Telegram Web Link
"ወደ ቀደመው ነገር እንመለስ!" በሚል መሪ ቃል የአባላት የቃል ኪዳን ማደሻ መርሐ ግብር መካሄዱን ማኅበረ ቅዱሳን የጎንደር ማእከል  አስታወቀ።

መጋቢት ፪/፳፻፲፯ ዓ.ም

በማኅበረ ቅዱሳን የጎንደር ማእከል “ወደ ቀደመው ነገር እንመለስ”  በሚል መሪ ቃል የአባላት የቃል ኪዳን ማደሻ መርሐ ግብር የካቲት 30 ቀን 2017 መካሄዱ ተገልጿል።

በመርሐ ግብሩ የማኅበረ ቅዱሳንን ተቋማዊ ለውጥ አስመልከቶ የጎንደር ማእከል ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፈቃዴ ፈጠነ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን የአቡን ቤት ቅዱስ ገብርኤል የቅኔ ምስክር ጉባኤ ቤት መምህር እና የ4ቱ መጽሐፍተ ጉባኤያት መምህር መጋቤ ምስጢራት የኔታ ነቅዓጥበብ እሸቴ ስብከተ ወንጌል ሰጥተዋል።

በጎንደር ማእከል የአባላትና ወረዳ ማእከላት ማስተባበሪያ ዋና ክፍል ኃላፊ አቶ ገብረሚካኤል መጣዓለም አማራጭ የአገልግሎት በር በሚል ርዕስ ሰፊ ሥልጠና የተሰጠ ሲሆን ተሳታፊዎች የተዘጋጀላቸውን የቃል ኪዳን ማጽናኛ ቅጽ እንዲሞሉ ተደርጓል።
የግቢ ጉባኤያት ተማሪዎች በመንፈሳዊ ሕይወታቸው እና በትምህርታቸው መጠንከር እንደሚገባቸው ተገለጸ፡፡

መጋቢት ፪/፳፻፲፯ ዓ.ም

በማኅበረ ቅዱሳን የጅግጅጋ ማእከል በዩኒቨርሲቲው ግቢ ጉባኤያት ተማሪዎች በ2016ና 2017 የትምህርት ዘመን የተገኙ ሦስት ዋንጫዎችና አንድ ሜዳሊያ ዋና ማእከልን በመወከል በቦታው ተገኝተው  ከተማሪዎቹ የተረከቡት መጋቤ ብርሃናት ቀሲስ ሙሉቀን ብርሃኑ ለማኅበረ ቅዱሳን ዋና ስራ አስፈጻሚ ለመምህር ዋሲሁን በላይ አስረክበዋል።

መምህር ዋሲሁን በላይ የማኀበሩ ዋና ስራ አስፈጻሚ ባስተላለፉት መልእክት አዲሱ የግቢ ጉባኤያት ሥርዓተ ትምህርት ተቀርጾ የግቢ ጉባኤያት ተማሪዎችን በማስተማር ቤተ ክርስቲያናቸውን፣ሀገራቸውን እንዲሁም ቤተሰቦቻቸውን እንዲጠቅሙ እየተተገበረ ይገኛል ብለዋል።

ማኀበረ ቅዱሳን ዛሬ የተረከባቸውን የዋንጫዎች እና የሜዳሊያ ሥጦታዎች ለሌሎች ተማሪዎች መነሳሻ ብሎም አርአያ እንዲሆኑ በቅርስነት እንደሚቀመጡ መምህር ዋሲሁን ጠቁመዋል፡፡

አክለውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ግቢ ጉባኤያት ተማሪዎች በዓላማቸው በመጽናት በመንፈሳዊ ሕይወታቸውና በትምህርታቸው መጠንከር እንደሚገባቸው ያሳሰቡ ሲሆን ማኀበሩን አክበረው ተማሪዎቹ የልፋታቸው ውጤት የሆኑትን ዋንጫዎችና ሜዳሊያ  በመስጠታቸው በእግዚአብሔር ስም አመስግነዋል፡፡
ጠንካራ ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብንና ማኅበረሰብን ለመፍጠር  እየተሠጡ ያሉ የአመካካሪዎች ሥልጠና ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለጸ ።

መጋቢት ፫/፳፻፲፯ ዓ.ም

የማኅበረ ቅዱሳን ሙያ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት ሥልታዊ ትኩረት አድርጎ ከሚሠራቸው አገልግሎቶች አንዱ በሁለንተናዊ የምክክር አገልግሎት የሚሰማሩ ካህናትና ባለሙያዎችን በማሠልጠንና በማሰማራት ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብንና ማኅበረሰብን የሚያጠናክሩ አካላትን ማፍራት አንዱ ነው።

በዚሁ መሠረት ከየካቲት 29 እስከ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ  በድሬዳዋ ሀገረ ስብከትና በድሬዳዋ ማእከል አስተባባሪነት ከሀገረ ስብከቱ የተውጣጡ 18 ካህናት፣ 6 የዘርፉ  ባለሙያዎች በድምሩ 24 አመካካሪዎች ሥልጠናውን እንዲወስዱ ተደርጓል።

በዚህ ሥልጠና ክብረ ክህነትና አበ ነፍስ፣ መንፈሳዊ የምክክር አገልግሎት አሰጣጥና የምክክር መስጫ ስለመፍጠር፣ ኦርቶዶክሳዊ ጋብቻና የልጆች አስተዳደግ፣ የሱስ ችግሮችን ለማቃለል የአመካካሪዎች ሚና እንዲሁም፣ ለድሬዳዋ ማእከል አባላት ምጣኔ ሐብታዊና ማኅበራዊ እድገትን በተመለከተ የተዘጋጁ ይዘቶች ተዳሰው ቀርበውበታል፡፡
በተመሳሳይ ይዘትና አቀራረብ በሌሎችም ማእከላት ሥልጠናው ሲሰጥ የቆየ መሆኑን የተገኘው መረጃ የሚያመለክት ሲሆን ማኅበረ ቅዱሳን ለሥልጠናው መሳካት ቦታ አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ጭምር ለተባበሩት የድሬዳዋ ሀገረ ስብከትና ማእከከሉን እያመሰገነ ቀጣይ በሌሎች አካባቢዎች ለሚሰጠው ሥልጠናም በገንዘብና ቁሳቁስ ጭምር በመደገፍ የቤተ ክርስቲያን አካላት በቅንጅት አብረው እንዲሠሩ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
ይህን የሥልጠና መርሐ ግብር በገንዘብ መደገፍ ለምትፈልጉም፡-
#በማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሒሳብ ቁጥሮች፡-
1. በአሐዱ ባንክ - 0025393810901
2. በአቢሲንያ ባንክ - 37235458
3. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000309803648
4. በወጋገን ባንክ - 0837331610101
5. በአዋሽ ባንክ 01329817420400 መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የማኅበረ ቅዱሳን ሙያ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት
2025/03/15 07:22:11
Back to Top
HTML Embed Code: