✍️ ሐመር መጽሔት የመጋቢት ወር እትም እንዳታመልጣችሁ
".. # የሊቃውንት ጉባኤ፣የቤተ ክርስቲያን አቅምና የችግሮች መፍትሔ" መጋቢት ዕትም በ፳፻፲፯ ዓ.ም ዐቢይ ጉዳይ ዐምድ ✍️
༺ ༻
#የኅትመት ዘመን ፦#መጋቢት ፳፻፲፯ ዓ.ም
#አዘጋጅ ፦በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኀበረ ቅዱሳን በልማት ተቋማት አስተዳደር በመጽሔት ዝግጅት ክፍል የሚዘጋጅ ትምህርታዊ መጽሔት
• ገጽ ብዛት፦፳፰
ዋጋ ፦፵ ብር
• ሐመር መጽሔት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖት ሥርዓትና ትወፊት ጠብቃ በልማት ተቋማት አስተዳደር በመጽሔት ዝግጅት ክፍል በየወሩ የምትወጣ መንፈሳዊ መጽሔት ናት፡፡
• ሐመር መጽሔት ፴፪ኛ ዓመት ቁጥር ፫ # የመጋቢት ፳፻፲፯ ዓ.ም መልእክት ዘማኅበረ ቅዱሳን " ዘመኑን የዋጀ የሊቃውንት ጉባኤ አገልግሎት ለቤተ ክርስቲያን ›› በሚል የዘመናችን ፈተናዎች ደግሞ ከቀደሙ አባቶች ዘመን ፈተናዎች የተለዩ መሆናቸው እሙን ነው፡፡
የዘመናችን ፈተናዎች ረቂቅ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ አስቸኳይ መፍትሔን የሚሹ ናቸው። የግሎባላይዜሽን፣የቴክኖሎጂ ግስጋሴዎች፣ የሴኩላሪዝም ርእዮት እና የአዳዲስ እምነቶች እንቅስቃሴዎች መስፋፋት ከዚህ በፊት በአይነትም በስፋትም ታይተው የማያውቁ ፈተናዎች እየሆኑ እነዚህን ችግሮች ከሥር ከሥራቸው እየፈቱና
መልክ እያሳዙ ለመሄድ የሊቃውንት ጉባኤ አቅምን የሚጠይቁ በመሆናቸው ሊቃውንቱ እንደ ጠቢባን በመጠበብ፣ እንደ መንፈሳውያን አበውም በመጸለይና የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሥርዓትና ሐዋርያዊ አስተምህሮ መጠበቅ ይገባል፡፡

በአጠቃላይ ሲታይ አንዳንድ ችግሮችን በቶሎ ለመፍታት ከመመኘት የተነሣ የተጣደፈ ውሳኔ ወደ መወሰን ከመሄድ መታቀብና ማስተዋልንና ጥናትን ማዕከሉ ያደረገ የአሠራር ስልት ቢዘጋጅ፤ ሊቃውንቶቻችን መረዳታቸውና መረጃቸው ቤተ ክርስቲያንን ከገጠሟት ፈተናዎች በላይ የሆነ፣ ከአካባቢያዊ እስከ
ዐለም አቀፋዊ ያሉ ሃይማኖታዊና መሰል ጉዮችን በንስር ዓይን የሚያይ ሊሆን የሚገባ መሆኑ በሆነ መንገድ ጠቆም ቢደረግ፣ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን “ጉባኤያዊነት” እንደ መሆኗ (በግለሰባዊነት ላይ የቆመች አይደለችምና)፣ ይህን የቤተ ክርስቲያንን ጉባኤያዊነት ማዕከል ያደረገ የአሠራርና ውሳኔ ሂደት እንዲጠናከር ቢደረግ በማለት ሐመር በመልእክት ዐምድ ታስነብባለች።
.#ዐውደ ስብከት ሥር” # ነገርን ሁሉ በልክ አድርጠው ” በሚል ርእስ በስፋት ታስነብባለች።
#በትምህርተ ሃይማኖት ዐምድ ሥር “# መኑ ይእቲ ዛቲ " ክፍል ሁለት " በሚል ዐቢይ ርእስ ድኅነታችን እና የእመቤታችን ድርሻ የሊቃውንት መጽሐፍ በማጣቀስ ትምህርት ይሰጣል ።
#ዐቢይ ጉዳይ ዐምድ ሥር ደግሞ “# የሊቃውንት ጉባኤ፣የቤተ ክርስቲያን አቅምና የችግሮች መፍትሔ" በሚል ርእስ የሊቃውንት ጉባኤ ትርጓሜን፣የሊቃውንተ ጉባኤ ጥንተ ነገር፣ የሊቃውንት ጉባኤ በቤተ ክርስቲያን ፣የሊቃውንት ጉባኤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፣ የሊቃውንት ጉባኤ አሁናዊ ሁኔታ ፣ የዘመናችን ሊቃውንት ጉባኤ ለወቅቱ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ፣ የሊቃውንት ጉባኤ አስተዳደራዊ አወቃቀሩና የአደረጃጀቱ በተመለከተ በዝርዝር ያሳያል ።
• #ክርስትና በማኀበራዊ ዐምድ ሥር ደግሞ "#የኦርቶዶክሳዊ ጋብቻ ትምህርት " ክፍል -፪ በሚል ርእስ ዐቢይ ርእስ በመልአከ ሰላም ቀሲስ ደጀኔ ሺፈራው የትዳር ጓደኛችንን ራሳችን መምረጥ እንዳለብን ፣ ምክረካህን እንደሚያስፈልግ ፣የቤተሰብ ምክር እንደሚያስፈልግ፣ መጠናናት እንደሚያስፈልግ ፣የባልንጀራ ምክር አስፈላጊነትና ትዳር አቅለለው ሁሉ ነገር ቀላል ነው ፣ካከበዱትም ሁሉ ነጠር ከባድ ነው በሚል ሰፊት ትምህርት ታሰተምራለች።
• #በእናስተዋውቃችሁ ዐምድ ሥር “#ጅማ ፈለገ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል" በሚል ርእስ ስለ ጅማ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አመሠራረት ፣ስለ ጸበሉ ፈዋሽነት፣ስለ ልማት አገልግሎት፣ ስለ ስብከት አገልግሎት ፣ ስለ አጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ መፍትሔዎች በስፋት ታስቃኛለች ።
• #በነገዋ ቤተ ክርስቲያን #ዐምድ ሥር “ መንፈሳውያን ማኅበራት ለነገዋ ቤተ ክርስቲያን " በመ/ር ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል ክፍል ፬ በሚል ርእስ በ፭ መንፈሳውያን ማኀበራት በሕግና ደንብ መሠረት በአግባቡ ካልተደራጁ በቤተ ክርስቲያን ላይ ሊያደርሱ የሚችሏቸውን መሠረታዊ ችግሮች በስፋት ይዛለች ።
#በኪነ ጥበብ ዐምድ "#ሞት የቀደመው ፀፀት "በሚል ርእስ ታስነብባለች ።
• #የጥያቄዎቻችሁ መልስ ዐምድ “የማዕረግ ስም አሰጣጥ # ክፍል ፪ " በሚል ርእስ #በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የሐዲስ ኪዳን የአንድምታ ትርጓሜ መምህር የሆኑትን #መጋቤ ሐዲስ ስቡሕ አዳምጤን ጋር የተደረገ ጥያቄና መልስ ይዛለች። የማዕረግ ስም ከቦታ አንጻር እንዴት እንደሚገለጽ፤የማዕረግ ስም የማውጣት ሥልጣን የማን እንደሆነ ፣የማዕረግ ስም አወጣጥ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮች፣ የማዕረግ ስም አወጣጥ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን እንዴት መፍታት እንደሚቻል መፍትሔ ተቀምጧል።
መጋቤ ሐዲስ ስቡሕ አዳምጤ "አሁን አሁን የአራቱ ጉባኤያት መምህር ይባሉና ግን አራቱን ጉባኤያት ያስተምራሉ ወይ ሲባል በተግባር አይገኙም "ይላሉ ።
ሐመር መጽሔት #፴፪ ኛ ዓመት ቁጥር ፫ በማሰራጨት ፡በማንበብና በማስነበብ የድርሻችን እንወጣ !
magazine @eotcmk.org #ሐመር #መጽሔትበ ዝግጅት ክፍል
━━━━━༺✞༻━━━━

አደራ አለብኝ
ዓለም ዓቀፍ የግቢ ጉባኤ ምሩቃን ኅብረት ጉባኤ ዛሬ ማታ ከምሽቱ 2:00-3:00 ሰዓት 👇👇👇👇👇👇https://www.tg-me.com/gibigubayat_mirukan_hibret ይካፈሉ።

‘’ኑ የእግዚአብሔርን ቤት በጋራ እንሥራ’’ በሚል መሪ ቃል ሥልጠናና ውይይት መካሄዱን በማኅበረ ቅዱሳን የደ/ታቦር ማእከል ገለጸ፡፡
መጋቢት ፫/፳፻፲፯ ዓ.ም
በማኅበረ ቅዱሳን የደ/ታቦር ማእከል በደ/ታቦር ከተማ ከሚገኙ የሰንበት ት/ቤት ሥራ አስፈጻሚዎች ጋር ‘’ኑ የእግዚአብሔርን ቤት በጋራ እንሥራ’’ በሚል መሪ ቃል ሥልጠናና የጋራ ውይይት አካሄዷል፡፡
መርሐ ግብሩ በደ/ታቦር ከተማ ከሚገኙ 50 የሰንበት ት/ቤት ሥራ አስፈጻሚዎች ጋር የሥልጠና፣ ተሞክሮ እና ውይይትያደረገ ሲሆን የሰ/ት/ቤቶች ምስረታ፣ ተግዳሮቶች፣ የአኃት አቢያተ ክርስቲያናት ተሞክሮ እና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች የሚሉ ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ያተኮረ ሥልጠና በማኅበረ ቅዱሳን የደ/ታቦር ማእከል ሰብሳቢ በዲ/ን ዶ/ር ለማ ጉልላት ተሰጥቷል፡፡
አሠልጣኙ ሰ/ት/ቤቶቻችን መሰረታዊ ዕውቀትን ማስገንብ፣ ነገረ ድኅነትን መሠረት ያደረገ አገልግሎት፣ መጭውን ዘመን መቅደም፣ ትውልዱን በሁለም መንገድ መጠበቅ፣ በሁሉም ነገር አዎንታዊ ተጽእኖ መፍጠር፣ አቅዶ መሥራትና በጋራ መልማት ላይ ሊያተኩሩ ይገባል ሲሉ ማጠቃለያ ሰጥተዋል፡፡
ከሥልጠናው በኋላም እንደ ደ/ታቦር ከተማ ሰ/ትቤቶቻችን ያሉበት ሁኔታ፣ ተሞክሮዎች እና ወደ ፊት ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች በሚሉ ነጥቦች ላይ ያወያዩትና ማጠቃለያ የሰጡት በደ/ጎንደር ሀ/ስብከት የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ምክትል ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ተስፋገኝ ጎበዜ ናችው፡፡

ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብንና ማኅበረሰብን ለመፍጠርና ሥልጠና ለመሥጠት ከሚሴ ማእከል ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ውይይት አደረገ።
መጋቢት ፫/፳፻፲፯ ዓ.ም
የማኅበረ ቅዱሳን ሙያ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት ሥልታዊ ትኩረት አድርጎ ከሚሠራቸው አገልግሎቶች አንዱ በሁለንተናዊ የምክክር አገልግሎት የሚሰማሩ ካህናትና ባለሙያዎችን በማሠልጠንና በማሰማራት ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብንና ማኅበረሰብን የሚያጠናክሩ አካላትን ማፍራት አንዱ ነው።
በዚሁ መሠረት ከመጋቢት 20 እስከ 21/2017 ዓ.ም በከሚሴ ሀገረ ስብከትና ማኅበረ ቅዱሳን በከሚሴ ማእከል አስተባባሪነት ለምእመን እና ካህናት አባቶች ሥልጠናውን ለመስጠት ከሰ/ት ት/ቤት፤ ከተስፋ ነደያን በጎ አድራጎት እና ከተለያዩ ጽዋ ማኅበራት ስራ አስፈፃሚዎች ጋር ውይይት ተደርጓል።
በውይይቱ ክብረ ክህነትና አበ ነፍስ፣ መንፈሳዊ የምክክር አገልግሎት አሰጣጥና የምክክር መስጫ ስለመፍጠር፣ ኦርቶዶክሳዊ ጋብቻና የልጆች አስተዳደግ፣ የሱስ ችግሮችን ለማቃለል የአመካካሪዎች ሚና እንዲሁም ምጣኔ ሐብታዊና ማኅበራዊ እድገትን በተመለከተ የተዘጋጁ ይዘቶች ተዳሰው እንደሚሠጡ ገለፃ ተደርጓል፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን ለዝግጅቱ መሳካት አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ለሚተባበሩት የከሚሴ ሀገረ ስብከትና በገንዘብና ቁሳቁስ ጭምር ድጋፍ ለሚያደርጉ የቤተ ክርስቲያን አካላት በቅንጅት አብረው እንደሚሠሩ በሰፊው ውይይት ተደርጓል፡፡
ሥልጠናው በሁለት ወረዳ ማእከላት ሲሰጥ የቆየ መሆኑን የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

የስብከተ ወንጌል ተደራሽነትን በሀገሪቱ ከፍሎች ለማስፋፋት ሥራዎች እየተሠሩ አንደሚገኙ በማኅበረ ቅዱሳን የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ አገልግሎት ማስተባበሪያ አስታወቀ
መጋቢት ፬/፳፻፲፯ ዓ.ም
በማኅበረ ቅዱሳን የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ አገልግሎት ማስተባበሪያ የስብከተ ወንጌል ተደራሽነትን በሀገሪቱ ክፍሎች ለማስፋፋት ሥራዎች እየተሠሩ እንደሚገኙ አስታውቋል፡፡
የማስተባበሪያው ዳይሬክተር ዲያቆን ሙሉጌታ ነጋ እንደገለጹት የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል ለሰው ልጆች እንዲዳረስና የቤተ ክርስቲያን ተልእኮ እንዲሳካ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡
ስብከተ ወንጌልን ለማስፋፋት የርቀት ትምህርት የመስጠት፣በድምፅ ወምስል የቤተ ክርስቲያን ትምህርቶችን በልዩ ቋንቋዎች የማሰራጨት፣ሰባክያነ ወንጌል መምህራንን የማሠልጠንና በቴክኖሎጂ የሀሎ መምህር አገልግሎት የመስጠት ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል፡፡
እየተከናወነ በሚገኘው የወንጌል አገልግሎት አዳዲስ አማንያን አምነው ተጠምቀው የሥላሴ ልጅነት ማግኘታቸው፣ ቤተ ክርስቲያን በሌለባቸው አካባቢዎች እየታነጹ መሆናቸው እንዲሁም ከተጠመቁት ውስጥ ተምረው ሰባክያነ ወንጌል፣ካህናት፣ዲያቆናትና የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት መገኘታቸው በመሠረታዊ አዲስ ለውጥ እንደሚጠቀሱ ዳይሬክተሩ አንሥተዋል፡፡
ዲያቆን ሙሉጌታ አክለውም የጸጥታ ችግሮች፣ የአጽራረ ቤተ ክርስቲያን እንቅስቃሴዎች መብዛት፣የበጀት እጥረቶች፣ የቤተ ርስቲያን አገልግሎት ከማኅበራዊ፣ከኢኮኖሚያዊና ከልማታዊ ሥራዎች ጋር አለመቀናጀት ስብከተ ወንጌልን ለማዳረስ ተግዳሮቶች ቢሆኑም በተቻለ አቅም የቤተ ክርስቲያንን ተልእኮ ውጤታማ እንዲሆን እየተሠራ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