“እኔን ያዘጋጀኝ ለዚህ ቀን ነበር ለካ?”
ዲ/ን ዶ/ር መገርሳ ዓለሙ የቀዶ ጥገና ሰብ ስፔሻሊስት
የካቲት ፳፫/፳፻፲፯ ዓ.ም
በማኅበረ ቅዱሳን የ13ኛው የግቢ ጉባኤ ዓለም አቀፍ ሴሚናር በከሰዓት መርሐ ግብር የልምምድ ልውውጥ ተደርጓል።
ከተጋባዥ አገልጋዮች መካከል አንዱ የሆኑትና የቀዶ ጥገና ሰብ ስፔሻሊስቱ ዲ/ን ዶ/ር መገርሳ ከምርቃት በኋላ ወደ አምቦ እና አጋሮ ለሥራ መመደባቸውን ተናግረው የእግዚአብሔርንም መልእክት የተረዳሁበት ነው ይላሉ።
በተለይም በአጋሮ ቆይታቸው በአካባቢው ወደ 22 አብያተ ክርስቲያናት እንደነበሩና ከ3 ወይ 4 የማይበልጡ አብያተ ክርስቲያናት ብቻ ክፍት ነበሩ ይላሉ።
አክለውም ወደ አካባቢው ስሄድ አባቶች ምእመናን የሚያስተምራቸው አጥተው ሊበተኑ ነው እባክህ ትንሽ ከቻልህ አስተምርልን አሉኝ። እኔ በግቢ ጉባኤ ብማርም መድረክ ይዤ አስተምሬ ስለማላውቅ ደነገጥሁ። ነገር ግን ከሚበተኑ ብዬ ከሕክምና ሥራዬ በተጨማሪ ወንጌል መስበክ ጀመርሁ።
የበለጠ ብዙ ቦታ ለመድረስም ሞተር ሳይክል ገዛሁና በቻልሁት ያወቅሁትን እውነት አስተማርሁ።
ዲ/ን ዶ/ር መገርሳ ለካስ እግዚአብሔር በግቢ ጉባኤ አስተምሮ ያስጨረሰኝ ለዚህ ቀን አስቦኝ አዘጋጅቶኝ ነበር? ለካ እኛን የሚጠብቁ በየቦታው አሉ? ብዬ ራሴን ጠየቅሁ ይላሉ።
እናም የግቢ ጉባኤ ተማሪዎች እንዲህ ያሉ የቤተ ክርስቲያን ክፍተቶችን ለመሙላት መዘጋጀት አለብን በማለት መልእክት አስተላልፈዋል።
በመርሐ ግብሩ ልምዳቸውን ያካፈሉት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር ዶ/ር ወርቁ ደጀኔ እና የማኅበረ ቅዱሳን ሥራ አመራር አባል ወ/ሮ የእሱነሽ ተሾመም የግቢ ጉባኤ ተማሪዎች በግቢ ሕይወታቸው ራሳቸውን ከውጫዊና ውስጣዊ ፈተናዎች በመጠበቅ ለሀገርና ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት እንዲዘጋጁ አሳስበዋል።

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፲፪ኛ ዓመት በዓለ ሢመት እየተከበረ ይገኛል
የካቲት ፳፬/፳፻፲፯ ዓ.ም
የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፲፪ኛ በዓለ ሢመት በዛሬው ዕለት የካቲት ፳፬/፳፻፲፯ ዓ.ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እየተከናወነ ነው።
ምንጭ :- Eotc broadcast

ለወጣቶች የሱስ ማገገሚያ ተቋም ለማቋቋም ጥናት ማካሄዱን የማኅበረ ቅዱሳን ሙያዊ፣ማኅበራዊና ኢኮኖያዊ አገልግሎት አስታወቀ
የካቲት ፳፬/፳፻፲፯ ዓ.ም
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርሰቲያን ሰ/ት/ማ/መ/የማኅበረ ቅዱሳን ሙያዊ፣ማኅበራዊና ኢኮኖያዊ አገልግሎት በሱስ ለተጠቁ ምእመናን ከበሽታቸው መላቀቅ የሚያስችላቸውን የሱስ ማገገሚያ ተቋም ለማቋቋም የሚያስችል ጥናት ማካሄዱን አስታውቋል።
በአገርም ሆነ በዓለም-አቀፍ ደረጃ አሳሳቢ ሁኔታ ከደረሱ ችግሮች አንዱና ዋነኛው ሱስ ሲሆን በተለይ ቤተክርስቲያን በተለያዩ ሱሶች የተጠቁ ልጆቿን ከህመማቸው የሚያገግሙበት ስፍራ በገዳማት፣ በአጥቢያ ቤተክርስቲያናት፣በጸበል ቦታዎች ፣ በሌላም አከባቢዎች በሚገነባ ተቋም ውስጥ ልጆቿን የምታክምበትን መንገድ ለመጠቆም የሚያስችል ጥናት መሆኑን አገልግሎቱ ገልጿል።
ጥናቱ በችግሩ ዙሪያ ዝርዝር መረጃዎችና ማስረጃዎችን በስፋት አካቶ የተዘጋጀ መሆኑንም ከተዘጋጀው ሰነድ መረዳት ተችሏል።
ቤተክርስቲያን ካለባት ኃላፊነት አንጻር ትውልዱን ከሱስ ተጠቂነት ማውጣትና እንደ ምዕመን ለቤተክርስቲያን የሚያገለግል፣ የእግዚአብሔርን ሕግ የሚጠብቅ፣ ሰውን የሚያከብር፣ ለእናት ለአባቱ የሚታዘዝ፣ሥርዓተ ቤተክርስቲያን፣ ሕገ እግዚአብሔር፣ ትውፊት፣ ቀኖና፣ ካህናትና እና የሥነ ልቦና ባለሙያ ምክር፣ በተዋሕዶ ከብሮ ለቅዱስ ሥጋና ለክቡር ደሙ የሚበቃ ምዕመን ለማፍራት የሚያስችሉ የሱስ ማገገሚያ ተቋማት መቋቋም እንዳለበት ተጠቁሟል፡፡

በቤተ ክርስቲያኒቱም ሆነ በሀገሪቱ ሰፊውን ቁጥር ይዞ የሚገኘው ወጣቱ ክፍል በሱስ ተይዞ መገኘቱ የማኅበረሰብ ክፍል ቤተክርስቲያንንም ሆነ ሀገርን በማገልገል ሂደት ውስጥ ያለው ሚና ቀላል የማይባል ሆኖ ሳለ ከሱስ ጋር በተያያዘ ግን እንደ ቤተክርስቲያንም እንደ ሀገርም አስጊ ሁኔታ በመድረሱ ትውልድን ለመታደግ ቤተክርስቲያን የሱስ ማገገሚያ ተቋማትን በማዘጋጀትና በማከም ሂደት ውስጥ ተሳትፎ በማድረግ የራሷን በጎ አሻራ ማሳረፍ ግድ እንደሚላት ተመላክቷል።
አገልግሎቱ እስካሁን እየሰጣቸው ባሉ የአማካሪዎች ሥልጠና የችግሩን አሳሳቢነት መነሻ በማድረግ የግንዛቤ ፈጠራ ሥራዎችን ለካህናትና በምክክር አገልግሎት ለሚሰማሩ ባለሙያዎችም በሥልጠና መልክ እያስገነዘበ እንዳለም ማወቅ ተችሏል።
ለዚህም ጥናት መፍትሔ ተግበራዊነት ማኅበረ ቅዱሳን ከባላድርሻ አካላት ማለትም ከጠቅላይ ቤተክህነት፣ ከሀገረ ስብከት፣ከወረዳ ቤተክህነት፣ ከሰንበት ትምህርት ቤት፣ከተለያዩ ማኅበራት፣ ከባለሀብቶች ጋር በጋራ መሥራት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል። በቀጣይነትም የተጠናው ጥናት ውጤትና ወደ ተግባራዊ ተቋምነት በሚቀየርበት ሁኔታ ላይ አጋርና ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ የምክክር ጉባኤ ለማካሄድ መታቀዱን የተገኘው መረጃ ያሳያል።