Telegram Web Link
የመዝገበ አእምሮ (ኢንሳይክሎፒዲያ) ደረጃውን በጠበቀ መንገድ ለማዘጋጀት እንዲቻል በተለያዩ የሙያ መስኮች የተሰማሩ ምሁራን ዕውቀታቸውንና ልምዳቸውን ማካፈል የሚችሉበት መድረክ
ዛሬ ሚያዝያ 19 ቀን 2016 ዓ.ም በኤሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል እየተካሄደ ነው።

ማኅበረ ቅዱሳን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊና ቁሳዊ ሀብቶች እንዲሁም አስተምህሮዎች ላይ ያተኰረ መዝገበ አእምሮ (ኢንሳይክሎፔዲያ) ለማዘጋጀት እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

የሚዘጋጀው መዝገበ አእምሮ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ፣ ጥንታዊና ሐዋርያዊ አስተምህሮ፣ ዶግማ፣ ቀኖና እና ትውፊት እንዲኹም የጳጳሳትን፣ የሊቃውንትን፣ የትልልቅ ገዳማትንና አድባራትን ታሪክ ወዘተ. የሚያካትት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

የመዝገበ አእምሮ (ኢንሳይክሎፒዲያ) ደረጃውን በጠበቀ መንገድ ለማዘጋጀት እንዲቻል በተለያዩ የሙያ መስኮች የተሰማሩ ምሁራን ዕውቀታቸውንና ልምዳቸውን ማካፈል የሚችሉበት መድረክ ማዘጋጀት አስፈልጓል ተብሏል።
ማኅበረ ቅዱሳን #በሽሬ እንደ ሥላሴ ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች 1.7 ሚሊዮን ብር ወጭ የሆነበት ማኅበራዊ ድጋፍ አደረገ፡፡ 
+++

ማኅበረ ቅዱሳን በሀገራችን እያጋጠሙ ያሉ መጠነ ሰፊ ማኅበራዊ ቀውሶች በምእመናን፣ በገዳማትና አብነት ት/ቤቶች ላይ እያስከተሉት ያለውን ሁለንተናዊ ችግር ለማቃለል የማኅበራዊ ድጋፍ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽና በመተግበር ማኅበራዊና ሰብአዊ ሚናውን እየተወጣ እንዳለ ይታወቃል።

ማኅበሩ እነዚህን ችግሮች በስፋት በማጥናት ላለፉት 6 ዓመታት በሙያና ማኅበራዊ አገልግሎት ማስተባበሪያው በኩል በአርሲ፣ በሐረር ፣በባሌ፣ በወሊሶ፣ በሻሸመኔ፣ በዶዶላ፣ በአጋርፋ፣ በጅጅጋ፣ በሲዳማ፣ በመተከል፣ በቤንሻጉል ጉምዝ፣ በፓዊ፣ በቡለን፣ ፣በሽሬ፣ በአክሱም፣ በቦረና ያቤሎ፣ በጎንደር አዘዞ፣ በአዲግራት፣ በማይ ጨው፣ በሽረ እንደ ሥላሴ ፣በመቐለ፣ በደብረ ብርሃን፣ በደሴ፣ በወልዲያ፣በሑመራ፣ በላሊበላ ፣በሐይቅ እስጢፋኖስ፣ በወሎ ገራዶ፣ በደባርቅ ፣በጃን አሞራና በሌሎችም የሀገራችን ክፍል ለሚገኙ ተጎጅዎች ፕሮጀክቶችን በመንደፍ ድጋፍ አድራጊ ምእመናንና ተቋማትን እያስተባበረ የአልባሳት፣ የምግብ እና መሠል አስቸኳይ ድጋፎችን በስፋት ሲያደርግ ቆይቷል። አሁንም አጠናክሮ ቀጥሏል።

በዚህ መሠረት በሰሜን ኢትዮጵያ በተከሰተው ጦርነት ተፈናቅለው #በሽሬ እንደ ሥላሴ የተፈናቃይ መጠለያ ጣቢያዎች ለሚገኙ 1033 አባወራዎች 1.7 ሚሊዮን ብር ወጭ የሆነበት 150 ኩንታል የምግብ ግብዓቶች ድጋፍ አድርጓል። በተጨማሪም በአካባቢው ለሚገኙ አገልጋዮች የአልባሳት ድጋፎች ተደርገዋል።

ድጋፉ የተደረገው ማስተባበሪያው ከአሜሪካ ማእከል ጋር በመሆን ባለፉት ጊዜያት በውጭ ዓለም ከሚገኙ ምእመናን ማኅበራዊ ድጋፍ ባሰባሰበበት ወቅት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ነው።
ሚያዚያ 12 ቀን 2016 ዓ.ም በቦታዎቹ በመገኘት በተደረገው በዚህ የእጅ በእጅ ድጋፍ ርክክብ ወቅትም፣ የማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል ልዑካንና የማኅበረ ቅዱሳን ሽሬ እንደ ሥላሴ ማእከል ተወካዮች እንዲሁም የመንግሥት አካላት ተገኝተው ለተፈናቃዮች ድጋፉን አስረክበዋል። ይህ ድጋፍ በዚህ ዓመት በክልሉ ከተደረጉ ድጋፎች 2ኛ ዙር ድጋፍ ሲሆን በቀጣይ በአካባቢው በድርቅና ማኅበራዊ ቀውስ የተጎዱ ወገኖችን ኦርቶዶክሳዊነትንና ሰብአዊነትን መርሕ ባደረገ አግባብ ተጨማሪ ድጋፎችን ለማድረስ የሚሠራ ይሆናል።

የማኅበረ ቅዱሳን #ሙያና ማኅበራዊ አገልግሎት ማስተባበሪያ በ2016 ዓ.ም ባለፉት 7 የአገልግሎት ወራት ብቻ በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅና ጃን አሞራ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች፣ በሰቆጣና አካባቢው ለሚገኙ ተፈናቃዮች፣ በደቡብ ኦሞ በናጸማይ ወረዳ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች፣ በሃይማኖት ተኮር ጥቃት ለተጎዱ የቅበት ኦርቶዶክሳዊያን፣ በደብረ ብርሃን ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ተፈናቃዮች፣ በትግራይ መቐለ ኩሓ መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ተፈናቃዮች እና በትግራይ አጽቢ ወንበርታ ወረዳ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ተመሳሳይ ድጋፎችን አድርሷል። በቀጣይ ጊዜያትም በድርቅ ለተጎዱ እንዲሁም በጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎች ለሚገኙ ተፈናቃዮች ተጨማሪ ድጋፎችን ለማድረስ #ኑ ቸርነትን እናድርግ” በሚል መሪ ቃል እስከ ሚያዚያ 27 ቀን 2016 ዓ.ም የሚቆይ የማኅበራዊ ድጋፍ ማሰባሰብ ዘመቻ እያደረገ ይገኛል። ስለሆነም የወገኖቻችንን ሕይዎት ለመታደግ ብሎም ገዳማትና የአብነት ት/ቤቶችን ከፍልሰት ለመታደግ በሚደረገው የሰብአዊነት ሥራ ምእመናን፣ ማኅበራት፣ ልዩ ልዩ ተቋማትና በጎ አድራጊ ድርጅቶች የተለመደ ድጋፍ እንድታደርጉልን ሲል ጥሪውን ያቀርባል።
ድጋፍ ለማድረግ፡-

#በማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሒሳብ ቁጥሮች፡-
1. በአሐዱ ባንክ - 0025393810901
2. በአቢሲንያ ባንክ - 37235458
3. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000309803648
4. በወጋገን ባንክ - 0837331610101
5. በአዋሽ ባንክ 01329817420400
6. በጎ ፈንድ ሚ https://www.gofundme.com/f/uerc8...
7. በወገን ፈንድ ፡- https://Www.wegenfund.com/mknu መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የማኅበረ ቅዱሳን ሙያና ማኅበራዊ አገልግሎት ማስተባበሪያ
ዝክረ ቅድስት እናት ኢሪን እና መንፈሳዊ የትርጉም ፊልም የምርቃት መርሐ ግብር ተከናወነ።

በማኅበረ ቅዱሳን መዝሙር እና ኪነ ጥበባት አገልግሎት ማስተባበሪያ አዘጋጅነት የዘመናችን የ21ኛው ክፍለ ዘመን ቅድስት እናት ኢሪንን የሚዘክር መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት ተካናውኗል። በመርሐ ግብሩ ላይ የቅድስቷን  የተጋድሎ ሕይወት እና ኦርቶዶክሳውያን ከሕይወቷ መማር የሚገባንን ትምህርት በተመለከተ መነሻ ጽሑፍ ቀርቧል።

በዕለቱ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የማኅበሩ አባላት እና ምእመናም የተገኙ ሲሆን በእናት ኢሪን ዙሪያ የተዘጋጀው መንፈሳዊ ትርጉም ፊልም የምርቃት ሥነ ሥርዓትም  ተከናውኗል።

መንፈሳዊ ፊልሙ  በዜማ ወጥበብ ዘማኅበረ ቅዱሳን የዩቲዩብ ቻናል ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።

https://youtube.com/@-zemawetibebzmk7905?si=2jTnKZXGAfEJWRi7
 
‹‹እባክህ አሁን አድነን!››
 
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹…ከእኔ ተማሩ፤ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና…››  በማለት  ትሕትናን በአንደበቱ ትምህርት ከማስተማሩ በተጓዳኝ በተግባር ሕይወቱም ተግብሮ ካሳየባቸው ዕለታት አንዱ በአህያ ውርንጭላ ተቀምጦ ቤተ መቅደስ የገባበት ዕለት ነው፤ (ማቴ.፲፩፥፳፱) ይህ ግሩም አምላክ በትሕትና ከተገለጠባቸው ዕለታት አንዱ የሆነው ድንቅ ቀን በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ‹‹ሆሣዕና›› በመባል ይታወቃል፡፡ ሆሣዕና መተርጉማነ አበው በአንድምታቸው ‹‹ ሆሣዕና በአርያም በሰማይ ያለ መድኃኒት››  ብለው ተርጉመውልናል(ማቴ.፳፩፥፱ ወንጌል አንድምታ)  አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ደግሞ በመዝገበ ቃላታቸው ሆሣዕና ማለት ‹‹…እባክህ አሁን አድነን፤…መድኃኒት፣ መድኃኒት መሆን …›› በማለት ገልጸውታል፡፡ (አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት፣ ገጽ ፫፻፸፫)
 
‹‹እባክህ አሁን አድነን››፡- ይህን የተማጽኖ ቃል የተናገሩት ጌታችን በአህያ ውርንጭላ ተቀምጦ ቤተ መቅደስ በገባ ጊዜ በኢየሩሳሌም የነበሩ ሕዝብ ናቸው፡፡ የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው፣ አንድም የወይራ ቅጠል እንዲሁም ልብሳቸውን ከምድር አንጥፈው ከልብ በመነጨ፣ ምስጋናቸው ከሊቅ እስከ ደቂቅ ያሉ ሆሣዕና በአርያም ‹‹…እባክህ አድነን…›› በማለት አመሰገኑት፡፡ የነቢየ እግዚአብሔር ንጉሥ ዳዊት ትንቢት ተፈጽሞ በእናታቸው ጀርባ ያሉ የሚጠቡ ሕፃናት አመሰገኑ፤ ‹‹…ከሕፃናት ከሚጠቡ ልጆች አፍም ምስጋናን አዘጋጀህ…›› እንዲል፡፡ (መዝ.፰፥፪) 
https://youtu.be/Q0WJSswrkTo?si=ajqfBbrGS6e31m5Y

ሰላምሽ ዛሬ ነው ኢየሩሳሌም
ወደ አንቺ መጥቷልና አምላክ ዘለዓለም/፪/

ሆሣዕና በአርያም እያሉ ዘመሩ
ሕፃናት በኢየሩሳሌም

አንቺ ቤተልሔም የዳዊት ከተማ
የሕዝቦችሽ ብርሃን መጣልሽ በግርማ/፪/
     አዝ
ሆሣዕና እያሉ አመሰገኑት
በኢየሩሳሌም አእሩግ ወሕፃናት/፪/
  አዝ
ኪሩቤል መንበሩን  የሚሸከሙት
መስቀል ተሸክሞ ሆነን መድኃኒት/፪/
  አዝ
የኢየሱስን ሕማም ደናግል አይተው
እያለቀሱለት ሄዱ ተከትለው/፪/
2024/09/28 12:13:38
Back to Top
HTML Embed Code: