Telegram Web Link
በማኅበረ ቅዱሳን ሐዋሳ ማእከል ለ15 ቀናት ያሰለጠናቸውን 27 የሲዳምኛ ቋንቋ ሰበኪያንን አስመረቀ።

በማኅበረ ቅዱሳን ሀዋሳ ማእከል በትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ዋና ክፍል ለ15 ቀናት ያሠለጠናቸውን 27 የሲዳምኛ ቋንቋ ደረጃ አንድ ሰባኪያነ ወንጌልን የካቲት 23 ቀን 2016 ዓ.ም በአባቶች ቡራኬ አስመረቀ።

በምረቃው መርሐግብር የሲዳማ ሀገረ ስብከት የዐራቱ ጉባኤያት የአብነት መምህር ሊቃ ሊቃውንት ብርሃነ ውልድ ሁነኛው ለሠልጣኞች በመንፈሳዊ ሕይወት በርትተው የተሰጠቸውን አደራ በትጋት እንዲወጡ አባታዊ መልዕክት አስተላልዋል።

በማኅበረ ቅዱሳን የደቡብ ማእከላት ማስተባበሪያ ኃላፊ ቀሲስ ኢንጅነር አሰፋ ቦረና የአገልጋይ ሕይወት ከተስተካከለ አገልግሎቱ የሠመረ አገልግሎት ይሆናል ስለሆነም እንደ ርግብ የዋህ እንደ እባብ ብልህ ሆናችሁ የሰባኪነትን ድርሻ እንድትወጡ በቅድስት ቤተክርስቲያን ስም አደራ እንላለን ብለው መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመጨረሻም ሥልጠናውን ለሰጡ መምህራን የምስጋና ምሥክር ወረቀት በሊቀ ሊቃውንት ብርሃነ ወልድ ሁነኛው ፤ ለሠልጣኞች መጽሐፍ ቅዱስና የሥልጠና ምሥክር ወረቀትና አባታዊ ምክር በሀዋሳ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ ጽዮን ቆሞስ አባ ገብረጻድቅ ተሰጥቷቸዋል።

ሰልጣኞቹ ለማእከሉ የሥዕለ አድኅኖ ስጦታ አበርክተዋል።
የማኅበረ ቅዱሳን ጅግጅጋ ማእከል ያስተማራቸውን የግቢ ጉባኤ ተማሪዎች አስመረቀ።

በጅግጅጋ ዩኒቨርስቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ እና በማኅበረ ቅዱሳን ጅግጅጋ ማእከል ማኅበረ ቅዱሳን አማካኝነት የግቢ ጉባኤ ትምህርት የተማሩ 68 ተማሪዎች የካቲት 24 ቀን 2016 ዓ.ም ተመርቀዋል።

በጅግጅጋ ም/ፀ/ቅድስት ኪዳነ ምሕረትና ቅዱስ አማኑኤል ካቴድራል ቤተክርስቲያን በተከናወነው የምርቃት ሥነ ሥርዓት ላይ ተመራቂ ተማሪዎች፣የተማሪዎች ወላጆች እና ጥሪ የተደረገላቸው አባላት ተገኝተዋል።

ከተመራቂዎች መካከል አብዛኞቹ በዩኒቨርስቲው ውስጥ በማእረግ እና በከፈተኛ ማእረግ የተመረቁ ሲሆን ሁለት ተማሪዎች ከዩኒቨርስቲው የተሸለሙትን ዋንጫ መንፈሳዊ ዕውቀትን እና ቤተ ክርስቲያንን ማገልገል ላስተማራቸው ማኅበረ ቅዱሳን አስረክበዋል።
የማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል የትውልድ ማእከል ግንበታ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተከናወነ።

የኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች ስብእና መገንቢያ እንደሚሆን የተነገረለት የማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል የሚያስገነባው ባለ 12 ወለል ሕንጻ ግንባታ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ዛሬ የካቲት 25 ቀን 2016 ዓ.ም ተጀምሯል።

በግንባታ ማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ ብፁእ አቡነ መቃርዮስ የጅግጅጋ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ፣ የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም፣ የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ጸሐፊ መ/ር ዋሲሁን በላይ እንዲሁም የትውልድ ማእከል ግንባታው አምባሳደሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የማኅበሩ ሰብሳቢ የሆኑት ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ እንደገለጹት አዲስ አበባ ማእከል የማኅበሩ ዐይን በመሆኑ ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅ ባለድርሻ አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

በተጨማሪም የትውልድ አምባሳደር በመሆን በማእከሉ የተመረጡት የተከበሩ የዓለም ሎሬት አያልነህ ሙላቱ እንደተናገሩት ይህን ሕንጻ ለመገንባታ የበኩላቸው አስተዋጽኦ ለማበርከት ጥረት እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።

በመርሐ ግብሩ ላይ እንደተገለጸው የሕንጻ ግንባታው ሲጠናቀቅ ማእከሉ በዋናነት የሚያከናውናቸውን አገልግሎቶች ከማገዝ በተጨማሪ ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብን ለማፍራት፣ ጠንካራ የሚዲያ አገልግሎት ለመስጠት እንዲሁም ዓለም አቀፍ ጫናን ለመቋቋም የሚያስችሉ ሥራዎችን ለማከናወን ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ተገልጿል።
2024/09/29 10:20:47
Back to Top
HTML Embed Code: