Telegram Web Link
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በደንብ እዩት ሁላችሁም በትርጉም ነው
ከፍጥሪያ በኋላ 💪🙄🙈😁
ጨረቃ ምንሼ ነው 😁

ነገ ነው እኮ የምትታየው ሳውዲ እንደውም እኛ ሰፈር ሳምንት ነው የምትመጣው ።
ብፁዕ አቡነ አረጋዊ ዶ/ር ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል!

ብፁዕ አቡነ አረጋዊ ዶ/ር የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት እና የውጪ ግንኙነት መምሪያ የበላይ ኃላፊ የድሬዳዋና የጅቡቲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል። ብፁዕነታቸው ለረጅም ጊዜ ከሀገር ውጪና በሀገር ውስጥ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ሊሻላቸው ሳይችል ቀርቶ ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ ተለይተዋል።
EOTC
25ቱ ህገወጥ ተሿሚዎች ጠቅላይ ቤተክህነት ተገኝተዋል።

ለይቅርታ የተሰጠው ቀን ከማለቁ በፊት ነው በ5ኪሎ ጠቅላይ ቤተክህነት እንዲገኙ የተደረገው። በአሁኑ ሰዓት 25ቱ ህገወጥ ተሿሚዎች ሙሉ ለሙሉ ከሮሚያ ክልል ወጥተው 5 ኪሎ ቤተክህነት ይገኛሉ።

እግዚአብሔር የእውነት ያድርገው
የብፁዕ ዶ/ር አቡነ አረጋዊ የሕይወት ታሪክ

#ውልደት
የቀድሞው አባ ኃይለ ማርያም መለሰ የኋላው ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) ከአባታቸው ከሊቀ መዘምር መለስ አየነው ደስታና ከእናታቸው ከወ/ሮ ፀሐይ ገብረ አብ በሰሜን ጎንደር ደብረ ሰላም ሎዛ ማርያም አካባቢ በ1961 ዓ.ም ተወለዱ።

#ትምህርት
• ፊደል፥ ንባብ፥ ዳዊትና ቅዳሴ ከመርጌታ ሙሴ ብፅዐ ጊዮርጊስ ተምረዋል።
• ቅኔ፥ ከግጨው መንከር ምንዝሮ ተክለ ሃይማኖት፥ ሐዲሳት፥ ከመጋቤ ሐዲስ ወልደ ሰንበት ግምጃ ቤት ማርያም ተምረዋል።
• 1ኛና 2ኛ ከፍተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በዐፄ ፋሲል፡ መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ደግሞ በዳግማይ ደብረ ሊባኖስ አዘዞ ተክለ ሃይማኖት ት/ቤቶች ተምረዋል።
• ከሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ በቴዎሎጂ ዲፕሎማ፥
• ከቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በቴዎሎጂ ዲግሪ፥
• ከኖርዌይ ስታቫንገር ስፔሻላይዝድ ዪኒቨርስቲ የማስተርስ ዲግሪ፥
• ከፕሪቶርያ ዩኒቨርስቲ በፍልስፍና የፒኤችዲ ዲግሪ አግኝተዋል።

#ቋንቋ
• ከእንግሊዝኛ በተጨማሪ የኖርዌይ፥ የስዊድንና የዴንማርክ ቋንቋዎችን ይችላሉ፡፡

#መዐርገ_ክህነት
• ዲቁና - በ1968 ዓ.ም. ከብፁዕ አቡነ እንድርያስ (ቀዳማዊ) በወቅቱ የሰሜን ጎንደር ሊቀ ጳጳስ ተቀብለዋል፥
• ምንኵስና - በ1984 ዓ.ም. በታዋቂውና ጥንታዊው ገዳም ጎንድ ተከለ ሃይማኖት ተቀብለዋል፥
• ቅስና - ከብፁዕ አቡነ ያዕቆብ (ኤርትራዊ) በወቅቱ የሰሜን ጎንደር ሊቀ ጳጳስ ተቀበለዋል፥
• ቁምስና - ከብፁዕ አቡነ ገብርኤል በወቅቱ የምዕራብ ሸዋ ሊቀ ጳጳስ ተቀብለዋል።
#አገልግሎት
• በሆለታ ደብረ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት፥ በሆለታ ገነት ደብረ ኤዶም ቅዱስ ገብርኤል፥ በሆለታ ገነት ደብረ ሣህል መድኃኔ ዓለም፥ በወሊሶ ጻድቁ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አብያተ ክርስቲያናት በአስተዳዳሪነት ሠርተዋል።
• የወልመራ ወረዳ ቤተ ክህነት ምክትል ሊቀ ካህናት ሆነው በቅንንነት አገልግለዋል።

• በኖርዌይ ስታሻንገር መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪና የሕፃናትና ቤተሰብ መምሪያ የቦርድ ምክትል ሰብሳቢ በመሆን መርተዋል።

• የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር የቦርድ አባል፡ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት የቦርድ አባል በመሆን እያገለገሉ አገልግለዋል።
• በቤተ ከህነት ጠቅላይ ጽ/ቤት ሲል በስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ ኃላፊ፥
• በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በመጀመሪያ የሪሰርችና ምርምር ኃላፊና አካዳሚክ ዲን፥ ም/ዋና ዲን በመሆን አገልግሎት ሰጥተዋል።
• የቅድስት ልደታ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ የቦርድ አባል በመሆንም ሠርተዋል።
• በዓለም አቀፍ ተሳትፎ ደግሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ከርስቲያንን በመወከል የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ማእከላዊ ኮሚቴ አባል፥ የመላው ኦርየንታል ኦርቶዶስ አብያተ ከርስቲያናትን በመወከል የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል በመሆን ተሳትፈዋል፡፡

• የመንበረ ፓትርያርከ ጠቅላይ ጽ/ቤት ምክትል ሥራአስኪያጅ ሆነው አገልግለዋል።

«በጎ ነገር የሆነው ሁሉ ያለ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ፍጻሜ ሊያገኝ አይችልም ተብሎ በተጻፈው መሠረት ምንም እንኳን ሁሉም ተመራጮች ቆሞሳት ከዕጩ ተወዳዳሪዎቻቸው ጋር የድምፅ ብልጫ በማግኘት ሊመረጡ የቻሉት በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ፈቃድ መሆኑ ቢታመንበትም ቅሉ ቆሞስ ዶ/ር ብፁዕ አቡነ አረጋዊ ግን ከእጩ ተወዳዳሪያቸው ጋር እኩል ድምፅ አግኝተው የተመረጠት በዕጣ ስለሆነ በእሳቸው ምርጫ በይበልጥ እደ መንፈስ ቅዱስ እንዳለበት ያሳያል፡፡

ብፁዕነታቸው ከሹመታቸው በኋላ የቅዱስ ፓትርያርክ  ልዩ ጽሕፈት ቤት እና የውጪ ግንኙነት መምሪያ የበላይ ኃላፊ እና የድሬደዋና ጅቡቲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በመሆን ቅድስት ቤተክርስቲያን ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል።

ብፁዕ  አቡነ አረጋዊ ያለፈውን ዓመት በሕመም ምክንያት በሀገር ውስጥ እና በውጪ ሀገር በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ትናንት መጋቢት 12 /2015 ዓ.ም በተወለዱ በ54 ዓመታቸው ከእዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል ።

የብፁዕ አባታችን በረከታቸው ይደርብን ።

ፎቶ:- መልአከ ሰላም አባ ኪሮስ ወልደ አብ
(የፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት)
በፍትሐ ነገሥቱ መሠረት አንድ ሰው አራስ ቤት ቢገባ ምን ችግር የለውም። መግባት ይችላል። ያ ብቻ ሳይሆን ለምሳሌ የአንድ ቄስ ሚስት ዛሬ ብትወልድ፣ ቄሱን ደም ካልነካው ነገ ጠዋት ቤተክርስቲያን ገብቶ መቀደስ ይችላል። በግምት የምትናገሩ ሰዎች አደብ ግዙ። ተሳስታችሁ ሌላ ሰው አታሳስቱ። ምእመናንንም ከእንደነዚህ ዓይነት ሰዎች መራቅ አለባቸው። ትክክለኛውን ትምህርት ከተጠያቂ መምህራን እንማር። የማንም መሰለኝ ማራገፊያ አንሁን።

ፍትሐ ነገሥቱን በደንብ ለመማማር እቅድ ይዘን ነበረ። ነገር ግን ኔትዎርክ ስላልተለቀቀ ሁሉም በአንድነት እንዲማር ይቆይ ስላላችሁኝ። ኔትወርክ እስኪለቀቅ ነው እየጠበቅሁ ያለሁት። ሥርዓተ ቤተክርስቲያን ላይ ደካሞች ስለሆንን በደንብ ለማየት ፍትሐ ነገሥቱን በቴሌግራም ቻናሌ በላይቭ እየተጠያየቅን እንማማራለን።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ምዕመናን ሾይጣን ይታሰራል ተብሎ አልነበር እንዴ 🙄
"ኦማርያም በእንተዝ ናፈቅረኪ ወነአብየኪ - ማርያም ሆይ ስለዚህ እንወድሻለን ከፍከፍ እናደርግሻለን"

         ቅዳሴ ማርያም
የሕገ ወጥ ቡድኑን  የሹመት ይጽደቅልን ጥያቄን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መቼውንም የማትቀበለው  ጥያቄ ነው።

የመንበረ ፓትርያርክ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

በዛሬ ዕለት የተካሔደውን  በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅና በሕገ ወጥ መንገድ በተሾሙ  የቀድሞ አባቶች  መካከል የነበረውን ውይይት አስመልክተው መግለጫ የሰጡት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  መንበረ ፓትርያርክ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ሓላፊ ሊቀ ሥዩማን እስክንድር ገብረ ክርስቶስ  ሲሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ ከመጋቢት ፮/፳፻፲፭ ዓ/ም ጀምሮ በሕገ ወጥ የተሾሙ ግለሰቦችን አስመልክቶ  በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት ለመቀበል   ያከናወነውን  ተግባራት አብራርተዋል።

በዚህም ቅዱስ ሲኖደስ ከሕገ ወጥ የተሾሙ ግለሰቦች በአምስት  የሥራ ቀናት  ውስጥ ለመንበረ ፓትርያርክ  ጠ/ጽ/ቤት የይቅርታ ማመልከቻ እንዲያስገቡ ቅዱስ ሲኖዶስ  ጥሪ ያስተላላፈ ቢሆንም በይቅርታ ደብዳቤ አስገብተው ከተመለሱት ከአንዱ " አባ "   ኃይለ ኢየሱስ ከተባሉት ውጭ ሌሎች ግን   በይቅርታ  ከመመለሰ ይልቅ ለውይይትና  ሕገ ወጥ ድርጊቱም እንዲጸድቅላቸው መጠየቃቸውን  ተገልጿል።

የመምሪያው ኃላፊ ሊቀ ሥዩማን እስክንድር  ገብረ ክርስቶስ ቀጥለው ቤተ ክርስቲያን የይቅርታ ቤት የሰላም ዓደባባይ የንስሓ  ሰገነት በመሆኗ ለፍቅር ረጅም ርቀት በመጓዝ  ግለሰቦቹ  ጋር በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሓፊ እንዲሁም በሌሎች ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት   አማካኝነት  መወያያቷን  አስታውሰዋል። ከዚህም አልፎ ቤተ ክርስቲያን የሀገር ሰላም የኢትዮጵያውያን የደኅንነት ኑሮ በእጅጉ ስለሚያሳስባት  በብዙ ርቀት ለይቅርታ በሯን ከፍታ ስትጠባበቅ እንደነበረችም አክለው ገልጸዋል።
2024/10/01 17:34:38
Back to Top
HTML Embed Code: