Telegram Web Link
ማኅበረ ቅዱሳን በተለያዩ 7 ቋንቋዎች የተዘጋጁ 261 መዝሙራትን ብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና ምእመናን በተገኙበት የካቲት 24/2016 ዓ.ም አስመረቀ።

የተመረቁት መዝሙራት አጠቃላይ 261 ሲሆኑ በዝርዝርም በኮንሶኛ 51፣ በአሊኛ 51፣ በሲዳምኛ 22፣ በደራሺኛ 52፣ በጋሞኛ 45፣ በአማርኛ 21 እና በእንግሊዘኛ 19 መዝሙራት ናቸው፡፡

መዝሙራቱ በብጹዕ አቡነ ቀውስጦስ የሰላሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና በብጹዕ አቡነ ኤልያስ የጋሞ ጎፋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ቡራኬ የተመረቁ ሲሆን ሊቃነ ጳጳሳቱ  አገልግሎቱ ብዙ ሥራ ስለሚጠይቅ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም አባታዊ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ሥዩምም ማኅበረ ቅዱሳን በተለያዩ ቋንቋዎች የመዝሙር አገልግሎትን ከዚህ በፊትም መሥራቱንና ተደራሽ ማድረጉን በመግለጽ ወደፊትም ምእመናን በሚሰሟቸው ቋንቋዎች የቤተክርስቲያንን ድምፅ የበለጠ ለማዳረስ አገልግሎቱ የበለጠ ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚጠናከር ገልጸዋል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ ስለ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙር ሥርዓትና ድንበር በሊቀ ሊቃውንት ሥሙር አላምረው ትምህርተ ወንጌል የተሰጠ ሲሆን፣ ስለ ቋንቋ መዝሙራት አገልግሎት አስፈላጊነትና ሚና ደግሞ በመምህር ሕሊና በለጠ ዳሰሳና ገለጻ ቀርቧል በተለያዩ ቋንቋዎችም በማኅበሩ ዘማርያን መዝሙራት ቀርበዋል፡፡

በመጨረሻም በተለያዩ ቋንቋዎች የሚፈጸም የመዝሙራት አገልግሎት በቀላሉ ስብከተ ወንጌልንና ዕቅበተ እምነትን ለማስፋትና ለማጠናከር ሚናው ከፍተኛ በመሆኑና ወጭውም ከባድ በመሆኑ ወደፊት በማኅበረ ቅዱሳን ለሚፈጸሙት አጠቃላይ 52 በላይ የተለያዩ ቋንቋዎች መዝሙራት ዝግጅት ፕሮጀክት ምእመናን ተገቢውን ድጋፍ  እንዲያደርጉ በማኅበረ ቅዱሳን መዝሙርና ኪነጥበባት አገልግሎት ማስተባበሪያ ጥሪ ተላልፏል፡፡
ኑ! ለወገኖቻችን ፈጥነን እንድረስ!
መጋቢት 15 ቀን 2016 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ፣
+++
ገቢው በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች ባጋጠመው ማኅበራዊ ቀውስና ድርቅ የተጎዱ ወገኖቻችንን፣ ገዳማትና አብነት ት/ቤቶች ለመደገፍ የሚውል።
የመግቢያ ትኬቱን፡-
1. በማኅበረ ቅዱሳን ሕንጻ 4ኛ ወለል (ቤተ አብርሃም)
2. በወረዳ ማእከላት ጽ/ቤቶች
3. በማኅበረ ቅዱሳን ንዋያተ ቅድሳት መሸጫ ሱቆች
4. በማኅበረ ቅዱሳን ሕንጻ የዕለት ገንዘብ መሰብሰቢያዎች
5. በአሐዱ ባንክ ሁሉም ቅርንጫፎች
6. በሰ/ት/ቤት ጽ/ቤቶች
ለበለጠ መረጃ
• 09 44 71 82 82
• 09 42 40 76 60

ማኅበረ ቅዱሳን
አደራ አለብኝ!

የ 2016 ዓ.ም 2ኛ ዙር ጉባኤ

ዓለም ዓቀፍ የግቢ ጉባኤ ምሩቃን መርሐ ግብር

• ቀን፡ መጋቢት 08/2016 ዓ.ም
• ሰዓት፡ ከ 7፡00 ጀምሮ
• ቦታ፡ በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ
ኑ! ለወገኖቻችን ፈጥነን እንድረስ!
መጋቢት 15 ቀን 2016 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ፣
+++
ገቢው በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች ባጋጠመው ማኅበራዊ ቀውስና ድርቅ የተጎዱ ወገኖቻችንን፣ ገዳማትና አብነት ት/ቤቶች ለመደገፍ የሚውል።
የመግቢያ ትኬቱን፡-
1. በማኅበረ ቅዱሳን ሕንጻ 4ኛ ወለል (ቤተ አብርሃም)
2. በወረዳ ማእከላት ጽ/ቤቶች
3. በማኅበረ ቅዱሳን ንዋያተ ቅድሳት መሸጫ ሱቆች
4. በማኅበረ ቅዱሳን ሕንጻ የዕለት ገንዘብ መሰብሰቢያዎች
5. በአሐዱ ባንክ ሁሉም ቅርንጫፎች
6. በሰ/ት/ቤት ጽ/ቤቶች
ለበለጠ መረጃ
• 09 44 71 82 82
• 09 42 40 76 60

