Telegram Web Link
መ. ቅዱሳን ሐዋርያት ከወሰኗቸው የሕግጋት መጻሕፍት መካከል አንዱ በሆነው በመጽሐፈ ዲድስቅልያ አንቀጽ 1 ንዑስ አንቀጽ 2 ላይ “ወአዘዝነ ከመዝ መዓርገ ሢመታት ለቤተ ክርስቲያን በአርአያ ዘበሰማያት የቤተ ክርስቲያናችን የሹመቶች መዓርግ በሰማያት ባለው አምሳል እንዲሆን አዘዝን” በማለት በንዑስ አንቀጽ 3 ላይ “ወንሕነ ንጌሥጽክሙ ከመ ይንበር ኲሉ ለለ አሐዱ አሐዱ እምኔክሙ ውስተ ዘተጸውዐ እምኀበ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ - ከእናንተ ሁሉ እያንዳንዱ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ በተጠራበት ተልእኮ ጸንቶ ይኖር ዘንድ እኛ እንመክራችኋለን በማለት እያንዳንዱ በቀኖና ቤተ ክርስቲያን በተሰጠው ፀጋና ተልእኮ ጸንቶ ከሚኖር በቀር ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን ውጭ ባልተሰጠውና ባልተፈቀደለት በሕገወጥ መንገድ ሊሾምም ሆነ ሊሾም እንደማይገባው የሚያስተምረን አምላካዊ ቃል ነው፡፡

ሠ. ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ በመጽሐፈ ዲድስቅልያ አንቀጽ 20 ላይ “በእንተ ዘይሰየም በህልያን እመሂ ኤጲስ ቆጶስ አው ቀሲስ አው ዲያቆን ዘይእኀዝ መዓርገ ሢመት በሕልያን ይሰአር፤ ወይሰዐር ዘሤሞሂ ወይትመተር ለዝሉፉ እምሥርዐተ ክህነት፤ ወኢይሳተፍዎ ወኢበምንትኒ በከመ ረሰይክዎ ለሲሞን መሠርይ እምኀቤየ አነ ጴጥሮስ - መማለጃ በመስጠት ስለሚሾም ኤጲስ ቆጶስ ወይም ቄስ ወይም ዲያቆን ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን ውጭ የሹመት መዓርግ ቢይዝ ይሻር፣ የሾመውም ይሻር ከክህነት ሥርዓትም እስከ መጨረሻው ይባረር፡፡ እኔ ጴጥሮስ ጠንቋዩ ሊሞንን እንዳደረግሁት በምንም ነገር አያሳትፉት (ሲኖ.ዘሐዋ.ክፍል 3 ቁጥር 20) በማለት ቅዱስ ጴጥሮስ ሥልጣነ ክህነትን ያለአግባብ የሰጠም ሆነ የተቀበለ አካል እስከመጨረሻው ድረስ ከሥርዓተ ክህነት ውጭ እንዲሆን አውግዟል፡፡ በማለትና ሌሎችንም ሕገ ቤተ ክርስቲያንንና ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ዋቢ በማድረግ በሊቃውንት ጉባኤ የቀረበውን የውሳኔ ምክረ ሐሳብ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በአድናቆትና በአክብሮት ተቀብሎ ተወያይቶበታል፡፡

በመሆኑም ከላይ ቀኖና ሕገ ቤተ ክርስቲያን መሠረት አድርጎ ከቀረበው ምክረ ሐሳብና በቤተ ክርስቲያኒቱና በምዕመናን ላይ ከደረሰው ሞት፣ የአካልና የሞራል ጉዳት፣ እስራትና እንግልት አንጻር ውግዘቱ ሊነሣ የማይገባውና በሕግም የሚያስጠይቅ ሕገወጥ አድራጎት ቢሆንም አሁን በተከሰተው ድርጊት በአጭር ጊዜ ውስጥ በእናት ቤተ ክርስቲያን ላይ እና በተከታዮቿ ምዕመናንና አገልጋዮቿ ላይ ከደረሰው ከፍተኛ ጉዳት አንጻር ችግሩን በሆደ ሰፊነትና በይቅርባይነት መፍታት ካልተቻለ አሁን ያለው መከራና ችግር ይቀጥል ቢባል በቀጣይ በቤተ ክርስቲያኒቱ አንድነትና ሐዋርያዊ ተልዕኮ እንዲሁም በምዕመናንና አገልጋዮቿ ሰላማዊ ጉሮ ላይ የሚያደርሰውን ከፍተኛ የሆነ አደጋ ከግምት ውስጥ በማስገባት እና ካሁን ቀደም ክቡር የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተገኙበትና በመቀጠልም ክቡር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮምያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት በተገኙበት በተደረገው ውይይት በተደረሰው 10ሩ የስምምነት ነጥቦች መሠረት ቅዱስ ሲኖዶስ በስፋት ከተወያየ በኋላ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አሳልፏል፡፡

1. የካቲት 8 ቀን 2015 ዓ.ም. በክቡር የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚ/ር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ መሪነት ወደ ጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ በመምጣት እስካሁን ድረስ በበዓታቸው ጸንተው የቆዩት 3ቱም የቀድሞ ሊቃነ ጳጳሳት ማለትም ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ፣ ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ እና ብፁዕ አቡነ ዜናማርቆስ ላይ አስቀድሞ ጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም. በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የተላለፈው ውግዘት ከዛሬ መጋቢት 21 ቀን 2015ዓ.ም. ጀምሮ ተነስቷል፡፡

2. ውግዘቱ የተነሣላቸው 3ቱም ሊቃነ ጳጳሳት ከዛሬ መጋቢት 21 ቀነ 2015ዓ.ም. ጀምሮ በቀድሞ የሊቀ ጳጳስነት ማዕረጋቸውና ስማቸው ማለትም ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ሊቀጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ሊቀጳጳስ እና ብፁዕ አቡነ ዜናማርቆስ ሊቀጳጳስ ተብለው እንዲጠሩና አስቀድሞ ተመድበው ይሰሩበት በነበረው የሥራ ኃላፊነታቸው ሥራቸውን እንዲቀጥሉ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

3. ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት በተደረገው ውይይት በተደረሰው ስምምነት መሠረት ጥሪውን ተቀብለው ለስምምነቱ ተገዥ በመሆን በጽሑፍ ጥያቄያቸውን ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ያቀረቡት 20ዎቹ የቀድሞ መነኮሳት ጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም. በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ውሳኔ የተላለፈው ውግዘት ከዛሬ መጋቢት 21 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ተነስቷል፡፡ ቀሪዎቹ 5ቱ ባለው ጊዜ ተጠቅመው ወደቤተ ክርስቲያናቸው እንዲመለሱ ቅዱስ ሲኖዶስ በድጋሚ እያሳሰበ ውግዘቱን በሚመለከት በቋሚ ሲኖዶስ በኩል ታይቶ እንዲፈጸም ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

4. ውግዘቱ የተነሣላቸው 20ዎቹም የቀድሞ መነኮሳት አስቀድሞ በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት ከዲቁና እስከ ቁምስና ባለው ማዕረገ ክህነታቸው እንዲያገለግሉ እና በምንኩስና ስማቸውም እንዲጠሩ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

5. 20ዎቹ የቀድሞ መነኮሳት የሥራ ምደባን በተመለከተ በተደረሰው ስምምነት መሠረት በቀድሞው የሥራ መደብ ደረጃቸው እንዲመደቡ ቅዱስ ሲኖዶስ በመወሰን ዝርዝር ጉዳዩ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በኩል እንዲፈጸም ቅዱስ ሲኖዶስ አዟል፡

6. በተከሰተው ሕገወጥ ድርጊት መነሻነት ለቤተ ክርስቲያናችን ክብርና ልዕልና ሲሉ ለሞት፣ ለአካልና የሞራል ጉዳት፣ ለእስራትና እንግልት እንዲሁም ለስደት የተዳረጉትን ምዕመናን፣ ወጣቶች፣ አገልጋይ ካህትና ከሀገረ ስብከት እስከ አጥቢያ ያሉ የሥራ ኃላፊዎችን ጉዳትና መከራ እንዲሁም ችግሩን በሕግ አግባብ እንዲፈታና የቤተ ክርስቲያኒቱ መብትና ጥቅም እንዲከበር ሌሊት ከቀን በማገልገል ላይ የሚገኙትን የሕግ ባለሙያዎች ማህበር የሰጡትን ሙያዊ አገልግሎት ቅዱስ ሲኖዶስ ዘወትር በከባድ ሐዘንና ጸሎት ሲያስታውሰው የሚኖርና በቀጣይ በቤተ ክርስቲያኒቱ የታሪክ መዛግብት ተመዘግቦ ለቀጣዩ ትውልድ መማሪያነት እንዲውል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

7. ውግዘቱ የተነሣላችሁ የቤተ ክርስቲያኒቱ አገልጋይ አባቶችም በቀጣይ በፈጸማችሁት ድርጊት የተጎዳውን መላው ሕዝበ ክርስቲያን እና ክብሯ የተደፈረውን እናት ቤተ ክርስቲያናችሁን ሊክስ በሚችል የትሕትና መንፈስ በማገልገልና ዳግመኛ ከእንዲህ ዓይነቱ ሕገወጥ አድራጎት በመራቅ የተጣለባችሁን ከፍተኛ ኃላፊነት በታማኝነት እንድትወጡ ቅዱስ ሲኖዶስ በጥብቅ ያሳስባል፡፡

8. በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የደረሰውን ፈተና እንዲወገድና የቤተ ክርስቲያኒቱ መብትና ክብር እንዲጠበቅ ቤተ ክርስቲያኒቱን ወክላችሁ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመሩት የውይይት መድረክ ላይ በመሳተፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከታችሁ ሦስቱ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ናትናኤል፣ ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ እና ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል እና አቀራራቢ የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም በፍትሕ አደባባይ ክስ በመመስረት የደከማችሁ የሕግ ባለሙያዎች ማህበር እና ችግሩን ለመላው ዓለም በማዳረስ ሰፊ ሥራ የሠራችሁ የሚዲያ ተቋማትን ቅዱስ ሲኖዶስ ለሰጣችሁት ታሪክ የማይረሳው አገልግሎት በእጅጉ ያመሰግናል፡፡
9. ምንም እንኳን አስቀድሞ ከክቡር የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ክቡር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮምያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ጋር በተደረገው ውይይትና ስምምነት መሠረት የታሰሩት ግለሰቦች በሙሉ እንደሚፈቱ ቃል የተገባ ቢሆንም እስካሁን ድረስ በርካታ ሰዎች በእስር ላይ የሚገኙ ስለሆነ መንግስት አስቀድሞ በገባው ቃል መሠረት ሁሉንም እስረኞች እንዲፈታልን ቅዱስ ሲኖዶስ በጥብቅ ያሳስባል፡፡

10. በተከሰተው ችግር ከሀገረ ስብከት እስከ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ባሉት የቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅር ላይ በኃላፊነት ተመድበው ሲሰሩ ቆይተው በችግሩ ምክንያት ተፈናቅለው የቆዩት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የሀገረ ስብከትና የወረዳ ቤተ ክህነት ሠራተኞች ያለምንም የፀጥታ ስጋት በምድብ ሥራቸው ላይ እንዲቀጥሉ ከፌዴራል ጀምሮ በየደረጃው ያሉ የመንግስት አካላት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳስባል፡፡


መጋቢት 21 ቀን 2015 ዓ.ም.
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ
#አትርሳ!

አንድ ሰው ወደ ቤተ መንግሥት አንዲት ሴተኛ አዳሪን ይዞ መጥቶ በንጉሡ ፊትም ሩካቤ ቢፈጽም፣ ወይም ቢሰክር፣ ወይም ይህን የመሰለ ሌላ ተግባር ቢፈጽም የቅጣት ቅጣት ይደርስበታል፡፡

አሁን ራሳችንን ጥያቄ እንጠይቅ፡፡ እግዚአብሔር የሰማይም የምድርን ንጉሥ ነው ወይስ አይደለም? ነው! የምናደርገውን ማንኛውም ድርጊት ይመለከታል ወይስ አይመለከትም? ኧረ ይመለከታል!
ታዲያ በምድራዊ ንጉሥ ፊት ከላይ የጠቀስናቸውን ነውሮች ደፍሮ የፈጸመ ሰው ጽኑ ቅጣት የሚቀጣ ከኾነ እንደዚህ ያሉ ተግባራትን በእግዚአብሔር ፊት ለማከናወን የምንደፍረው ለምንድን ነው? ምድራዊው ንጉሥ ቢቀጣ ምድራዊ ቅጣትን ነው፡፡ ሰማያዊው ንጉሥ ሲቀጣ ግን ሰማያዊ ቅጣት እንደ ኾነ አናውቅምን? ...

ሰው ሆይ! እያንዳንዷን ድርጊትህ የሚመለከት የሰማይም የምድርም ንጉሥ እንዳለ በፍጹም አትርሳ፡፡

(
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ- አምስቱ የንስሐ መንገዶች እና ሌሎች - ገጽ 119)
በትግራይ የሚገኙ በጦርነት የተጎዱ አብያተክርስቲያናት በክፍት ጣራ፣ በተቀደዱ ልብሰ ተክኖ፣በተሰባበሩ ነዋዬተ ቅዱሳት ስርዓተ ቅዳሴ እየተከናወነባቸው ነው።
***
ድጋፍ ይፈልጋሉ እና እንረባረብ።

በሰሜኑ ጦርነት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ገዳማት እና አድባራት ጣሪያቸው በከበባድ መሳርያ ከመገንደሱ የተነሳ ዝናብ እና ንፋስ በሚያስገባባቸው ህንጻ መቅደሶች፣ በመሣርያ በተቃጠሉ ልብሰ ተክኖ፣በተሰባበሩ ነዋዬተ ቅዱሳት

የክርስቶስን አማናዊ ሥጋ እና ቅዱስ ደሙን ለምዕመናንን እያቀበሉ ነው። አሁን ጥቂት የአከባቢው ምዕመናንን ይህኝን አደጋ የደረሰባቸውን ህንጻ መቅደሶች ለመደገፍ እንቅስቃሴ የጀመሩ ሲሆን ከታች ባለው ከወጋገን ባንክ አድራሻ የበኩላችንን አስተዋጽኦ ታበረክቱ ዘንድ ቅድስት ቤተክርስቲያን ጥሪዋን ታስየላልፋለች።

// ደብረ መድሃኒት ኢየሱስ ኣዘባ ( 09592937_30301) ወጋገን ባንክ )(0914029950 //
***
// ቅድስቲ ማርያም ቤተክርስትያን ዓዲ ዓጻውር (0013201135931300) ወጋገን (0914779474) //
***
//ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስትያን ማይ ዓይኒ (0960017230101) ወጋገን ባንክ( ስልኪ 0933112299 //
***
ኣቡነ ኣረጋዊ ማይ ሽኻ 0958794930101(ወጋገን ባንክ (0914557450
ጌታዬ ጨነቀኝ !

መክሊት የስሜት ሕዋሳት
የህሊና ዙፋን ፥ የልቦና አብርሆት
የተፈጥሮ መስተጋብር ፥ ስርዓተ ዑደት
የሕይዎት ውጣ ውረድ ፥ ማግኜትና ማጣት
መታመም ፥ መፈወስ ፤ መኖርና መሞት
ርሀብና ጥም
ብርታትና ድካም

ሀዘንና ደስታ ፣... እነዚህ ሁላቸው
የማተርፍባቸው ፥ በርግጥም መክሊት ናቸው።

ማትረፍ ማለት ለእኛ ...
የሰጠኸን መክሊት ፥ ሲሆነን መዳኛ !

በምድራዊው መክሊት ፥ በኃላፊው ዓለም
በጥቂቱ ታምኖ ፥ በብዙው መሸለም
በዘላለማዊነት ፥ በሰማዩ መሾም
በሕይዎት ስጦታነት ፥ በተሰጡት መክሊት
የክርስቶስ መሆን ፥ ወደ ደስታ መግባት።

ነገር ግን ጌታዬ..!

ወደ ጌታዬ ደስታ ፥ መግባትን ብወድም
የአንተ መሆንና አንተን መምሰል ብሻም
በሰጠኸኝ መክሊት ፥ አተርፍበት ዘንድ ግን ፥ ለእኔ አልሆነልኝም

ይልቁንም !

የስሜት ሕዋሳቴ ፥ በዓለም ፍቅር ባክነው
ሁካት ጫጫታን ፥ ለመስማት ጀግነው
ስጋዊ ፍትወት ፥ ዓለምና አምሮቷ
ረጋፊ መልኳ ፥ ሚከስም ውበቷ

በማይቆይ በማይበረክት ፥ በማይጠቅም ጥማት
በተሰሎንቄ ፍቅር ፥ ወድቀው በምርኮነት

ለከንቱነት ተግተው
እንቅልፋቸውን ሰውተው
የምድራዊ ዕንቅብ በላያቸው ተከድኖ
በዓለማዊነት ልብ ውስጥ ሀሳባቸው ተዳፍኖ ...

በርሱ ልከብርበት ፥ ልመሰገንበት
ወደ ጌታ ደስታ ፥ ከቶ ልገባበት
ለእኔ ያዘጋጀኸው ፥ የሰጠኝ መክሊት
ስለ ስንፍናዬ ፥ አንገቴን ሲያስደፋኝ ፥ ሆኖብኝ  ለውርደት...

ከቀናት በፊት ፥ እንደምትመጣ በነገርከኝ ሳምንት
በልቤ በሀሳቤ ተራራ ወጥቼ ፥ ውዬ በደብረዘይት
መጥተህ ዝም እንዳትል ፥ ሳሰላስል ሳለሁ
ከአገልጋዮችህ ነገር ፥ ከገብርሄር ደረስሁ

ጌታዬ አምላኬ ፥ እውነት ነው አምናለሁ !
አንተ ትመጣለህ ፥ ጌታዬን አምላኬን ፥ በዙፋን አይሃለሁ ፤
ስትመጣም ፥ ዝም አትልም ፥ ስለሰጠኸኝ መክሊት ፥ አወ እጠየቃለሁ ፤

በስንፍና ብዛት ፥ መክሊቶቼ ባክነው
ትርፍንም ያይደለ ፥ በኪሳራ ሳለው
ያኔ ወደ እኔ ስትመጣ ፥ ምን እመልሳለሁ ?

እያልኩ አወጣለሁ
እያልኩ አወርዳለሁ...

አወ !

አንተ አምላኬ ፥ ያኔ ስትጠይቀኝ
ምን ልመልስልህ ፥ ጌታዬ ጨነቀኝ !

ዮሴፍ ጌትነት
ከሕገ ወጡ ሹመት ጋር በተያያዘ የታሰሩ የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት የሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች ትናንት በዋለው የፍርድ ቤት ውሎ የ4 ቀን ቀነ ቀጠሮ ተሰጠባቸው።
++++++++++
በሕገ ወጡ ሹመት ምክንያት የታሠሩት የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ፀሐፊው፣ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊው፣ የአርሲ ነጌሌ የወረዳ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ እንዲሁም ተጨማሪ 6 ግለሰቦችን የያዘው የክስ ሒደት ትናንት በዋለው የፍርድ ቤት ውሎ የ4 ቀን ቀነ ቀጠሮ እንደተሰጠባቸው ተገልጿል።

ሀገረ ስብከቱ ዋና ፀሐፊ ቀሲስ ወንድወሰን ጥላሁንና የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊው መምህር ሰሎሞን ዘገየን ጨምሮ 7ቱ ግለሰቦች ሕገ ወጡን ሹመት ባለመቀበላቸው ምክንያት ከታሰሩ 60 ቀናትን አስቆጥረዋል።

ትናንት መጋቢት 21 ቀን 2015 ዓ/ም በተደረገው የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልዐተ ጉባኤም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮምያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ጋር በተደረገው ውይይትና ስምምነት መሠረት የታሰሩት ግለሰቦች በሙሉ እንደሚፈቱ ቃል የተገባ ቢሆንም እስካሁን ድረስ በርካታ ሰዎች በእስር ላይ የሚገኙ ስለሆነ መንግስት አስቀድሞ በገባው ቃል መሠረት ሁሉንም እስረኞች እንዲፈታልን ሲል ቅዱስ ሲኖዶስ በጥብቅ ማሳሰቡ ይታወሳል ሲል የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ሕዝብ ግንኙነት ዘግቧል።

©ተዋሕዶ ሚድያ


ኒቆዲሞስ (የዐቢይ ጾም ሰባተኛ እሑድ)
የዕለተ ሰንበት መዝሙር፣ ሖረ ኀቤሁ


ምስባክ፡
መዝ 16:3-4
ሐወፅከኒ ሌሊተ ወፈተንኮ ለልብዬ
አመከርከኒ ወኢተረክበ ዓመፃ በላዕሌየ
ከመ ኢይንብብ  አፉየ ግብረ እጓለ እመሕያው

ትርጒም፦
ልቤን ፈተንኸው በሌሊትም ጐበኘኸኝ፤
ፈተንኸኝ፥ ምንም አላገኘህብኝም።
የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር ፈቃዴ ነው፤


መልእክታት
👉 ሮሜ 7፡1-12
👉 1ኛ ዮሐ 4፡18-ፍጻሜው
👉 ግብ ሐዋ 5፡34-ፍጻሜው


ወንጌል
👉 ዮሐ 3፡1-12


የሚቀደሰው ቅዳሴ
👉ቅዳሴ :ዘእግትነ (ጎሥዓ)

ጾሙን ጾመ በረከት ያድርግልን!
☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️
እንኳን ለጻድቁ አባታችን ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት በዓለ ጽንሰት በሰላም አደረሳችኹ፤ አደረሰን!

"ሰላም ለፅንሰትከ ወለልደትከ እምከርሥ። አመ እሥራ ወረቡዑ ለወርኀ ታኅሣሥ። ተክለ ሃይማኖት በኵሉ ወበውስተ ኵሉ ውዱስ። ናሁ ወጠንኩ ወእቤ ለስብሐቲከ ሐዲስ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ

ተክለ ሃይማኖት ኾይ፤ አስቀድሞ በማኅፀን ለተፀነስከው ፅንሰትኽና በታኅሣሥ ሃያ አራት ቀን ለተወለድክበት መወለድኽ ሰላም እላለኹ። ቅዱስ አባት፤ ኹሉ በኹሉ የተመሰገንኽ ነኽና እኔም በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ብዬ እነኾ አዲስ ምስጋናን እጀምራለኹ።"

      መልክአ አቡነ ተክለ ሃይማኖት

"ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም!"

🌿💫🌿💫🌿💫🌿💫🌿💫🌿💫🌿💫
ኒቆዲሞስ ክቡር
ዝማሬ ዳዊት On Telegram
#ኒቆዲሞስ

ኒቆዲሞስ ኒቆዲሞስ ክቡር
ሌቱን በብርሃን የሚማር መምህር

በጨለማው ግርማ ኮከብ የደመቀ
በመከራው ፅናት ይህን ዓለም ናቀ
መምህር ሆኖ ሳለ ከመማር ያልራቀ
የትዕቢትን ጅረት በትህትና ተዋርዶ አደረቀ

ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
አኮኑ አፅባይት እምነ አፅባይት የአቢ
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ

#አዝ......

ፍርሃትን በሚጥል ፍፁም ፍቅር ያደረ
ከመስቀል አውርዶ ጌታውን ቀበረ
የመግነዙን በፍታ በሽቶ አከበረ
ከመቅደሱ አንቀፅ ላይረሳ አምድ ሆኖ ታጠረ

ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
አኮኑ አፅባይት እምነ አፅባይት የአቢ
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ

#አዝ......

ለሊትም ለሊት ዕውቀትን ነገረች
ህጉን ለሚያስበው ምክር አለኝ እያለች
ከጨለማ ሀጢያት ነግታ ብርሃን ከአየች
እንደ ኒቆዲሞስ ነፍስህም ተምራ ተመለሰች

ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
አኮኑ አፅባይት እምነ አፅባይት የአቢ
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ

#ዘማሪ፦ ዲያቆን ዘማሪ ቀዳሚፀጋ
አልሃምዲሊላህ

ጉልባኑም ጥሩ ነው 😂 እንደ ንግስት ስንዱ ደባልቄ አባባል በሄኖክ አቆጣጠራ ሰሞነ ህማማት ላይ ነን ። በቃ ሳምንት አርብ መፈሰካች ነው 😂

ይችን ባዶ መላ የሚል ጠፋ ከነ አምላኪዎቾ 😡
እፎ ሰቀሉከ ካህናተ ይሁዳ ወሌዊ 🙄
ምንሼ ነው ራስታ
2024/10/01 09:28:19
Back to Top
HTML Embed Code: