Telegram Web Link
Audio
🛑በሰሙነ ሕማማት ምን ማድረግ አለብን? በዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ || Tadias Addis

ለሁሉም ኦርቶዶክሳዊያን እንዲደርስ ሼር በማድረግ ክርስቲያናዊ ግዴታዎን ይወጡ 🙏
Audio
የሕማማት መዝሙሮች ስብስብ | ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ | Himamat Mezmur | like mezemran yilma hailu | ህማማት መዝሙር | ሕማማት
Audio
የሰሙነ ህማማት መዝሙር ኪራላይሶን - Kiralayson mezmur | Ethiopia | Ethiopian Orthodox
[ ስብሐት ለከ = ምስጋና ላንተ ]
┄┉✽̶»̶̥༺✞༻»̶̥✽̶┉┄

ዘበሰማያት አቡነ ወዘበምድር ዓዲ
ግብተ እንበለ ታጐንዲ
ዘታብዕል ወዘታነዲ ፤ ስብሐት ለከ።

በሰማያት ያለህ አባታችን ፡ በምድርም የምትኖር
ፈጥነህ የምትደርስ ፡ የማትዘገይ የማታስቀር
የምታደኸየውም አንተ ነህ ፡ በሀብትም የምታከብር
. ምስጋና ላንተ
━━━━━━━༺✞༻━━━━━━

ይትቀደስ ስምከ እግዚኦ ዘኢትመውት ሕያው
በአፈ ኵሉ ፍጥረት በበመታልው
በክላሕ ወበንቃው ፤ ስብሐት ለከ።

ስምህ ይቀደስ አቤቱ : ሕያው ነህና የማትሞት
በፍጥረት ሁሉ አንደበት: እነርሱንም በሚመስሉት
እየጮኹ የሚያመሰግኑህ: ድምጻቸውን በማሰማት
. ምስጋና ላንተ
━━━━━━━༺✞༻━━━━━━

መንግሥትከ ትምጻእ እግዚኦ ወትምህርትከ ቅድስት
እንተ ፈተውዋ በኵሉ ሰዓት
ቀዳሚ ማኅበረ ነቢያት ፤ ስብሐት፡ ለከ።

መንግሥትህ ትምጣ አቤቱ : ልዩ የሆነችውም ያንተ ትምህርት
ሁል ጊዜ እየናፈቁ ፡ እየተመኙም ያላይዋት
የነቢያቱ ጉባኤ ነው፡ የቀደመው ታላቅ ህብረት
. ምስጋና ላንተ
━━━━━━━༺✞༻━━━━━━

ፈቃድከ ይኩን እግዚኦ ወሥምረትከ ሠናይ
በምድር አንተ ወበሰማይ
እግዚእ ወአዶናይ፤ ስብሐት፡ ለከ።

ፈቃድህ ይሁን አቤቱ፡ በጎ ፈቃድህን እንድናይ
በምድር ያለህ አንተ ነህ፡ እንዲሁም ደግሞ በሰማይ
የአማልክት አምላካቸው ፡ የጌቶች ጌታ ሁሉን ቻይ
. ምስጋና ላንተ
━━━━━━━༺✞༻━━━━━━

ሲሳየነ ኵሉ ወዘልብነ ይፈቱ
እግዚኦ ሀበነ ጸጋ በከንቱ
ዘየአክል ለለዕለቱ ስብሐት ለከ።

ምግባችንን ሁሉ ሥጠን ፡ እንደ ልባችን መሻቱ
ያለዋጋ አድለን እንጂ፡ ጸጋህን አትንሳን አቤቱ
የዛሬውን ለዛሬ እናግኝ ፡ የሚበቃንንም በየዕለቱ
. ምስጋና ላንተ
━━━━━━━༺✞༻━━━━━━

አበሳነ ሥረይ እግዚኦ ወዳኅፃቲነ እምሕግ
ብዙኃ ምሕረት አምላክ ከመ ማየ ዐይግ
የዋህ እንበለ ፁግ፤ ስብሐት ለከ።

በደላችንን ተው አቤቱ ፡ ከሕግህም ስንወድቅ
ምሕረትህ የበዛ ቸር አምላክ ፡ እንደ ኩሬ ውኃ የማያልቅ
የዋህ ሆነህ የምትምር ፡ ክፋትና ተንኮል የማታውቅ
. ምስጋና ላንተ
━━━━━━━༺✞༻━━━━━━

ከመ ንሕነኒ ንኅድግ አበሳ ወዘቢጽነ አበሰ፣
ፍጥር ለነ ኅሊና ቅዱሰ
ወልበ መስተዐገሠ፤ ስብሐት፡ ለከ።

እኛም እንድንተውለት ፡ ባልንጀራችን የበደደለንን
የተቀደሰውን ኅሊና ፡ በውስጣችን ፍጠርልን
ልበችን ከቂም ርቆ ፡ የሚታገስ እንዲሆን
. ምስጋና ላንተ
━━━━━━━༺✞༻━━━━━━

ኢታብአነ እግዚኦ ውስተ መንሱት ብዙኅ
ዘኢትነውም ሕቀ ኖላዊ ትጉህ
በሠርክ ወበፍና ነግህ፤ ስብሐት፡ ለከ።

እንዳታገባን አቤቱ ፡ ወደበዛውም ፈተና
ጥቂት እንኳ የማትተኛ ፡ ትጉህ እረኛ ነህና
በሠርክ እንዳትለየን፡ በማለዳውም ጎዳና
. ምስጋና ላንተ
━━━━━━━༺✞༻━━━━━━

አድኅነነ ዘልፈ እግዚኦ ለመልአከ ስሕተት እምቀትሉ
ወባልሐነ እምእኩይ ኵሉ
ለዓለም እንተ ትሄሉ፤ ስብሐት፡ ለከ።

አቤቱ ዘወትር አድነን ፡ ከሚያስተው መልአክ ግድያ
ከክፉ ሁሉ ታደገን ፡ የፈጠርከን ባንተ አምሳያ
ለዘለዓለም የምትኖር ፡ የሕያው ፍጥረት መጠለያ
. ምስጋና ላንተ
━━━━━━━༺✞༻━━━━━━

በላዕለ ብዙኅ አድኅኖ ወዲበ ኵሉ ሰላም፣
እስመ ዚአከ መንግሥት ግሩም
ለዓለም ወለዓለመ፡ ዓለም፤ ስብሐት፡ ለከ።

በብዙ ማዳንህና ፡ በሰላምህም ላይ የጸና
ታላቅ ኃይልና መንግሥት ፡ ሁሉም ያንተ ነውና
ከዘልዓለም እስከ ዘልዓለም ፡ ይድረስህ ክብር ምስጋና
. ምስጋና ላንተ
━━━━━━━༺✞༻━━━━━━

✞ በቴዎድሮስ በለጠ ✞ Яερ๑รтεδ ƒя๑๓ ሚያዝያ ፲ ፳፻፲፬ ዓ.ም. ከደብረ ሊባ
ኖስ
ከሰ/ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ቀለምንጦስ የተሰጠ መግለጫ!
****,*****

የተከሰተውን ሀገራዊና ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክተው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ የተከሰተው ችግር በውይይትና በሠላም እንዲፈታ ጥሪ አቀረቡ።

ብፁዕነታቸው የሰላም ችግሩም በሃይማኖት አባቶችና በሀገር ሽማግሌዎች በሽምግልና እንዲፈታም ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ እንደተናገሩት ይህ ወቅት በመላው ኢትዮጵያ በክርስትና እና በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ ታላቅ የጾምና የጸሎት ወቅት ሲሆን በተለይም በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ ሰሙነ ሕማማት በመሆኑ ሕዝበ ክርስቲያኑ ለጸሎት፣ ለጾምና ለስግደት ወደ ቤተ ክርስቲያን ከወትሮው በተለየ መልኩ የሚመጣበት እና የሕዝቡ ፍሰት የሚጨምርበት ወቅት ነው ብለዋል።

ይሁን እንጂ በዚህ ከፍተኛ የጾምና የጸሎት ወቅት እንደሀገርም ሆነ እንደ ደብረ ብርሃን ከተማ የሰላም ችግር ያጋጠመን በመሆኑ አዝነናል ብለዋል።

ዞኑም ሆነ ከተማችን ደብረ ብርሃን በፈጣን ልማትና እድገት ላይ የሚገኙ ቢሆንም በዚህ ሰዓት የሰላም እጦት ያጋጠመ በመሆኑ ይህን የተከሰተ ችግር በመፍታት በኩል በተለይም መንግስት በሚመራው ህዝብ ላይ ጉዳት እንዳይደርስ በሆደ ሰፊነት ችግሩን እንዲፈታ አሳስበዋል።

ብፁዕነታቸው አያይዘውም አሁን ያለነው ፆም፣ ጸሎትና ስግደት ላይ ቢሆንም የሰላም ቀውስ የገጠመን በመሆኑ በዞኑ አብያተ ክርስቲያናት ያላችሁ ሁሉ ከወትሮው በተለየ መልኩ እስከ ስቅለቱ ድረስ በልቅሶ፣ በዕንባና በመሪር ሀዘን ፀሎተ ምህላን እንድታከናውኑ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ብፁዕነታቸው የተከሰተውን የሰላም ችግሩም በኃይማኖት አባቶችና በሀገር ሽማግሌዎች በሽምግልና ለመፍታት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
#በግብረ_ሕማማት_ውስጥ_የሚገኙ_እንግዳ_ቃላት_እና_ትርጉማቸው

በግብረ ሕማማት ውስጥ ወደ ግእዝም ሆነ በኋላ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡ የዕብራይስጥ፣ የቅብጥ እና የግሪክ ቃላት ይገኛሉ፡፡ የእነዚህ ቃላት ትርጉም የሚከተለው ነው፡፡

#ኪርያላይሶን
ቃሉ የግሪክ ሲሆን አጠራሩ "ኪርዬ ኤሌይሶን" ነው፡፡ "ኪርያ" ማለት "እግዝእትነ" ማለት ሲሆን "ኪርዬ" ማለት ደግሞ "እግዚኦ" ማለት ነው፡፡ ሲጠራም "ኪርዬ ኤሌይሶን" መባል አለበት፡፡ ትርጉሙ "አቤቱ ማረን" ማለት ነው፡፡ "ኪርያላይሶን" የምንለው በተለምዶ ነው፡፡ ይኼውም ኪርዬ ከሚለው "ዬ" ኤላይሶን ከሚለው ደግሞ "ኤ" በመሳሳባቸው በአማርኛ "ያ" ን ፈጥረው ነው፡፡

#ናይናን
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ "መሐረነ፣ ማረን" ማለት ነው፡፡

#እብኖዲ
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ "አምላክ" ማለት ነው፡፡ "እብኖዲ ናይናን" ሲልም "አምላክ ሆይ ማረን" ማለቱ ነው።

#ታኦስ
የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ "ጌታ፣ አምላክ" ማለት ነው፡፡ "ታኦስ ናይናን" ማለትም "ጌታ ሆይ ማረን" ማለት ነው፡፡

#ማስያስ
የዕብራይስጥ ቃል ሲሆነ ትርጉሙ "መሲሕ" ማለት ነው፡፡ "ማስያስ ናይናን" ሲልም "መሲሕ ሆይ ማረን" ማለት ነው

#ትስቡጣ
"ዴስፓታ" ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ደግ ገዥ ማለት ነው።

#አምነስቲቲ_ሙኪርያ_አንቲ_ፋሲልያሱ
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም "ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ- አቤቱ በመንግሥትህ አስበኝ" ማለት ነው፡፡

#አምንስቲቲ_ሙዓግያ_አንቲ_ፋሲልያሱ
የቅብጥ ቃል ሲሆን "ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በውስተ መንግሥትከ ቅዱስ ሆይ በመንግሥትህ አስበን" ማለት ነው፡፡

#አምንስቲቲ_ሙዳሱጣ_አንቲ_ፋሲልያሱ
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም "ተዘከረነ እግዚአ ኩሉ በውስተ መንግሥትከ የሁሉ የበላይ የሆንክ ሆይ በመንግሥትህ አስበን" ማለት ነው፡፡
ዘጠና ዘጠኙ የአላህ ስሞች 😂😂😂

አንዶን ምን አሰቦ ቀነሳት 🙄
ኢሳይያስ 53
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ የሰማነውን ነገር ማን አምኖአል? የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገልጦአል?
² በፊቱ እንደ ቡቃያ ከደረቅም መሬት እንደ ሥር አድጎአል፤ መልክና ውበት የለውም፥ ባየነውም ጊዜ እንወድደው ዘንድ ደም ግባት የለውም።
³ የተናቀ ከሰውም የተጠላ፥ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው፤ ሰውም ፊቱን እንደሚሰውርበት የተናቀ ነው፥ እኛም አላከበርነውም።
⁴ በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፤ እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው።
⁵ እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።
⁶ እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ።
⁷ ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም።
⁸ በማስጨነቅና በፍርድ ተወሰደ፤ ስለ ሕዝቤ ኃጢአት ተመትቶ ከሕያዋን ምድር እንደ ተወገደ ከትውልዱ ማን አስተዋለ?
⁹ ከክፉዎችም ጋር መቃብሩን አደረጉ፥ ከባለጠጎችም ጋር በሞቱ፤ ሆኖም ግፍን አላደረገም ነበር፥ በአፉም ተንኮል አልተገኘበትም ነበር።
¹⁰ እግዚአብሔርም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈቀደ፤ ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል፥ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል።
¹¹ ከነፍሱ ድካም ብርሃን ያያል ደስም ይለዋል፤ ጻድቅ ባሪያዬም በእውቀቱ ብዙ ሰዎችን ያጸድቃል፥ ኃጢአታቸውን ይሸከማል።
¹² ስለዚህም እርሱ ብዙዎችን ይወርሳል፥ ከኃያላንም ጋር ምርኮን ይከፋፈላል፤ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶአልና፥ ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጥሮአልና እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ፥ ስለ ዓመፀኞችም ማለደ።
መዝሙር 22
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹¹ ጭንቀት ቀርባለችና የሚረዳኝም የለምና ከእኔ አትራቅ።
¹² ብዙ በሬዎች ከበቡኝ፥ የሰቡትም ፍሪዳዎች ያዙኝ፤
¹³ እንደ ነጣቂና እንደሚጮኽ አንበሳ በላዬ አፋቸውን ከፈቱ።
¹⁴ እንደ ውኃ ፈሰስሁ አጥንቶቼም ሁሉ ተለያዩ፤ ልቤ እንደ ሰም ሆነ፥ በአንጀቴም መካከል ቀለጠ።
¹⁵ ኃይሌ እንደ ገል ደረቀ፥ በጕሮሮዬም ምላሴ ተጣጋ፥ ወደ ሞትም አሸዋ አወረድኸኝ።
¹⁶ ብዙ ውሾች ከብበውኛልና፤ የክፋተኞች ጉባኤም ያዘኝ፤ እጆቼንና እግሮቼን ቸነከሩኝ።
¹⁷ አጥንቶቼ ሁሉ ተቈጠሩ፤ እነርሱም አዩኝ ተመለከቱኝም።
¹⁸ ልብሶቼን ለራሳቸው ተከፋፈሉ፥ በቀሚሴም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ።
¹⁹ አንተ ግን፥ አቤቱ፥ ከእኔ አትራቅ፤ አንተ ጕልበቴ፥ እኔን ለመርዳት ፍጠን።
²⁰ ነፍሴን ከሰይፍ አድናት፥ ብቻነቴንም ከውሾች እጅ።
ዮሐንስ 19
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ በዚያን ጊዜም ጲላጦስ ኢየሱስን ይዞ ገረፈው።
² ወታደሮችም ከእሾህ አክሊል ጐንጕነው በራሱ ላይ አኖሩ ቀይ ልብስም አለበሱት፤
³ እየቀረቡም፦ የአይሁድ ንጉሥ ሆይ፥ ሰላም ለአንተ ይሁን ይሉት ነበር፤
⁴ በጥፊም ይመቱት ነበር። ጲላጦስም ደግሞ ወደ ውጭ ወጥቶ፦ እነሆ፥ አንዲት በደል ስንኳ እንዳላገኘሁበት ታውቁ ዘንድ እርሱን ወደ ውጭ አወጣላችኋለሁ አላቸው።
⁵ ኢየሱስም የእሾህ አክሊል ደፍቶ ቀይ ልብስም ለብሶ ወደ ውጭ ወጣ።
⁶ ጲላጦስም፦ እነሆ ሰውዬው አላቸው። የካህናት አለቆችና ሎሌዎች ባዩትም ጊዜ፦ ስቀለው ስቀለው እያሉ ጮኹ። ጲላጦስም፦ እኔስ አንዲት በደል ስንኳ አላገኘሁበትምና እናንተ ወስዳችሁ ስቀሉት አላቸው።
⁷ አይሁድም መልሰው፦ እኛ ሕግ አለን፥ እንደ ሕጋችንም ሊሞት ይገባዋል፥ ራሱን የእግዚአብሔር ልጅ አድርጎአልና አሉት።
⁸ ስለዚህ ጲላጦስ ይህን ነገር በሰማ ጊዜ እግጅ ፈራ፤
⁹ ተመልሶም ወደ ገዡ ግቢ ገባና ኢየሱስን፦ አንተ ከወዴት ነህ? አለው። ኢየሱስ ግን አንድ እንኳ አልመለሰለትም።
¹⁰ ስለዚህ ጲላጦስ፦ አትነግረኝምን? ልሰቅልህ ሥልጣን እንዳለኝ ወይም ልፈታህ ሥልጣን እንዳለኝ አታውቅምን? አለው።
¹¹ ኢየሱስም መልሶ፦ ከላይ ካልተሰጠህ በቀር በእኔ ላይ ምንም ሥልጣን ባልነበረህም፤ ስለዚህ ለአንተ አሳልፎ የሰጠኝ ኃጢአቱ የባሰ ነው አለው።
¹² ከዚህ በኋላ ጲላጦስ ሊፈታው ፈለገ፤ ነገር ግን አይሁድ፦ ይህንስ ብትፈታው የቄሣር ወዳጅ አይደለህም፤ ራሱን ንጉሥ የሚያደርግ ሁሉ የቄሣር ተቃዋሚ ነው እያሉ ጮኹ።
¹³ ጲላጦስም ይህን ነገር ሰምቶ ኢየሱስን ወደ ውጭ አወጣው፥ በዕብራይስጥም ገበታ በተባለው ጸፍጸፍ በሚሉት ስፍራ በፍርድ ወንበር ተቀመጠ።
¹⁴ ለፋሲካም የማዘጋጀት ቀን ነበረ፤ ስድስት ሰዓትም የሚያህል ነበረ፤ አይሁድንም፦ እነሆ ንጉሣችሁ አላቸው።
¹⁵ እነርሱ ግን፦ አስወግደው፥ አስወግደው፥ ስቀለው እያሉ ጮኹ። ጲላጦስም፦ ንጉሣችሁን ልስቀለውን? አላቸው። የካህናት አለቆችም፦ ከቄሣር በቀር ሌላ ንጉሥ የለንም ብለው መለሱለት።
¹⁶ ስለዚህ በዚያን ጊዜ እንዲሰቀል አሳልፎ ሰጣቸው።
¹⁷ ኢየሱስንም ይዘው ወሰዱት፤ መስቀሉንም ተሸክሞ በዕብራይስጥ ጎልጎታ ወደ ተባለው የራስ ቅል ስፍራ ወደሚሉት ወጣ።
¹⁸ በዚያም ሰቀሉት፥ ከእርሱም ጋር ሌሎች ሁለት፥ አንዱን በዚህ አንዱን በዚያ ኢየሱስንም በመካከላቸው ሰቀሉ።
¹⁹ ጲላጦስም ደግሞ ጽሕፈት ጽፎ በመስቀሉ ላይ አኖረው፤ ጽሕፈቱም፦ የአይሁድ ንጉሥ የናዝሬቱ ኢየሱስ የሚል ነበረ።
²⁰ ኢየሱስም የተሰቀለበት ስፍራ ለከተማ ቅርብ ነበረና ከአይሁድ ብዙዎች ይህን ጽሕፈት አነበቡት፤ በዕብራይስጥና በሮማይስጥ በግሪክም ተጽፎ ነበር።
²¹ ስለዚህ የአይሁድ ካህናት አለቆች ጲላጦስን፦ እርሱ፦ የአይሁድ ንጉስ ነኝ እንዳለ እንጂ የአይሁድ ንጉሥ ብለህ አትጻፍ አሉት።
²² ጲላጦስም፦ የጻፍሁትን ጽፌአለሁ ብሎ መለሰ።
²³ ጭፍሮችም ኢየሱስን በሰቀሉት ጊዜ ልብሶቹን ወስደው ለእያንዳንዱ ጭፍራ አንድ ክፍል ሆኖ በአራት ከፋፈሉት፤ እጀጠባቡን ደግሞ ወሰዱ። እጀ ጠባቡም ከላይ ጀምሮ ወጥ ሆኖ የተሠራ ነበረ እንጂ የተሰፋ አልነበረም።
²⁴ ስለዚህ እርስ በርሳቸው፦ ለማን እንዲሆን በእርሱ ዕጣ እንጣጣልበት እንጂ አንቅደደው ተባባሉ። ይህም፦ ልብሴን እርስ በርሳቸው ተከፋፈሉ በእጀ ጠባቤም ዕጣ ተጣጣሉበት የሚለው የመጽሐፍ ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው።
²⁵ ጭፍሮችም እንዲህ አደረጉ፦ ነገር ግን በኢየሱስ መስቀል አጠገብ እናቱ፥ የእናቱም እኅት፥ የቀለዮጳም ሚስት ማርያም፥ መግደላዊትም ማርያም ቆመው ነበር።
²⁶ ኢየሱስም እናቱን ይወደው የነበረውንም ደቀ መዝሙር በአጠገቡ ቆሞ ባየ ጊዜ እናቱን፦ አንቺ ሴት፥ እነሆ ልጅሽ አላት።
ማቴዎስ 27
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ሲነጋም የካህናት አለቆችና የሕዝቡ ሽማግሎች ሁሉ ሊገድሉት በኢየሱስ ላይ ተማከሩ፤
² አስረውም ወሰዱት፥ ለገዢው ለጴንጤናዊው ጲላጦስም አሳልፈው ሰጡት።
³ በዚያን ጊዜ አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ እንደ ተፈረደበት አይቶ ተጸጸተ፥ ሠላሳውንም ብር ለካህናት አለቆችና ለሽማግሎች መልሶ፦
⁴ ንጹሕ ደም አሳልፌ በመስጠቴ በድያለሁ አለ። እነርሱ ግን፦ እኛስ ምን አግዶን? አንተው ተጠንቀቅ አሉ።
⁵ ብሩንም በቤተ መቅደስ ጥሎ ሄደና ታንቆ ሞተ።
⁶ የካህናት አለቆችም ብሩን አንሥተው፦ የደም ዋጋ ነውና ወደ መባ ልንጨምረው አልተፈቀደም አሉ።
⁷ ተማክረውም የሸክላ ሠሪውን መሬት ለእንግዶች መቃብር ገዙበት።
⁸ ስለዚህ ያ መሬት እስከ ዛሬ ድረስ የደም መሬት ተባለ።
⁹ በዚያን ጊዜ በነቢዩ በኤርምያስ የተባለው፦ ከእስራኤል ልጆችም አንዳንዶቹ የገመቱትን፥ የተገመተውን ዋጋ ሠላሳ ብር ያዙ፥
¹⁰ ጌታም እንዳዘዘኝ ስለ ሸክላ ሠሪ መሬት ሰጡት የሚል ተፈጸመ።
¹¹ ኢየሱስም በገዢው ፊት ቆመ፤ ገዢውም፦ የአይሁድ ንጉሥ አንተ ነህን? ብሎ ጠየቀው፤ ኢየሱስም፦ አንተ አልህ አለው።
¹² የካህናት አለቆችም ሽማግሎችም ሲከሱት ምንም አልመለሰም።
¹³ በዚያን ጊዜ ጲላጦስ፦ ስንት ያህል እንዲመሰክሩብህ አትሰማምን? አለው።
¹⁴ ገዢውም እጅግ እስኪደነቅ ድረስ አንዲት ቃል ስንኳ አልመለሰለትም።
¹⁵ በዚያም በዓል ሕዝቡ የወደዱትን አንድ እስረኛ ሊፈታላቸው ለገዢው ልማድ ነበረው።
¹⁶ በዚያን ጊዜም በርባን የሚባል በጣም የታወቀ እስረኛ ነበራቸው።
¹⁷ እንግዲህ እነርሱ ተሰብስበው ሳሉ ጲላጦስ፦ በርባንን ወይስ ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን ማንኛውን ልፈታላችሁ ትወዳላችሁ? አላቸው፤
¹⁸ በቅንዓት አሳልፈው እንደ ሰጡት ያውቅ ነበርና።
¹⁹ እርሱም በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ሳለ ሚስቱ፦ ስለ እርሱ ዛሬ በሕልም እጅግ መከራ ተቀብያለሁና በዚያ ጻድቅ ሰው ምንም አታድርግ ብላ ላከችበት።
²⁰ የካህናት አለቆችና ሽማግሎች ግን በርባንን እንዲለምኑ ኢየሱስን ግን እንዲያጠፉ ሕዝቡን አባበሉ።
²¹ ገዢውም መልሶ፦ ከሁለቱ ማንኛውን ልፈታላችሁ ትወዳላችሁ? አላቸው፤ እነርሱም፦ በርባንን አሉ።
²² ጲላጦስ፦ ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን እንግዲህ ምን ላድርገው? አላቸው፤ ሁሉም፦ ይሰቀል አሉ።
²³ ገዢውም፦ ምን ነው? ያደረገው ክፋት ምንድር ነው? አለ፤ እነርሱ ግን፦ ይሰቀል እያሉ ጩኸት አበዙ።
²⁴ ጲላጦስም ሁከት እንዲጀመር እንጂ አንዳች እንዳይረባ ባየ ጊዜ፥ ውኃ አንሥቶ፦ እኔ ከዚህ ጻድቅ ሰው ደም ንጹሕ ነኝ፤ እናንተ ተጠንቀቁ ሲል በሕዝቡ ፊት እጁን ታጠበ።
²⁵ ሕዝቡም ሁሉ መልሰው፦ ደሙ በእኛና በልጆቻችን ላይ ይሁን አሉ።
²⁶ በዚያን ጊዜ በርባንን ፈታላቸው፥ ኢየሱስን ግን ገርፎ ሊሰቀል አሳልፎ ሰጠ።
²⁷ በዚያን ጊዜ የገዢው ወታደሮች ኢየሱስን ወደ ገዢው ግቢ ውስጥ ወሰዱት ጭፍራውንም ሁሉ ወደ እርሱ አከማቹ።
²⁸ ልብሱንም ገፈው ቀይ ልብስ አለበሱት፥
²⁹ ከእሾህም አክሊል ጎንጉነው በራሱ ላይ፥ በቀኝ እጁም መቃ አኖሩ፥ በፊቱም ተንበርክከው፦ የአይሁድ ንጉሥ ሆይ፥ ሰላም ለአንተ ይሁን እያሉ ዘበቱበት፤
³⁰ ተፉበትም መቃውንም ይዘው ራሱን መቱት።
³¹ ከዘበቱበትም በኋላ ቀዩን ልብስ ገፈፉት፥ ልብሱንም አለበሱት ሊሰቅሉትም ወሰዱት።
³² ሲወጡም ስምዖን የተባለው የቀሬናን ሰው አገኙ፤ እርሱንም መስቀሉን ይሸከም ዘንድ አስገደዱት።
³³ ትርጓሜው የራስ ቅል ስፍራ ወደሚሆን ጎልጎታ ወደሚባለው ስፍራ በደረሱ ጊዜም፥
³⁴ በሐሞት የተደባለቀ የወይን ጠጅ ሊጠጣ አቀረቡለት፤ ቀምሶም ሊጠጣው አልወደደም።
³⁵ ከሰቀሉትም በኋላ ልብሱን ዕጣ ጥለው ተካፈሉ፥
³⁶ በዚያም ተቀምጠው ይጠብቁት ነበር።
³⁷ ይህ ኢየሱስ የአይሁድ ንጉሥ ነው የሚል የክሱን ጽሕፈት ከራሱ በላይ አኖሩ።
³⁸ በዚያን ጊዜ ሁለት ወንበዶች አንዱ በቀኝ አንዱም በግራ ከእርሱ ጋር ተሰቀሉ።
³⁹ የሚያልፉትም ራሳቸውን እየነቀነቁ ይሰድቡት ነበርና፤-
⁴⁰ ቤተ መቅደስን የምታፈርስ በሦስት ቀንም የምትሠራው፥ ራስህን አድን፤ የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንህ ከመስቀል ውረድ አሉት።
⁴¹ እንዲሁም ደግሞ የካህናት አለቆች ከጻፎችና ከሽማግሎች ጋር እየዘበቱበት እንዲህ አሉ።
⁴² ሌሎችን አዳነ፥ ራሱን ሊያድን አይችልም፤ የእስራኤል ንጉሥ ከሆነ፥ አሁን ከመስቀል ይውረድ እኛም እናምንበታለን።
⁴³ በእግዚአብሔር ታምኖአል፤ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ብሎአልና ከወደደውስ አሁን ያድነው።
⁴⁴ ከእርሱ ጋር የተሰቀሉት ወንበዶች ደግሞ ያንኑ እያሉ ይነቅፉት ነበር።
⁴⁵ ከስድስት ሰዓትም ጀምሮ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በምድር ሁሉ ላይ ጨለማ ሆነ።
⁴⁶ በዘጠኝ ሰዓትም ኢየሱስ፦ ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ? ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህም፦ አምላኬ አምላኬ፥ ስለ ምን ተውኸኝ? ማለት ነው።
⁴⁷ በዚያም ከቆሙት ሰዎች ሰምተው፦ ይህስ ኤልያስን ይጠራል አሉ።
⁴⁸ ወዲያውም ከእነርሱ አንዱ ሮጠ፤ ሰፍነግም ይዞ ሆምጣጤ ሞላበት፥ በመቃም አድርጎ አጠጣው።
⁴⁹ ሌሎቹ ግን፦ ተው፥ ኤልያስ መጥቶ ያድነው እንደ ሆነ እንይ አሉ።
⁵⁰ ኢየሱስም ሁለተኛ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ነፍሱን ተወ።
⁵¹ እነሆም፥ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ፥ ምድርም ተናወጠች፥ ዓለቶችም ተሰነጠቁ፤
⁵² መቃብሮችም ተከፈቱ፥ ተኝተው ከነበሩትም ከቅዱሳን ብዙ ሥጋዎች ተነሡ፤
⁵³ ከትንሣኤውም በኋላ ከመቃብሮች ወጥተው ወደ ቅድስት ከተማ ገቡና ለብዙዎች ታዩ።
ማርቆስ 15
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ወዲያውም ማለዳ የካህናት አለቆች ከሽማግሌዎችና ከጻፎች ከሸንጎውም ሁሉ ጋር ከተማከሩ በኋላ፥ ኢየሱስን አሳስረው ወሰዱትና ለጲላጦስ አሳልፈው ሰጡት።
² ጲላጦስም፦ አንተ የአይሁድ ንጉሥ ነህን? ብሎ ጠየቀው። እርሱም፦ አንተ አልህ ብሎ መለሰለት።
³ የካህናት አለቆችም ብዙ ያሳጡት ነበር፤ እርሱ ግን ምንም አልመለሰም።
⁴ ጲላጦስም ደግሞ፦ አንዳች አትመልስምን? እነሆ፥ በስንት ነገር ያሳጡሃል ብሎ ጠየቀው።
⁵ ኢየሱስም ከዚያ በኋላ ጲላጦስ እስኪደነቅ ድረስ ምንም አልመለሰም።
⁶ በዚያም በዓል የለመኑትን አንድ እስረኛ ይፈታላቸው ነበር።
⁷ በዓመፅም ነፍስ ከገደሉት ከዓመፀኞች ጋር የታሰረ በርባን የተባለ ነበረ።
⁸ ሕዝቡም ወጥተው እንደ ልማዱ ያደርግላቸው ዘንድ እየጮኹ ይለምኑት ጀመር።
⁹ ጲላጦስም፦ የአይሁድን ንጉሥ እፈታላችሁ ዘንድ ትወዳላችሁን? ብሎ መለሰላቸው፤
¹⁰ የካህናት አለቆች በቅንዓት አሳልፈው እንደ ሰጡት ያውቅ ነበርና።
¹¹ የካህናት አለቆች ግን በርባንን በእርሱ ፈንታ ይፈታላቸው ዘንድ ሕዝቡን አወኩአቸው።
¹² ጲላጦስም ዳግመኛ መልሶ፦ እንግዲህ የአይሁድ ንጉሥ የምትሉትን ምን ላደርገው ትወዳላችሁ? አላቸው።
¹³ እነርሱም ዳግመኛ፦ ስቀለው እያሉ ጮኹ።
¹⁴ ጲላጦስም፦ ምን ነው? ያደረገው ክፋት ምንድር ነው? አላቸው። እነርሱ ግን፦ ስቀለው እያሉ ጩኸት አበዙ።
¹⁵ ጲላጦስም የሕዝቡን ፈቃድ ሊያደርግ ወዶ በርባንን ፈታላቸው፥ ኢየሱስንም ገርፎ እንዲሰቀል አሳልፎ ሰጠ።
¹⁶ ወታደሮችም ፕራይቶሪዮን ወደሚባል ግቢ ውስጥ ወሰዱት፥ ጭፍራውንም ሁሉ በአንድነት ጠሩ።
¹⁷ ቀይ ልብስም አለበሱት፥ የእሾህ አክሊልም ጎንጉነው ደፉበት፤
¹⁸ የአይሁድ ንጉሥ ሆይ፥ ሰላም ለአንተ ይሁን እያሉ እጅ ይነሱት ጀመር፤
¹⁹ ራሱንም በመቃ መቱት ተፉበትም፥ ተንበርክከውም ሰገዱለት።
²⁰ ከተዘባበቱበትም በኋላ ቀዩን ልብስ ገፈፉት፥ ልብሱንም አለበሱት፥ ሊሰቅሉትም ወሰዱት።
²¹ አንድ መንገድ አላፊም የአሌክስንድሮስና የሩፎስ አባት ስምዖን የተባለ የቀሬና ሰው ከገጠር ሲመጣ መስቀሉን ይሸከም ዘንድ አስገደዱት።
²² ትርጓሜውም የራስ ቅል ስፍራ ወደሚሆን ጎልጎታ ወደተባለ ስፍራ ወሰዱት።
²³ ከርቤም የተቀላቀለበትን የወይን ጠጅ እንዲጠጣ ሰጡት፤ እርሱ ግን አልተቀበለም።
²⁴ ሰቀሉትም፥ ልብሱንም ማን ማን እንዲወስድ ዕጣ ተጣጥለው ተካፈሉ።
²⁵ በሰቀሉትም ጊዜ ሦስት ሰዓት ነበረ።
²⁶ የክሱ ጽሕፈትም፦ የአይሁድ ንጉሥ የሚል ተጽፎ ነበር።
²⁷ ከእርሱም ጋር ሁለት ወንበዶች አንዱን በቀኙ አንዱንም በግራው ሰቀሉ።
²⁸ መጽሐፍም፦ ከአመፀኞች ጋር ተቆጠረ ያለው ተፈጸመ።
²⁹ የሚያልፉትም ራሳቸውን እየነቀነቁ ይሰድቡት ነበርና። ዋ፥ ቤተ መቅደስን የምታፈርስ በሦስት ቀንም የምትሠራ፥
³⁰ ከመስቀል ወርደህ ራስህን አድን አሉ።
³¹ እንዲሁም የካህናት አለቆች ደግሞ ከጻፎች ጋር እርስ በርሳቸው እየተዘባበቱ፦ ሌሎችን አዳነ፤ ራሱን ሊያድን አይችልም፤
³² አይተን እናምን ዘንድ የእስራኤል ንጉሥ ክርስቶስ አሁን ከመስቀል ይውረድ አሉ። ከእርሱም ጋር የተሰቀሉት ይነቅፉት ነበር።
³³ ስድስት ሰዓትም በሆነ ጊዜ፥ እስከ ዘጠኝ ሰዓት በምድር ሁሉ ላይ ጨለማ ሆነ።
³⁴ በዘጠኝ ሰዓትም ኢየሱስ፦ ኤሎሄ፥ ኤሎሄ፥ ላማ ሰበቅታኒ? ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ፤ ትርጓሜውም አምላኬ፥ አምላኬ፥ ለምን ተውኸኝ? ማለት ነው።
³⁵ በዚያም ከቆሙት ሰዎች ሰምተው፦ እነሆ፥ ኤልያስን ይጠራል አሉ።
³⁶ አንዱም ሮጦ ሆምጣጤ በሰፍነግ ሞላ በመቃም አድርጎ። ተዉ፤ ኤልያስ ሊያወርደው ይመጣ እንደ ሆነ እንይ እያለ አጠጣው።
³⁷ ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ጮኸ ነፍሱንም ሰጠ።
ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግስትከ ..
በከመ ተዘከርኮ ለፈያታዊ ዘየማን
ኦ ዘጥዑመ ሞተ በስጋ 😭
ጊዜ ትወፅእ ነፍስከ እስከ ይሰማዕ ኩለሄ
ኦ ዘትቤ ኤሎሄ ኤሎሄ ።
ኢየሱስ ክርስቶስ ርኅራኄ።
Audio
መዳፉ ላይ ቁስል ካያችሁ

መዳፉ ላይ ቁስል ካያችሁ
የህማም ሰው ካስተዋላችሁ
ውዴ እርሱ ነው ነፍሴን የያዛት
በዕንቁ ሳይሆን በደም የገዛት....

መዝሙር
ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን


ትንሳኤ (ፍፃሜ ጾም)

የዕለተ ሰንበት መዝሙር፣ ይትፌሳህ

🔔ምስባክ(ዘቅዳሴ)፡
መዝ 117: 24-25

ዛቲ ዕለት እንተ ገብረ እግዚአብሔር
ንትፈሳህ ወንትሐሰይ ባቲ
ኦ እግዚኦ አድህንሶ

ትርጒም፦
እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት፤
ሐሤትን እናድርግ፥ በእርስዋም ደስ ይበለን።
አቤቱ፥ እባክህ፥ አሁን አድን፤

🔔መልእክታት
👉 1ቆሮ 15፡20-41
👉 1ኛ ጴጥ 1፡1-13
👉 ግብ ሐዋ 2፡22-37

🔔ወንጌል
👉 ዮሐ 20፡1-19
………………….

👉ቅዳሴ : ዘዲዮስቆሮስ (እምቅድመ ዓለም)

ጾሙን ጾመን ለመጨረስ የረዳን እግዚአብሔር የዛሬ ዓመት በሰላም በጤና ጠብቆ ያድርሰን!🙏
"ሙሴም ሞትን ያጠፋ ዘንድ አልቻለም፤ እርሱንም ይዞ ገዛው እንጂ፤ ከእርሱም በኋላ የተነሡ ነቢያትንም ሁሉ ሞት ገዛቸው እንጂ፡፡ ክርስቶስ ግን በቸርነቱ ለሁሉ ሕይወትን ሰጠ።"
       ቅዱስ አቡሊዲስ ዘሮም

እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤ በሰላም አደረሰን፣ አደረሳችሁ
2024/10/01 09:22:09
Back to Top
HTML Embed Code: