Telegram Web Link
"…እንዴ፣ እንዴ ኧረ በማርያም በአዛኝቷ፣ ደጀኔ ቶላም (ደጁም) ጳጳስ ሊሆን ነው ማለት ነው…? አዛኜን በፍፁም ይሄማ አይሆንም። ነውር ነው። 😂😂። ወይ 3ሚልዮን ብር… ? አባ ሳዊሮስና አባ ሩፋኤል ፈጣሪ ብድራቱን ይክፈላችሁ።

• እንግዲህ ሊጀምረኝ ነው።፣
"…የአይጥ ምስክሯ…😂😂

"…ኦቦ ተስፋዬ ይሄ አምቡላ መጋፊያ አረቄ ቤት አይደለም። እንከባበር። ይሄ የጋራ ሃይማኖታችን የከበረ የቅድስና ሥነ ሥርዓት የሚፈጸምበት ሃይማኖታዊ ጉዳይ ነው። ተጣድፎ ምስክርነትህን እዚያው በጃምቦ ቤት አድርገው። ምዕራብ አሩሲ አለፈላት ይላል እንዴ ደግሞ እንዲያውም ጉድ ፈላባት በል እንጂ አባው።

"…በዚህ የማይረባ የጎጥ ኔትወርክ ውስጥ ያላችሁ በሙሉ በሙሉ ከሀ እስከ ፐ የቅርብ ሰዎቼንም ሆነ የሩቅ ወዳጆቼን በሙሉ በአስቸኳይ አቁሙ። እኔ ዘመዴ አልፋታችሁም። ሸዋን በዚህ መልክ አትጠቅሙትም። ሸዋም በዚህ መልክ አይከብርም። ሌሎች ሰዎች ጠፍተው ነው…?

"…ምንአልባትም የማከብርዎት አረጋዊው ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስም በዚህ ጉዳይ ቢተዉ ነው የሚሻለው። ኧረ ደስ አይልም በማርያም። ገና ለገና… ብቻ ደስ አይልም። በቃ መጠጡ ነው ችግሩ እሱን እንዲተው እንመክረዋልን ይለኛል እንዴ በማርያም። አዛረ ምን ጉድ ነው።

"…ደጀኔ ቶላም በማኅበራዊ ሚድያው ላይ የማኅበረ ቅዱሳን አንዳንድ የሸዋ ጎጠኞች፣ እንደ ተስፋዬ ሞሲሳ ዓይነት የአምቡላ ጋን ስር ሰባኪዎች በየፌስቡኩ ስለመሰከሩ፣ ስለተጯጯሁልህ እንዳትኮፈስ። አይገባኝም አይሆንም በል። ይሄን ስታይ ቢያንስ የቀሲስ አብርሃምስ እህት ምን ትላለች አይባልም እንዴ…?  ቀሲስ በላይ መኮንንም እኮ የ3 ልጆች አባት ነው። እንዲያ ከሆነ እሱስ የማይሾም ለምንድነው…?

• አባ ሩፋኤል
• አባ ሕርያቆስ
• አባ ሳዊሮስ
• እና ሌሎችም በዚህ ጉዳይ ላይ ወጥራችሁ ከሸዋ ጳጳስ መብዛት አለበት ብላችሁ የተሳተፋችሁ በሙሉ በየሄዳችሁበት አንገታችሁን ከመድፋታችሁ በፊት በቶሎ ነገርየውን አስተካክሉ። ሌሎቹም ላይ እንዲሁ እቀጥላለሁ።

• ወይ ምስክርነት መች በፍሬንድስነት ሆነና…? ሃኣ…!
where were you hajieee 😂
ሐኪማችን የሚደክም፤ የሚሰላችም አይደለም፡፡ እልፍ ጊዜ ብንቆስል ያድነናል፤ ስለዚህ ጥበብ በማጣት በአካላችን ላይ ትንሽ ብንቆስልም ሐኪማችን ሁል ጊዜ ሊያድነን ይተጋል፡፡ እርሱ በኤርምያስ እጅ ለተነሳሕያን በተላከ ደብዳቤ ላይ በነቢዩ አፍ ድምጹን ከፍ አድርጎ ‹‹አሁንም መንገዳችሁንና ሥራችሁን አሳምሩ፤ የአምላካችሁንም የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፧ እግዚአብሔርም የተናገረባችሁን ክፉ ነገር ይተዋል›› ይለናል (ኤር ፳፮፥፲፫)፡፡ ስለዚህ ነቢዩ በመሓላ ቃል ‹‹በኃጢአተኛው ሞት አልደሰትም›› ይላል፡፡

ለአዳም ልጆች ሁሉ ተስፋ ቃል ኪዳን እንደ ገባላቸው ወደ በሩ መጥተው ለሚያንኳኩ ሁሉ የእግዚአብሔር በር ሁል ጊዜ እንደ ተከፈተ ነው፡፡ የቸርነቱ ፍቅር በንስሓ ለሚመላለሱት ይደሰታል፤ ስለዚህ እጆቹን ዘርግቶ ይቀበላቸዋል፡፡

ክብሩ ተነሳሕያንን ይረዳቸዋል፤ በእቅፉ ውስጥ መሆን ይቅርታን ያስገኛል፡፡ እርሱ በወንጌል ‹‹ንስሓ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኙ ጻድቃን ይልቅ ንስሓ ስለሚገባ ስለ አንድ ኃጢአተኛ በሰማያት ፍጹም ደስታ ይሆናል›› አለ (ሉቃ ፲፭፥፯)፡

በሰማያት ያሉ መላእክትን ደስ ይላቸዋል፣ የቅዱሳን ማኅበርም ሐሴት ያደርጋሉ፡፡ ጠባቂ መላእክትም ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ሆሣዕና እያሉ ይዘምራሉ፤ ሊቃነ መላእክትም በኅብረት ድምጻቸውን አሰምተው ይዘምራሉ፡፡

በአስፈሪ ግርማ ሞገስ የገነትን በር የሚጠብቅ ኪሩቤል እናንተ ተነሳሕያን እንኳን ደኅና መጣችሁ ብሎ ይቀበላችኋል፤ እናንተ አዲሶቹ የገነት ወራሾች ናችሁ ብሎ ደመ ማኅተሙን ከመስቀል ይዞ እንደ ሔደ ቀማኛ የምታጓጓዋን የገነት በር ይከፍትላችኋል።

ከሕይወት ዛፍም ትበላላችሁ ትጠግባላችሁም፡፡ የገነት ዛፍ ሕያው ፍሬውን ይሰጣችኋል፡፡ የኤደን አትክልትም ዙርያችሁን ይሞላል፡፡ የበለጸጉ ዛፎችም ይከባችኋል፡፡ በዚያ ከቅዱሳን ጋር ተሰምቶ የማያውቅ ምስጋናን ለአምላካችሁ ታቀርባላችሁ። በዚያ ቅዱሳኖቹ ይጠብቋችኋል፤ ባሸበረቀው አዳራሽ ውስጥ ታላቅ ደስታ በዚያ ይጠብቋችኋል፡፡ እናንተም የዚህ ታላቅ በዓል ታዳሚዎች ትሆናላችሁ፡፡

በዚያ በብርሃን በተሞላ ግዛት ውስጥ ብዙ ቅዱሳን አሉ፤ እናንተም ለቅዱሳን የሚሰጥ አክሊል ተዘጋጅቶላችሁ እየጠበቃችሁ ነውና። እንግዲህ ጠቢባን ሁኑ፤ ከንስሓ ወደ ኋላ በመመለስ ከዚህ ክብር አትራቁ፡፡

እናንተ በንስሓ ውስጥ ያላችሁ ሰዎች ሆይ እንግዲህ ሙሽራው እስኪመጣ ድረስ መጠበቅ፣ መዘግየትም የለባችሁም፡፡ ይልቁን ለሰርግ የሚገባውን ልብስ፤ የክብር ካባ ለብሳችሁ ተዘጋጅታችሁ ጠብቁ እንጂ፡፡ ወደ ሰርጉ ለመግባት የሙሽራውን ነጭ ልብስ ውሰዱ፡፡ የሙሽራው መምጫ ሳይደርስ የመብራቱን ዘይት አዘጋጁ፡፡ የመለከቱ ድምፅ ሳይሰማ በፊት በእጃችሁ ያለውን አሳዩ፡፡

እናንተ ኃጥአን ሆይ ዕዳችሁ የተተወላችሁ ይመስል በቸልታ መቀመጥን፣ ስንፍናንስ ማን አስተማራችሁ? እርሱ ዝም ብሎ ቢያያችሁ ትዕግሥቱን ሲያሳችሁ ነውና እንግዲህ በንስሓችሁ ዕንባ ነፍሳችሁን አድኑ፤ መጸጸታችሁንም አሳዩት፡፡ ይቅር ባይነቱ ታግሦአችኋልና እንግዲህ ዲናሩን ከነ ትርፉ መልሱለት፡፡

ጌታ ሆይ በሁሉም መንገድ ቸርነትህ ትጠራኛለች በቃልኪዳኖችህም ሁሉ ክብርህ እና ፈቃድህ ሕይወት እንድናገኝ ነው፡፡ ጌታ ሆይ ታላቅ የሆነ ቸርነትህን ለሰው ልጆች ሁሉ ሰጠህ። ለምዕመናንም፣ ለዘማውያንም መረብህን ዘረጋህ፡፡ አመጸኛው ሰላማዊ ይሆን ዘንድ፤ የጠፉትም ይገኙ ዘንድ፡፡ ለድኅነታችን ይሆን ዘንድ በታላቅ ይቅርታው በቸርነት ዓይኖቹ አየን፡፡

ጌታ ሆይ ወፍ ከአዳኝ ወጥመድ እንደምታመልጥ እኔም ከኃጢአት አመለጥኩ፤ በመስቀልህ ሥርም መሸሸጊያ ጎጆን ሠራሁ፡፡ ወደዚህ ሥፍራ አሳች ከይሲ ሊደርስ አይችልምና፡፡

ጌታ ሆይ እርግብ ከመረብ እንደምትወጣ ከኃጢአት ወጥመድ ወጣሁ። በመስቀልህም ሥር ሆኜ ወደ ላይ እወጣለሁ፡፡ በዚያ ክፉ ጠላት የሆነ ዘንዶ ሊያገኘኝ አይችልምና፡፡ በዚያ ሆኜ ሕይወት የሚሰጠውን ስምህን የልጅህንም ስም የእውነት መንፈስ የመንፈስ ቅዱስንም ስም አመሰግናለሁ፡፡

#ቅዱስ_ኤፍሬም

(በእንተ ንስሐ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ወ አፍርሐት ገጽ 35-38 ➛በዲ/ን መዝገቡ የተተረጎመ)
ይቅርታ…!

• ቅዱስ ሲኖዶስ የትግራይ ሕዝብንና ምዕመናንን ይቅርታ በይፋ ጠይቋል።

• “የሚምሩ ብፁዓን ናቸው፥ ይማራሉና።” ማቴ 5፥7

• “የሚያስተራርቁ ብፁዓን ናቸው፥ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና።”ማቴ 5፥9

"2ኛ. በክልል ትግራይ (በአማርኛ ትግራይ ክልል ለማለት ነው) በተካሄደው ጦርነት ወቅት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊትና ታሪካዊት ቤተ ክርስቲያን እንደመሆኗ መጠን ጦርነቱ እንዲቆም በወቅቱ መግለጫ ባለመስጠቷ፣ በጦርነቱ መካከል ወደ ትግራይ ከልል መግባትና መውጣት በሚቻልበት ወቅትም በክልሉ የሚገኙ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንንና መላው ሕዝበ ትግራይን (በአማርኛ የትግራይን ሕዝብ ለማለት ነው) በአካል በቦታው ተገኝታ ባለመጠየቋና ባለማጽናናቷ፣ ጦርነቱ ቁሞ በአገር እቀፍ ደረጃ እርቀ ሰላም ከወረደበት ጊዜ ጀምሮ ለደረሰው ጉዳት በቅዱስ ሲኖዶስ የተወሰነውን ሰብአዊ ድጋፍ በውሳኔው መሠረት በወቅቱ ማድረስ ባለመቻሏ፣ በዚሁም የተነሣ በቤተ ክርስቲያኗና በመላው ሕዝበ ትግራይ (በአማርኛ የትግራይ ሕዝብ ለማለት ነው) መካከል ለተፈጠረው ቅሬታና አለመግባባት ቅዱስ ሲኖዶስ ይቅርታ ጠይቋል።

እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርከ።

ወሰብሐት ለእግዚአብሔር አሜን!
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት"

ማስታወሻ፥

ብአዴን በትግርኛ ሲጠራ ነው። ብሔረ ዐማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ እንደማለት ነው። ለብአዴን ዐማራዎች ስሙን ቢያወጡለት ኖሮ ብአዴን ሳይሆን የሚባለው አብዴን ነበር ተብሎ የሚጠራው። የዐማራ ብሔር ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ነበር የሚባለው። ሕዘበ ትግራይም እንደዚያው ነው።

•አባቶቻችን የይቅርታ ቃል ከእናንተ ወጥቷል። አሁን ዕዳው በትግራይ ላሉት አባቶች ነው።
ሰበር ዜና! አቋርጠው ወጡ

"ቤተክርስቲያን ስትፈርስ መዶሻ አላቀብልም"

ትናንት በዋለው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ ለሹመት በተመረጡ ኤጲስ ቆጶሳት ዙሪያ በተጀመረው ውይይት ከፍተኛ ውዝግብ ያስተናገደ ሲሆን ከጅምሩ በነበረው የአካሄድ ክፍተትና የቀኖና ጥሰት ቅሬታ የነበራቸው ብፁዓን አባቶች ባለ መገኘታቸው የምልዓተ ጉባዔው አባላት ሳይሟሉ እንዲቀጥል ተደርጓል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በምልዓተ ጉባዔው ተገኝተው እየተሳተፉ ያሉ ብፁዓን አባቶች በግንቦቱ ለተሰየሙ አስመራጭ ኮሚቴ አባላት ለሚቀርብላቸው ጥያቄ ቀጥተኛ ማብራሪያና ምላሽ ባለመስጠታቸው አሁንም ግልጽነት የጎደለውና ከስርዓተ ቤተ ክርስቲያን ውጭ የሆነ አካሄዳቸውን በመቃወም አቋርጠው ለመውጣት ተገደዋል።

ከእነዚህም ብፁዐን አባቶች ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል የከፋ ሸካ ቤንች ማጂ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ሓላፊ ቤተክርስቲያን ስትፈርስ መዶሻ አላቀብልም በማለት አቋርጠው መውጣታቸውን ለማወቅ ተችሏል።
እስኪ ፀልዩ አባቶቻችን ምን ነካቸው ?
"…ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ከምዕራብ ሸዋ ሃገረ ስብከት፣ ከምሥራቅ አፍሪካ፣ የኬሠኒያ፣ ኡጋንዳ፣ ታንዛኒያ፣ ሩዋንዳ ሃገረስብከት ሊቀጳጳስነት በተጨማሪ የሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት አደራጅ ሊቀ ጳጳስ ተብለው ተሹመዋል ተብሏል።

• ሹመት ያዳብር…!
መዝሙር 21
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ አቤቱ፥ በኃይልህ ንጉሥ ደስ ይለዋል፤ በማዳንህ እጅግ ሐሤትን ያደርጋል።
² የልቡን ፈቃድ ሰጠኽው፥ የከንፈሩንም ልመና አልከለከልኸውም።
³ በበጎ በረከት ደርሰህለታልና፤ ከክቡር ዕንቍ የሆነ ዘውድን በራሱ ላይ አኖርህ።
⁴ ሕይወትን ለመነህ ሰጠኸውም፥ ለረጅም ዘመን ለዘላለሙ።
⁵ በማዳንህ ክብሩ ታላቅ ነው፤ ክብርንና ምስጋናን ጨመርህለት።
⁶ የዘላለም በረከትን ሰጥተኸዋልና፥ በፊትህም ደስታ ደስ ታሰኘዋለህ።
⁷ ንጉሥ በእግዚአብሔር ተማምኖአልና፥ በልዑልም ምሕረት አይናወጥም።
⁸ እጅህ ጠላቶችህን ሁሉ ታግኛቸው፥ ቀኝህም የሚጠሉህን ሁሉ ታግኛቸው።
⁹ በተቈጣህም ጊዜ እንደ እሳት እቶን አድርጋቸው፤ እግዚአብሔር በቍጣው ያጠፋቸዋል፥ እሳትም ትበላቸዋለች።
¹⁰ ፍሬአቸውን ከምድር ዘራቸውንም ከሰው ልጆች ታጠፋለህ።
¹¹ ክፋትን በአንተ ላይ ዘርግተዋልና፥ የማይቻላቸውንም ምክር አሰቡ።
¹² ወደ ኋላቸው ትመልሳቸዋለህ፤ ፍላጻን በፊታቸው ላይ ታዘጋጃለህ።
¹³ አቤቱ፥ በኃይልህ ከፍ ከፍ በል፤ ጽናትህንም እናመሰግናለን እንዘምርማለን።
ሰላም ለልደትከ ከመ ገብርኤል አደሞ
ስድስተ አውራኃ ለልደተ ክርስቶስ እንተ ቀደሞ
ዮሐንስ ስኂን ወምዑዝ እምቀናንሞ 😍
ለለነበብኩ በፅሒቅ ለመልክእከ ሰላሞ
ከመ ከላስት በሕፅንከ ሲሞ 😍
ግዛቱ የተሽፋፋለት የሸገር ሃገር ስብከት አዲስ ጣጣስ 😡
+ የበረሃው መናኝ +

መጥምቁ ዮሐንስ በሕፃንነቱ የመነነ የምድረ በዳ ሰው ነበር፡፡ የቀን ሐሩሩን የሌሊት ቁሩን ታግሦ በማይመቸው በረሃ ውስጥ ይኖር ነበር፡፡ የምድረ በዳው ሰው የዮሐንስ ድምፅ ታዲያ ከአይሁድ ሸንጎ እስከ ሔሮድስ ቤተ መንግሥት ድረስ ዘልቆ ይሰማ ነበረ፡፡

የምናኔን ኃይል ተመልከቱ! በምድረ በዳ ለመኖር የጨከነ ባሕታዊ ድምፅ ግርማው በከተማ ይሰማል፡፡ እርሱ በዋሻ ውስጥ እያደረ በቤተ መንግሥት በምቾት አልጋ የሚያድሩትን ሰዎች ያንቀጠቅጥ ነበር፡፡

‘ያን ጊዜ ኢየሩሳሌም ይሁዳም ሁሉ በዮርዳኖስም ዙሪያ ያለ አገር ሁሉ ወደ እርሱ ይወጡ ነበር’ (ማቴ. 3፡3) መናኙ ዮሐንስ ለስብከት ወደ ከተማ መምጣት አላስፈለገውም፡፡ ሕዝቡ ‘ወደ እርሱ ይወጡ ነበር’ ባሕታዊ ዮሐንስ ምድረ በዳውን አልለቀቀም፡፡ ሕዝቡን ለማምጣትም ወደ ሕዝቡ ገብቶ አብሮ መኖር አላስፈለገውም፡፡ ሕዝቡ ለነፍሳቸው ዕረፍት ፍለጋ ወደ ዮሐንስ ይሔዱ ነበር፡፡

ወደ ዮሐንስ ያልሔደ ማን አለ? ወታደሩ ፣ ባለ ሥልጣኑ ፣ ፈሪሳውያኑ ፣ ሰዱቃውያኑ ሁሉ ከሚመጣው ቁጣ ሊሸሹ ወደ ዮሐንስ ይመጡ ነበር፡፡

እውነተኛው መናኝ ዮሐንስ ሰዎችን ፈልጎ ወደ ዓለም የሚመጣ ሳይሆን ዓለማውያኑ ፈልገውት ወደ እርሱ የሚሔዱለት ነበር፡፡ አባ መቃርስን አባ እንጦንስን ፈልገው ወደ አስቄጥስ በረሃ ሰዎች እንደገሰገሱ ፣ አባ ሳሙኤልን ፈልገው ወደ ዋልድባ እንደተጓዙ ፣ አባ አረጋዊን ብለው ወደ ደብረ ዳሞ እንደገሰገሱ ሰዎች የዮሐንስን ፈለግ የተከተሉ የምድረ በዳ መናኞች ዓለምን ወደ እነርሱ ይስባሉ እንጂ እነርሱ በዓለም አይሳቡም፡፡

ዮሐንስ ምግቡ አንበጣና የበረሃ ማር ፣ ልብሱ የግመል ጠጉር ነበረ፡፡ ሰውነት የሚኮሰኩስ ቆዳን የሚረብሽ ልብስ ለብሶ ነበር፡፡ የግመል ጠጉር ዕርቃንን ከመሸፈኑ ውጪ ለብርድም ለሙቀትም የማይመች ዓይነት ልብስ ነበር፡፡ ዮሐንስን በሕይወቱ ከሚመስለው ከኤልያስ በስተቀር እንዲህ ዓይነቱን ልብስ ሊለብሰው የሚወድ ሰው አልነበረም፡፡

ጌታ ወደ ዮሐንስ የመጡትን ሰዎች ‘ምን ልታዩ ወጣችሁ? ቀኝን ልብስ የለበሰ ሰውን? እነሆ ቀጭን ልብስ የለበሱ በነገሥታቱ ቤት አሉ’ ብሎ ነበር፡፡ ማቴ. 11፡8 እውነት ነው ዮሐንስ አለባበሱን ለማየት የሚጓጓለት ሰው አልነበረም፡፡ ምን ዓይነት ልብስ ለብሶ ይሆን ብላችሁ ልታዩ ከመጣችሁ የሚያምር ልብስ የሚለብሱት ሰዎች ያሉት በነገሥታቱ ቤት ነው፡፡ ዮሐንስ ልብሱ የግመል ጠጉር ነው፡፡

የግመል ጠጉር ሰውነት ይኮሰኩሳል:: ለልብስነት አይመችም ለአገልግሎት ግን ይመቻል:: ልብስህ ግመል ምግብህ አንበጣ ቤትህ ምድረ በዳ ከሆነ ያለሃሳብ ታገለግላለህ:: እንደ በረሃው መናኝ እንደ ምድረ በዳው ባሕታዊ እንደ ቅዱስ ዮሐንስ ቤቴ ሚስቴ ድስቴ ልብሴ ምግቤ ሳትል ዝም ብለህ ለጌታህ መንገድ ትጠርጋለህ:: የማታጥበው የማትተኩሰው የግመል ጠጉር ከለበስህ ቃሉን ከመስበክ በቀር ምን ያሳስብሃል?

ዮሐንስ የስብከቱ ኃይል ምድርን ያንቀጠቀጠውም ለዚህ ነው፡፡ ነገሥታቱን ለመገሠፅ ያልከበደውም ለዚህ ነው፡፡ ምን አጣለሁ ብሎ ይፈራል? ምን እበላለሁ እንዳይል ቀድሞውንም ምግቡ አንበጣ ነው፡፡ ምን እለብሳለሁ? ብሎ እንዳይሰጋ የሚለብሰው የግመል ጠጉር ነው፡፡ ሰውነቱን ምቾት ስላላስለመደ ዮሐንስ እንዳያጣው የሚፈራው ምንም ነገር አልነበረም፡፡ ቤቴን እንዳይቀሙኝ ብሎ እንዳይፈራም እርሱ የምድረ በዳ መናኝ ነው፡፡

ባሕታዊው ዮሐንስ ሆይ ያማረ በፍታና ቀጭን ልብስ የለበስን ፣ ያማረ የምንበላ የምንጠጣ ፣ ባማረ አልጋ የምንተኛ ሰባኪያን አንተ መንገድ የጠረግህለትን ጌታ መንገድ ስንዘጋበት ስታይ ምንኛ ትታዘበን ይሆን? ሔሮድስ ከሔሮድያዳ ቢጋባና ቢወልድ ትንፍሽ የማንል ይልቁንም ሰርጉን ለመባረክ የምንሮጠው ለምን ይመስልሃል? ሔሮድስ እንኳን እናቲቱን ልጅትዋንም ጨምሮ ቢያገባ ሰምተን እንዳልሰማ የምንሆነው ልብሳችን እንዳንተ የግመል ጠጉር ፤ ምግባችንም የበረሃ አንበጣ ስላልሆነ ነው::

ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ ዛሬ "ለጌታ መንገድ አቅኑ ተራራው ዝቅ ይበል" ልትለን የሚገባህ የሐዲስ ኪዳን ፈሪሳውያንን በዝተናል:: በክርስቶስ የምናምን ሰዱቃውያንን የሔሮድስ ሰርግ ደጋሾች የሔሮድያዳ ጠጅ አሳላፊዎች እልፍ አእላፋት ሆነናል:: በልደትህ ቀን ወደ እኛ ተመልከት::

እኛ እንዳንተ "ዳዕሙ ከመ ያእምርዎ እስራኤል" (እስራኤል ያውቁት ዘንድ ነው) ማለት የምንችል አይደለንምና የምድረ በዳው መናኝ ሆይ ጌታህን እኛ እንድናውቀው አድርገን::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሰኔ 30 2015 ዓ.ም.
የመናኙን ምልጃ ለመማጸን የተጻፈ

ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን አጥብቃችሁ ስለ እኔ ጸልዩልኝ!
በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ [ዋጋን በምድር የሚያስቀር ውዳሴም ሆነ ሌላ] ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)
"አንተ ራስህ ለገዛ ወንድምህ ጨካኝና ይቅር የማትል ኾነህ ሳለስ እግዚአብሔር እንዲራራልህና እንዲምርህ እንዴት መለመን ይቻልሃል?

"ባልንጀራህ ምናልባት ንቆህ ሊኾን ይችላል፡፡ አዎ! አንተ ግን እግዚአብሔርን ኹልጊዜ እንደናቅኸው ነው፡፡ በባልንጀራና በእግዚአብሔር መካከልስ ምን ንጽጽር አለ? ባልንጀራህ ምናልባት ጉዳት ሲደርስበት ሰድቦህ ይኾናል፤ አንተም በዚህ ተበሳጭተህ ይኾናል፡፡ አንተ ግን ምንም ሳይጎዳህና በአንተ ላይ ክፉ ሳያስብ ይልቁንም ዕለት ዕለት በረከቱን እየተቀበልክ እያለ እግዚአብሔርን ሰድበኸዋል፡፡ እንግዲህ ተመልከት! ነቢዩ፡- “እመሰ ኃጢአተኑ ትትዐቀብ እግዚኦ መኑ ይቀውም - አቤቱ ኃጢአትንስ ብትጠባበቅ ማን ይቆማል?” ብሎ እንደ ተናገረ እግዚአብሔር በእርሱ ላይ የምንፈጽመውን በደል ቢመረምር ኖሮ አንዲት ቀንስ እንኳን በሕይወት መቆየት አንችልም ነበር (መዝ.129፡3)፡፡

እያንዳንዱ በደለኛ ሰው ለራሱ የሚያውቀውንና ሌላ ሰው የማይመሰክርበትን እግዚአብሔር ብቻዉን ግን የሚያውቀውንስ ይቅርና የተገለጠውና ሰው ኹሉ የሚያውቀው ኃጢአታችንን እንኳን እግዚአብሔር ቢቈጣጠር ኖሮ ከእነዚህ ኃጢአቶች በኋላ የምንጠብቀው ምንድን ነው? እግዚአብሔር ንዝህላልነታችንንና ጸሎት ስናደርስ የምናሳየው ግድየለሽነታችንን፣ ሠራተኞች ለአሠሪዎቻቸው ወታደሮችም ለአለቆቻቸው ጓደኛሞች ለጓደኞቻቸው የሚያሳዩትን ፍርሐትና ክብር ያህልስ እንኳን ለጸሎትና ለልመና በፊቱ በቆምን ጊዜ አለማሳየታችንን ቢቈጣጠር ኖሮ ምን ነበር የምንኾነው?

አንተ ከጓደኛህ ጋር ስትነጋገር ለምታደርገው ማንኛውም ነገር ትጠነቀቃለህ፡፡ ስለ በደሎችህ እግዚአብሔርን ስትጠብቀው፣ ለብዙ መተላለፎችህ ይቅርታን ስትጠይቀው፣ ሥርየትን ለማግኘት ስታሳስበው ግን [በፊቱ ላይ] ኹልጊዜ ግድየለሽ ትኾናለህ፡፡ ጉልበትህ በምድር ላይ ተንበርክኮ ሳለ ልቡናህ ግን እዚህም እዚያም፣ በገበያ ሥፍራም፣ በቤት ውስጥም ይዋልላል፤ ከንፈርህ በከንቱና እንዲሁ ያነበንባል፤ ይህን የምንፈጽመው ደግሞ አንዴ ወይም ኹለቴ ሳይኾን ኹልጊዜ ነው።

እንግዲህ እግዚአብሔር ይህን ብቻ እንኳን ቢመረምር ይቅርታን ወይም ምሕረትን እንደምናገኝ ታስባለህን? በእውነት አይመስለኝም!"

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

#ትምህርት_በእንተ_ሐውልታት_መጽሐፍ
ገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተረጎመው
#ሩማ ክብር ለቅድስት ድንግል ማርያም

ይህ ፎቶ በዓለም መነጋገሪያ የሆነው የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል ነው። በሩማ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ የቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል ብቻ ሲቀር ህንፃው ሙሉ ለሙሉ ወድሟል።

ክብር ለእናታችን
2024/09/28 13:27:35
Back to Top
HTML Embed Code: