ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ለ582 ደቀመዛሙርት መዓርገ ክህነት ሰጡ።
ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ የምዕራብ አርሲ ፣ጉጂ፣ምዕራብ ጉጂ ፣ቦረና ሊበን አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ለ582 ደቀመዛሙርት መዓርገ ክህነት በዛሬው ዕለት በሻሸመኔ ደብረ አስቦ አ/ተ/ሃይማኖት ቤተክርስቲያን ሰጥተዋል።
ለዲቁና ለቅስና እና ለቁምስና ፈተና ሲፈተኑ የቆዩ አግልጋዮች 546 ዲቁና፤34 የቅስና እና 3 የቁምስና መዓርግ የተሰጣቸው ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 171 ዲቁና እና 5 የቅስና መዓርግ በአጠቃላይ 176 የተሰጣቸው በማኅበረ ቅዱሳን ሻሸመኔ ማእከል እና ሰሜን አሜሪካ ሀገረ ስብከት ሰ/ት/ቤቶች አንድነት ጉባኤ ጋር በመተባበር ሲያስተምራችው የነበሩ ደቀመዛሙርት ናቸው።
ማኅበረ ቅዱሳን ሻሸመኔ ማእከል ከሰሜን አሜሪካ ሀገረ ስብከት ሰ/ት/ቤቶች አንድነት ጋር በመተባበር በዚህ ዓመት ከዚህ ቀደም መዓርገ ክህነትን የተቀበሉ 61 ካህናትን ጨምሮ በአጠቃላይ 237 መዓርገ ክህነት እዲቀበሉ አድርጓል።
በዛሬው ዕለት ክህነት የተቀበሉት አገልጋዮች በአካባቢው ያለውን የካህናት እጥረት ለመፍታት ከፍተኛ ድርሻ እንደሚኖራቸው ተጠቁሟል።

በማኅበረ ቅዱሳን የጀርመን ንዑስ ማእከል ለገዳማትና ጉባኤ ቤቶች ድጋፍ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር አካሄደ።
ንዑስ ማዕከሉ የድጋፍ ማሰባሰቢያ ጉባኤውን በሙኒክ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የደብሩ አስተዳዳሪ ሊቀ ብርሃናት ቆሞስ አባ ያሬድ ምስጋናው፣ መምህራነ ወንጌል፣ ካህናት እና ምዕመናን በተገኙበት አከናውኗል።
በዚህ መርሐ ግብር በሀገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ አህጉረ ስብከት ለሚገኙ ለአብነት ትምህርት ቤት መምህራን እና ተማሪዎች ድጋፍ የሚውል የገቢ ማሰባሰብ ሥራ ተከናውኗል።
ማኅበረ ቅዱሳን በገዳማትና አብነት ትምህርት ቤቶች የተገበራቸውን ፕሮጀክቶችና ልዩ ልዩ ድጋፎችን ገለጻ የተደረገ ሲሆን በዚህም ምእመናን እየተተገበሩ ስላሉ ሥራዎች ግንዛቤ አግኝተዋል። የሙኒክ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ሊቀ ብርሃናት ቆሞስ አባ ያሬድ ምእመናን የቤተ ክርስቲያን አእማድ የሆኑ ገዳማትና ጉባኤ ቤቶችን እንዲደግፋ ባስተላለፉት አባታዊ መልእክት መሠረት ድጋፍ መሰብሰብ ተችሏል።
በተመሳሳይ ሚያዚያ 12ና 13 /2016 ዓ.ም በሩስልስሃይም ደ/ምጥማቅ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን የደብሩ አስተዳዳሪ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ አብርሃም፣ የደብሩ ካህናትና ምእመናን በተገኙበት ዐውደ ርዕይ እና ለገዳማትና አብነት ት/ቤቶች የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር የተከናወነ ሲሆን በወቅታዊ ጉዳይ ጉዳት ለደረሰባቸው ገዳማትና አብነት ት/ቤቶች ገንዘብ መሰብሰብ ተችሏል፡፡
የተሰበሰቡ ድጋፎች ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ገዳማትና አብነት ት/ቤቶች በማኅበሩ በኩል እንደሚውል ንዑስ ማእከሉ አስታውቋል።

በ አውሮፓ ማእከል የዩኬ ንዑስ ማእከል አዘጋጅነት የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር ተካሄደ፡፡
በእንግሊዝ ሀገር በ ሃደርስ ፊልድ ከተማ በደብረ ፀሐይ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን የደብሩ ካህናት እና አገልጋዮች እንዲሁም ተጋባዥ ካህናትና መምህራን ከተለያዩ የዩኬ ከተማዎች የተሰባሰቡ ምእመናን በተገኙበት ለ6ኛ ጊዜ የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር ተካሄዷል።
በመርሐ ግብሩ ላይ የስዊድን፣ ስካንድናቪያን እና ግሪክ ሀገሮች ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ መልአከ አሚን ቀሲስ ለማ በሱፈቃድ እና ከሀገር ቤት መምህር ያረጋል አበጋዝ ተገኝተዋል፡፡
በምክረ አበው ክፍለ ጊዜ ከምእመናን ለተነሱ ጥያቄዎች መልስ የተሰጠ ሲሆን፤ “ፈውስ እና ድኅነት፣ ክርስቲያናዊ ጋብቻ፣ የቤተሰብ አስተዳደር ፈተናዎች እና መፍትሔዎቻቸው” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ተኮር ትምህርቶችም ተሰጥተዋል፡፡ ከትምህርት እና ከአጥቢያው መዘምራን እና ሕጻናት ክፍል መዝሙር በተጨማሪም ማኅበረ ቅዱሳን በሀገር ቤት ስብከተ ወንጌልን ከማስፋፋት እና የአብነት ትምህርት ቤቶችን ከመደገፍ አንጻር ያከናወናቸውና በሂደት ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን በሚመለከት በምስል ወድምጽ የታገዘ ዘጋቢ ዝግጅት ቀርቧል፡፡
በ መጨረሻም የደብሩ አስተዳዳሪ ቀሲስ ሳሙኤል ለማኅበሩ እና ለተጋባዥ መምህራን ምስጋና እና የምስክር ወረቀት እንዲሁም ለቅዱሳት መካናት እና የስብከተ ወንጌል አገልግሎት የሚውል የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ መርሐ ግብሩ በጸሎት ተጠናቅቋል፡፡
ከመደበኛው የሐዊረ ሕይወት በተጓዳኝ የሕጻናት መርሐ ግብር ለብቻው በእንግሊዝኛ ቋንቋ በሁለት መምህራን መሠጠቱን ንዑስ ማእከሉ ያደረሰን መረጃ ያስረዳል፡፡

ጸሎተ ሐሙስ!
ጸሎተ ሐሙስ ጌታችን ምሥጢረ ቊርባንን ከምሥጢረ ጸሎት ጋር አዋሕዶ የገለጠበት ዕለት ነው፡፡
በወንጌልም እንደተጻፈው ፋሲካውን የሚያከብሩበት ቀን ሲደርስ ጌታ ኢየሱስም ጴጥሮስንና ዮሐንስን ሒዳችሁ ፋሲካን እንበላ ዘንድ አዘጋጁልን አላቸው፤ እነርሱም በየት እንድናዘጋጅልህ ትወዳለህ አሉት? ወደ ከተማ ገብታችሁ የውኃ ማድጋ የሚሸከም ስምዖን የተባለ ሰው ታገኛላችሁ፤ ወደ ገባበት ቤት እርሱን ተከተሉት፤ መምህር ከደቀ መዛሙርቶቼ ጋር ፋሲካ የሚያደርግበት አዳራሽ ወዴት ነው ይልሃል? በሉት እርሱ የተነጠፈውንና ታላቁን አዳራሽ ያሳያችኋል፤ በዚያም ፋሲካን አዘጋጁልን አላቸው፤ እነርሱም ወደ ተላኩበት ከተማ ገብተው አልዓዛርን የውኃ ማድጋ ተሸክሞ አገኙት፡፡ ጴጥሮስና ዮሐንስም ለስምዖን ጌታ በቤቱ ፋሲካን ሊያዘጋጅ መሻቱ እንደሆነ ነገሩት፤ እርሱም የፍጥረታት ጌታ በቤቱ ሊመጣ እንዳለ አስቦ ተደሰተ፤ ወደ ሚስቱ አክሮሲናም ሔዶ ይህ አልዓዛርን ከሞት ያስነሳ እኔንም በኃጢአቴ ይቅር ይለኛል፤ ያነጻኝ ዘንድ ከሐዋርያት ጋር በቤታችን ይመጣል አላት፤ አክሮሲናም እጅግ ተደሰተች፡፡