ማኅበረ ቅዱሳን የግቢ ጉባኤ መምህራን ማሰልጠኛ ማእከል ፕሮጀክት ይፋ አደረገ።
የካቲት ፳፫/፳፻፲፯ዓ.ም
በዓለም አቀፍ የግቢ ጉባኤያት ሴሚናር “የግቢ ጉባኤ መምህራን ማፍሪያ” የሚል ፕሮጀክት እንደተቀረጸ የጥናቱ አቅራቢ አቶ ዳንኤል ተስፋዬ አስታውቀዋል።
ፕሮጀክቱ የግቢ ጉባኤ መምህራን ማሰልጠኛ ማእከል በማዘጋጀት መምህራንን በሥርዐተ ትምህርቱ በበቂ ሁኔታ ለማፍራት የሚያስችል ነው ተብሏል።
ማኅበረ ቅዱሳን በሀገር ውሰጥ በ467 እና በውጭ ሀገራት በ18 ግቢ ጉባኤያት ከ160 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ሥርዓተ ትምህርት ቀርጾና መጽሐፍትን አሳትሞ እያስተማረ ይገኛል።
መምህራንንም ከደረጃ 1 እስከ ደረጃ 3 በመለየትም አሰልጥኖ ለአገልግሎት እያሰማራ ነው።
ነገር ግን በበቂ ሁኔታ ለማስተማርና የበለጠ ተደራሽነቱን ለመጨመር የመምህራን እጥረት ትልቅ ፈተና እንደሆነበት ገልጿል።
ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታትም በ4 ዓመት ተፈጻሚ የሚሆን ፕሮጀክት ቀርጿል።
በ13ኛው የግቢ ጉባኤያት ሴሚናርም ፕሮጀክቱ ቀርቦ ተፈጻሚነቱ ላይ ውይይት እየተደረገ ይገኛል።

ማኅበረ ቅዱሳን ከ113 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ ፕሮጀክት አጸደቀ።
የካቲት ፳፫/፳፻፲፯ ዓ.ም
የማኅበረ ቅዱሳን ዓለም አቀፍ ግቢ ጉባኤ ሴሚናር በሁለተኛ ቀን ውሎው ከ113 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ ፕሮጀክት አጽደቋል።
ፕሮጀክቱ የግቢ ጉባኤ መምህራን ማሰልጠኛ ማእከል በማዘጋጀት መምህራንን በሥርዐተ ትምህርቱ በበቂ ሁኔታ ለማፍራት የሚያስችል ነው።
በግቢ ጉባኤያት በተለያዩ ቋንቋዎች ያለውን የመምህራን እጥረት በመቅረፍ ወንጌልን በሁሉም ቋንቋ ለማድረስ የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዝም ይታመናል።
አፈጻጸሙን መደበኛው የማኅበረ ቅዱሳን ሥራ አመራር ጉባኤ ሲያጸድቀው በያዝነው ዓመት ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል።

“ማንም የእኔ ያላለው ችግር ሁሉ የሚጠብቀው እኛን ነው”
የካቲት ፳፫/፳፻፲፯ ዓ.ም
እየተካሄደ በሚገኘው 13ኛው ዓለም አቀፍ የግቢ ጉባኤ ሴሚናር “የቤተ ክርስቲያን ፈተናዎችና የግቢ ጉባኤ አገልግሎት” በሚል ርእስ አቶ አማረ በፍቃዱ ጽሑፍ አቅርበዋል።
ሉላዊነት እና የወቅቱ ዓለም ዓቀፋዊ አመለካከት በኦርቶዶክሳዊነት ላይ ያሳደረውን ተጽዕኖ በአሀት እና በአጠቃላይ በምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናት በተለይም በሶሪያ፣ በዩክሬንና ሩሲያ እየደረሰ ያለው በማሳያነት ቀርቧል።
አቶ አማረ በማብራሪያቸው ወደ ኢትዮጰእያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስንመጣም ይኸው ችግር በተቋማዊ ሕልውና ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳደረ ሲሆን አስተምህሮዋን በመበረዝ አንዲሁም በምእመናንን እና በማኅበረ ቅዱሳን አገልግሎት ላይ ያሳደረው ተጽዕኖ ከፍተኛ ነው ብለዋል።
ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትም (ግቢ ጉባኤያት) የዚሁ ችግር ተጠቂ ሲሆኑ በተለይም ተማሪዎች በዓለም ሃሳብ በመጠመድ ለሃይማኖት የሚሰጠው ዋጋ እነቀነሰ መምጣት እያሳደረ ያለው ተጽዕኖ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።
ስለሆነም ግቢ ጉባኤያት ችግር ፈቺ መሆን፣ ዘመኑ ለሚጠይቀው አገልግሎት መዘጋጀት፣ ራስን ከዘመኑ ጋር ማብቃት፣ የቀደሙ አርአያዎቻችንን ማሰብ ያስፈልጋል ብለዋል።
ማንም የእኔ ነው የማይለው ችግር ሁሉ የሚጠብቀው እኛን ነው ያሉት አቶ አማረ በፍቃዱ ከቤ/ክ ነባራዊ ሁኔታ አንጻር፣ ለማኅበረሰቡ አስተዋጽዖ ከማድረግ እና ማኅበረ ቅዱሳን የተሻለ እንዲያገለግል ከማድረግ አንጻር ራስን ማዘጋጀት አለብን ሲሉ አፅዕኖት ሰጥተዋል።