Telegram Web Link
ይሁን እንጂ በዛሬው ዕለት ወደ ጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ የመጡት  ሁሉንም እንወክላለን  ያሉት  6  ግለሰቦች  ከብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅና ከብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሓፊ ጋር የተወያዩ ሲሆን በውይይቱ ግን  የተዘረጋው የቤተ ክርስቲያን  የፍቅርና ይቅርታ እጅ በግለሰቦቹ ግን እንደመልካም አልታየም። ከዚህ ይልቅ  ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት ከተደረሱ 10 የስምምነት ነጥቦች  መካከል በተራ ቁጥር 6 የሚገኘው ውሳኔ  "በሕገ ወጥ መንገድ  የተሾሙት  "አባቶች"   ወደ ቀደመ አገልግሎታቸው  ይመለሳሉ" የሚል  ቢሆንም ግለሰቦቹ ግን በመርሕ ደረጃ ስምምነቱን እንቀበለዋለን  በአፈጻጸም ደረጃ ግን   ቅዱስ ሲኖዶስ  ሹመታችንን ያጽድቅልን" የሚል ጥያቄ ማቅረባቸውን  የመምሪያው የሓላፊ  ገልጸዋል።

ስለሆነም ይላሉ የመምሪያው ሓላፊ ቤተ ክርስቲያን እስካሁን የሄደችበት የይቅርታ መንገድ  እጅግ የሚያስመሰግን ሲሆን ከዚህ በኋላ  ሕገ ወጦቹን  በተመለከተ ቤተ ክርስቲያን የሚከተለውን ውሳኔ መወሰኗን አስታውቀዋል።
፩.በየትኛውም መንገድ  የጋራ ውይይት አይኖርም
፪.ለይቅርታ የሚመጡ ከሆነ  በቡድን  ተሰባስቦ  ሳይሆን በግለሰብ ደረጃ እንዲሆን
፫.የይቅርታ ማመልከቻውን እያንዳንዳቸው  ለመንበረ  ፓትርያርክ ጠ/ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ማስገባት  ይኖርባቸዋል።

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በዚህና በሌሎች መሠረታዊ የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ለማሳለፍ  መጋቢት  ፳፩ ቀን  ፳፻፲፭ ዓ/ም  (21/07/2015 )  ምልዓተ ጉባኤ መጠራቱ የሚታወስ ነው።

ዘገባው የኢኦቴቤ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት  ነው።
#ገብር_ኄር (የዐቢይ ጾም 6ኛ ሳምንት)

የዐቢይ ጾም ስድስተኛው እሑድ ወይም ሳምንት ገብር ኄር ይባላል፡፡ በዚህ ሳምንት የሚዘመረው ዝማሬ፣ የሚሰበከው ስብከት፣ የሚሰጠው ትምህርት ገብርኄርን የሚያወሳ ነው። ማለትም ስለ ታማኝ አገልጋይ ነው፡፡

የማቴ.25፥14-25 የሚነግረን ይህን ነው፦ “አንድ ባዕለ ጸጋ ሰው ባሪያዎችን ጠርቶ ለአንዱ አምስት መክሊት ሰጠው፣ ሁለት መክሊት የሰጠውም አለ፣ አንድ መክሊትም የሰጠው አለ፡፡ ከዚህ በኋላ ወደሩቅ አገር ሄደ፡፡ አምስት መክሊት የተቀበለውም ወጥቶ ወርዶ ሌላ አምስት አትርፎ አስር አደረገ፡፡ ሁለት የተቀበለውም አትርፎ አራት አደረገ፡፡ አንድ የተቀበለው ግን ሄዶ መሬቱን ቆፍሮ በሻሽ ጠቅልሎ የጌታውን መክሊት ቀበራት፡፡

ከብዙ ጊዜ በኋላ ጌታቸው መጥቶ ተቆጣጠራቸው፡፡ አምስት መክሊት የተቀበለው ቀርቦ ጌታዬ አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር እነሆ አምስት አተረፍኩ አለው፡፡ “ገብርኄር ወምዕመን ዘበሁድ ምዕምነ ኮንከ ዲበ ብዙህ እሰይመከ ባዕ ውስተ ፍስሐሁ ለእግዚእከ” “አንተ ታማኝ ባሪያ በጥቂቱ ታምነሃል በብዙ እሾምሃለሁ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ” አለው፡፡ ሁለት የተቀበለውም ቀርቦ ጌታዬ ሁለት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር እነሆ ወጥቼ ወርጄ ሌላ ሁለት አትርፌ አራት አድርጌአለሁ፡፡ “አንተ ታማኝ በጎ አገልጋይ በጥቂቱ ታምነሃል በብዙ እሾምሃለሁ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ” አለው፡፡ አንድ መክሊት የተቀበለው ግን ቀርቦ “ጌታዬ አንተ ክፉና ጨካኝ ካልዘራህበት የምታጭድ ካልበተንህበት የምትሰበስብ እንደሆንክ ስለአወቅሁ መሬቱን ቆፍሬ ቀበርኋት እነኋት መክሊትህ” አለው፡፡ “አንተ ሰነፍ ባሪያ መክሊቴን በጊዜ ልትሰጠኝ በተገባህ ነበር እኔም ወጥቶ ወርዶ ለሚያተርፍ በሰጠሁት ነበር”፡፡ ኑ የዚህን ሀኬተኛ መክሊት ውሰዱና አስር መክሊት ላለው ስጡት፡፡ ላለው ይሰጡታል ይጨመርለታል ለሌለው ግን ያለውን ይቀሙታል፡፡ ኑ ይህን ሰነፍና ሃኬተኛ ባሪያ እጅ እግሩን አሥራችሁ ጽኑዕ ጨለማ ወደአለበት ውሰዱት ጩኸትና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት ጨምሩት” አለ ማቴ. 25፥14-25፡፡

ባለ ጸጋ የተባለው ጌታ ነው፡፡ መክሊት የተባለው ልዩ ልዩ የአገልግሎት ጸጋ ነው፡፡ ያተረፉት በሚገባ በታማኝነት ያገለገሉ ቅዱሳን ሰዎች ናቸው መክሊቱን የቀበረው ደግሞ በታማኝነት በተሰጠው ጸጋ ማገልገል ሲገባው ያላገለገለ ነው፡፡ ጌታቸው ሊቆጣጠራቸው መጣ ማለት በዕለተ ምጽአት ለሁሉም በአገለገለው አገልግሎት ዋጋ ለመስጠት እንደሚመጣ ያሳየናል፡፡ ያገለገሉትን ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አላቸው ማለት ታማኝ አገልጋዮች መንግሥተ ሰማያትን ይወርሳሉና፡፡ ሰነፎች ደግሞ ጥርስ ማፋጨት ስቃይ ጽኑዕ ጨለማ ባለበት ሲዖል መግባታቸውን የሚያሳይ ነው፡፡

#የዕለተ_ሰንበት_መዝሙር_ከጾመ_ድጓ
መኑ ውእቱ ገብር ኄር ወምእመን ዘይረክቦ እግዚኡ በምግባረ ሠናይ ወይሠይሞ ዲበ ኲሉ ንዋዩ ካዕበ ይቤሎ እግዚአብሔር ገብር ኄር ወምእመን ዘበውኁድ ምእመነ ኮንከ ዲበ ብዙኅ እሠይመከ ባእ ውስተ ፍሥሐሁ ለእግዚእከ፡፡

ትርጉም፦ ጌታው በመልካም ሥራ የሚያገኘው በሐብቱ ኹሉ ላይ የሚሾመው፤ የታመነ በጎ አገልጋይ ማን ነው? ዳግመኛም እግዚአብሔር አንተ የታመንክ በጎ አገልጋይ በጥቂቱ የታመንህ ስለኾንህ በብዙ እሾምሃለሁ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ ይለዋል፡፡

#መልዕክታት
2ኛ ጢሞ.2÷1-15
"ልጄ ሆይ÷ አንተም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ በርታ፡፡ በብዙ ምስክሮች ፊት ከእኔ የሰማኸውን ትምህርት ለሌሎች ሊያስተምሩ ለሚችሉ ለታመኑ ሰዎች እርሱን አስተምራቸው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደሚያገለግል በጎ አርበኛ ሆነህ መከራ ተቀበል፡፡" (ተጨማሪ ያንብቡ)

1ኛ ጴጥ.5÷1-11
"እንግዲህ እኔ ከእነርሱ ጋር ሽማግሌ÷ የክርስቶስም መከራ ምስክር÷ ደግሞም ሊገለጥ ካለው ክብር ተካፋይ የሆንሁ በመካከላቸው ያሉትን ሽማግለዎችን እማልዳቸዋለሁ፡፡ በእናንተ ዘንድ ያሉትን የእግዚአብሔርን መንጋዎች ጠብቁ፤ ስትጠብቁአቸውም እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ እንጂ በግድ አይሁን፤ በበጎ ፈቃድ እንጂ መጥፎውን ረብ በመመኘትም አይሁን፡፡" (ተጨማሪ ያንብቡ)

#ግብረ_ሐዋርያት
የሐዋ.1÷6-8
"እነርሱም ተሰብስበው ሳሉ÷ "ጌታ ሆይ÷ በዚህ ወራት ለእስራኤል ልጆች መንግሥትን ትመልሳለህን?” ብለው ጠየቁት፡፡ እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው÷ “አብ በገዛ ሥልጣኑ የወሰነውን ቀኑንና ዘመኑን ልታውቁ አልተፈቀደላችሁም፡፡ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኅይልን ትቀበላላችሁ፤ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ሁሉ፣ በሰማሪያና እስከ ምድር ዳርቻ ድረስም ምስክሮቸ ትሆኑኛላችሁ።"

#ምስባክ
መዝ. 39÷8
"ከመ እንግር ፈቃደከ መከርኩ አምላኪየ፡፡ ወሕግከኒ በማዕከለ ከርሥየ፡፡ ዜኖኩ ጽድቀከ በማኅበር ዐቢይ፡፡"

ትርጉም፦ አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ለማድረግ መከርሁ፥ ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው። በታላቅ ጉባኤ ጽድቅህን አወራሁ

#ወንጌል
ማቴ. 25÷14-30
“መንገድ እንደሚሄድ÷ አገልጋዮቹንም ጠርቶ ሊያተርፉበት ገንዘቡን እንደ ሰጣቸው ሰው እንዲሁ ይሆናልና፤ ለእያንዳንዱ እንደ ችሎታው ለአንዱ አምስት÷ ለአንዱ ሁለት÷ ለአንዱም አንድ ሰጠና ወዲያውኑ ሄደ፡፡” (ተጨማሪ ያንብቡ)

#የዕለቱ_ቅዳሴ ➛ ቅዳሴ ባስልዮስ
ይሁዳ አልነበርክ እንዴ ነው ሰላሳ ብሩ አላወጣህም 🙄 ? ስለዚህ ከሰቀሉት ከሮማውያን ጋር ለመተባበር መጣህን ። ቆይ እኔ እምለው ስንቴ ነው የምትሰቅሉት መቶ አለቃ በጋሻው ደስ አለኝ 🙄
[ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች ]

+አባታችን ሆይ እንዴት ትላለህ?🤔

እንደ ልጅ ካልኖርህ እንዴት "አባት" ትለዋለህ? ሌላውን ጠልተህ ራስ ወዳድ ከሆንክ እንዴት አባት "አችን" ብለህ በአንድነት ትጠራዋለህ? ምድራዊ ነገር ብቻ እያሰብህ እንዴት "በሰማያት የምትኖር" ትለዋለህ? ልብህ ከእርሱ ርቆ በአንደበትህ ብቻ እየጠራኸው "ስምህ ይቀደስ" እንዴት ትለዋለህ?
ሥጋዊና መንፈሳዊውን እየቀላቀልህ "መንግሥትህ ትምጣ" ለምን ትለዋለህ? መከራን በጸጋ የማትቀበል ከሆነ "ፈቃድህ ይሁን" ለምን ትላለህ? ለራስህ ሆድ እንጂ ለተራቡት ግድ የማይሰጥህ ከሆነ ለምን "እንጀራችንን ሥጠን" ትላለህ?
በወንድምህ ላይ ቂም ይዘህ "እኛም የበደሉልን ይቅር እንደምንል" እንዴት ትላለህ? የኃጢአትን አጋጣሚዎች ሳትሸሽ "ወደ ፈተና አታግባን" እንዴት ትላለህ? ክፉን ለመቃወም አንዳች ሳታደርግ "ከክፉ አድነን" እንዴት ትላለህ?
ጸሎቱን ከልብህ ሳትሰማውስ እንዴት አሜን ትላለህ?

ዲ/ን ሄኖክ ሀይሌ
ነፍስ ይማር
+በመሳሪያ ተደብድበው በቤተክርስቲያን ጊቢ ተሰዉ+
እጅግ ልብ የሚሰብር አስደንጋጭ ዜና ተሰማ 💔😭

አባ ተወልደው ያደጉት በቀድሞ ደቡብ ክልል በወላይታ ዞን ዳሞት ጋሌ ወረዳ ነበር! ምንኩስናን ከልባቸው ወደውና በምንኩስና ለመኖር መርጠው በትምህርትም ለማጽናናት ሲሉ ወደ ሰሜን ከተጓዙ ቆይተው ነበሩ። ይህንንም ትምህርት በድል አጠናቀው እግዚአብሔር በፍጹም ቅድስና እያገለገሉ በአካባቢው ከሚገኙ ከሰው ሁሉ ጋር ሰላም ነበሩ!

*የሞታቸውን ዜና በድንገት ሰማን አባን ማን ገደላቸው ለትልቅ ማዕረግ ከፊታችን ባለው በዓል ስመት ስንጠብቅ አርፈዋል ተብሎ ተነገረን ልባችን አለቀሰ ደማም😭💔

አባቶች ሲሞቱ በረከታቸው ይደርብን እያልን ማለፍ ብቻ ከሆነ ነገሩ ወዴት እየተጓዝን ነው ስለዚህ ገዳዮች በሕግ ቁጥጥር ውስጥ እንዲያርፉ መንግስት ስራ ሊሰራ ይገባል የተዋህዶ ዝምታ ከንግግር በላይ ነው ቢገባችሁ።

መነኩሴ እግዚአብሔርን ከማገልገል ሌላ አላማ የለውም ስለምን ትገሏቸዋላችሁ!😭💔😭

* አባ ኃይለ ገብርኤል እግዚአብሔር በፍጹም ቅድስና ሲያገለግሉ ሙሉ ጊዚያቸውን በጾምና በጸሎት ሲያሳልፉ የቆዩ ድንቅ እና ትሁት የልማትም አርበኛ ነበሩ በትምህርትም ያስመሰከሩ አባት ነበሩ።

እኚህ ክቡር አባት አባ የፊታችን ግንቦት ርክበ ካህናት ዕጩ ጳጳስ የነበሩት አባ ኃ/ገብርኤል በጎንደር በጥይተ ተመተው ተገድለዋል ።

😭 ግባዓተ መሬታቸው በዋልድባ ገዳም ተፈፀሟል!

በተዉልድ ሀገራቸው ወላይታ ዳሞት ጋሌ ዛሬ የባህል ለቅሶ ስርዓት ይከናወናል። በረከታቸው ይደርብን!

ፍትህ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ! ልጆቿን በድንጋይና በመሳሪያ እየደበደቡ መግደል በፍጥነት ይቁም ገዳዮችም ለፍርድ ይቁሙ የአቤል ደም ይጮሃል 😭💔

በረከታቸው ይድረሰን ይደርብን 😭😭😭
ለምን መሐመድን እናምነዋለን ?🙄
ኑ በብርሃኑ እንመላለስ
የማሜ እውነተኝነት በምን ይታወቃል 🙄
ዋሽቶንስ ቢሆን 😂🙄

በኡስታዝ ዩሱፍ የተሰጠ አጭር ሸጋ ትምህርት
በሰሜን ካሊፎርንያ የተገዛው የቅዱስ ዮሐንስ ወቅድስት አርሴማ ገዳም ቅዳሴ ቤት  ሚያዝያ 13 ቀን 2015 ዓ.ም ይከበራል።
++++++++++++
በሰሜን ካሊፎርንያ 3700 ሄክታር ቦታ በሳን ሚግየል የተገዛው ቅዱስ ዮሐንስ ወቅድስት አርሴማ ገዳም ቅዳሴ ቤት  ሚያዝያ 13 ቀን 2015 ዓ ም /Apri| 21 - to 22,2023/ ጀምሮ ይከበራል።

በሰሜን ካሊፎርንያ ፣ ኔቫዳና አሪዞና ሀገረ ስብከት  ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ እንደገለጹት የኆኅተ ሰማይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አንድነት ገዳም ቅዳሴ ቤት በዓል የሚከበረው ከዋዜማው ሚያዝያ 13 ቀን 2015 ዓ ም /Apri| 21 ' to 22 2023/ ጀምሮ መሆኑን ገልጸው  ኦርቶዶክሳውያን በቅዳሴ ቤቱ በዓል ላይ በአካል በመገኘት በረከት እንዲቀበሉ ጥሪ አድርገዋል።

©ኢኦተቤክ ቴቪ
✞የጴጥሮስን ዕንባ✞
♡የመዝሙር ግጥሞች♡
✞የጴጥሮስን ዕንባ✞

የጴጥሮስን እንባ ስጠኝ እልሃለሁ
ኃጢአቴን ልናዘዝ ፍቅርህን እያየሁ
በሞት ጥላ ውስጥ እንኳን ብሄድ ጌታሆይ(፪)
ልቤን በፍቅር ውሃ እጠበው እባክህ

ቸርነትህ በዝቶ ምህረት ቢያሰጠኝ
እጀቼን ዘርግቼ እማጸናለሁኝ
ደምህ የፈሰሰው ለኔ ስለሆነ(፪)
በኃጢአት ልተወኝ ልብክ አልጨከነም
አዝ= = = = =
ዓለማዊ ምግባር ልቤ ቢከተልም
ከዚህ ሁሉ ማዳን ጌታ አይሳንህም
ኃጢአት እየሰራሁኝ ባስቀይምህም(፪)
በሄሶጵ እርጨኝ ጌታ እጠበኝ እባክህ
አዝ= = = = =
ዲያቢሎስ ያመጣው ጸጸት የውድቀት ነው
የይሁዳ ምሬት የሞት ነው ፍፃሜው
ይህንን መማረር እኔ አልፈልግም(፪)
የውድቀት ጉዞ እንጂ ትንሳኤ የለውም

ጴጥሮስ አባብሎ የተማጸነበት
ፍቅሩን በንስሐ ስቦ ያመጣበት
ፍፃሜው የሚያምር ንስሐ ስጠኝ(፪)
የለቅሶ አምሀ የእንባን ይወት ስጠኝ

መዝሙር
ይልማ ኃይሉ

"ጴጥሮስም ወደ ውጭ ወጥቶ ምርር ብሎ አለቀሰ።"
ሉቃ፳፪፥፷፪
በህገወጥ  መንገድ ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት የተፈጸመላቸውና ተሹመናል ያሉ  17 ግለሰቦች የይቅርታ ደብዳቤ አስገቡ።
+++++++++++++++++++++++++++++++
ጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሶዶ ዳ ወረዳ ከወሊሶ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኘው ሀሮ ባለ ወልድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተፈጸመውን እጅግ አሳዛኝ እና ኢ-ሲኖዶሳዊ የሆነ  ሕገ ወጥ የቀኖና ቤተ ክርስቲያን ጥሰት የተሳተፉ ግለሰቦች
መጋቢት 19 ቀን 2015 ዓ.ም በጠቅላይ ቤተ ክህነት ከብፁዕ አቡነ አብርሃም እና ከብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ጋር ወይይት በማድረግ የይቅርታ ደብዳቤያቸውን ያስገቡ ሲሆን ደብዳቤውን ብፁዕ አቡነ አብርሃም አንብበው በመቀበል ለቅዱስ ሲኖዶስ እንደሚያቀርቡ ተናግረዋል።
አንድ አባት ደብዳቤ የላኩ ሲሆን ቀሪዎቹ በቅርብ ቀን እንደሚያስገቡ ተገልጿል።
መ/ር ማርቆስ ተበቃ
EOTC TV
እንኳን ለአረፋ በዓል አደረሳችሁ ብላለች ንግስት ስንዱ ደባቄ ንግስተ ዝልጠት ወስግጥና 😍
"ጾምህና ምጽዋትህ ሁለት ዋጋ አላቸው፡፡ ከሰው ክብርን ሽተህ የምትጾም ከሆነ ኃጢአት በአንተ ላይ እንድትበረታ ደንቁርናህም እጅግ ጽኑ እንዲሆን እወቅ፡፡ ነገር ግን እጆችህን ለተቸገረ ሰው የምትዘረጋ ሕሊናህን ግን ወደ አምላክ የምታነሣ ከሆነ፣ እንዲሁም ስትጾም ጾምህን በእግዚአብሔር ፊት ያደረግህ እንደሆነ ከፈጣሪህ ዘንድ መልካምን ዋጋ ትቀበላለህ፡፡ ይህ ኃይለ ቃል “ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና፡፡” (ማቴ.6፥21) ብሎ ጌታችን ካስተማረው ትምህርት ጋር አንድ ዓይነት ትርጉም ያለው ነው፡፡

ጾምና ምጽዋታችን በከንቱ ፈቃዳችን ምክንያት ለኃጢአት አሳልፎ እንዳይሰጠንና በደላችንንም እጥፍ ድርብ እንዳያደርግብን አምላካችን ይህን ማስተዋል ዘወትር ይሰጠን ዘንድ በዚህ የጦም ወቅት እንለምነው፡፡

ለወደደንና በእኛ ጥቂት ድካም ዘለዓለማዊ ዋጋን ለሚሰጠን ለእርሱ ምስጋና ይሁን ዛሬም ዘወትርም  ለዘለዓለሙ አሜን፡፡

#ቅዱስ_ኤፍሬም
ሰበር ዜና

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የሦስቱን አባቶችና የ20ቹን መነኮሳት ውግዘት ከዛሬ 21/07/2015 ዓ/ም ጀምሮ ማንሳቱን በመግለጫው አሳወቀ።

ውግዘቱ የተነሳላቸው ቤተ ክርስቲያን በሰጠቻቸው ማዕረግ እንዲጠሩም ገልጿል።

በዚህ መሠረት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ፣ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ተብለው እንደሚጠሩና ወደ ነበረ የአባትነት ኃላፊነታቸው የሚመለሱ ሲሆን በይቅርታ የተመለሱት በቁጥር 20ዎቹ መነኮሳትም ቤተ ክርስቲያን በሰጠቻቸው የክህነት አገልግሎት እንዲያገለግሉ ሆኖ በምንኩስና ስማቸው እንዲጠራ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል።
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥር 14 ቀን 2015ዓ.ም. በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሐሮ ባለወልድ ቤተ ክርስቲያን የተፈጸመውን ሕገወጥ የኤጲስ ቆጶሳት ሹመትን ተከትሎ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጥር 18 ቀን 2015ዓ.ም. ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የተከናወነው ድርጊት የቤተ ክርስቲያኒቱን ዶግማ፣ ቀኖና አስተዳደራዊ መዋቅር የጣሰ ሕገወጥ አድራጎት መሆኑን አጽንኦት ሰጥቶ በመወያየት ሕገወጡን ሹመት ያከናወኑትና ተሿሚዎችን በቤተ ክርስቲያናችን ቀኖናዊ ሥርዓት ከዲቁና ጀምሮ የነበራቸውን ማዕረገ ክህነት በሙሉ በመሻር ከቤተ ክርስቲያኒቱ አባልነት አውግዞ መለየቱ የሚታወስ ነው፡፡

ምንም እንኳን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በውሳኔው ውግዘቱ እንደተጠበቀ ሆኖ በድርጊታቸው ተጸጽተው እና ከስህተታቸው ተመልሰው በቤተ ክርስቲያኒቱ ሥርዓት መሠረት የሚሰጣቸውን ቀኖና ተቀብሎ ለመመለስ ዝግጁ ከሆኑ የቤተ ክርስቲያኒቱ የይቅርታ በር ክፍት መሆኑን በማሳወቅ መግለጫ የሰጠ ቢሆንም ግለሰቦቹ ከስህተታቸው ተምረው በይቅርታ እድሉ ከመጠቀም ይልቅ በሕገወጥ መንገዱ ቀጥለውና ውግዘቱን ጥሰው በቤተ ክርስቲያኒቱ ሕጋዊ መዋቅራዊ አደረጃጀት መሠረት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በቅዱስ ሲኖዶስ ተመድበው በሚያገለግሉባቸው አህጉረ ስብከት ላይ እርስ በርሳቸው በመመዳደብ እያደረጉት የነበረውን ሕገወጥ እንቅስቃሴ መንግስት በሕግ የተጠላበትን ሕግን የማስከበር ኃላፊነት በመወጣት የቤተ ክርስቲያናችንን ተቋማዊ ልዕልና እንዲያስከብርልን ከመግለጫም አልፎ በደብዳቤ ያቀረብነው ጥያቄ ተቀባይነት አጥቶ በሕገወጥ መንገድ የተሾሙት ግለሰቦች በመንግሥታዊ የፀጥታ አካላት ታጅበው በኦሮምያ ክልል የሚገኙትን አህጉረ ስብከት፣ ወረዳ ቤተ ክህነት፣ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናትን በኃይል ሰብረው ተቋማቱን በመውረር ሀብትና ንብረት የተዘረፈ ሲሆን ይህም ሕገወጥ ድርጊት በሚከናወንበት ወቅት ሕገ ቤተ ክርስቲያናችን አይጣስም፣ ሲኖዶሳችን አይከፈልም፣ ቀኖናችን አይደፈርም በማለት በጽናትና በአንድነት ድርጊቱን የተቃወሙት ምዕመናን፣ ወጣቶችና አገልጋይ ካህናት እንዲሁም በየደረጃው ያሉ የቤተ ክርስቲያኒቱ ልዩ ልዩ የሥራ ኃፊዎች በተለይም የሻሸመኔና አካባቢው ምእመናንና አገልጋይ ካህናት ለሞት፣ ለአካልና የሞራል ጉዳት፣ ለእስራትና እንግልት ተዳርገዋል፡፡

በዚህም ምክንያት ቅዱስ ሲኖዶስ ችግሩን እና ፈተናውን የማሳለፍ ሥልጣን ሁሉ ባለቤት የሆነው እግዚአብሔር አምላካችን በምሕረት አይኑ ተመልክቶ የመጣውን ፈተና ያስወግድልን ዘንድ በጾመ ነነዌ ለ3 ቀናት ሁሉም የቤተ ክርስቲያኒቱ እምነት ተከታዮች ማቅ ለብሰው በጸሎትና በምህላ ወደ እግዚአብሔር እንዲያመለክቱ በወሰነው መሠረት በቤተ ክርስቲያናችን ታሪክ ተፈጽሞ በማያውቅ ሁኔታ እንኳንስ ልጆቿ ምእመናን ይቅርና እራሷ እናት ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም የሀዘን መገለጫ የሆነውን ጥቁር ማቅ ለብሳ ከሀገር አቀፍም አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሀዘኗን ገልጣለች፡፡
የእናት ቤተ ክርስቲያንና የልጆቿ ምዕመናን እንባና ጸሎት በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት በማግኘቱ ለውይይት ዝግ የነበረው የመንግስታችን በር ለውይይት ተከፍቷል፡፡ የደረሠብን የጉዳት ከፍተኛነት በሀገራችን መንግስታዊ ሚዲያዎች ዘንድ ቦታ ቢያጣም አለም አቀፍ ሚዲያዎችና የቤተ ክርስቲያናችን የሚዲያ ተቋማት ለአለም አቀፍ ማህበረሰብ እንዲደርስ በማድረጋቸው ችግሩን ከእኛም አልፎ በሁሉም አኃት አብያተ ክርስቲያናት፣ የአለም አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት፣ የምሥራቅ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት እና ሌሎች ሲቢክ ማህበራት ድርጊቱን በማውገዝ ለእናት ቤተ ክርስቲያናችን ያላቸውን አጋርነት ገልጸዋል፡፡ በዚህም በችግራችን ወቅት ከጎናችን ለቆሙት አካላት በሙሉ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አሁንም በድጋሚ ከፍ ያለ ምስጋናዋን ታቀርባለች፡፡

በመጠቀልም ክቡር የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ባመቻቹት የውይይት መድረክ በተወከሉ ብፁዓን አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች በኩል በተደረገው መጠነ ሰፊ ውይይት መሠረት ባለ10 ነጥቦች ላይ የጋራ ስምምነት በተደረሰው መሠረት ሦስቱ የቀድሞ አባቶች የካቲት 8 ቀን 2015 ዓ.ም. ወደ ጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ መጥተው በቀድሞ በዓታቸው ተወስነው እስካሁን የቆዩ ሲሆን 20ዎቹ ተሿሟዎች ደግሞ በስምምነቱ መሠረት ለውሳኔው ተገዥ መሆናቸውን በመግለጽ መጋቢት 15 ቀን 2015 ዓ.ም. እያንዳንዳቸው በጽሑፍ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ባቀረቡት መሠረት ውግዘቱ እንዴት ሊፈታ እንደሚገባ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሊቃውንት ጉባኤ የውሳኔ ሐሳብ እንዲያቀርብ በታዘዘው መሠረት የቤተ ክርስቲያኒቱን የቀኖና ቅዱሳት መጻሕፍት ዋቢ በማድረግ የውሳኔ ሐሳቡን ያቀረበ ሲሆን እንደሚከተለው በአጭሩ ተገልጿል፡፡

ሀ. “ኢይክል ሰብእ ነሢአ ፀጋ ለሊሁ ወኢምንተኒ እመ ኢተውህበ ሎቱ እምሰማይ” ሰው ከእግዚአብሔር ካልተሰጠው በስተቀር እርሱ ራሱ ጸጋን ገንዘብ ማድረግ አይችልም” (ዮሐ. 3፣27) በማለት በቅዱስ ወንጌል እንደተነገረው የእግዚአብሔር ጸጋ ከላይ የሚሰጠው በቅንነት፣ በትሕትና፣ በትዕግሥትና በጸሎት በመሳሰለው እንጅ በሥርዓተ አልበኝነትና በሕገወጥ የድፍረት መንገድ የሚገኝ የእግዚአብሔር ጸጋ የለም፤ አልኖርም፤ አልነበረም፤ ወደፊትም አይኖርም፡፡

ለ. ብርሃና ለቤተ ክርስቲያን የተባለው ደጉ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስም “ወአልቦ ዘይነሥእ ክብረ ለርእሱ ዘእንበለ ዘጸውዖ እግዚአብሔር በከመ አሮን” እንደ አሮን በእግዚአብሔር ከተጠራ በቀር ማንም ክብርን ለራሱ የሚወስድ የለም ሲል ክብረ ክህነትን በሚገባ ገልጿል፡፡ (ዕብ.5፡4) እንዲህም በመሆኑ በአሁኑ ሰዓት ከቅዱስ ሲኖዶሱ ውሳኔ ውጭና ቅዱስ ፓትርያርኩ በሌሉበት በድብቅ የተፈጸመው ሕገወጥ ሢመተ ክህነት ለሿሚውም ሆነ ለተሿሚው የእግዚአብሔርን ጸጋ በራስ ፈቃድ እንደመውሰድ ስለሚቆጠር ከፍተኛ የሆነ የዶግማ ጥሰት ተግባር ነው፡፡

ሐ. ከቅዱስ ቃሉ እንደተማርነው “ቀዳሚሃ ለጥበብ ፈሪሀ እግዚአብሔር - የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው” (መዝ.109፣10 ምሳ.1፣7) ይህንም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል መሠረት በማድረግ ስግዱ ለእግዚአብሔር በፍርሀት - ለእግዚአብሔር በፍርሀት ስገዱ (መዝ.28፣2)

ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሀት - ለእግዚአብሔር በፍርሀት ተገዙ (መዝ.2፣11)

ንትነሣእ በፍርሀተ እግዚአብሔር - እግዚአብሔርን በመፍራት እንነሣ (ቅዳ.ማ) በማለት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እስከ እስትንፋሰ ደኃሪት መልእክቷን ዘወትር ታስተላልፋለች፡፡ የቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓት ይህ ሆኖ እያለ አሁን የተፈጸመው ድርጊት ግን በከፍተኛ ድፍረትና በሕገወጥ መንገድ ከመፈጸሙና የሥልጣነ ክህነትን ክብር ከማጉደፉም በላይ ከውግዘትም በኋላ ከጥፋቱ ባለመማር ሕገወጥነትን እንደ ሕጋዊነት፣ ጥፋትን እንደ ልማት፣ ሐሰትን እንደ እውነት፣ የነፍስ ጥፋትን እንደ ነፍስ ማዳን ተቆጥሮ በልበሙሉነት የአህጉረ ስብከትና የአጥቢያ አበያተ ክርስቲያናት በር በኃይል ተሰብሮ የመውረር ሕገወጥ ተግባር ተፈጽሟል፡፡ ይህም ድርጊት ከውግዘት በኋላ በመሆኑ ሕገ እግዚአብሔርን እያወቁ ወደጎን በመተው የተፈጸመ ድርጊት በመሆኑ የዶግማ ጥሰት ነው፡፡
2024/10/01 15:29:40
Back to Top
HTML Embed Code: