤ የዮሐንስ ብርሃንነት ግን ከክርስቶስ ብርሃንነት ጋር ሲተያይ የሻማና የፀሐይ ብርሃን ያህል ነውና ብርሃን አልነበረም ተብሏል ብለን እንረዳዋለን፡፡(ዮሐ. 1፡8 ፤ 5፡35)

የእግዚአብሔርን ክብር አስጠብቃለሁ ብሎ የትርጉም ልዩነቱን ሳይረዳ ለቅዱሳን የሚቀርብን ምስጋና የመተቸት ዝንባሌ ያለው ሰው ግን ይህ አካሔዱ ከመጽሐፍ ቅዱስ የሚያጣላው ነው፡፡ ሰሞኑን አንዳንድ ሰዎች ‹የአዳም ፋሲካው ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ› የሚለውን ቃል በመጥቀስ እንዴት ድንግል ማርያም ፋሲካ ትባላለች ‹ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአል› ይል የለምን እንዳሉ ሰማን፡፡ ስለ እንክርዳድ ማውራት እንክርዳድን ዝነኛ እንጂ ስንዴ ስለማያደርገው ተናጋሪዎቹን ትተን ጉዳዩን እናስተውለው፡፡

ወደ ሌላ ዝርዝር ሳንገባ አንድ ጥያቄ እናንሣ ፤ ክርስቶስ ፋሲካ ነው ወይንስ የፋሲካ በግ? ፋሲካ የሚባለው በዓሉ ነው? ወይንስ በጉ ነው? የታረደው በዓሉ ነው? ቢባል ምን ይመለሳል? "ፋሲካን እረድ" ሲል በጉን ነው (2ዜና 35:5)፣ "ይህ ፋሲካ ለእግዚአብሔር ተፈሰከ" ሲል በዓሉን ነው። (2ነገሥ 23:23)

ፋሲካ ሲል በዓሉን ከሆነ መሻገሪያ ፣ ደስታ ማለት ነውና ለድንግል ማርያምም ሊነገር ይችላል፡፡ ‹ታርዶአል› የተባለው ግን በጉን ነውና እመቤታችንን እመ በግዑ (የበጉ እናት) እንጂ የታረደችው በግ ብለናት እንደማናውቅ ግልጥ ነው፡፡ ጨርሶ ለክርስቶስ የተነገረ ቃል ለእርስዋ ለምን ይደገማል? ከሆነ ደግሞ እስቲ የቅዱስ ጳውሎስን ንግግር እንመልከት፡-

ቅዱስ ጳውሎስ በገላትያ 2:20 ላይ ፡- ‹‹ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ›› ብሏል፡፡ አልፎ ተርፎም ‹‹እኔ ለዓለም ከተሰቀልሁበት ከክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ›› ብሏል፡፡ (ገላ. 6፡14)

የዚህ ንግግር ትርጉም ምንድን ነው? ቅዱስ ጳውሎስ ከክርስቶስ ጋር ተሰቅሎ ነበር ማለት ነው? የተሰቀለው በቀኙ ነው የግራው?"ለዓለም ተሰቀልኩ" እንዴት አለ? እውን ለዓለም የተሰቀለው ጳውሎስ ነውን? ክርስቶስ አይደለምን? የፋሲካው ሲገርምህ ለዓለም ተሰቅዬአለሁ ያለ መጣ? ጳውሎስ የተሰቀለውን የክርስቶስን ክብር መሸፈኑ ነውን?

እንደዚያ እንዳንል ደግሞ ራሱ ጳውሎስ ‹‹ጳውሎስ ስለ እናንተ ተሰቅሎአልን? እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን›› ብሎ አሳርፎናል፡፡ (1ቆሮ 1፡13) ስለዚህ መተርጎም መብራራት አለበት እንጂ ቃሉ ተመሳሰለ ተብሎ አይብጠለጠልም። ጫማ ይስተካከላል እንጂ እግር አይስተካከልም እንደሚባለው መስተካከል ያለበት የእኛ አረዳድ እንጂ የመጽሐፉ ቃል አይደለም።
ሐዋርያው ከክርስቶስ ጋር ተሰቅያለሁ ሲል የክርስቶስን የመከራ መንገድ ተከትያለሁ ፣ የመከራው ተሳታፊ በመሆን የክብሩ ተካፋይ እሆናለሁ ሲል ነው። "ለዓለም ተሰቅልኩ" ያለው ደግሞ በክርስቶስ መከራ በማመኔ ለዓለማዊ የኃጢአት ሥራ ሙት ሆኜአለሁ ማለቱ ነው ብለን እናብራራለን እንጂ ጳውሎስ የጌታን ክብር ተጋፋ አንልም፡፡

ቅዱሳንን የምናመሰግናቸው የእግዚአብሔር ስለሆኑና ነቢዩ እንዳለው "እግዚአብሔርም በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ስለሆነ ነው" ሥዕሉ ሲደነቅለት የሚበሳጭ ሠዓሊ እንደሌለ ሁሉ የእርሱ ድንቅ ሥራዎች ሆነው ፣ እርሱን አገልግለው ሲወደሱ ፈጣሪን ደስ ይለዋል እንጂ አያዝንም። ጠርሙስ ሰብራ ሽቱን በእግሩ ላይ ላፈሰሰለች ሴት "ወንጌል በሚነገርበት ሥፍራ ሁሉ ያደረገችው ነገር ለእርስዋ መታሰቢያ እንዲሆን ይነገራል" ብሎ የተናገረ ጌታ አንገታቸው ተሰብሮ ደማቸውን ስለ ስሙ ስላፈሰሱ ቅዱሳን በዓለም ሁሉ ቢነገርና ቢዘመር የሚከለክል አይደለም። (ማቴ 26:13)

ምስጋና እንኳን ለቅዱሳን በሃይማኖታችን ከጸናን ለእኛም ለደካሞቹም አልተከለከልንም ፣ እንዲህ ተብሎ ተጽፎአልና :–

"ሥር ሰዳችሁ በእርሱ ታነጹ፥ እንደ ተማራችሁም በሃይማኖት ጽኑ፥ ምስጋናም ይብዛላችሁ" ቆላስ 2: 7

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
[email protected]
ሚያዝያ 19 2010 ዓ ም
አዲስ አበባ
ቤተክርስቲያን ተዘጋባቸው

ቤተክርስቲያን ለትግራይ ሀገረስብከት ጳጳሳት ደሞዛቸውን በየወሩ ትልካለች፣ ለተፈጠረው ጥፋትም በይፋ ይቅርታ ጠይቃለች፣ ለደረሰው ጉዳትም የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጋለች።

ቅዱስነታቸው መቀሌ ኤርፖርት ሲደርሱ አንድም ጳጳስ ሊቀበላቸው ግን አልፈለገም ይባስ ብሎም የሚመሩትን ቤተክርስቲያን እንዳይሳለሙ ቤተክርስቲያኒቱን ቆልፈው ጠፍተዋል። ቅዱስነታቸው ከውጭ ብቻ ተሳልመው እንዲመለሱ ተደርገዋል።

እንአዳነች አበቤን አጨብጭበው የተቀበሉ የትግራይ ጳጳሳት ለቅዱስነታቸው ግን ፊት ነስተዋል። የትግራይ አባትች መቼ ይሆን ወደ ራሳቸው የሚመለሱት???
"የምድር ሐጥአን ሁላችሁ ወደ ቅድስት ድንግል ኑ፡ በእርሷ ስጦታ ፃድቃን ትሆኑ ዘንድ ልብሳችሁም ያደፈ ሁላችሁ ወደዚህች ቅድስት ምንጭ ኑ፡ የይቅርታ ዉሃ ወደ ምታፈስ፤ ልብሳችሁንም በልጇ ደም እጠቡ፡ ለሰማያዊ ሙሽርነት ዝግጁ ትሆኑ ዘንድ፡፡ ድውያነ ስጋ ሁላችሁ ወደ ድንግል ኑ፡ በፀሎቷ ሃይል እንድትፈወሱ፡፡ የእውቀት ድሆች ሁላችሁ ኑ፡ የእውቀት ምንጭን ከእሷ ትቀዱ ዘንድ፡ ያማረ የተወደደውን የጥበብ ምክር ታገኙ ዘንድ”
(አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ - አርጋኖን)
ብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ

እነሆ ሐምሌ 5 የብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ የዕረፍታቸው መታሰቢያ ነው። ቅዱስ ጴጥሮስ ከዐሣ አስጋሪነት፣ ቅዱስ ጳውሎስ ከአሳዳጅነት የተጠሩ፣ በኋላም ዓለምን በወንጌል ብርሃን ያበሩ እና ክርስትናን ያስፋፉ ናቸው።
ስለ ክርስቶስ ብዙ መከራ ተቀብለውም የሰማዕታትን አክሊል ተቀዳጅተዋል። ቅዱስ ጴጥሮስ በጠላቶቹ እጅ ወድቆ በመስቀል ሊሰቅሉት ሲሉ፣ እንደ ክርስቶስ ወደ ላይ እሰቀል ዘንድ አይገባኝምና ዘቅዝቃችሁ ስቀሉኝ በማለት ቁልቁል ተሰቅሏል። ቅዱስ ጳውሎስም ስለ ሃይማኖቱ መከራን ተቀብሎ አንገቱ ተቀልቶ አርፏል።
በረከታቸው ይድረሰን!
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ሐምሌ 5 እና 6 ቀን 2015 ዓ/ም አስቸኳይ ስብሰባ ማካሄዱ የታወቀ ሲሆን ይህን ከስብሰባው መጠናቀቅ በኃላ መግለጫ ሰጥቷል።

ቅዱስ ሲኖዶስ በመግለጫው :-

በትግራይ በሚገኙ አህጉረ ስብከት የተመደቡ አባቶች የቅዱስ ሲኖዶስ የሰላም ጥሪን ቸል ከማለት ባሻገር ሐምሌ 9 እናደርገዋለን ያሉት የኤጲስ ቆጶስነት ምርጫ ሕገ ቤተክርስቲያንን ያልተከተለ መሆኑን ገልጾ የሚመለከታቸው አካላት ሂደቱን በማስቆም ከቤተክርስቲያን ጎን እንዲቆሙ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን አቅርቧል።

ይደረጋል የተባለው የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን አንጻር ተገቢ ያልሆነ የቤተ ክርስቲያንን ማዕከላዊነት የሚጥስ፣ የቤተ ክርስቲያንን አንድነት የሚጎዳና በጦርነት የተጎዳውን ሀብት ንብረቱ የወደመበትን ገዳማቱና አብያተ ክርስቲያናቱ የተጎዱበትን ሕዝብ የማይጠቅም ተገቢነት የሌለው በመሆኑ እንዲቆም ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

በትግራይ ክልል ተከስቶ የነበረውን ችግር የፌዴራል መንግሥትና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ችግሩን በውይይት የፈቱት መሆኑ እየታወቀ የሰላም ባለቤት የሆነችው ቤተ ክርስቲያን እስካሁን ሰላም መፈለጓ ያልተቋረጠ ቢሆንም አለመሳካቱ የሚያሳዝን በመሆኑ ለሰላም የሚደረገው ጥረት ዘላቂ መፍትሔ እስከሚገኝ ድረስ የማይቋረጥ መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ገልጿል።

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ክቡር አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት እንዲሁም የፌዴራልና የክልሉ መንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እየተደረገ ያለውን ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ያልተከተለ የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ እንዲያስቆሙ ብሎም ሰላም ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት በመደገፍ ችግሮቹ በውይይት እንዲፈቱ መንግሥታዊ እገዛ በማድረግ የውይይት መድረክ እንዲያመቻቹ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጥሪውን አቅርቧል።

ቅዱስ ሲኖዶስ፤ " በመላው ዓለም የምትገኙ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና ሕዝበ ክርስቲያን እናት ቤተ ክርስቲያናችሁ ያስተላለፈችውን የሰላም ጥሪ ተግባራዊ ሆኖ አንድነቷ ጸንቶ ይኖር ዘንድ በጸሎት ተግጋችሁ ከቤተ ክርስቲያናችሁ ጎን እንድትቆሙ " ሲል ጥሪ አስተላልፏል።
ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ። ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ። መራርነትና ንዴት ቁጣም ጩኸትም መሳደብም ሁሉ ከክፋት ሁሉ ጋር ከእናንተ ዘንድ ይወገድ።

(ኤፌሶን 4፥29-31)
2024/09/28 11:23:07
Back to Top
HTML Embed Code: