Telegram Web Link
የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ነፃ የትምሕርት ዕድል መርሐ ግብር ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ተባለ።
  ( ግንቦት 18/2017)
የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ነፃ የትምሕርት ዕድል መርሐ ግብር አፈጻጸምና ቀጣይነቱ ላይ ትኩረት ያደረገ የዳሰሳ ጽሑፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ ውይይቱ በማኅበረ ቅዱሳን የቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ ዕድገትና መንፈሳዊ ትምሕርት ቤቶች አገልግሎት  አዘጋጅነት በራስ አምባ ሆቴል ባሳለፍነው ቅዳሜ  ግንቦት 16/2017 ዓ/ም የተከናወነ ሲሆን ‘’የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ነፃ የትምሕርት ዕድል መርሐ ግብር አፈጻጸምና ቀጣይነቱ’’ በሚል ርእስ የዳሰሳ ጽሑፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል ።
                                                                    በማኅበረ ቅዱሳን የተጀመረው ነፃ የትምሕርት ዕድሉ  በሦስት ዘርፎች ላይ ያተኮረ ሲሆን ከዘመናዊ ት/ት ወደ አብነት ት/ት፣ ከአብነት ወደዘመናዊ  እና  የአገልጋይ እጥረት ካለባቸው ጠረፋማ አከባቢዎች ወደ ነገረ መለኮት ዪኒቨርሲቲና ኮሌጆች  ገብተው እንዲማሩ የሚያስችል መርሐ ግብር  ሲሆን መርሐግብሩ  ባለፉት አሥር  ዓመታት  ተስፋ ሰጪ አፈጻጸም   እንደታየበት  በውይይቱ ተገልጿል። በዚህም 93 በመቶ መርሐ  ግብሩ ውጤታማ እንደሆነ ነው የተነገረው፡፡
                                                                                                                                                                                  
👍2
  በበጀት እጥረት፣ መስፈርቱን የሚያሟሉ ተማሪዎችን  አለማግኘት እና በመሳሰሉት ችግሮች ቀሪዎቹን ሰባት በመቶ ማሳካት አልተቻለም ተብሏል። ከ180 በላይ አገልጋዮችን የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ነፃ የትምሕርት ዕድል ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉንም በቀረበው የዳሰሳ ጽሑፍ ተጠቅሷል።
   
    የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ነፃ የትምሕርት ዕድል መሰጠት በመቻሉ በተለያዩ  ዩኒቨርሲቲዎች የግእዝ መምህራንን ማፍራት ተችሏል፣ ደቀ መዛሙርት ወደየ ሀገረ ስብከታቸው ተመልሰው ቤተ ክርስቲያንን በብቃት እንዲያገለግሉም አስችሏል ተብሏል።
                                                                   መርሐ ግብሩን   የሚያስፈጽም አደረጃጀት ጠንካራ አለመሆን፣ የበጀት እጥረት እና ግልጽ የሥምሪት አቅጣጫ አለመቀመጥ   መርሐ ግብሩን  በታሰበለት ልክ ማከናወን  እንዳይቻል ያደረጉ ተግዳሮቶች  መሆናቸው የገተገለጸ ሲሆን  በቀጣይ የፋይናንስ አቅምን በማጠናከር፣ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ፣ ፖሊሲ እና መመሪያ በማዘጋጀት የመርሐ ግብሩን ዓላማ በማሳካት ቀጣይነቱ ላይ መሥራት እንደሚያስፈልግ  ተጠቁሟል።
    
   የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ሥራ አስፈጻሚ መ/ር ዋሲሁን በላይን ጨምሮ የማኅበረ ቅዱሳን የሥራ አመራር እና ፣  የሥራ አስፈጻሚ ተወካዮች፣ ከጉዳዩ ጋር ቅርበት ያላቸው ተጋባዥ እንግዶች፣  በማኅበረ ቅዱሳን የቤተክርስቲየን ሁለንተናዊ እድገት እና መንፈሳዊ ት/ቤቶች አገልግሎት አገልጋዮች ፣ የጉባኤ ቤት መምህራን እና በአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ነጻ የትምህርት ዕድል ተጠቃሚ የነበሩና  መምህራን  በውይይቱ ላይ ተሳትፈዋል። 
👍14🙏21
ማኅበረ ቅዱሳን ወርኅ ግንቦትን “ግንቦት ልደታን ለግቢ ጉባኤያችን” በሚል መሪ ቃል 33ኛውን የግቢ ጉባኤያት ምስረታ አስመልክቶ በልዩ ልዩ መርሐ ግብራት እያከበረ ይገኛል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ግንቦት 24 ቀን 2017 ዓ.ም የሚካሔደው የገቢ ማሰባሰቢያ የቀጥታ ስርጭት መርሐ ግብር ዋነኛው ነው፡፡ እርስዎም በዕለቱ በሚኖረው የቀጥታ ስርጭት በመሳተፍ የድርሻዎን ይወጡ፡፡
11👍2
ማኅበረ ቅዱሳን እየተገበረ በሚገኘው ስልታዊ ዕቅድ ላይ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን የዐሥር ዓመት መሪ ዕቅድ ለማሳካት እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ አስታወቀ

ግንቦት ፲፱/፳፻፲፯ ዓ.ም

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዐሥር ዓመት እተገብራቸዋለው ብላ የያዘቻቸው መንፈሳዊና ኢኮኖሚያዊ ዕቅዶች ለመተግበር ማኅበረ ቅዱሳን በስልታዊ ዕቅዱ ላይ አካቶ በሁሉም ማእከላት እንዲተገበሩ እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቋል።

የማኅበረ ቅዱሳን ሕዝብ ግንኙነትና ትብብር አገልግሎት ማስተባበሪያ ም/ሥራ አስኪያጅ ዲ/ን ሲሳይ ብርሃኑ እንደገለጹት የማኅበረ ቅዱሳን ስልታዊ ዕቅድ የቤተ ክርስቲያኒቱን መሪ ዕቅድ ተከትሎ ለመደገፍ በሚያስችል ሁኔታ የተዘጋጀ በመሆኑ ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ ከ2016 ዓ.ም ወዲህ በርካታ ተግባራት የተከናወኑ ሲሆን ማኅበሩ ለዚህ መሪ ዕቅድ ተግባራዊነትና ውጤታማነት ሊሠራባቸው በሚገቡ ጉዳዮች ላይ ውይይቶች ተደርገዋል ብለዋል።

ማኅበረ ቅዱሳን በሀገር ውስጥና በውጭ በሚገኙ ማእከላቱ እንዲሁም የግንኙነት ጣቢያዎች ያሉትን አባላትና ባለሙያዎች በማሳተፍ ለመሪ ዕቅዱ መሳካት ከሀገረ ስብከቶቻቸው መመሪያ በመቀበል ድጋፍ እንዲያደርጉ አቅጣጫ ማስቀመጡም ተጠቅሷል።

ማኅበረ ቅዱሳን በስልታዊ ዕቅዱ ውስጥ ከቤተ ክርስቲያን መሪ ዕቅድ ጋር የሚጣጣሙ በርካታ አገልግሎቶችን አካቶ እንዲተገበሩ እያደረገ ሲሆን እነዚህ ዕቅዶች ለቤተ ክርስቲያን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንደሚኖራቸውም ተጠቁሟል። 

የቤተ ክርስቲያን መዋቅር ላይ ያሉ አካላት መሪ ዕቅዱ ትልቅ ጥቅም እንዳለው በማመን ለውጤታማነቱ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ሊያበረክቱ እንደሚገባ ም/ሥራ አስኪያጁ ገልጸዋል።
👍98🕊2
የቦታ ለውጥ ተደርጓል፡-
👇   👇   👇

በማኅበሩ 3ኛ ወለል ላይ የነበረው ወደ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ ተቀይሯል፡፡
ግቢ ጉባኤያትን በተሻለ ጥራት የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ለማስተማር፣ መምህራንን ለማፍራትና አስፈላጊውን አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ መሠረተ ልማቶችን ለማሟላት በገቢ ማሰባበስብ መርሐ ግብሩ ላይ ይሳተፉ፤ የድርሻዎንም ይወጡ፡፡
1
የቅዱስ ሲኖዶስ  መግለጫ

ግንቦት ፳/፳፻፲፯ ዓ.ም

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡፡
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 በተደነገገው መሠረት የርክበ ካህናት መደበኛ ስብሰባውን ከግንቦት 6 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ግንቦት 19 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ አካሂዷል፡፡
የመንበረ ሐዋርያት ወራሽ የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ ለቤተ ክርስቲያናችን አንድነትና እድገት፣ ለሀገር ሰላምና መረጋጋት፣ ለሐዋርያዊ ተልእኮ መስፋፋትና ለመንፈሳዊ ልዕልና ልዩ ትኩረት በመስጠት አስፈላጊ ውሳኔዎችን አሳልፎአል፡፡
በዚሁ መሠረት፡-
1. ለሰላምና ለአንድነት ቅድሚያ መስጠት፣ምትክ ለሌለው የሰው ልጅ ሕይወት ባለአደራ የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ ስለ ሰላም ያለማቋረጥ መጸለይ፣ ጸሎተ ምሕላ ማወጅ፣ የሰላምና የአንድነት ጥሪ ማስተላለፉ እንደተጠበቀ ሆኖ ለሰላምና ለአንድነት ልዩ ትኩረት ሰጥተው ሁሉን አቀፍ ሥራ የሚሠሩ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን “የሀገራዊ ሰላምና የቤተ ክርስቲያን አንድነት ኮሚቴ” በማድረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፡፡
ኮሚቴውም ዘላቂ ሰላምንና አንድነትን ለማስፈን፣ የዜጎችን ሕይወት እየነጠቀ ያለው ግጭት እንዲቆም ጥረት እንዲያደርግ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላትን ባካተተ መልኩ በየደረጃው የምክክርና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና፣ ውይይቶችንና የጥናት መድረኮችን እንዲያዘጋጅ፤ አፈጻጸሙንም በየሦስት ወሩ ለቋሚ ሲኖዶስ ሪፖርት እንዲያደርግ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
2. ለሰዋስው ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የትርጓሜ መጻሕፍትና የሴሚናሪ ደቀ መዛሙርት የሚሰጠው የምስክር ወረቀት ዲግሪ እንዲሆን በተወሰነው መሠረት በመማር ላይ ያሉትና በቀድሞው ሥርዓተ ትምህርት ተምረው በመመረቅ ቤተ ክርስቲያናችንን በማገልገል ላይ የሚገኙት ምሩቃን ተጓዳኝ ትምህርቱን ተምረው ዲግሪያቸውን ማግኘት እንዲችሉ የቀረበው ሥርዓተ ትምህርት ተግባራዊ እንዲደረግ፣በኮሌጁ የተጀመረው ሁለገብ ሕንፃም በተያዘለት የጊዜ ሠሌዳ መሠረት እንዲጠናቀቅ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
3. በገዳማት አስተዳደር መምሪያ አስፈጻሚነት የተደረገው የአንድነት ገዳማት ሀገር አቀፍ የምክክር ጉባኤ በየዓመቱ እንዲካሄድና የአቋም መግለጫው ላይ የቀረቡት ሐሳቦች በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት በኩል እየታዩ በቅደም ተከተል እንዲፈጸሙ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አስልፏል፡፡
4. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለሀገራችን እድገትና ሥልጣኔ ፈር ቀዳጅ በመሆን ያበረከተችው አስተዋጽኦ በታሪክ ምዕራፍ ውስጥ ጉልህነት ያለው ሲሆን፣ አሁንም እየተሠራ ባለው የኮሪደር ልማት መርሐ ግብር ላይ ኃላፊነቷን እየተወጣች ትገኛለች፡፡
ይኽን ቋሚ ታሪክ ያልዘነጋው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ የቤተ ክርስቲያንን ይዞታ ለግንባታ በሚያመች ሁኔታ አሰባስቦ በመስጠት ለፈረሱ ቤቶች ካሣ በመክፈል፣ በጽርሐ ምኒልክ ሕንጻ ምትክ በነባሩ ቦታ ላይ B+G+4+ቴራስ በመንግሥት በጀት መልሶ እንዲገነባ በማድረጋቸው ቅዱስ ሲኖዶስ ምስጋናውን ያቀርባል፡፡

በይዞታዎቻችንም ላይ ደረጃውን የጠበቀ ግንባታ ለማካሄድ የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ ተሰይሞ ገቢ የማሰባሰብ ሥራው በሕጋዊ መንገድ እንዲከናወን ቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያ ሰጥቷል፡፡
በመሆኑም በፈረሱት ቤቶች ምትክ የተረከብናቸውን ክፍት ቦታዎች በአጭር ጊዜ ማልማት ግዴታ ስለሆነ በዓለም ዙሪያ ያላችሁ ኦርቶዶክሳውያን የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን እንደ አባቶቻችሁ የታሪክ ባለቤቶች ትሆኑ ዘንድ ልማቱን በገንዘብና በእውቀት እንድታግዙ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
5. በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት የተፈጠረውን የአስተዳደር ችግር አስመልክቶ በብፁዓን አባቶች የሚመራው አጣሪ ልዑክ ባቀረበው ሪፖርት መሠረት ውይይት በማድረግና የሥራ ኃላፊዎቹን በማንሣት ቅዱስ ሲኖዶስ አስተዳደራዊ ውሳኔዎችን አስተላልፏል፡፡
ወደፊትም በየደረጃው ያለውን ችግር ማስተካከል ይቻል ዘንድ ችግሩን እያጠና የሚያቀርብ ኮሚቴ እንዲቋቋም ምልአተ ጉባኤው ወስኗል፡፡

6. ዝክረ ኒቅያ በሚል መሪ ቃል ከመላው ሀገራችን በተወከሉ የምስክር ጉባኤ ቤቶች መምህራን በተካሄደው ጉባኤና የጥናት ውይይት የቀረበው ምክረ ሐሳብ እጅግ የሚጠቅም የሊቃውንት ድምጽ በመሆኑ፣በነገረ ማርያም፣ በነገረ ክርስቶስና በሌሎችም አስተምህሮዎች ዙሪያ የተሰጡት ሐሳቦች የቅዱሳት መጻሕፍት ትርጓሜን መሠረት በማድረግ ተብራርቶና ተስተካክሎ፣ የጎደለው ሞልቶ፣ የጠመመው ተቃንቶ በሊቃውንት ጉባኤ በኩል በመጽሐፍ መልክ እንዲታተም፣በሚዲያ ሊተላለፍ የሚገባው አስተምህሮ ደግሞ በሊቃውንት ጉባኤ ብቻ እንዲተላለፍ፣
የሊቃውንት ጉባኤውም በተሟላ የሰው ኃይልና በጀት ተጠናክሮ እንዲደራጅ፣ሀገር አቀፍ ጉባኤው በዓመት ሁለት ጊዜ እንዲደረግና የጉባኤው መዋቅር በየአህጉረ ስብከቱ እንዲጠናከር ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

7. የመናገሻ አምባ ማርያምና የጋራው ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም አንድነት ገዳም ጥንታዊ የሆነ ሰፊ ታሪክ ያለው በመሆኑ ሁለቱ ገዳማት በአንድ አበምኔት በአንድነት ገዳም ሥርዓት በጋራ እንዲመሩ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤

8. በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ገዳማት መነኰሳትን ከመላክ ጀምሮ፣በአስተዳደራዊና ቀኖናዊ አሠራር ክፍተት ምክንያት የተከሰቱ ችግሮችን በማረምና ሊቀ ጳጳሱን በማዛወር ማእከላዊ መዋቅር እንዲጠበቅ ቅዱስ ሲኖዶስ የወሰነ ሲሆን፣ነባሩ መተዳደሪያ ደንብ ተሻሽሎ እንዲቀርብ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የሚመራ ኮሚቴ ሰይሟል፤

9. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሕገ ልቡና፣በሕገ ኦሪትና በሕገ ወንጌል ያገኘቻቸው ዶግማዊ፣ ቀኖናዊና ትውፊታዊ ሀብቶቿ የሕግ ጥበቃና ከለላ አግኝተው ሃይማኖታዊ፣ታሪካዊና ሁለንተናዊ ይዘታቸውን ሳይለቁ ተከብረውና ተጠብቀው ለትውልድ እንዲተላለፉ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡
10.  የ2018 ዓ.ም የመደበኛ እና የካፒታል ዓመታዊ በጀት ብር 5,407,415,607.25/አምስት ቢሊየን አራት መቶ ሰባት ሚሊዮን አራት መቶ ዐሥራ አምስት ሺህ ስድስት መቶ ሰባት ብር ከሃያ አምስት ሣንቲም/እንዲሆንና የበጀት አርዕስቱ ተጠብቆ ሥራ ላይ እንዲውል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

11. በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርስቲ በመገንባት ላይ የሚገኘውን ሕንጻ በተመለከተ የተፈጠረው የአሠራር ግድፈት እንዲታረም፣ዩኒቨርስቲው ከባንክ ጋር የገባው የብድር ውል እንዲቋረጥና የተጀመረውን ሕንፃ በራሱ አቅም እንዲገነባ ሆኖ፤ የቤተ ክርስቲያናችንን አንጡራ ሀብት ማለትም ሕንጻዎችን፣መሬቶችንና ሌሎች ቋሚ ንብረቶችን በማስያዝ የሚደረጉ ብድሮች ተፈጻሚ እንዳይሆኑ የሚያደርግ መመሪያ ለሁሉም አህጉረ ስብከት እንዲተላለፍ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
12. የቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደር ልማት ድርጅትን አስመልክቶ በቀረበው ሪፖርት መሠረት የሥራ ክፍተቱን በማረም በየደረጃው ያሉ ኃላፊዎች እንደየጥፋታቸው እንዲጠየቁና እንዲታረሙ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡
13. የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ምርጫን አስመልክቶ በሥራ ላይ የነበሩት ብፁዓን አባቶች የሥራ ዘመናቸውን ያጠናቀቁ በመሆኑ ለቀጣይ ሦስት ዓመታት የሚሠሩ ብፁዓን አባቶችን ለመምረጥ ዕጩዎችን የሚያቀርቡ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን በመሰየም ምልዓተ ጉባኤው ተገቢውን ምርጫ አከናውኗል፡፡
በዚሁም መሠረት ፡-
*. ለቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊነት ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ፣ በደቡባዊ ዞን ማይጨው፣ የደቡባዊ ምሥራቅ ትግራይና የራያ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስን መርጦ ሰይሟል

*. ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪጅነት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣የሸገር ከተማ እና የምስካዬ ኀዙናን መድኃኔዓለም ገዳም የበላይ ኃላፊ ሊቀጳጳስን መርጦ ሰይሟል፡፡
* ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የሀድያና ስልጤ አህጉረ ሰብከትን እንደያዙ  የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
* ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲሠሩ ቅዱስ ሲኖዶስ መርጦ ሰይሟል፡፡
* ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የደቡብና ምዕራብ አፍሪካ ሀገረ ሰብከት ሊቀ ጳጳስ
* ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የሜኖሶታና የኮሎራዶ አህጉረ ሰብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲሠሩ ቅዱስ ሲኖዶስ መድቧል፡፡

14. ብፁዕ አቡነ ገብርኤል የምዕራብ ሸዋ ሀገረ ሰብከት ጳጳስ፣ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች አህጉረ ሰብከት ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዕ አቡነ በርናባስ የደቡብ ካልፎርኒያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በሚዲያ ያስተላለፏቸው ትምህርቶች ስሕተትና ነቀፋ ያለባቸው  መሆናቸውን አምነው ቅዱስ ሲኖዶስንና መላውን ሕዝበ ክርስቲያን ይቅርታ በመጠየቅ ሊቃውንት ጉባኤ ከቅዱሳት መጻሕፍት በማጣቅስ ያቀረበውን አስተምህሮ የተማሩት የሚያምኑትና የሚያስተምሩት መሆኑን በመግለጻቸው ቅዱስ ሲኖዶስ የሦስቱን አባቶች ይቅርታ ተቀብሎ ወደፊት እንዲህ ዐይነት የስሕተት  ትምህርት ውስጥ
9
2025/07/08 15:13:48
Back to Top
HTML Embed Code: