እንዳይገኙና ነቀፋ ያለበትን ትምህርታቸውን በማረምና በማስተካከል ርቱዕ የሆነውን የቤተ ክርስቲያናችንን አስተምህሮ መሠረት በማድረግ በኢትዮጵያ ኦርቶዶስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መገናኛ ብዙኀን ሥርጭት ድርጅት በመቅረብ ትምህርት እንዲሰጡ በማለት ምልዓተ ጉባኤው ወስኗል፡፡
15. በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሚኖሩ በግልና በቡድን ተደራጅተው ማኅበራዊ ሚዲያዎችን በመክፈት ከሃይማኖት ሥነ ምግባር በወጣ መልኩ የቤተ ክርስቲያናችንን ልዕልና የቅዱስ ሲኖዶስን ክብር የሚጋፋ ፣የአባቶችንና የአገልጋዮችን ተልእኮ የሚያደናቀፍ ያልተገባና መሠረት የሌለው መግለጫ የሚያሰራጩ አካላት እንዲታረሙ ቅዱስ ሲኖዶስ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በጥብቅ ያሳስባል፡፡
በመጨረሻም በሀገራችን በአንዳንድ ቦታዎች የሚታየው ግጭትና መፈናቀል ተወግዶ፣የሰው ልጅ የመኖርና የመዘዋወር መብት ተከብሮ፣ ሰብዓዊ ክብሩ ተጠብቆ ሁሉም ዜጋ በእኩልነት፣ በሰላምና በፍቅር ተከባብሮ በጋራ እንዲኖር፤ አለመግባባቶች በውይይት እንዲፈቱ ቤተ ክርስቲያን የሰላም ጥሪዋን ታስተላልፋለች፡፡
ግጭት፣ ጥላቻና ደም መፋሰስ፣ አካል ከማጉደልና ንብረት ከማጥፋት በቀር የሚያመጡት ክብርና ዘላቂ ሰላም ስለሌለ ልጆቻችን ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ እንድትፈቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ደጋግሞ ጥሪውን በማቅረብ በመላው ዓለም ጦርነት ባለባቸው ሀገራት ሁሉ ሰላምና ዕርቅ እንዲሰፍን በመጸለይ ቅዱስ ሲኖዶስ ግንቦት 20 ቀን 2017 ዓ.ም ዓመታዊ ጉባኤውን በጸሎት አጠናቋል፡፡
እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ግንቦት ፳ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
ምንጭ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

❤9🕊2
በዓለ ዕርገት
በዓለ ዕርገት ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ከተነሣ በኋላ በአርባኛው ቀን በአባቱ ፈቃድ፣ በራሱም ሥልጣን፣ በመንፈስ ቅዱስም ፈቃድ ወደ ሰማየ ሰማያት ያረገበትን ታላቅ ምሥጢር የምናስታውስበትና የምናከብርበት በዓል ነው። ይህ በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከዘጠኙ ታላላቅ የጌታችን በዓላት አንዱ ሲሆን በልዩ መንፈሳዊ ሥርዓትና በታላቅ ደስታ ይከበራል።
በዓለ ዕርገትን ስናከብር የሚከተሉትን ክርስቲያናዊ ተግባራት ከአበው አስተምህሮ ጋር በማስተባበር ማናከናውን እንዳለብን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታስተምረናለች፡፡ በዋነኛነትም በጸሎት፣ በምስጋናና በቅዳሴ መትጋት ነው። ስለዚህ ጌታችን ላደረገልን የማዳን ሥራ በተለይም ሥጋችንን አክብሮ ወደ ሰማይ ስላሳረገልን ልባዊ ምስጋና ማቅረብ ይገባል። በቤተ ክርስቲያን ተገኝቶ በቅዳሴ ሥርዓት መሳተፍ፣ የዕለቱን ምስጋና፣ ጸሎትና የቅዱስ ቊርባን ሥርዓት በመካፈል ከጌታችን ጋር ያለንን ኅብረት ማጽናት ይገባል።
ከእነዚህ ክርስቲያናዊ ተግባራት በተጨማሪ የቅዱሳት መጻሕፍትንና የአበውን ትርጓሜ ማጥናት ያስፈልጋል፡፡ የዕርገቱን ምሥጢር በሚገባ ለመረዳት ተገቢ የሆኑትን የቅዱሳት መጻሕፍት ክፍሎች (ግብረ ሐዋርያት ምዕራፍ ፩፣ ሉቃስ ምዕ. ፳፬፣ መልእክት ኀበ ሰብአ ኤፌሶን ምዕራፍ ፩ እና መልእክት ኀበ ዕብራውያን ምዕራፍ ፩) እንዲሁም የአበውን ድርሳናት ማንበብ መንፈሳዊ ዕውቀታችንን ያሰፋሉና ቅዱሳት መጽሐፍቱን ማንበብ ይገባል።
ጌታችን "ለእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ያደረጋችሁት ለእኔ እንዳደረጋችሁት ነው" እንዳለው፣ በበዓለ ዕርገት ምጽዋትና የክርስቶስን ፍቅር በተግባር መግለጽ እንዲሁም በረከትን ማካፈል ያስፈልጋል። (ማቴዎስ ፳፭፥፵)
አምላካችን እግዚአብሔር ከበዓሉ በረከት ረድኤት ይክፈለን፤ አሜን!

❤5
ግቢ ጉባኤያትን በተሻለ ጥራት የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ለማስተማር፣ መምህራንን ለማፍራትና አስፈላጊውን አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ መሠረተ ልማቶችን ለማሟላት በገቢ ማሰባበስብ መርሐ ግብሩ ላይ ይሳተፉ፤ የድርሻዎንም ይወጡ፡፡
❤12

"ግንቦትን ለግቢ ጉባኤያት" በሚል መሪ ቃል በመጪው እሑድ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር እንደሚካሄድ ተገለጸ
ግንቦት ፳፫/፳፻፲፯ ዓ.ም
ማኅበረ ቅዱሳን የግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ማስተባበሪያ "የግንቦት ወርን ለግቢ ጉባኤያት" በሚል መሪ ቃል እሑድ ግንቦት 24 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ እስከ ሌሊቱ 6ሰዓት ድረስ የሚቆይ የቀጥታ ስርጭት የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር በማኅበሩ የቴሌቪዥን ጣቢያ እንደሚካሄድ ገልጿል።
በገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ግቢ ጉባኤ ያት አገልግሎት ውስጥ የነበሩ አባላት፣ መምህራን፣ አርቲስቶች የሚሳተፉ ሲሆን ተሞክሮ የማካፈል፣ ውይይትና ሌሎች ተግባራት እንደሚከናወን ተመላክቷል።
አቶ አበበ በዳዳ የግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ማስተባበሪያ ሥራ አስፈጻሚ እንዳሉት የማኅበሩን ፴፫ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል በማስመልከት ከግንቦት አንድ ጀምሮ የግቢ ጉባኤያት አገልግሎትን ለማገዝ የሚረዱ መርሐ ግብራት እየተከናወኑ እንደሆነ የገለጹ ሲሆን የግቢ ጉባኤን ዓላማ ለተማሪ ወላጆች፣ ለአጋርና ተባባሪ አካላት ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ ከማኅበሩ ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር በጋራ በመሆን እየተሠራ እንደሆነም ጠቁመዋል።
ማኅበረ ቅዱሳን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎችን ሲያስተምር በቅድሚያ ሃይማኖታቸውን ጠንቅቀው እንዲያቁና በሥነ ምግባር የታነጹ እንዲሆኑ ነው በማለት የገለጹት ሥራ አስፈጻሚው አክለውም በዚህ መልኩ ታንጸው የሚወጡ ምሩቃን ለቤተክርስቲያንና ለሀገር ጠቃሚ ትውልድ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል ብለዋል።

❤7🕊6
ለዚህም ግቢ ጉባኤያት አገልግሎት በይበልጥ ተደራሽ ለመሆን የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ማሟላት በተለይ የመማሪያ ስፍራ ለማመቻቸት፣ ለመምህራን ሥልጠናዎችን ለመስጠትና ተደራሽነትን ለማስፋት፣ለቨርቿል የሥልጠና ማእከል፣ ለተማሪዎች መማሪያ መጽሐፍት ኅትመት የሚሆን ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ተመላክቷል።
በመጨረሻም አገልግሎቱን በስፋት ተደራሽ ለማድረግና አስፈላጊው ድጋፍ ለማድረግ ከግቢ ጉባኤያት ተምረው የወጡ ምሩቃን ፣ አጋርና ተባባሪ አካላት እንዲሁም ምእመናን የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።

❤16
የ፲፪ኛ ክፍል ተማሪዎች ለአገር አቀፍ ፈተና የሥነ ልቡና ሥልጠና እንደተሰጣቸው የድሬዳዋ ማእከል አስታወቀ
ግንቦት ፳፮/፳፻፲፯ ዓ.ም
ማኅበረ ቅዱሳን ድሬዳዋ ማእከል ከድሬዳዋ ሀገረ ስብከት የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ኅበረት ጋር በመቀናጀት አገር አቀፍ ፈተና ለሚወስዱ የ፲የ
ኛ ክፍል ተማሪዎች ለፈተናው የተሻለ ሥነ ልቡናዊ ዝግጅት እንዲኖራቸው ግንቦት ፳፬ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም በኆ/ሰ/ቅድስት ማርያም ካቴድራል ሁለ ገብ አዳራሽ ሥልጠና መሰጠቱን አስታውቋል።
መርሐ ግብሩ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ኅብረት መቋቋም በጋራ ለማገልገል፣ለመተጋገዝ እና በሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ በአገር አቀፍ ደረጃ የተዘጋጀውን ሥርዓተ ትምህርት ለማስተግበር ምቹ ሁኔታ መፍጠሩ መልካም መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ማኅበረ ቅዱሳን ታሪካዊው ዳራው እና ተልእኮው ላለፉት ፴፫ ዓመታት ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ ሆኖም በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ ከሚደርሱት የተለያዩ ጫናዎች አንጻር ማኅበሩ ርዕዩን ማሻሻያ አድርጎ ለመሥራት መገደዱን ለዚህም የነገ መሪ ከሚሆኑት ታዳጊ ወጣቶች ቅድስት ቤተክርስቲያን ብዙ እንደምትጠብቅ ና የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን የመገናኛ ብዙኃንን ማበረታታት እንደሚገባ መልእክት ተላልፏል፡፡

❤14🙏1
በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የሥነ አእምሮ ትምህርት ክፍል ባለሙያዎች እና በማእከሉ አባልነት እያገለገሉ የሚገኙት ዲ/ን ሲሳይ ስዩም፣ዲ/ን ብርሃኑ የሻነው እና ነጻነት ርስቱ ሥልጠናው የተሰጠ ሲሆን በአጠቃላይ ቅድመ ፈተና፣ጊዜ ፈተና እና ድኅረ ፈተና ሊደረጉ ስለሚገባቸው ተግባራት ላይ ያተኮረ ፣ ስለ ስኬት፣ለስኬት እንዳንበቃ የሚያደርጉ አደናቃፊ ነገሮች፣ ሰዓት አጠቃቀም ፣ ስለፈተና ምንነትና አስፈላጊነት፣ ስለ አእምሮአዊ ዝግጅት ፣ የፈተና ጭንቀት መንስዔዎችና ማስወገጃ መንገዶች ፣ስለጥናት ቦታዎች ምርጫ እና የአጠናን ዘዴ ፣ በራስ መተማመን፣መመሪያዎችን ስለማክበር እና ጥያቄዎችን በአግባቡ መረዳት፣ ለማይችሉት ነገር እርዳታ መጠየቅ የመሳሰሉ ርዕሰ ጉዳዮች ተዳሰውበታል።
በተጨማሪም ተፈታኞች ከልክ በላይ መጨነቅ እንደሌለባቸው ተገቢውን ዝግጅት ካደረጉ የሌላውን ለእግዚአብሔር መስጠት እንደሚገባ፣ከኩረጃ እና መሰል አሉታዊ ተግባራት ሊቆጠቡ እንደሚገባ፣ፈተናን መውደቅ የሕይወት መጨረሻ አለመሆኑን አንስተው ቀሪውን ጊዜ በአግባቡ እንዲጠቀሙበት መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
የሕዝብ ግንኙት ዋና ክፍል ኃላፊ የሆኑት አቶ መሰንበት ደጉ በበኩላቸው ሠልጣኞች ለሚኖራቸው ማንኛውም ጥያቄ እንደ አስፈላጊነቱ አሠልጣኞቹን ማግኘት እንደሚችሉ እና የዚህ መርሐ ግብር አዘጋጆች መምህራንን በመጠቀም የክለሳ እና ፈተና የመሥሪያ መርሐ ግብር እንደሚያዘጋጁ የገለጹ ሲሆን ተሳክቶላቸው ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለሚገቡ ተማሪዎች የሽኝት እና ከግቢ ጉባኤያት ጋር የማገናኘቱን ሥራ በቀጣይ እንደሚሠራ ገልጸው በመልካም ምኞት የማኅበሩን መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
ከተሣታፊዎች መካከል በመርሐ ግብሩ ደስተኛ እንደሆኑ ‹‹ቤተ ክርስቲያንን በሙያ ማገልገልን እንድናስብ ስላደረጋችሁን እናመሰግናለን ብለዋል፡፡››
አዘጋጆች ደክመው የእረፍትና ቤተሰብ ጊዜያቸውን አጣብበው ይህን ስላመቻቹ ያመሰገኑ ሲሆን አገር አቀፉን ፈተና ከመፈተናቸው በፊት ቀደም ብሎ የጋራ የጸሎት መርሐ ግብር እንዲመቻች አስተያየት ሰጥተው ሥልጠናው በዚሁ ተቋጭቷል፡፡
በሥልጠናው ከየሰ/ት/ቤቱ የተውጣጡ ፻ ተሣታፊዎች ተሣታፊ እንደነበሩ ከሚዲያ ክፍል ያገኘነው ዘገባ ያስረዳል፡፡

❤4🙏1
የማኅበራዊ ድጋፍ ጉባኤ ጥሪ
+++
ማኅበረ ቅዱሳን በሀገራችን ኢትዮጵያ በማኅበራዊ ቀውሶች ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ እያሰባሰበ በማድረስ ላይ ይገኛል።
እርስዎም፡- ድጋፍ በማድረግ ኃላፊነትዎችን እንዲወጡ ተጋብዘዋል።
በዙም ለሚካሄድ የድጋፍ መርሐ ግብር ለመሳተፍ
• Date: June 21st, 2025
• Time: 21 - 22:30 CET, 20 - 21:30 UK, 22 - 23 :30 Helsinki
ድጋፍ ለማድረግም፡-
1. በአውሮፓ ለምትገኙ -
• Mahibere Kidusan in Europa e.V.
• IBAN: DE14 3704 0044 0307 8037 00
• BIC: COBADEFFXXX
• Reason: Code 007 (Social support)
Phone for What Sapp/Telegram/Imo: +421950741387
2. በዩኬ ለምትገኙ ፡-
Mahibere Kidusan in UK
Banking: Nat West
Sort code 601251
Acco. No: 36425591
• Reason: Code 007 (Social support)
3. በስዊድን ለምትገኙ ፡-
Swish Number
123 054 28 29
Market Name
Mahibere Kidusan I Sverige

❤5👍2
"ሥነ ልቦናዊ ዝግጅት ለአገር አቀፍ ፈተና" በሚል ርእስ ሥልጠና መሰጠቱን የሐረር ማእከል አስታወቀ
ግንቦት፳፯/፳፻፲፯ ዓ.ም
ማኅበረ ቅዱሳን ሐረር ማእከል ከሐረር ሰ/ት/ቤት አንድነት ጋር በመተባበር አገር አቀፍ ፈተና ለሚፈተኑ ከ 90 በላይ የ12ተኛ ክፍል ተማሪዎች "ሥነ ልቦናዊ ዝግጅት ለአገር አቀፍ ፈተና" በሚል ርእስ ግንቦት 24 ቀን 2017 ዓ.ም በመካነ ሥላሴ ሕንፃ 4ተኛ ወለል ላይ ሥልጠና ሰጠ።
አሠልጣኞች በሥልጠናዉ ተማሪዎች ራሳቸውን ለፈተናው ብቁ ለማድረግ ፣ አዎንታዊ አስተሳሰብ ለመገንባትና በጊዜ ዕቅድ ለመመራት የሚችሉበትን ርእሰ ጉዳዮችን ዳሰው ከተፈታኞች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።
በመጨረሻም "በጠንካራ መንፈስ፣ በልበ ሙሉነት፣ በይሳካል መንፈስ ተነስተን በመሥራት ዉጤታማ እንሆናለን" !! በማለት ተፈታኞችን አነቃቅተዋል። .

❤13👍1🙏1