ማኅበረ ቅዱሳን
ኑ! ቸርነት እናድርግ!
መጋቢት 15 ቀን 2016 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ፣
+++
ገቢው በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች ባጋጠመው ማኅበራዊ ቀውስና ድርቅ የተጎዱ ወገኖቻችንን፣ ገዳማትና አብነት ት/ቤቶች ለመደገፍ የሚውል።
የመግቢያ ትኬቱን፡-
1. በማኅበረ ቅዱሳን ሕንጻ 4ኛ ወለል (ቤተ አብርሃም)
2. በወረዳ ማእከላት ጽ/ቤቶች
3. በማኅበረ ቅዱሳን ንዋያተ ቅድሳት መሸጫ ሱቆች
4. በማኅበረ ቅዱሳን ሕንጻ የዕለት ገንዘብ መሰብሰቢያዎች
5. በአሐዱ ባንክ ሁሉም ቅርንጫፎች
6. በሰ/ት/ቤት ጽ/ቤቶች
ለበለጠ መረጃ
• 09 44 71 82 82
• 09 42 40 76 60

ማኅበረ ቅዱሳን
  " . አድዋ የወሰነው የመላውን ዓለም የነፃነት ዕጣ ፈንታ እንጂ የአንዲት አገር  ዕድል ብቻ አልነበረም "(ገጽ-፲፫)

ርእሰ፦ሐመር መጽሔት ፴፩ኛ ዓመት  ቁጥር  ፫
  የህትመት ዘመን ፦ መጋቢት  ፳፻፲፮ ዓ.ም
አዘጋጅ ፦በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ  ቤተ ክርስቲያን ማኀበረ ቅዱሳን በልማት ተቋማት አስተዳደር  በመጽሔት ዝግጅት ክፍል የሚዘጋጅ ትምህርታዊ መጽሔት
•  ገጽ ብዛት፦፳፰
   ዋጋ ፦፵ ብር 
   •  ሐመር  መጽሔት  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖት  ሥርዓትና ትወፊት ጠብቃ በልማት ተቋማት አስተዳደር  በመጽሔት ዝግጅት ክፍል  በየወሩ የምትወጣ መንፈሳዊ መጽሔት ናት፡፡
      •  ሐመር መጽሔት ፴፩ኛ ዓመት  ቁጥር ፫   መጋቢት ፳፻፲፮ ዓ.ም በመልዕክት ዐምድ "#ኢየሩሳሌም ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ " በማለት ኃይለ ቃሉ ትንቢታዊ ገጽታ ያለው መሆኑን  በመጥቀስ የአድዋን በዓል ስናስብ ለአፍታም ቢሆን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማንም ቢሆን ሊዘነጋ እንደማይገባው ፣በአድዋ ድል ቤተ ክርስቲያን የነበራት ጉልህ ሱታፌ ሊዘከር እንደሚገባ  ያሳያል፡፡
.ዐውደ ስብከት  ሥር”  #ደስታዬን ፈጽሙልኝ"  በሚል ርእስ   ደስታ የክርስቲያኖች መተባበር  እኖደሆነ፣ ለመለያየት ምክንያቶችን መፈለግ እንዴት አለመታደል እንደሆነ ፣ ክርስቲያኖች ሲተባበሩ እግዚከብሔር በመካከላቸው እንደሚገኝ ፣መለያየት የሰይጣን ነጥሎ መምቻ መሳሪያም መንገድም እንደሆነ ይዳስሳል።
  በትምህርተ ሃይማኖት ዐምድ ሥር “#የምግባራት ሁሉ ንግሥት  "በሚል ዐቢይ ርእስ ሃይማኖት  ባለበት ሁሉ ጾም እንዳለ፣የጾም  ጥቅም፣ እንዴት መጾም እንዳለብን፣በጾም ወቅት መጥነን መመገብ እንዳለብን ፣ዕለት ዕለት የማያቋርጥ ጾም ምን አይነት እንደሆነ በበቂ  ማስረጃ የተደገፈ  ትምህርት ይዛለች።
• ዐቢይ ጉዳይ  ዐምድ  ሥር  ደግሞ “ #የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተዋጽኦ  #በዐድዋ ጦርነት “ በሚል ርእስ   ታሪክ ብዙ ገንዘብ ከተከፈለባቸው ማስታወቂያዎች እና ገበያን ዓላማ አድርገው ከሚነገሩ ዲስኩሮች በላይ ድምፁ የሚያስተጋባ  እንደሆነ ፤ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ያላትን ነገር ሁሉ ወደ አድዋ ጦርነት አንቀሳቀሰች ፡፡ ሕዝቧን ካህናቷንና ታቦቷን ይዛ ዘመተች ፡፡ ቆዳ እና ሌጦ የለበሱ ባሕታውያን ሳይቀሩ የዘመቻው ተሳታፊዎች ነበሩ፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ያላትን ነገር ሁሉ ወደ አድዋ ጦርነት አንቀሳቀሰች ፡፡ ሕዝቧን ካህናቷንና ታቦቷን ይዛ ዘመተች ፡፡ ቆዳ እና ሌጦ የለበሱ ባሕታውያን ሳይቀሩ የዘመቻው ተሳታፊዎች  እንደነበሩ ያትታል ።
•  ክርስትና በማኀበራዊ ዐምድ ሥር  ደግሞ  " ከሚያለቅሱ ጋር አልቅሱ   “በማለት  የሚገባ ኅዘን እና የማይገባ ኅዘን እንዳለ ፣ በዘመናችን  በልዩ ልዩ ምክንያቶች ጩኸታቸው ያልተሰማላቸው ፤ዕንባቸው ያልታበሰላቸው ፤ከኀዘናቸው መረጋጋት ያልቻሉ ፣በረኅብ አልጋ የሚገረፉ  ወገኖቻችን ከዕለት ወደ ዕለት እየተበራከቱ እንደሆነ፣ የሰው ልጆች ለረኅብ የሚዳረጉባቸውን ዋና ዋና ምክንያቶች በዝርዝር ይዳስሳል፡፡  በዚህ ወቅት  እነዚህን ኀዘን የደረሰባቸውን ማጽናናት እንደሚገባ ይጠቁማል ።
•  በእናስተዋውቃችሁ ዐምድ ሥር “#በእንተ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርዊ  ክፍል_፩ "  በሚል ርእስ ስለ ቅዱስ ኤፍሬም ልደትና ዕድገት ፣ስለ ቅዱስ ኤፍሬም አገልግሎትና የገጠሙትን ፈተናዎች  በስፋት ይዳስሳል ።
•  በነገዋ  ቤተ ክርስቲያን ዐምድ  ሥር “ለነገዋ ቤተ ክርስቲያን ተረካቢ እናዘጋጅላት _ክፍል ፫ “ በሚል ልጆች በወላጆቻቸው ብቻ የሚያድጉ እንዳልሆነ ፣ጎረቤት፤ትምህርት ቤት ፣ማኅበረሰብ ወዘተ ሁሉ ለልጆች ዕድገት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሚና እንዳላቸው  ያስነብባል፡፡ 
•  በኪነ ጥበብ ዐምድ “ አጋዥነት “ በሚል ርእስ ሰፊና አስተማሪ ታሪክ ይዛለች ፡፡
•  የጥያቄዎቻችሁ መልስ ዐምድ “# ግብረ ሶዶማዊነትና ክፉቱ   ክፍል -፩ "   በሚል ርእስ ከመምህር ግርማ ባቱ የቅድስት ሥላሴ ዪኒቨርስቲ መምህር ጋር የተደረገ  ወቅታዊ ምላሽ ይዛለች  ።
        #መ/ር ግርማ ባቱ ".ሴት ከሴት ጋር ወንድም ከወንድ ጋር የሚፈጽሙት ኃጢአት እንደሆነ ገልጸዋል።
        #ማዕከላት፣የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት ሐመር መጽሔት ፴፩ኛ ዓመት  ቁጥር ፫  ዕትም ለአንባቢያን እንድትደርስ  የድርሻችሁን እንደትወጡ  ምክንያቱም .ሐመር መጽሔት ትምህርተ ወንጌል ለመላው ዓለም ለማዳረስ አንዱ መሣረያ ናት፡፡

  አስተያየት ለመስጠት
magazine @eotcmk.org  ወይም በ0111540484/0944259014 ያግኙን

  ሐመር መጽሔት ፴፩ኛ ዓመት  ቁጥር ፫   በማሰራጨት ፡በማንበብና በማስነበብ የድርሻችን እንወጣ !
[email protected]  ሐመር መጽሔት  ዝግጅት  ክፍል
"ጾማችን በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት የሚኖረው የተፈናቀሉት ወገኖቻችን ወደ ቀያቸው ተመልሰው ሰላማዊ ኑሮ መኖር ሲችሉ፣ የተራቡት ሲደገፉ፣ ፍትሕ ያጡት ፍትሕ ሲያገኙ ነው፡፡"
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የ 2016 ዓ.ም ዐቢይ ጾምን አስመልክተው መልእክት አስተላልፈዋል።

ቅዱስነታቸው ያስተላለፉት ሙሉ መልእክት እንደሚከተለው ቀርቧል።

መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

በሀገር ውስጥና በዓለም ዙሪያ ሁሉ የምትገኙ ምእመናንና ምእመናት ልጆቻችን በሙሉ!

እንኳን ለሁለት ሺሕ ዐሥራ ስድስት ዓመተ ምሕረት የጾመ ኢየሱስ ሱባኤ በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!

“ወእምዝ ኃደጎ ዲያብሎስ ወናሁ መጽኡ መላእክት ይትለአክዎ፡- ከዚህ በኋላ ዲያብሎስ ትቶት ሄደ፤ እነሆም ያገለግሉት ዘንድ መላእክት መጡ›› (ማቴ ፬፲፩)፡፡

በቀጣዮቹ ሁለት ወራት በከፍተኛ ሃይማኖታዊ ተመሥጦ የምንጾመው ጾም፣ ጾመ ኢየሱስ ተብሎ የሚታወቀው ነው፡፡ ይህ ጾም በጥንት ጊዜ ሰው በኃጢአት የወደቀበትን ምክንያት፣ እንደዚሁም ሰው ኃጢአትንና ዲያብሎስን እንዴት እንደሚያሸንፍ ጌታችን እኛን ያስተማረበት ጾም ነው፡፡
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በቅዱስ መጽሐፏ እንደምታስተምረን፣ ኃጢአትና ዲያብሎስ የአንድ ሳንቲም _ ሁለት ገጽታዎች ናቸው፤ ይህም ማለት ዲያብሎስ ባለበት ኃጢአት አለ ፤ ኃጢአት ባለበትም ዲያብሎስ አለ ማለት ነው፤ እነዚህ ሁለቱ የሚለያዩ አይደሉም፤ የመጨረሻ ግባቸው ደግሞ ሰውን መጣል ነው፡፡ዲያብሎስ የሰውን ደካማ ዝንባሌ ወይም በሆነ ነገር መጐምጀትን በሰው ሲመለከት ያንኑ የጐመጀበትን ክፉ ምኞት እንዲፈጽም፣ በረቂቅ የሰው ኅሊና ውስጥ ገብቶ በከፍተኛ ደረጃ ይገፋፋል፤ ሰውም በራሱ የመጐምጀት ዝንባሌና በዲያብሎስ ግፊት ለመንፈሳዊ ሕይወቱ ጐጂ የሆነውን ድርጊት ይፈጽማል ፤ ቀጥሎም ድርጊቱ በእግዚአብሔር ፊት በደል ይሆንና ከእግዚአብሔር ይለየዋል፡፡ ሰው ከእግዚአብሔር ከተለየ ደግሞ ዘለዓለማዊ ሕይወትንና ክብርን ጨምሮ ብዙ መልካም ነገርን ያጣል፤ ኃጢአት የሚባለውም ይህ ነው፤ በቀደሙት አባትና እናት ማለትም በአዳምና ሔዋን የተከሠተው ነገርም ይኸው ነው፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት

ኃጢአትን በጽድቅ፣ ዲያብሎስን በጾም በማሸነፍ የአሸናፊነትን መንገድ ሊያሳየን የመጣው አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአዳምና በሔዋን የተፈጸመው ውድቀት እንዴት እንደሚቀለበስ በዚህ ጾም አስተምሮናል፡፡ ጌታችን ዐርባ ቀንና ዐርባ ሌሊት ከጾመ በኋላ ተራበ፤ ዲያብሎስም መራቡን አይቶ ይጐመጅልኛል ብሎ በምግብ ፈተነው፡፡ የጌታችን መልስ ግን ሰው በእንጀራ ብቻ አይኖርም ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ የሚል ነበረ፣ በተመሳሳይም በፍቅረ ንዋይና በአምልኮ ባዕድ ፈተነው የጌታ መልስ ግን በተቃራኒው ነበረ፡፡

ዲያብሎስ በሦስቱም የማስጐምጃ ፈተናዎች ጌታ ሊሸነፍለት ካለመቻሉም በላይ "አንተ ሰይጣን ከኋላዬ ሂድ" ብሎ ሲገሥጸው ተሸንፎ ትቶት ሂዶአል፡ በአሸናፊነቱ የተደሰቱ መላእክትም ወዲያውኑ መጥተው በክብረ አምልኮ አገለገሉት፤ በዚህ ድርጊት የምንመለከተው እውነታ ቀዳማይ አዳምን ባሸነፈበት ስልት ዳግማይ አዳም ክርስቶስን ለመጣል ዲያብሎስ የሄደበትን ርቀት በአንድ በኩል ስናይ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ዳግማይ አዳም ክርስቶስ የቀዳማይ አዳም ተሸናፊነትና ውድቀት ለመቀልበስ ያሳየውን ጥብዓት እናያለን፡፡

በዚህም የቀደመው ውድቀት በኋለኛው አሸናፊነት ሙሉ በሙሉ ተቀልብሶ፣ ዲያብሎስ ጓዙን ጠቅልሎና ተስፋ ተስፋ ቆርጦ መሄዱን እናስተውላለን።

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!

ጌታችን የአሸናፊነትን መንገድ በቃልና በተግባር አስተምሮናል፤ አሳይቶናልም፤ ይህንም ያደረገው እሱ አሸንፎልናል እያልን ለመኵራራት ሳይሆን፣ በእሱ ኃይል እየታገዝንና እሱ ባሸነፈበት ስልት እየተጠቀምን እንድናሸንፈው ነው፡፡ ሰይጣን የሚሸነፍበት ስልት በሌላ ሳይሆን፤ ሥጋዊ መጐምጀትን ከአእምሮአችን አውጥተን በመወርወር ነው፡፡

ሥጋችን በፍቅረ ንዋይ፣ በሥልጣን፣ በዝሙት እንደዚሁም በተለያዩ ሥጋዊ ምኞቶች ሊጐመጅ ይችላል፤ ያን ጊዜ ሰይጣን እነሱን እንድንፈጽም ሊገፋፋን ከበኋላችን እንደቆመ እናስብና "አንተ ሰይጣን ከኋላዬ ሃድ” እንበለው፡፡ በቃል ብቻ ሳይሆን በተግባር ያስጐመጁን ነገሮችን ከኅሊናችን አውጥተን በመጣል እሱን ማሸነፍ አለብን፤ በዚህ ጊዜ ሰይጣን ይሸሻል፤ መላእክትም ወደኛ መጥተው ይረዱናል፣ ይጠብቁናል፤ ያግዙናል፣ ያድኑናል፡፡ ዲያብሎስ የሰዎችን የመጐምጀት ዝንባሌን ተከትሎ በመገፋፋት ዛሬም ዓለማችንን ለከፋ ውድቀት እየዳረጋት ነው፣ ሀገራችንን ጨምሮ በየአካባቢው የሚቀሰቀሱት አለመግባባቶችና ግጭቶች መንሥኤያቸው ከመጐምጀት ውጭ ሊሆን አይችልም፡፡ ግማሹ በሥልጣን፣ ግማሹ በሀብት፥ ግማሹ በራስ ወዳድነት፣ ግማሹ ደግሞ የበላይ ለመሆን በሚል እሳቤ የሰው ኅሊና በክፉ ምኞት ይጐመጅና በዲያብሎስ ገፋፊነት ወደ ተግባራዊ ጥፋት ይገባል፡ በውጤቱም ሰው ይጎዳል፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት

ጾም ማለት እህልንና የእንስሳት ውጤቶችን ከመመገብ መከልከል ብቻ አይደለም፣ የእንስሳት ውጤት የሆኑትን ላለመመገብ ከምንወስነው በላይ እኩያት ፍትወታትንና ኃጣውእን ላለማስተናገድ በቁርጥ መወሰን ይጠበቅብናል፡፡ ስንጾም መገዳደልን፤ መጣላትን መለያየትን፤ መገፋፋትን በሆነ ነገር መጐምጀትን እርም ብለን በመተው ዲያብሎስን የምናሸንፍበት የአሸናፊነት ኅሊና መላበስ አለብን፣ ከክፉ ኅሊና እና ተግባር የተለየን ያህል በአንጻሩ ደግሞ በጎ ነገርን ለመስራት በእጅጉ መበርታት ይጠበቅብናል፡፡

ዲያብሎስ ተስፋ ቆርጦ የሚሸሸው ይቅር ይቅር ስንባባል፤ ለሰላምና ለአንድነት፣ ለፍቅርና ለስምምነት ስንቆም ነው! ከዚህም ጋር በእግዚአብሔር ፊት እጅግ ጸያፍ የሆነው ግብረ ኃጢአት በዚህች ምድር እንዳይፈጸም ማኅበረ ሰባችን በተጠንቀቅ ሲቆም ነው፤ እንደዚሁም ደም መፋሰስ፣ አለመተማመንና በሴት ልጆቻችን የሚደርስው አካላዊ፣ መንፈሳዊና ሞራላዊ ጥቃት ሲቆም ነው፡፡ ጾማችን በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት የሚኖረው የተፈናቀሉት ወገኖቻችን ወደ ቀያቸው ተመልሰው ሰላማዊ ኑሮ መኖር ሲችሉ፣ የተራቡት ሲደገፉ፣ ፍትሕ ያጡት ፍትሕ ሲያገኙ ነው፡፡

ይህ ዓይነት መልካም ሥነ ምግባር በእያንዳንዱ የማኅበረሰብ አእምሮ ቦታ አግኝቶ ሲተገበር ትክክለኛውን ጾም ጾምን ማለት እንችላለን፣ ዲያብሎስም በእርግጠኝነት በዚህ ይሸነፋል፤ የሰው ጣዕመ ሕይወትም በዚህ ይለመልማል! ምድሪቱም በእግዚአብሔር በረከት ትሞላለች፡፡ ይህን ቅዱስ ተግባር በወርኃ ጾሙ በደንብ እንድንተገብረው ለመላው ኢትዮጵያውያን በተለይም ለኦርቶዶክሳዊው ማኅበረሰብ መንፈሳዊና አባታዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

በመጨረሻም

በሀገራችን ረሃብ የሚያጠቃቸው ወገኖች በበዙበት በአሁኑ ወቅት፤ ሳንመጸውት ጾምን ጾምን ማለት ማጣፈጫ ወጥ የሌለው ምግብ መመገብ ማለት ስለሆነ፣ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የቁርስ በጀቱን ለተራቡ ወገኖች በመለገስ ወገኖቹን በረሃብ ከመሞት እንዲታደግ ወቅታዊ ጥሪያችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፡፡

መልካም የጾም ወቅት ያድርግልን! እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ !! ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!! አሜን፡፡

አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት መጋቢት ፩ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም. አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
የዐቢይ ጾም የመጀመሪያ ሳምንት

ዘወረደ


በዚህ ሳምንት የቃል ርደት፣ የወልድ ልደት፣ የአዳም ድኅነት ቢነገርም እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ከሰማይ የወረደ ሰማያዊ፣ በክብር ያረገ በኩረ ትንሣኤ መሆኑ አይዘነጋም፡። ለዚህም ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ “እውነት እውነት እልሃለሁ፥ የምናውቀውን እንናገራለን፤ ያየነውንም እንመሰክራለን፥ ነገር ግን ምስክርነታችንንም አትቀበሉትም። በምድር ያለውን ስንነግራችሁ ካላመናችሁኝ፥ በሰማይ ያለውን ብነግራችሁ እንዴት ታምኑኛላችሁ? ከሰማይ ከወረደው የሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው ነው። ሙሴ በምድረ በዳ እባቡን እንደ ሰቀለው የሰው ልጅ እንዲሁ ይሰቀል ዘንድ አለው፡፡ያመነበት ሁሉ ለዘለዓለም ሕያው ሆኖ እንዲኖር እንጂ እንዳይጠፋ፣ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ሕይወትን እንዲያገኝ እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ቤዛ አድርጎ እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶታልና” እንዳለ እርሱ ምድራዊ ያይደለ ሰማያዊ ነው። (ዮሐ.፫፥፲፩-፲፮)  “ተጠምቀ ሰማያዊ በእደ መሬታዊ” ስለ ፍቅሩ በፈጠረው የተጠመቀ ሰማያዊ ነው።

ጾመ ድጓው የሚጀምረውም እንዲህ በማለት ነው፤ “ዘወረደ እምላዕሉ፣ አይሁድ ሰቀሉ…. እግዚአ ኩሉ ዘየሐዩ በቃሉ፤ ….በቃሉ የሚያድነውን ከላይ የወረደውን የሁሉን ጌታ አይሁድ ሰቀሉት…”
ዘወረደ የዐቢይ ጾም የመጀመሪያ ሳምንት ነው። ስያሜውም የቅዱስ ያሬድ ነው። ትርጉሙም “ከሰማያት የወረደ” ማለት ነው። ቅድመ ዓለም ከአባቱ ከአብ የተወለደ ፣ድኅረ ዓለም ከድንግል ማርያም የተወለደ ነው። ስም አጠራሩ  ያለና የነበረ፣ እግዚአብሔር፣ በፈቃዱ ዓለምን ለማዳን የመምጣቱን ምሥጢር የምንረዳበት ሳምንት ነው። ይህ የመጀመሪያው ሳምንት ‹ጾመ ሕርቃል› እየተባለም ይጠራል፡፡ ሕርቃል (ኤራቅሊዮስ) በ፮፻፲፬ ዓ.ም የነበረ የቤዛንታይን ንጉሥ ነው፡፡ለክርስቲያኖች ባደረገው ርዳታ ምክንያት አንድ ሳምንት ጾመውለት ነበር፡፡ ዛሬም ድረስ ጾመ ሕርቃል እየተባለ ይጠራል፡፡ ሙሉ ታሪኩ በፍትሐ ነገሥት ትርጓሜ አንቀጽ ፲፭ ላይ ይገኛል፡፡

በዚህ ሳምንት ቤተ ክርስቲያን ስለ ጾም ጥቅምና እንዴት መጾም እንዳለብን ታስተምረናለች፡፡ቅዱስ ያሬድ በጾመ ድጓው “አከለክሙ መዋዕል ዘኃለፈ ዘተቀነይክሙ ለግዕዘ ሥጋክሙ፤ ለሥጋቸሁ ፈቃድ የተገዛችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃችኋል፤ ከአሁን በኋላ ግን ጹሙ፣ ጸልዩ ለእግዚአብሔር ተገዙ” እያለ የጾም አዋጅ ያውጃል። ጾም ፈቃደ ሥጋን ለፈቃደ ነፍስ፣ ፈቃደ ነፍስን ለፈቃደ እግዚአብሔር የምናስገዛበት መንፈሳዊ መሣሪያ ነው፡፡

ጾሙ በሚጀመርበት ሰንበት በሚሰበከው ምስባክ እንዲህ ብሎ ያሳስበናል፤ “ለእግዚአብሔር በፍርሃት ተገዙ፣ በረዓድም ደስ ይበላችሁ” ጾም ከምግብና ከመጠጥ እንዲሁም ከሌሎች ምቾቶችና ደስታዎች ከመከልከል ያለፈ ጥልቅ ትርጉም ያለው ተግባር ነው። (መዝ.፪፥፲፩-፲፪) “ንጹም ጾመ ወናፍቅር ቢጸነ ከመ ያብርህ ብርሃነ ስብሐቲሁ በላዕሌነ፤ (የእግዚአብሔር) የክብሩ ብርሃን በላያችን ላይ ያበራ ዘንድ ጾምን እንጹም፤ወንድማችንንም እንውደድ” እንዲል። (ጾመ ድጓ)

በዘወረደ እሑድ የሚነበቡት ምንባባትም ይህንን የጾምን ጸጋ የያዙ ናቸው።

“ነገር ግን ፈጣሪያችን የምትበልጠውን ጸጋ ይሰጣል፤ ስለዚህም “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል” ይላል፡፡ እንግዲህ እግዚአብሔርን እሺ በሉት፤ ሰይጣንን ግን እንቢ በሉት፤ ከእናንተም ይሸሻል፡፡ እግዚአብሔርን ቅረቡት፤ ይቀርባችሁማል፤ እናንተ ኃጥኣን እጆቻችሁን አንጹ፤ ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ ልባችሁን አጥሩ፡፡ እዘኑና አልቅሱ፤ ሳቃችሁን ወደ ልቅሶ÷ ደስታችሁንም ወደ ኀዘን መልሱ፡፡ በእግዚአብሔር ፊት ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ፤ እርሱም ከፍ ከፍ ያደርጋችኋል፡፡” (ያዕ.፬፥፮-፲)

“በውኑ እንግዲህ በስሙ እናምን ዘንድ የከንፈሮቻችን ፍሬ የሚሆን የምስጋና መሥዋዕትን በየጊዜው ለእግዚአብሔር ልናቀርብ አይገባንምን? ነገር ግን ለድሆች መራራትን፥ ከእነርሱም ጋር መተባበርን አትርሱ፤ እንዲህ ያለው መሥዋዕት እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋልና፡፡” (ዕብ.፲፫፥፲፭-፲፮)

በጾም የተጠቀሙ ቅዱሳንን እያሰብን ለጾም እንድንተጋም ወደ እነርሱ እንድንመለከት ቤተ ክርስቲያን ታስተምራለች፡፡“ ልባችሁ በመብል ያይደለ በጸጋ ቢጸና ይበልጣልና፤ በዚያ ይሄዱ የነበሩ እነዚያ አልተጠቀሙምና።” (ዕብ.፲፫፥፱) ሳምንቱ በሚጀምርበት ሳምንት የሚነበበው የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት እንዲህ ይላል፡፡ ጾመ ድጓው አባቶቻችን ያገኙትን በረከት እንደምናገኝበት ሲገልጽ “የእግዚአብሔር የክብሩ ብርሃን በላያችን ላይ ያበራ ዘንድ ጾምን እንጹም፤ ወንድሞቻችንም እንውደድ፤ ኤልያስ በጾም ወደ ሰማይ አርጓልና፤ዳንኤልም ከአናብስት አፍ ድኗልና፡፡”

ጾም ፈቃደ ነፍስን በፈቃደ ሥጋ ለማሠልጠን የአጋንንት ኃይል ለመቋቋም የሚያስችል የክርስቲያኖች ጋሻ በመሆኑ በሃይማኖት ለሚመሩ ምእመናን እጅግ አስፈላጊና ከምንም በላይ የሕይወታቸው መርሕ መሆን እንደሚገባ ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቱ እንዲህ በማለት   ያስተምራል፡፡ ” አሁንም ወንድሞቻችን በዚህ በሥጋችን ሳለን ፈቃደ ሥጋችንን ልንሠራ አይገባም፤ ፈቃደ ሥጋቸውን የሚሠሩ ሰዎች በወዲያኛው ዓለም ምውታን ናቸውና፡፡ የሥጋችሁን ፈቃድ በነፍሳችሁ ፈቃድ ድል ከነሣችሁት ለዘለዓለም ሕያዋን ትሆናላችሁ፡፡ የነፍሳቸውን ፈቃድ የሚሠሩ ሰዎች ሁሉ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና፡፡" (ሮሜ ፰፥፲፪-፲፬)

ጾም አበው ቅዱሳን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በጊዜ ቀምረው፣ በበታ ወስነው፣ በሁኔታ ገድበው... ባስቀመጡልን ወቅት ከእህልና ከውኃ በመከልከልና ሰውነትን በማድከም ብቻ ሳይሆን ለስሕተት ከሚዳርጉ ነገሮችና ቦታዎች ተቆጥቦ በጸሎት መትጋትም እጅጉን አስፈላጊ ነው፡፡ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊትም ይህንን እውነታ በተመለከተ እንዲህ ይላል፡፡ “እኔ ግን እዘንልን፤ ለምንልን ባሉኝ ጊዜ ማቅ ምንጣፍ ለብሼ አዘንኩላቸው፤ ሰውነቴን በጾም አደከምኩዋት፤ ልመናዬም እኔም ወደመጥቀም ተመለሰችልኝ፡፡” (መዝ. ፴፬/፴፭፥፲፫)

ጾም ከሥነ ምግባራት ሕግ አንዱ በመሆኑ እንኳንስ ያልተፈቀደውን የተፈቀደውም ቢሆን የማይጠቅም ከሆነ ፈጽሞ በመተው ለእግዚአብሔር ያለንን ፍጹም ፍቅር የምናስመሰክርበት ምሥጢር ነው፡፡

ጾም ከመብልና ከመጠጥ ጋር የተያያዘም በመሆኑ መብል ጊዜያዊ ስለሆነ ማለትም በዚህ ዓለም እስካለን ብቻ የምንገለገልበት እንጂ ዘለዓለማዊ ስላይደለ ለጊዜያዊ መብልና መጠጥ ምክንያት ከሃይማኖት ሥነ ምግባር እንዳንወጣ ቅዱሳን አባቶቻችን ሐዋርያት ሲመክሩ “መብል በእግዚአብሔር ዘንድ ግዳጅ አይፈጽምልንም ወደ እግዚአብሔር አያቀርበንም፤ ብንበላም አይረባንም፤ አይጠቅመንም፤ ብንተወውም አይጎዳንም” በማለት ሲመክሩን ቅዱስ ጳውሎስም የመብልና የሆድ ጊዜያዊነት አስመልክቶ እንዲህ በማለት አስተምሯል፡፡ (፩ኛቆሮ.፰፥፰)

“ሁሉ ነገር ተፈቅዶልኛል፤ ሁሉ ግን አይጠቅመኝም፡፡ ሁሉ ተፈቅዶልኛል በእኔ ላይ ግን አንድ ነገር እንኳን አይሠለጥንብኝም፡፡ መብል ለሆድ ነው ሆድም ለመብል ነው፡፡ እግዚአብሔር ግን ሁለቱንም ያሳልፋቸዋል”፤ (፩ኛቆሮ.፮፥፲፪-፲፫) “ለሚጠፋ ምግብ አትሥሩ፤ ይልቅስ የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ የዘለዓለም ሕይወት ስለሚሆን ምግብ ሥሩ” እንደ ተባለ (ዮሐ. ፮፥፳፯) ካለን ጊዜ ለመንፈሳዊ ሕይወታችን ጊዜ በመስጠት ቢበሉት የማያስርበውን፣ ቢጠጡት የማያስጠማውን፣ የዘለዓለም ሕይወት የምናገኝበትን ሥጋ እና ደሙን ተቀብለን መንግሥቱን እንድንወርስ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን።

ሥርዓት ቅዳሴ
ከሠራኢ ካህን፣
ቅዳሴ፡
ዘእግዚእነ
“ዘበእንቲኣነ ለሰብእ ወበእንተ መድኃኒትነ፡ ወረደ እምሰማያት። ተሰብአ፡ ወተሠገወ እመንፈስ ቅዱስ ወእማርያም እምቅድስት ድንግል፤ ስለ እኛ ስለ ሰዎች እኛን ለማዳን ከሰማይ ወረደ፤ በመንፈስ ቅዱስ ግብር  ከቅድስት ድንግል ማርያም ፍጹም ሰው ሆነ፡፡”

ወንጌል፡ ዮሐ.፫፥፲-፳፬
የዕለቱ ምንባባት:-
•  በሠራኢ ዲያቆን (ዕብ.፲፫፥፯-፲፯)
•  በንፍቅ ዲያቆን (ያዕ.፬፥፮-ፍጻሜ)
•  በንፍቅ ካህን (የሐዋ. ፳፭፥፲፫-ፍጻሜ)

ምስባክ፡ “ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሃት ወተሐሠዩ ሎቱ በረዓድ አጽንዕዋ ለጥበብ ከመ ኢይትመዐዕ እግዚአብሔር” (መዝ.፪፥፲፩)

ወንጌል፡ ዮሐ.፫፥፲-፳፬

ስብሐት ለእግዚአብሔር ኪያነ ዘፈጠረ ከመ ናምልኮ፤ እንድናመልከው እኛን ለፈጠረ ለእግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይሁን!
2024/09/29 08:22:51
Back to Top
HTML Embed Code: