Telegram Web Link
“ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ” በሚል መሪ ቃል የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር መካሄዱን የአቡዳቢ የግንኙነት ጣቢያ  ገለጸ

የካቲት ፳፭/፳፻፲፯ ዓ.ም 

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/ በሰ/ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የአቡዳቢ ልዩ ግንኙነት ጣቢያ 5ተኛውን የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር “ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ” (ኤፌ ፭፥፲፮) በሚል መሪ ቃል ቅዳሜ የካቲት 22 ቀን 2017 ዓ.ም በአቡዳቢ ምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም መከናወኑ ተገልጿል።

ጸባቴ አባ ፍ/ማርያም ተከስተ (ቆሞስ) የአቡዳቢ ምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ወአቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም አስተዳዳሪ፣ መላከ ፀሐይ ቀሲስ ኪሩቤል ይገዙ የራስ አልኬማ ደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ፣ የገዳሙ ቀሳውስት፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም የተስፋ ስዱዳን ሰንበት ትምህርት ቤት አባላትና ምእመናን በተገኙበት ዝግጅቱ ተካሂዷል።

በመርሐ ግብሩ መዝሙር በማኅበሩ፣ በተስፋ ስዱዳን ሰንበት ትምህርት ቤትና በግቢ ጉባኤ አባላት የቀረበ ሲሆን መምህር እስጢፋኖስ “ከእርሱም በተደረገው ድንቅ ነገር ሕዝቡ ሁሉ ደስ አላቸው” በሚል የዕለቱን ወንጌል ሰጥተዋል።

የዋናው ማእከል የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዲ/ን ሲሳይ ብርሃኑ የማኅበሩ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን በማስከተልም ስለ ግንኙነት ጣቢያው አጠር ያለ የስራ ሂደት በግንኙነት ጣቢያው የሕዝብ ግንኙነት ተወካይ መቅረቡ ተገልጿል።

በመጨረሻም በአባቶች ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ተሰጥቷል።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
Ready for an Epic Gathering, yet again?

Calling all incoming freshmen, college students, and recent grads! Join us for our 7th in-person General Assembly this July in Atlanta! Don’t miss out – register now to secure your spot using the link below. Let’s embark on this spiritual journey of connection and enlightenment together.
We can’t wait to see you!

Registration form:
https://forms.gle/cqgiQz4tcv8SwNhU6
"ምንጮች እንዳይደርቁ ጉባኤ ቤቶችን እንገንባ" በሚል መሪ ቃል የምክክርና የዉይይት መርሐ ግብር መካሔዱን ማኅበረ ቅዱሳን የባሕር ዳር ማእከል ገለጸ

የካቲት ፳፰/፳፻፲፯ ዓ.ም

ማኅበረ ቅዱሳን የባሕር ዳር ማእከል ከባሕር ዳርና ሰሜን ጎጃም አኅጉረ ስብከቶች ጋር በመተባበር የአብነት ጉባኤ ቤቶች ልዩ የምክክርና የውይይት መርሐ ግብር ከየካቲት 26 እስከ 27/6/2017 ዓ.ም ማካሔዱን ተልጿል፡፡

በጉባኤው የባሕር ዳርና የሰሜን ጎጃም አኅጉረ ስብከቶች፣ የወረዳ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጆች፣ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ የሰበካ ጉባኤ ተወካዮች፣ የአብነት ጉባኤ ቤት መምህራን ተወካዮችና ከ130 በላይ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የባሕር ዳር ማእከል ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አይሸሹም የኔው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን በጉባኤው መክፈቻ መርሐ ግብር ክቡር መልአከ ሰላም ኤፍሬም ሙሉዓለም የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ተገኝተው መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ በመልእክታቸውም ጉባኤ ቤቶች መሠረቶቻችን መሆናቸውን አንስተው “ሁላችንም በጉባኤ ቤቶቻችን ላይ በትኩረት ልንሠራ ይገባል” ብለዋል፡፡

መርሐ ግብሩ የአብነት ት/ቤቶችን የሚመለከት ዳሰሳዊ ጽሑፍ በዲ/ን ግሩም መሠረትና የአብነት ት/ቤቶች ሚና ትናንት፣ ዛሬና ነገ የሚል ጽሑፍ በመ/ር አስተርዓየ ገላው ቀርበው ሰፊ ዉይይት የተደረገባቸው ሲሆን በውይይቱም የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ቀርበው የቀጣይ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል፡፡

በዝግጅቱ የግብጽ ኮፕቲክ ቤተ ክርስቲያን ተሞክሮ በመ/ር ኃይለማርያም ዘውዱና የአብነት ት/ቤቶችን አስተዳደር ለማዘመን የተዘጋጀው የመረጃ ቋት መተግበሪያ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሶፍትዌር ባለሙያ፣ የገዳማትና መንፈሳዊ ት/ቤቶች አገ/ት ዋና ክፍል አባል በሆኑት ወንድም ጌትነት መቅረቡ ተጠቁሟል።
በጉባኤው የመፍትሔ ሐሳቦችን የሚያመላክት አጭር መነሻ ሐሳብ በዲ/ን አዲሱ ሙሉጌታ በማንሳት በቡድን በውይይቱ የተደረገ ሲሆን የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት የትምህርት መምሪያ ኃላፊ ሊቀ ጉባዔ ሙሉጌታና የሰሜን ጎጃም ሀገረ ስብከት ትምህርት ክፍል ኃላፊ መ/ገነት መልአከ የማጠቃለያ ሃሳብ ሰጥተዋል፡፡

ከሰሜን ጎጃም ሀገረ ስብከት ተወክለው የተገኙት መልአከ ምህረት ግሩም አለነ የሰሜን ጎጃም ሀገረ ስብከት ስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ አገልግሎት ክፍል ኃላፊ ጉባኤውን ያዘጋጀውን ማእከሉን አመስግነው ሁሉም የቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ መዋቅር ለጉባኤ ቤቶች ልዩ ትኩረት መስጠት እንደሚገባ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በመጨረሻም ጉባኤዉን በተመለከተና በቀጣይ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር መሥራት በሚቻልባቸዉ ጉዳዮች  ዙሪያ የማኅበሩን አቅጣጫዎች የማአከሉ ጽ/ቤት ኃላፊ በሆኑት አቶ አይሸሹም የኔው ቀርበው መርሐ ግብሩ ተጠናቋል፡፡
2025/03/16 11:00:28
Back to Top
HTML Embed Code: