Telegram Web Link
የአላህ ገነትና የአዲስ አበባ ቡና ቤቶች ልዩነታቸው ምንድነው
ዛሬ በዚህ ዙሪያ ውይይት ስለሚኖረን ይቀላቀሉን
👇👇
https://www.tg-me.com/utzys
+  በርባን ይፈታልን +

ሕዝቡ ‹በርባን ይፈታልን! ክርስቶስ ግን ይሰቀል!› ማለታቸውን ስንሰማ መቼም ሁላችንም ማዘናችንና ‹ምን ዓይነት ክፉዎች ናቸው?!› ብለን መውቀሳችን አይቀርም፡፡ ወዳጄ ሆይ! እባክህን እስቲ አይሁድንና ጲላጦስ ለአፍታ እንተዋቸው! አንተ ብትሆን ኖሮ ከጌታና ከበርባን ማናቸውን ትፈታለህ? የእስክንድርያው ትምህርት ቤት ዲን የነበረው ሊቅ ‹‹በሥጋው ክፉ ነገርን የሚሠራ ሁሉ በርባንን ፈትቶ ክርስቶስን አሰረው ፤ መልካም ነገርን የሚያደርግ ደግሞ ክርስቶስን ፈትቶ በርባንን አስሮታል›› ይላል፡፡

ወዳጄ ሆይ! አንተ በሰውነትህ ላይ ፈትተህ የለቀቅከው ማንን ነው? በርባንን ነው ወይንስ ጌታን ነው? በርባንን ፈትተኸው ከሆነ ዛሬውኑ በንስሓ ተመልሰህ ፈጣሪህን በሰውነትህ ውስጥ አክብረው፡፡ ‹በርባንን የፈታሁት እኮ ወድጄ አይደለም! ሁኔታዎች አስገድደውኝ ነው› ብለህ እንደ ጲላጦስ ለራስህ ይቅርታ ማድረግና እጅህን መታጠብ አይበጅህም፡፡ ይልቅስ አሁኑኑ ጌታህን ፈትተህ በርባንን የተባለ ኃጢአትን ስቀለው! ያን ጊዜ የክርስቶስ መሆንህ ይታወቃል፡፡ ‹‹የክርስቶስ ኢየሱስ የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ምኞቱ ጋር ሰቀሉ›› ተብሎ ተጽፎአልና፡፡ (ገላ. ፭፥፳፬)  

ሕዝቡ ‹በርባን ይፈታ› ብለው ቢጮኹም ሁሉም ለበርባን ፍቅር አላቸው ማለት አይደለም፡፡ ሊቃነ ካህናቱ ባያባብሏቸው ኖሮ በዚያች ዕለት ሊያስፈቱት የሚፈልጉት ሌላ እስረኛ ዘመድ ያላቸውም ሰዎች መኖራቸው አይቀሬ ነው፡፡ ሆኖም ሊቃነ ካህናቱ ለጌታችን ካላቸው ጥላቻ የተነሣ ሕዝቡን ተለማምጠው በርባን እንዲፈታ አስደረጉ፡፡ ዛሬ በርባንን አግኝተን ‹በርባን ሆይ ማን ነው ያስፈታህ?› ብለን ብንጠይቀው ምናልባትም ‹የሰው መውደድ ይሥጥ ማለት ነው! የሚወደኝ ሕዝብ ነዋ ጮኾ ያስፈታኝ!› ማለቱ የማይቀር ነው፡፡ ሆኖም ሊቃነ ካህናቱና ተከታዮቻቸው ግን ‹በርባን ይፈታ› ብለው የጮኹት ለበርባን ፍቅር ኖሯቸው ሳይሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ በነበራቸው ጥላቻ ምክንያት ነው፡፡ ስለዚህ በርባንን ከሞት ፍርድ አድኖ ያስፈታው ሕዝቡ ሳይሆን ጌታችን ነበር፡፡

ጌታችን በዚያች ዕለት የበርባንን ሞት ወስዶ የእርሱን ሕይወት ለበርባን ሠጠው ፤ የበርባንን ሰንሰለት አስፈትቶ እርሱ ታሰረ ፤ ከበርባን ጓደኞች ጋር በርባን ሊሰቀል በነበረበት ቦታም ተሰቀለ፡፡ ወዳጄ ሆይ! ልብ ብለህ ከተረዳኸው በርባን እኮ አንተው ነህ! ለበርባን ከተደረገለት ለአንተ ያልተደረገ ነገር ካለ እስቲ ንገረኝ! እንደ በርባን ክርስቶስ ሞትህን ወስዶ ሕይወቱን ፣ እስራትህን ወስዶ ነጻነትን አልሠጠህምን?
ይህንን ያደረገውም ለአንተ ብቻ ሳይሆን ለአዳም ልጅ ሁሉ ነው ፡- ‹‹የእስረኛው በርባን (ወልደ አባ) መፈታቱ አምላካዊ ምሥጢርን የሚያስታውስ ነው፡፡ በኃጢአቱ ምክንያት በሲኦል ውስጥ ታሥሮ የነበረው አዳምን በአዳኙ መሰቀል ምክንያት መድኃኒት አግኝቶ ነጻ መውጣቱን ያስታውሳል›› / ‹‹እስመ ተፈትሕዎቱ ለወልደ አባ ሙቁሕ ያዜክር ምሥጢራተ አምላካዊ ያሌቡ ግዕዛነ አዳም ዘኮነ ሙቁሐ ውስተ ሲኦል በእንተ ኃጢአቱ ወረከበ መድኃኒተ በስቅለተ መድኅን›› እንዲል፡፡ 

በዚያች የዕለተ ዓርብ ረፋድ ላይ ያስፈታውን የማያውቀው ይህ ወንበዴ ሰንሰለቱ ተፈትቶ ወደ ቤቱ ሲሔድ ጌታችን ግን ለመከራና ለመስቀል ተሠጠ፡፡ እውነቱንስ ለመናገር እኛ ክርስቲያኖች በርባን በመፈታቱ ላይ ላዩን ብናዝንም ውስጥ ውስጡን ግን ደስ ብሎናል!

‹‹…በርባን ቢሰቀል ኢየሱስ ቀርቶ
ምን ይጠቅመናል ሽፍታ ሞቶ
እንኳን ኢየሱስን ሰቀሉት
የሞቱን መድኃኒት …››
ብለው መሪጌታ ፍቅሩ ሣህሉ በበገናቸው ጨርሰውታል፡፡

(ሕማማት ከሚለው መጽሐፍ ለመድኃኔ ዓለም የስቅለቱ መታሰቢያ የተወሰደ)
✔️ወሎ ላይ ያውም መሀል ሀገር ደሴ 🤔

ቤተ መቅደስ ሊፈርስ ጫፍ ደርሶ እኛ ችላ ብለናል ሙስሊም ክርስቲያኑ አባቶቻችን እና እናቶቻችን ሲያደርጉት እንደነበረው እኛም አሁን ትኩረት ለደሴ ደብረ ሀይል ቅዱስ ዑራኤል ቤ /ክ እንሰጥ ዘንድ ግድ ይላል 🙏🙏🙏

#share በማድረግ ለሁሉም ሰው እንዲዳረስ እናድርግ 🙏
✧✧✧ያዪትን ነገር ማመን ተሳናቸው✧✧✧

በእውነት ይህን እያየ ዝም የሚል ክርስቲያን ልጄ ልለው ይከብደኛል።

። ።።። ልጂነትዎን ያሳዪ።።።
✤ ከእርስዎ ጀርባ በረከቱን የሚፈልግ አንድ ሰው አይጠፋምና ሸር አድርገው በረከቱን ያሳትፋ
✤አካውንት✟✟።የደብረ ኃይል ቅዱስ ዑራኤል ህንፃ ማሠሪያ

➽አቢሲኒያ ባንክ 105822774
➽ ንግድ ባንክ1000327155017
➽አዋሽ ባንክ 01304135417300

✥ለበለጠ መረጃ የደብሩን አስተዳዳሪ
እና ህንፃ አሠሪ ኮሚቴውን ያናግሩ
👉 በ0914610771ቆሞስ አባ ኋይለማርያም
👉በ0914604815 አቶ ዋሲሁን
👉በ0987011601 አቶ ኤፍሬም
👉በ0914711620 አቶ ብርሃን
+++ ከሆሣዕና በፊት የተደረገው ክልከላ +++

ጌታችን በኢያሪኮ የነበረውን አገልግሎት ፈጽሞ ሲወጣ የቃሉን ትምህርት የእጁን ተአምራት አይተው የተከተሉት ብዙ ሕዝብ  ነበሩ። እነሆም ከመንገድ ዳር የተቀመጡ ሁለት ዕውሮች ኢየሱስ ክርስቶስ በዚያ እያለፈ መሆኑን ሲሰሙ "የዳዊት ልጅ ሆይ ማረን?" ብለው ጮኹ። ከእነዚህ ሁለት ዓይነ ሥውራን አንዱ በርጤሜዎስ እንደሚባል ቅዱስ ማርቆስ ይነግረናል።(ማር 10፥46) ወንጌላዊው የአንዱን ስም ለይቶ መጥራቱ ይህ ሰው በከተማው ከነአባቱ የሚታወቅ በመሆኑ ሳይሆን አይቀርም። የሆነው ሆኖ አሁን ሁለቱም ነዳያን "ማረን" ሲሉ እየጮኹ ነው።

ነገር ግን ከጌታችን ፊት ቀድመው ይሄዱ የነበሩት ሰዎች እኒህን ነዳያን "ዝም በሉ!" ብለው ገሰጿቸው።(ሉቃ 18፥39) ልብ በሉ! የገሰጿቸው ሰዎች ጌታን ከኋላ የሚከተሉ ወይም ከአጠገቡ አብረው የሚሄዱት አልነበሩም። ከፊት ከፊት የሚቀድሙት እንጂ። በእርግጥም ከጌታው ፊት ቀደም ቀደም የሚል ሰው ጠባይ ይህ ነው። ራሱን ከባለቤቱ በላይ ዐዋቂ ያደርጋል። ምስኪኖችን "ዝም በሉ" እያለ የሚያሳቅ፣ የጌታውን ቸርነት የሚሸፍን አጉል ጠበቃ ይሆናል። እስኪ አሁን "ማረን" ማለት ምን ነውር አለው?! ቃሉስ የስድብ ያህል የሚያስቆጣና "ዝም በሉ" የሚያሰኝ ነው?! እነዚህ ሁለቱ ዕውሮች የገጠሟቸው እንዲህ ያሉ "በባለቤቱ ያልተወከሉ ጠበቆች" ነበሩ። ግን አልተበገሩም "ጌታ ሆይ፥ የዳዊት ልጅ ማረን" እያሉ ከቀድሞው ይልቅ አብዝተው ጮኹ።

ለሚያንኳኩ በሩን የሚከፍት በጎውንም ነገር ለለመኑት የሚሰጥ መድኃኔዓለም የእነዚህን ምስኪናን ጩኸት ሰምቶ ቆመላቸው። "ኑ" እንዳይላቸው ዓይተው መራመድ አይችሉምና ሁለቱንም እንዲያመጡለት አዘዛቸው።(ሉቃ 18፥40) ከፊተኞቹ ይልቅ ቅን የሆኑት እና ባለቤቱ የላካቸው መልካሞቹ ሰዎች "አይዟችሁ ተነሡ ይጠራችኋል" በማለት በሚያጽናና ቃል ወደ ጌታ አቀረቧቸው። ወደ እርሱም ሲቀርቡ "ምን ላደርግላችሁ ትወዳላችሁ?" ሲል የችግረኞች አምላክ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ በፍቅር ጠየቃቸው። እነርሱም "እናይ ዘንድ" አድርገን አሉት። ዓይናቸውን ዳስሶ ፈወሰውና አይተው ተከተሉት።

ይህን የበርጤሜዎስን ታሪክ ቅዱስ ፊልክስዩ ደግሞ ለሚጸልይ ሰው በመስጠት ውብ አድርጎ ይተረጉመዋል። በርጤሜዎስ "የዳዊት ልጅ ሆይ ማረኝ" ብሎ ሲጮህ "ዝም በል" ብለው እንደ ገሰጹት፣ እኛም ወደ አምላካችን ጸሎት ስናቀርብ ልመናችንን እንድናቆም "አይሰማችሁም" እያሉ ኅሊናችንን በመረበሽ አጋንንት ዝም ሊያሰኙን ይሞክራሉ። ነገር ግን የዚህ መፍትሔው እንደ በርጤሜዎስ ተስፋ ሳይቆርጡ እምቢ ብሎ ወደ ፈጣሪ መጮህ ነው። ያን ጊዜ ጌታ ልመናችንን ሰምቶ "ጥሯቸው" ይላል። "አይዟችሁ ተነሡ፤ ይጠራችኋል" ብለው የራቅነውን የሚያቀርቡ እና ረድኤተ እግዚአብሔርን የሚያሰጡ ቅዱሳን መላእክትን (ቅዱሳን ሰዎችን) ወደ እኛ ይልክልናል።

በርጤሜዎስም ወዲያው ተነሥቶ ጠልፎ ሊጥለውና ሸክም ሆኖ ሊያዘገየው የሚችለውን ድሪቶ ጥሎ ፈጥኖ ወደ ጌታ እንደ ቀረበ። እኛም ወደ አምላካችን እንዳንቀርብ አንቀው የሚይዙንን እና የሚያዘገዩንን አጉል ልማዶቻችንን ጥለን ወደ እርሱ ልንቀርብ ይገባል። ይህ ከሆነ እንደ በርጤሜዎስ እሴተ ጸሎታችንን (የጸሎታችንን ዋጋ) እናገኛለን። ከዚያ መድኃኒታችንን ተከትለን እስከ ኢየሩሳሌም እንሄዳለን። "ሆሣዕና በአርያም" እያልንም የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘን እናመሰግነዋለን።

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
[email protected]
አዲስ አበባ

ድረ ገጹን ይጎብኙ
https://dnabel.com
ለምን ጠላኸኝ ወንድሜ
አኮቴት ዘማኀሌት
ለምን ጠላኸኝ ወንድሜ
ለምን ጠላኸኝ ወንድሜ የአንድ አባት ልጆች እኮነን
ለምን ጠላኸኝ ወዳጄ የአንድ እናት ልጆች እኮነን
ብዙ ነው መንግሥቱ አብረን እንወርሳለን
ሰፊ ነው ግዛቱ አብረን እንወርሳለን
#አዝ
የተካፈልኩትን ንብረት አጥፍቼ ብመለስ ዛሬ
አባቴ ናፍቆኝ ብመጣ ልቤን አንገቴን ሰብሬ
ለሁላችንም ይበቃል ብዙ ነው የሱ መንግስት
አይክፋህ ባክህ ወንድሜ ፍቅር ይበልጣል ከሃብት
#አዝ
ፊትህ በሃዘን አይጥቆር ድንጋዩን ጣለው ወንድሜ
ተቅበዝባዥ እንዳያደርግ እጅህ ቆሽሾ በደሜ
ልብህን መልካም ብታደርግ የአንተም መስዋዕት ያደርጋል
ጌታ ለሁሉም እኩል ነው መታዘዝ ንጉስ ያደርጋል
#አዝ
ብልጥ ስለሆንኩ አይደለም የተባረኩት በጌታ
ጽኑ መሻቴን አይቶ ነው በኩር ያደረገኝ ስመታ
የበቀል ጦርክን ሸሽቼ በባእድ ሃገር ብኖርም
በልጅ በትዳር ባርኮኛል አብረን እንኑር በሰላም
ለምን ጠላኸኝ ወንድሜ የአንድ አባት ልጆች እኮነን
ቢፈልግባትም
አኮቴት ዘማኀሌት
ቢፈልግባትም መልካሙ ገበሬ

ቢፈልግባትም መልካሙ ገበሬ
አልተገኘባትም ከበለስዋ ፍሬ

ለስልሶላት ነበር ሀይማኖት መሬቱ
ተቀጥሮላት ነበር አጥር ስርዓቱ
ተለቅሞላት ነበር ድንጋይ ፈተናዋ
ፍሬ ግን ታጣባት በመጨረሻዋ

ፍሬ የሌለባት ቅጠል ስለሆነች
ተካይዋ በምግባር ስላላስደሰተች
መልካሙን ገበሬ ሊቆርጣት ተነሳ
ሌሎች እንዳይጠፉ ከእርሷ የተነሳ

ለንስሐ የሚሆን እድሜ እንዲሰጣት
ጠባቂ መላእኳዋ ተማጸነላት
ምክር እና ተግሳጽ ይጨመርላት
ታፈራ እንደሆነ ለዓመት እንያት

ልመናውን ሰምቶ ጌታውም ፈቀደ
ጥቂት እድሜ ሊሰጥ ሊታገስ ወደደ
ዳግመኛ ሲመጣ ፍሬ ካላፈራች
ተቆርጣ ወደ ቶን እሳት ትጣላለች
ቅድስት
አኮቴት ዘማኅሌት
#ሰንበተ_ክርስትያን

በኩር ናት የበዓላት
ኑ ከፍ ከፍ እናድርጋት
በእሷ ደስ ይበለን
በሰንበተ ክርስቲያን

በዝማሬ እንበርታ በገናውን እንያዝና
መልካም ስራ የሚሰራባት
ሰንበት ቅድስት ናት እና
ከጨለማ ብርሀን ከመገዛት ነፃነት
እግዚአብሔር ይህን ሰጠን
ደስ ይበለን በሰንበት
#አዝ
ለአብርሃም ተገልጣለች
ለሙሴም በደብረ ሲና
በነቢያት የታወቀች
ሰንበት ዳራዊት ናት እና
በሳምንቱ ሰለጠነች
ተሰበከች በሐዋርያት
ሃሌ ሉያ ዕለተ ሰንበት
ተሰጠችን ልናርፍባት
#አዝ
በእልልታ እንሞላ እንደ ነቢዩ አሳፍር
በከበረች የሰንበት ቀን ኑ ለቅኔ እንሰለፍ
በመቅደሱ ናቸው እና ቅዱስነትና ግርማ
ውዳሴያችን ይሰማልን
ከምድር እስከ እዮር እራማ
#አዝ
እግዚአብሔር አብ የባረካት
እግዚአብሔር ወልድ የቀደሳት
ከእለታት ሁሉ መርጦ
መንፈስ ቅዱስ ከፍ ያደረጋት
በእርሷ ሀሴት እናድርግ
እናክብራት እንድንከብር
የደጀሰላሙ ታዛ በመቅደሱ እንሰብሰብ

👇👇👇👇👇👇👇👇👇
      
♦️የትኘዋ ሄዋን ነሽ⁉️

                 👇👇

🔘የገነቷ ሄዋን ከእግዚያብሄር ፍቃድ የተገነጠለች/የተለያች ነበረች😔

🔘የገነቷ ሄዋን ቶሎ የምትታለል ልቧም ቶሎ የሚሰረቅ ነበረች🤦‍♀

🔘የገነቷ ሄዋን የምትሰማውን ነገር መመርመር ያቃታች🤷‍♀ የሚወራት ሁሉ መልካም መስሎ የሚሰማት አይነት ሴት ነበረች😳

🔘የገነቷ ሄዋን ራሷም ስታ ለሌላው ስህተት መንስኤ የሆነች ነበረች😔

🔘የገነቷ ሄዋን ከበረከት እርግማንን የመረጠች ከፍሬያማነት ድካምን ያተረፈች ነበረች🤦‍♀

🔺ዳግሚት ሔዋን ደግሞ ማርያም ግን👇

🔘የምታደርገውን የምታውቅ አስተዋይ
🔘ለሌላው ጥፋት ሳትሆን አስተማሪ
🔘ብኩን ሳትሆን ፍሬያማ💪
🔘የመኖሯ ሚስጥር የገባትና ለአላማዋም ፀንታ የምትንኖር🙋
🔘የምትሰማው ነገር አሰላስላ ደግሞም መርምራ አስተውላ🤔 መልሳ የምትናገር ከመፍጠን የዘገየች ናት💁 መልዓክ እንኳን ቢሆን

⚠️ታዲያ አንቺ ዛሬ የየቷ ሄዋን ነው መሆን የምትሽው የቀደመችውን የገነቷ ወይስ የዳግሚት ሔዋንን⁉️ ዛሬ ላይ ያለሽበትን የቆምሽበትንም ነገር ተመልከቺ👍 ቆም በይና አስቢው🤔 እንደ የትኛዋ ሄዋን እየተንቀሳቀስሽ ነው⁉️ ይህን በግላችሁ አስቡና መልሱት ነገር ግን እኔ አንድ ነገር ልበል👇

የሚበጃቹ እንደ ማርያም ዳግማዊቷ ሄዋን መመላለስ ነው👉 በክርስቶስ ዳግም ህይወትን እንደገኘችዋ ፣ የምታደርገውን እንደምታውቀዋ👍፣ የበረከት ምንጭ እንደሆነችዋ እንደሷ ሴት መሆን ምርጫችሁ አድርጉት🙏

https://www.tg-me.com/lebam_set
አንዱ ዛሬ ኢድ አደባባይ እንገናኝ ብሎኝ ይሄው ስንት ሰዓቱ ሀገር ምድሩን እየዞርኩ ነው ።

ምዕመናን የት ነው 🤔 እኔ አላወቅኩትም
እንኳን ለሆሳዕና በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን 🕊️🕊️🕊️r✝️⛪️💐💐💐💐🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🕊️🕊️🕊️🕊️🕊️🕊️🕊️🕊️

ዮሐንስ ምዕረፍ 12÷13

የዘንባባ ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው ሊቀበሉት ወጡና፦ ሆሣዕና፤ በጌታ ስም የሚመጣ የእስራኤል ንጉሥ የተባረከ ነው እያሉ ጮኹ።
ቢያን ለ 10 ሰው ሼር አድርጉት🙏🙏🙏
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ለዋይፋይ ተጠቃሚዎች በምስል ወድምፅ [ Video ]
ማሻ አላህ ነው እንኳን ውሻ ያልሆነ 😂
በስግደት ወቅት የእጅ ጣታችንን እንዲህ በማድረግ ይሁን
ደም ግባት አልባ | Dem Gbat Alba | ቴዎድሮስ ዮሴፍ | Tewodros Yosef
<unknown>
#ጌታዬ_ሆነህ_ደም_ግባት_አልባ

ጌታዬ ሆነ ደም ግባት አልባ፣
ጀርባዉ በጅራፍ ስለኔ ደማ፣
የኔን መገርፍ እረሱ ተገርፎ፣
ክብር አለበሰኝ እርሱ ተገፎ/2/

በሀሰት ሸንጎ ወጥመድ ተጠምዶ፣
ጌታ ተያዘ ህይወቴን ፈቅዶ፣
ክፉዎች ቢያዩት እንደ ወንበዴ፣
ለኔ ግን ሆኗል መዉጫ መንገዴ/2/

ታስረኃል ስለኔ ኢየሱስ መድኅኔ፣
ታስረኃል ስለኔ ኢየሱስ መድኅኔ፣

አዝ

ሲዘብቱበት ምራቅ ሲተፉ፣
የማይደፈር ደፍረው ሲዘልፉ፣
በከበቡት ፊት ቃል ከለከለ፣
እኔ እንድናገር እርሱ ዝም አለ/2/

ታርደኃል ስለኔ ኢየሱስ መድኅኔ፣
ታርደኃል ስለኔ ኢየሱስ መድኃኔ ፣

አዝ

ህይወት መንጭቷል ተወግቶ ጎኑን
ለከሳሾቹ ተርፏል ማዳኑ፣
እጅ እግሩን ምስማር ሲቸነክርዉ
የሞትን እሾህ ከኔ ነቀለዉ/2/

ተወጋ ስለኔ ኢየሱስ መድኃኔ፣
ተወጋ ስለኔ ኢየሱስ መድኃኔ፣

አዝ

እርቃኑን ሆኖ ፈተነዉ ልብሴን፣
አንዲሁ ወዶኝ ጠጣ ቆምጣጤ፣
በምህረቱ ጥል ነብሴን አርክቶ፣
አለመለመኝ አርሱ ተጠምቶ/2/

ተጠማ ስለኔ ኢየሱስ መድኃኔ ፣
ተጠማ ስለኔ ኢየሱስ መድኃኔ፣

          
2024/10/01 11:40:19
Back to Top
HTML Embed Code: