ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የዘመነ ክረምት አዳር የሕጻናት ት/ት መርሐግብር (Summer Camp 🌞⛺️)
📢 የሥራ ቅጥር ማስታወቂያ
📋 የሥራ ዘርፍ ዝርዝሮች:
1. 🙏📚 የትምህርት እና መንፈሳዊ ክንውኖች ማስተባበሪያ ኃላፊ (Head of Spiritual & Educational Formation Department)
2. 🤝⚖️ የሥነ ምግባር እና የተማሪዎች ቁጥጥር ማስተባበሪያ ኃላፊ (Head of Community Life & Conduct)
3. 📅✏️ የት/ት መርሐግብር �ይጊዜ ሠሌዳ እቅድ እና ዝግጅት ማስተባበሪያ ኃላፊ (Head of Program & Schedule Management)
4. 🎉📢 ዐበይት ኩነቶች እና ስልታዊ ማስተማሪያ ዘዴዎች ማስተባበሪያ ኃላፊ (Head of Events & Extracurricular Activities)
5. 🚚📦 የሎጂስቲክስ ኃላፊ (Head of Logistics)
6. 💻📱 የግንኙነት እና መረጃ አስተዳደር ኃላፊ (Head of Communication, IT & Media Department)
7. 💼👥 የሰው ኃይል አስተዳደር (Human Resource & Management)
📍 ቦታ: አዲስ አበባ (Addis Ababa)
⏳ የቅጥር ሁኔታ: ጊዜያዊ (Temporary | ከግንቦት – ጷግሜ)
📅 የስራ ጊዜ ሁኔታ:
- ሐምሌ እና ነሀሴ በነዋሪነት (24 ሰዓት በት/ቤቱ ውስጥ 🏠)
- 🍴🏠 ነጻ የምግብ እና የመኖሪያ አገልግሎት
💰 ደመወዝ: በፕሮጀክቱ እስኬል መሰረት
🔗 ለማመልከት: ከሥር ያለውን ሊንክ ይጫኑ 👇👇👇
https://tripetto.app/run/6H55RKSEPS
⏰ የማመልከቻ ጊዜ: እስከ ግንቦት 19 ብቻ
📞 ለተጨማሪ መረጃ: 0909437444
❤6👍3
ማኅበረ ቅዱሳን ከደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ አንድነት ገዳም በደባርቅ ከተማ በትብብር እያስገነባ የሚገኘው የገቢ ማስገኛ ሕንጻ 58 በመቶ መጠናቀቁ ተጠቆመ
ግንቦት ፲፬/፳፻፲፯ ዓ.ም
በማኅበረ ቅዱሳን አስተባባሪነት በደባርቅ ከተማ የሚገነባው የደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ አንድነት ገዳም ሁለ ገብ የገቢ ማስገኛ ሕንጻ ግንባታ ፕሮጀክት የገዳሙን ኢኮኖሚ አቅም በዘላቂነት ማጠናከር ዋነኛ ተልእኮ ነው።
ይህ የሚገነባው G+4 የገቢ ማስገኛ ሕንጻ ግማሹ ወጪ በማኅበረ ቅዱሳን የሚሸፈን ፣ ቀሪው ደግሞ በገዳሙ የሚሸፈን ሲሆን ይህን ተከትሎ ማኅበሩ ከሚጠበቅበት 58 በመቶ ማጠናቀቁ ተገልጿል።
ኢ/ር ማስተዋል አበበ በማኅበረ ቅዱሳን የፕሮጀክት ዝግጅትና ትግበራ ም/ኃላፊ እንደገለጹት ግንባታው የደረሰበትን ሁኔታ በማብራራት 58 በመቶ መድረሱን ተናረዋል።
ማኅበሩ ከያዘው ዕቅድ አንጻር ደግሞ 42 በመቶ እንደሚጠበቅባቸው ም/ኃላፊዋ አክለውም ጠቁመዋል።
ይሁንና የሕንጻ ግንባታው በአንድ ዓመት ጊዜ ተጠናቆ አገልግሎት እንዲሰጥ ታስቦ ወደ ሥራ ቢገባም አገሪቱ ላይ ያሉ የግንባታ ዕቃዎች ዋጋ ንረትና በስፍራው ያለው የሰላም መደፍረስ ግንባታውን እንዳጓተተው ተመላክቷል።
የደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ አንድነት ገዳም ታላቁ የዜማ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ የተሰወረበት በመሆኑ የስፍራውን ታሪካዊነት ከማስቀጠል ረገድ እና በገዳሙ ላይ መነኮሳት ጸንተው ለአገር፣ ለወገን አስፈላጊውን መንፈሳዊ የጸሎትና የመንፈሳዊ አገልግሎት ለመስጠት እንዲችሉ ለማድረግ ቀሪውን ግንባ እንዲጠናቀቅ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ ም/ኃላፊዋ ገልጸዋል።

👍24🙏3
ማኅበረ ቅዱሳን በአገራችን ያለውን ማኅበራዊ ቀውስ ለማርገብ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ተገለጸ
ግንቦት ፲፭/፳፻፲፯ ዓ.ም
ማኅበረ ቅዱሳን በአገሪቱ የሚታየውን የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ለመቅረፍ እንዲሁም ሥነ ልቦናዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ከባለፈው ዓመት ጀምሮ እየሠራ እንደሚገኝ የማኅበረ ቅዱሳን ሙያ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት ክፍል ገልጿል።
የማኅበረ ቅዱሳን ሙያ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ዲያቆን ንጉሤ ባለው ጊዜ እንደገለጹት በኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ ላይ ከጋብቻ፣ ከማኅበራዊ ቀውስ ጋር ተያይዞ የወጣቶች ሕይወት ላይ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ እየተሠራ እንደሚገኝ ገልጸው ካህናት ንስሐ ልጆቻቸውን በትክክል እንዲይዙ፣ ቤተሰብን የሚያማክሩ ፣ ወጣቶችን በትክክል የሚመክሩ እንዲሆኑ ለማድረግና በተጨማሪም በዘርፉ ያሉ የጤና ባለሙያዎች የሳይኮሎጂና የሳይካትሪስት ባለሙያዎችን ጨምሮ እየተሠራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ማኅበረ ቅዱሳን ባለፉት ስድስት ወራት በ 11 ማእከላት 483 አመካካሪዎችን ያሠለጠነ ሲሆን እነዚህ ማኅበራዊ ቀውስ እንዳይኖር በመሥራት ለቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ሆነ ለአገር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዲኖረው ማድረግ እንደሚቻል ዲያቆን ንጉሤ አክለው ገልጸዋል።
በመጨረሻም እስካሁን በተከናወኑ ሥልጠናዎች አጋር ለነበሩ አካላት ምስጋናቸውን የገለጹት ም/ ዳይሬክተሩ ሥልጠናውን ለማስቀጠል የሎጅስቲክ፣ የቁሳቁስ፣ የሥልጠና ስፍራ፣ የካህናትና የባለሙያዎች ማረፊያ የሚያስፈልግ ቢሆንም የገንዘብ፣ የቁሳቁስና የሠለጠነ የሰው ኃይል ለማግኘት ተግዳሮት ሆኖብናል ብለዋል።

👍7❤1
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ባደረገው ስብሰባ የሚከተለውን ውሳኔ ማስተላለፉ ተገለጸ
1. ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆርስን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፤
2. ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤
3. ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስን የሐዲያ ሀ/ስብከትን እንደያዙ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤
4. ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ዘኮሎራዶን የቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ገዳማት ሊቀ ጳጳስ፤
5. ብፁዕ አቡነ ናትናኤልን ሚኒሶታን እንደያዙ የኮሎራዶ ሀ/ስብከትን እንዲመሩ፤
6. ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የደቡብ አፍሪካ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳ ጳስ፤
7. ብፁዕ አቡነ ዕንባቆምን የገዳማት መምሪያ ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲመሩ፤
8. ብፁዕ አቡነ ሙሴ አውስትራልያን እንደያዙ የግቢ ቅዱስ ገብርኤልና የበዐታ ለማርያም ገዳም ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲመሩ ወስኗል።
ምንጭ የኢኦተቤክ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

👍17🕊4
የግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ማስተባበሪያ ግንቦት 24 ቀን 2017 ዓ.ም በማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት በሚያካሂደው የገቢ ማሰባሰቢያ የቀጥታ ሥርጭት ላይ ይሳተፉ፡፡ ግቢ ጉባኤያትን ይደግፉ፡፡
• የመማሪያ መጻሕፍት ዝግጅትንና ኅትመት ወጪን በመደገፍ የቅድስት ቤተ ክርስተያንና ሃይማኖቱን የተረዳ፣ በሙያው፣ በገንዘቡ፣ በጉልበቱ የሚረዳ ትውልድን ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት ውስጥ አሻራዎን ያሳርፉ፡፡
የግቢ ጉባኤያት ተማሪዎች፣
በግቢ ጉባኤያት ተምራችሁ ያለፋችሁ፣
የግቢ ጉባኤት ምሩቃን ኅብረት፣
የተማሪዎች ቤተሰቦች፣
በጎ አድራጊ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች፣ … በገቢ ማሰባሰቡ ላይ ይሳተፉ፡፡

👍11❤1