Telegram Web Link
በቀጣይነትም የወንጌል አገልግሎት ተደራሽነትን ለማሳደግ ሥራዎች በትኩረት እየተሠሩ በመሆናቸው ምእመናንና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን እንዲወጡ መልእታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በዚህ ዓመት 20 ሺህ 57 አዳዲስ አማንያን ተጠምቀው ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የተቀላቀሉ ሲሆን 1ሺህ 19 ተማሪዎች በአማርኛና በኦሮምኛ ቋንቋዎች የርቀት ትምህርት እየተማሩ ይገኛሉ፡፡

በተጨማሪም በ0111 55 32 32 32 ወደ ሀሎ መምህር በመደወል ከሰኞ እስከ ዐርብ ባሉት ቀናት ሃይማኖታዊ ጥያቄዎችን በመጠየቅ ምላሽ ማግኘት እንደሚቻል ተገልጿል፡፡
በቤንሻንጉል ጉሙዝ አሶሳ ሀገረ ስብከት ለሚተገበረው አዳሪ አብነት ት/ቤት የመሠረት ድንጋይ  ተቀመጠ።

መጋቢት፭/፳፻፲፯ ዓ.ም

ማኅበረ ቅዱሳን ድጋፍ አድራጊዎችን በማስተባበር በአሶሳ ሀገረ ስብከት ለሚተገብረው ኘሮጀክት በአምባ አራት ሐመረ ኖኅ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ገዳም መጋቢት ሦስት ቀን 2017 ዓ.ም የመሠረት ድንጋይ የማስቀመጥ መርሐ ግብር ተከናውኗል።

በመርሐ ግብሩ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል ፣ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ፀሐይ ቆሞስ አባ ዘካርያስ ፀጋው ፣ የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ሥራ አስፈፃሚ መምህር ዋሲሁን  በላይ ፤ የሀገረ ስብከቱ የየመምሪያ ኃላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የአካባቢው ምእመን በተገኙበት የመሠረት ድንጋይ ተቀምጧል።

ብፁዕነታቸው በመልእክታቸው  የሚገነባው የአብነት ትምህርት ቤት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ሀገረ ስብከት ሥር ላሉ የዞኖችና ወረዳዎች በተለይም ለጉሙዝ፤ ለሽናሻ እና ለመሳሰሉት ብሔረሰቦች መማሪያ እና የቅድስት ቤተክርስቲያን አገልጋዮችን የሚያፈራ ታላቅ ኘሮጀክት ነው ብለዋል።

አብነት ትምህርት ቤቶች ከሌሉ አቢያተ ክርስቲያናት አይኖሩም ያሉት ብፁዕነታቸው አክለውም  ማኅበረ ቅዱሳን በሀገረ ስብከቱ የሚተገብረው ኘሮጀክት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።

የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ፀሐይ ቆሞስ አባ ዘካርያስ ፀጋው በበኩላቸው ማኅበረ ቅዱሳን ፕሮክቱን በዚህ ለመተግብር ይህን የመሠረት ድንጋይ ሲያስቀምጥ ለተዘጋችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በጎ አድራጊዎችን አስተባብሮ በመሆኑ የተሰጠንን ዕድል በአግባቡ መጠቀም እና የሚጠበቅብንን ድጋፍ ማድረግ ይጠበቅብናል በማለት በመርሐ ግብሩ ላይ ለታደሙ ምእመናን መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
ማኅበረ ቅዱሳን በ2017 ዓ.ም ከሚተገብራቸው ፕሮጀክቶች ውስጥ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ሀገረ ስብከት አሶሳ  ከተማ አምባ 4 ሐመረ ኖኅን ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ገዳም የሚገነባው አዳሪ አብነት ትምህርት ቤት አንዱ ፕሮጀክት መሆኑን በመጥቀስ የፕሮጀክቱ ዓላማ በሀገረ ስብከቱ  መሠረታዊ የክህነት ትምህርት እና ሥልጠና በመስጠት ቀሳውስት ፣ዲያቆናት ፣ ሰባኪያን እና አስተዳዳሪ ደቀ መዛሙርትን በማፍራት የተዘጉ አብያተ ክርስቲያናት እንዲከፈቱ ፣ የተሟላ መንፈሳዊ አገልግሎት የማይሰጡትም እንዲሰጡ በማድረግ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ተልዕኮ ማፋጠን ነው በማለት የማኀበረ ቅዱሳን ዋና ሥራ አስፈፃሚ መምህር ዋሲሁን በላይ ተናግረዋል።

ማኅበሩ ትኩረት ሰጥቶ ከሚሠራቸው  ተግባራት መካከል የአዳሪ አብነት ት/ቤቶችን በመገንባት የሐዋርያዊት ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ ሳይበረዝ እና ሳይከለስ ለትውልድ ለማስተላለፍ እየሰራ እንደሚገኝም መምህር ዋሲሁን በላይ በመልእክታቸው አክለዋል።

የሚገነባው አዳሪ የአብነት ትምህርት ቤት ዲዛይን  32 ደቀመዛሙርትን በአዳሪነት ፣ ለሁለት መምህራን ማደሪያ ፣ መማሪያ ጉባኤ ቤት ፣ መጸዳጃ ቤት እንዲሁም መመገቢያ አዳራሽን ያካተተ ሲሆን ለፕሮጀክቱ የተያዘለት በጀት 11,523,366 ብር እንደሆነ ዋና ሥራ አስፈጻሚው መምህር ዋሲሁን በላይ ገልጸዋል።

በተጨማሪም መምህር ዋሲይሁን እንደገለጹት  የአሶሳ ሀገረ ስብከት ሲታወስ ሁልጊዜም ከሚነሱት አባቶች መካከል የምእራቡ ኮከብ በመባል ይጠሩ የነበሩት መልአከ ኃይል አባ እንየው ውቤ አንዱ መሆናቸውን ጠቅሰው የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ በነበሩበት ወቅት ታላላቅ አገልግሎቶችን የፈጸሙ የቤተ ክርስቲያን አባት መሆናቸውን ገልጸዋል። 

መምህር ዋሲሁን ጨምረው እንደተናገሩት አባ እንየው ውቤ ትምህርት በቃኝ የማይሉ ትጉህ መምህር የነበሩና ረጅም ዘመናት ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የደከሙ ሲሆን ትውልዱ እሳቸውን የመሰሉ የቀደሙ አባቶች ያቀኑትን አገልግሎት ማስቀጠል ይገባል ብለዋል ።

መልአከ ኃይል አባ እንየው ውቤ በአገልግሎት ጊዜያቸው በአካባቢው ከ117 በላይ አጥቢያ ቤተ ክርስቲንን ያሳነጹ፣ የልማት ሥራዎችን የሠሩ  መሆናቸው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

"ሰውን ሞት እንጂ ሥራ አያሸንፈውም" በሚል መሪ ቃል የሚታወቁት መልአከ ኃይል አባ እንየው ምዕመናንን በመምከር፣ ወጣቱን በመገሰጽና በማስተማር ሥራቸውን በታማኝነት የተወጡ እና አንድም ቀን ያለ ሥራ እና ያለ ዕቅድ ውለው የማያውቁ መሆናቸውን ብዙዎች ይናገሩላቸዋል።
2025/03/14 17:25:54
Back to Top
HTML Embed Code: